እንደሚታወቀው የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ለሁሉም ሰንበት ት/ቤቶች ወጥ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ማስተግበር ከጀመረ ዓመታት አስቆጥሯል ።
በዚህም መሰረት አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ ከ90% በላይ ሰንበት ት/ቤቶች እየተገበሩት ይገኛሉ ። በዚህም መሰረት አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት 4 እርከኖች ያሉት ሲሆን ተማሪዎች ከአንዱ እርከን ወደሌላው እርከን ሲዘዋወሩ በሀገረ ስብከት ደረጃ ምዘና ተደርጎላቸው ማለፍ ይጠበቅባቸዋል ።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነትም ይሔንን ምዘና ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ እየሰጠ ይገኛል ።
በዚህ አመትም ሥርዓተ ትምህርቱን እየተገበሩ ከሚገኙ የ4ኛ ፣ 8ኛ እና 10ኛ ክፍል እያስተማሩ ለሚገኙ ሰንበት ት/ቤቶች የካቲት 22 እና 23 / 2017 ዓ.ም ከ130 በላይ በሚሆኑ ሰንበት ት/ቤቶች ላይ የመጀመሪያ መንፈቅ አመት ምዘና ሰጥቷል ።
በቀጣይም በዚህ አመት የማጠቃለያ ምዘናውን የሚዉስዱና ወደ ቀጣዩ እርከን (ክፍል ) መዛወር የሚችሉት እነዚህ ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውን እንገልጻለን ።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት