Latest Posts from የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት (@aasundayschool) on Telegram

የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት Telegram Posts

የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
ይህ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ልሳን ነው።
10,161 Subscribers
3,317 Photos
37 Videos
Last Updated 05.03.2025 22:10

The latest content shared by የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት on Telegram

የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

05 Dec, 15:51

1,957

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

በ2016 ዓ.ም በሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ትምህርታቸውን  ተከታትለው  ያጠናቀቁ እና በሀገረ ስብከት በብሔራዊ ደረጃ ምዘና ተደርጎላቸው ያለፉ 
#የ4ኛ , #የ6ኛ እና #የ10ኛ ክፍል  ተማሪዎች የዕውቅና መስጠት መርሐ ግብር !!!

#ታህሳስ_6_2017_ዓ_ም  
#በቦሌ_መድኃኔዓለም_ካቴድራል

#በመርሐግብሩ_ላይ 👇
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፤ ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፤ የጠቅላይ ቤተክህነት የየመሪያው ኃላፊዎች ፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና የክፍለ ከተማ ቤተክህነት  የየክፍሉ ኃላፊዎች ፤ የደብራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፤ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አባቶች ፤ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፤ የየሰንበት  ት/ቤቱ አባላቶች ፤ የተመራቂ ተማሪ ወላጆች እንዲሁም ምዕመናን/ት ይገኛሉ።

 
#ኑ_ተማሪዎቻችን_በጋራ_እንመርቅ!!!
         
#የአዲስ_አበባ_ሰንበት_ትምህርት_ቤቶች_አንድነት
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

04 Dec, 05:32

2,037

በቦሌ ክፍለ ከተማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የገርጂ ምድብ የአንድነት መርሐግብር ህዳር 29/2017 ዓ.ም ከቀኙ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በገርጂ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ኆኀተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት አድራሻ ይከናወናል፡፡እርሶም መርሐግብሩ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

03 Dec, 07:27

2,049

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
በ2016 ዓ.ም በሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ እና በሀገረ ስብከት በብሔራዊ ደረጃ ምዘና ተደርጎላቸው ያለፉ የ4ኛ ፤ የ6ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች የዕውቅና መስጠት መርሐ ግብር !!!
#ታህሳስ_6_2017_ዓ_ም
#በቦሌ_መድኃኔዓለም_ካቴድራል ይደረጋል
#በመርሐግብሩ_ላይ 👇
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፤ ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፤ የጠቅላይ ቤተክህነት የየመሪያው ኃላፊዎች ፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና የክፍለ ከተማ ቤተክህነት የየክፍሉ ኃላፊዎች ፤ የደብራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፤ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አባቶች ፤ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፤ የየሰንበት ት/ቤቱ አባላቶች ፤ የተመራቂ ተማሪ ወላጆች እንዲሁም ምዕመናን/ት ይገኛሉ።
«ኑ_ተማሪዎቻችን_በጋራ_እንመርቅ!!!»
አዘጋጅ፡- የአዲስ_አበባ_ሰንበት_ትምህርት_ቤቶች_አንድነት
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

02 Dec, 09:58


Channel photo updated
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

02 Dec, 05:21

2,972

‹‹ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ›› መዝ 117፤26
ታላቅ የምርቃት መርሐግብር
በአ.አ ሀገረ ስብከት የአ/አ/ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ለ4ኛ ጊዜ በ2016 ዓ.ም 4ኛ 6 እና 10ኛ ክፍል ያስተማቸውን ተማሪዎች ታህሳስ 6/2017 በደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወአቡነ አረጋዊ ካቴድራል በድምቀት ያስመርቃል።በዕለቱም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት የየመምሪያው ሃላፊዎች የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ተመራቂ ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው ይገኛሉ። እርሶም በዕለቱ ተገኝተው ልጅዎን እንዲመርቁ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የአ.አ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

02 Dec, 05:20

2,606

በኢ/ኦ/ር/ተ/ቤ/ክ/የሰ/ት/ቤ/ማ/መ ማኀበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማዕከል <<ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ>> በሚል መሪቃል ልዩ የአባላት መርሐግብር ህዳር 22,2017 ዓ.ም በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወአቡነ አረጋዊ ካቴድራል አካሂዷል ።
በመርሐግብሩ ላይ የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል አባላት ወደቀድሞ የአገልግሎት ፍቅር እና ትጋት እንዲመለሱ መልክት ተላልፏል ።
ምንጭ፦የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

29 Nov, 06:53

2,865

በቦሌ ክፍለ ከተማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የገርጂ ምድብ የአንድነት መርሐግብር ህዳር 29/2017 ዓ.ም ከቀኙ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በገርጂ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ኆኀተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት አድራሻ ይከናወናል፡፡እርሶም መርሐግብሩ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

28 Nov, 10:50

5,299

🔔🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

በ2016 ዓ.ም በሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ትምህርታቸውን  ተከታትለው  ያጠናቀቁ እና በሀገረ ስብከት በብሔራዊ ደረጃ ምዘና ተደርጎላቸው ያለፉ 
#የ4ኛ , #የ6ኛ እና #የ10ኛ ክፍል  ተማሪዎች የዕውቅና መስጠት መርሐ ግብር !!!

#ታህሳስ_6_2017_ዓ_ም  
#በቦሌ_መድኃኔዓለም_ካቴድራል

#በመርሐግብሩ_ላይ 👇
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፤ ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፤ የጠቅላይ ቤተክህነት የየመሪያው ኃላፊዎች ፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና የክፍለ ከተማ ቤተክህነት  የየክፍሉ ኃላፊዎች ፤ የደብራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፤ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አባቶች ፤ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፤ የየሰንበት  ት/ቤቱ አመራር እና አባላቶች እንዲሁም ምዕመናን/ት ይገኛሉ።

 
#ኑ_ተማሪዎቻችን_በጋራ_እንመርቅ!!!
         
#የአዲስ_አበባ_ሰንበት_ትምህርት_ቤቶች_አንድነት

🔔🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

26 Nov, 06:57

3,144

.....መልካም ነገሮችን ካገኘህ ባንተ ምክንያት ሳይሆን ከእግዚአብሔር እንደመጡ እርግጠኛ ሁን ። ምክንያቱም ጌታ እንዳለው እሱ ብቻ መቼም ጥሩ፣ፍፁምና ቅዱስ ነው። "መልካም የሆነ አንድ ነው" ማቲ19:17
መልካም ነገሮችን በውስጥህ ባገኘ ጊዜ ኩራትና ትምክህት አይሰማ። በመመጻደቅ ራስህን ከመልካም ነገር ጋር አትገዳድር ለእግዚአብሔር ምስጋናን አቅርብ እንጂ በጽድቅ አትመካ ይህ ከእግዚአብሔር እንጂ ከአንተ አይደለምና። የመልካም ነገር መገኛ እሱ ብቻ ነው። እርሱ በባህሪው መልካም ነው። አንተ ከእግዚአብሔር ውጪ ቦይ ነህ። አንዳች ልትሰራም አትችልም። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ለአንተ አታድርግ አይገባህምና። ለምሳሌ ያህል አንተ እንደ ጨረቃ ብታበራ፣ ብርሃንህም አድጎ እንደ ጨረቃ ለብዙዎች ሲደርስም በእነዚህ ሁሉ ጨረቃ በጨለማው ሰማይ ላይ ነግሳ የምትሽከረከረው ብርሀኗን ቀን ከፀሀይ በመሰብሰብ እንጂ በራሷ የብርሃን ባለቤት እንዳልሆነች አስታውስ።ፀሀይ ከሌለች ጨረቃ በራሷ ልትኖር አትችልም። ስለዚህ ጨረቃ ስለ ብርሃኗ በፀሀይ ፊት መናገር ትችል ይሆን? ወዳጄ ሆይ አንተም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ራስህ ማውራት አትችልም፡፡ .....
ምንጭ፡- የመንፈስ ነፃነት
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

25 Nov, 05:15

2,764

የአ/አ/ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ከልማት ጋር ተያይዞ የመኖሪያ አካባቢ ለቀዉ ወደ ሌላ አካባቢዎች የተዘዎወሩ እና የሚዘዋወሩ  አባላትን  መንፈሳዊ ትምህርታቸው እና አገልግሎታቸው  ለማስቀጠል ውይይት ተደረገ ።

የአ/አ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ኅዳር 15/2017ዓ.ም ባደረገው ውይይት በኮሪደር ልማት ምክንያት ከየአጥቢያው የተነሱ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላቶቻቸው ወደ ሌሎች አካባቢዎች በመዘዋወራቸው በአጥቢያ ቤተክርስቲያኑ ብሎም በሰንበት ት/ቤቱ  አባላቶቻቸው ቁጥር ማነስ እና በአገልግሎት ላይ የሚያሳድረውን እና እያመጣ ያለውን ተግዳሮት አሳሳቢ መሆኑን በውይይቱ ላይ  በስንበት ት/ቤቶቹ ተነስቷል።
በዚህም ሰንበት ት/ቤቶቹ ከአባላት ከአካባቢው መነሳት ጋር ተያይዞ ከአምስት ፐርሰንት እስከ ሰማንያ ፐርሰንት አባላቶቻቸው መቀነሳቸው እና በስርአተ ትምህርት እየተማሩ ከነበሩ ተማሪዎች ከአንድ አጥቢያከ500 በላይ ተማሪ የነበረበት ወደ 30 የመቀነስ ሁኔታዎች እንደገጠሙ በውይይቱ ተነስቷል ከዛም ባለፈ ከሳምንታዊ ጉባኤያት ወደ ወርሐዊ ጉባኤ ለመዘዋወር የተገደዱ እንዳሉ እና በቀጣይም ሙሉ በሙሉ የህጻናት ጉባኤያት በአዲስ ሌላ ተማሪ  እስኪመጣ ሊቋርጥ የሚችልበት ስጋት መኖሩን ገልጸዋል።

በልማት አገልጋዮቻቸው  እና አባላቶቻቸው የተነሱባችው ሰንበት ት/ቤቶችም አሁን
ያለውን  የአገልግሎት  ችግር ለመቅረፍ እና አባላቶቻቸው በሄዱበት አካባቢ በሚገኝ አጥቢያ  አገልግሎታቸውን ለማሰቀጠል እና ከቤተክርስትያን እንዳይርቁ የሚያደርጉበትን ዋና ዋና ምክረ ሐሳቦችን ተወያይተዋል። ይህ ሁኔታ ቀጣይ ከመሆኑ አንጻር ሌሎችም ወደፊት ይህ ተግዳሮት ሲመጣ እንዴት ይለፋት ለሚለው ጥናቶች በችግሮቹ እና መፍትሔዎቻቸው ዙሪያ እንዲጠኑ እና ከባለድርሻ አካላት እና ከቤተክርስትያን የመዋቅር አመራር አባቶች ጋር ውይይት መደረግ እንዳለበት በጉባኤው ሀሳብ ተነስቷል

አንድነቱም ከክ/ከተማ ከሰንበት ትቤቶች አንድነት አመራሮች እና ከተነሺ  እና ተቀባይ አጥቢያ  ሰንበት ት/ቤት አመራሮች ጋር በመወያየት እና በማስተባበር አባላቱ ባሉበት መንፈሳዊ ትምህርታቸውን እና አገልግሎታቸውን ለማስቀጠል እንደሚሰራ እና የግንዛቤ መፍጠሪያ  ውይይቶችን በቀጣይም እንደሚደረግ ተገልጿል ። በማጠቃለያውም ሁሉም በጋራ በመተባበር በአጭር ጊዜ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜመሠራት ያለባቸውን ጉዳዮች ጥናት ላይ ተሞርኩዞ ተግዳሮቶቹን ለመቀነስ የሚፈጠሩ እድሎችን ለማስፋት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ለነገ ሳይል ከዛሬ ጀምሮ በጸሎት እና በተግባር ስራ ርብርብ እንዲያደርግ  ጥሪ ቀርቧል።

     ምንጭ ;;  የአ/አ ሰንበት ት ቤቶች አንድነት