AAFDA

@aafmhaca


AAFDA

22 Oct, 13:30


ተቋማት እራሳቸውን እንዲቆጣጠሩ (self-regulation) ለማስቻል ስልጠና ተሰጠ።

አዲስ አበባ 12/2/2017 ዓ.ም

የጤና ተቋማትና ባለሞያዎች ቁጥጥር ዘርፍ ተቋማት እራሳቸውን እንዲቆጣጠሩ( self-regulation )እንዲያደርጉ ለማስቻል ለማእከልና በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለተወከሉ የጤና ባለሞያዎችና ስልጠና ተሰጠ።

የጤና ተቋማትና ባለሞያዎች ቁጥጥር ዘርፍ ም/ል ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ተሬሳ ተቋማት በራሳቸው ቁጥጥር በመስራት (self-inspection audit) እራሳቸውን ማብቃት እንዲችሉ የተጀመረውን ስራ ወጥነት ባለው መልኩ ለማስተግበርና ስራዎችን ለመደገፍ ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን ግልጸዋል።

የስልጠናው አላማ እራስን መቆጣጠር ( self-regulation ) ማለት ምን ማለት እንደሆነ ፣እራስን መቆጣጠር ስናካሂድ ልንከተላቸው የሚገቡ ሂደቶች ፣ የስታንዳርድ ምንነትና አተገባበር ምን እንደሚመስል በመገንዘብ ስራውን ወጥነት ባለው መልኩ ወደ መሬት ለማውረድ እንዲያስችል እንደሆነ ተገልጻል።

የጤና ተቋማትና ባለሞያዎች ቁጥጥር ዘርፍ ዳሬክተር አቶ ገልገሎ ኦልጅራ በጤናና ጤና ነክ ስታንዳርድ ዙሪያ ስልጠና የሰጡ ሲሆን የስታንዳርድ ምንነት ፣የስታንዳርድ አስፈላጊነት ፣የ ፈቃድ እና የአስገዳጅ ስታንዳርድ ምንነት እንዲሁም የጤና ተቋማት ሊከተሉት ስለሚገባ ስታንዳርድ ፣እንደሀገር ሊተገበሩ የወጡ አዲስ የጤና ተቋማት ስታንዳርድ ዙሪያ ፣የተሻሻሉ፣ አዲስ የወጡ እንዲሁም በተሻሻሉ ስታንዳርዶች ዙሪያ የተደረጉ ዋና ዋና ለውጦች ፣ ተቋማት እራስ መቆጣጠር ሲሰሩ የሚሰጡት የነጥብ አሰጣጥ እንዲሁም ደረጃ አሰጣጥ አሰራር ዙሪያ ሰፊ ስልጠና ሰተዋል።

የጤና ተቋማት የቁጥጥር ባለሞያ ወ/ሮ ዲና የጤና ሚኒስተር የራስ መቆጣጠር ( self-regulation) ለማስተግበር ባወጣው መመሪያ ዙሪያ ስልጠና የሰጡ ሲሆን የራስ መቆጣጠር ( self-regulation ) ለማስተግበር መከተል ስለሚገባቸው ሞዴልና የአሰራር ቅደም ተከተል ፣ እራስ መቆጣጠር ማድረግ የሚገባቸው ተቋማት የሚመረጡበት መስፈርቶች፣እራስ መቆጣጠር ለማስተግበር የሚጠቀሙባቸው መርሆች እንዲሁም ስራዎችን ለማስጀመር ከእያንዳንዱ ባለድርሻ የሚጠበቁ ተግባርና ሀላፊነት በተጨማሪም የክትትልና ድጋፍና ሪፖርት አደራረግ ሂደቶች ላይ ሰፊ ስልጠና ተሰቶባቸዋል።