የልብ ቋንቋ

@yefkr_tube


🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀

⚡️WELLCOME TO የልብ ቋንቋ💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE

Contact @ethio1226

❤የልብ ቋንቋ❤ (Amharic)

የልብ ቋንቋ ቻናል በተጠቀሰው ውይይት ቋንቋ ምርጥ ፍቅር ቃላትን፣ ግጥሞችንና መልኩ ታሪኮችን ያገኛሉ! ስለሆነ ከዚህ ቻናል ውስጥ የቀረዉለት አስተያየት ፕላቶችን ማንም ብቻ የለም። ስለመረጃዎትና ግለሰብ ይሠራል፡፡ እባኮት ወደ @ethio1226 ገጽ ተመልከቱ፡፡

የልብ ቋንቋ

22 Oct, 17:38


😋የጠበሳ ዘዴዎች ለወንድም ለሴትም 👌🤦‍♀ሴቶች ደፍረዉ የማይናገሩት ግን ከወንዶች🤷‍♂ የሚጠብቋቸዉ 7 ነገሮች❤️❤️
           ⬜️⬜️OPEN⬜️⬜️

የልብ ቋንቋ

22 Oct, 17:31


ጥቁር ልብን ያላነበባችሁ ክፍል 4 ተለቋል ከታች ባለው ቻናል መከታተል ትችላላችሁ
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/yefikirtelegramet

የልብ ቋንቋ

22 Oct, 17:00


    🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

                 
💙  መራራው እውነት   🌹🔸


❤️  ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ❤️



                       #ክፍል_ 4️⃣


እሱ ሚወጣበትን ስዓት እየጠበኩ አውቄ እንዲያየኝ እንዲያዋራኝ እወጣለሁ ሆን ብዬ  ሰላም ብዬው የማላውቀውን  ሰላም እለዋለሁ እሱ ግን እንኳን ሰላም ሊለኝ ጭራሽ ቀና ብሎ እንኳን አላይ ሲለኝ አይ በቃ ጠዋት ስለሆነ ሰዎች ያዩኛል ብሎ ነው ብዬ አሰብኩ እና ማታ ሲመጣ ልጠብቀው ወሰንኩ ።

እንዳሰብኩትም ማታ ውጪ ማንም የለም እስኪመጣ ጠበኩት አሁንም ጠዋት እንዳረኩት ሰላምታ ሰጠሁት እሱ ግን ምንም ሳይለኝ እራቱን ሊበላ ሳይመለከተኝ እንኳን ገባ።

ክፍሌ ገብቼ እንደው በቃ ተብከነከንኩ የምይዘው ምጨብጠው ጠፍኝ ንዴት አንገበገበኝ እንዴት ይህን ሁሉ ግዜ አያየኝም ጭራሽ ደሟ ለሱ ብዬ እየወጣሁ ወይኔ ወይኔ እያልኩ እየተብከነከንኩ ምን ልሰራ እንደሆነ አላቅም እራት የሚበሉበት ቤት ሄድኩኝ ሲስቅ አየሁት አቤት ፈገግታ አቤት ሳቅ በዛ ላይ ጥርሱ እንዴት አባቱ እንደሚያምር የጥጥ ፍልቃቂ ነው ሚመስለው ሳያዩኝ  ቀስ ብዬ ወደ ክፍሌ አመራሁ።

ክፍሌ ቆይቼ ሳብሰለስለው እንደዚ ተጫዋች ሳቂታ ከሆነ ለምን እኔ ጋር እንደዛ አይሆንም እኔ አስጠልቼው ነው አልታይ ያልኩት እኔ መጠላት እችላለሁ ሁሌም እኮ እንደምወደድ ነበር ማስበው ለካ ሰው እኔን መጥላት ይችላል  ብዬ ከልቤ ከፍቶኝ ለመጀመሪያ ግዜ አለቀስኩ።

እዛው በተቀመጥኩበት እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ ጠዋት ተነሳሁ እንደ ሁልግዜው እሱን ለማየት አልወጣሁም እሱ ከሚወጣበት ሰዓት አረፋፍጄ ተነሳሁ ምንም ምሰራው አልነበረም ትምህርት እንኳን የኔታ እቤት ድረስ እየመጡ ነበር የሚያስተምሩኝ እሳቸውን ተዘገጃጅቼ መጠበቅ ጀመርኩ ሲመጡ አስተምረውኝ ለነገ የቤት ስራ ሰጥተውኝ ሄዱ።
እኔም የቤት ስራውን ሰበብ አድርጌ ከቤት አልወጣሁም ነገር ግን ሲመጣ ቀስ ብዬ ተደብቄ በቀዳዳ አየዋለሁ የዛኔ ደስ ይለኛል።

እየውልህ ልጄ በእልህ የጀመርኩት ነገር መልሶ እራሴ ላይ ችግር አመጣ አፈቀርኩት መቅናት መነጫነጭ ከሰው ጋር አለመቀራረብ ጀመርኩ ላፍታ ውጭው የሚናፍቀኝ ልጅ ከቤት አልወጣም ምወጣውም እራት ለመብላት ወደ እነ አበይ የሚቀመጡበት ቤት ነው በልቼ ትንሽ አውርቼ ወደ እራሴው ክፍል እመለሳለሁ ይህ የየእለት ተግባሬ ሆነ።

እሱን ግን ሳላየው አልውልም ነበር ጭራሽ ደሟ ከሴቶች ጋር ካየሁት ደሜ ፍልት ይላል ከሱ ጋር ስትስቅ ያየኋት ልጅ እንዴ ለአይኔ ትቀፈኛለች ባላያት እኔ ጋር ባትመጣ እንደው ደስታዬ ግን እነሱን መግፋት ማንቋሸሽ ስለ ማልፈልግ ምንም አልላቸውም ንዴቴን ዋጥ አድርጌ ለመያዝ እሞክራለሁ እንጂ ከአፌ ክፍ አይወጣም ነበር።

እኔ ብቻ እያፈቀርኩት ሲስቅ ደስ ይለኝ ስለነበር ተደብቄ እያየሁት አንዳንዴም ሳላየው ከዋልኩ ልክ ግቢ ውስጥ እንደ ሚዞር ሰው በበሩ በኩል አልፌ እንዳለ እና እንደሌለ አይቸው እገባለሁ ።

እኔ 16 አመት ሲሞላኝ አባቴ በሰው እጅ ተገደለ እናቴ መገደሉን ልክ ስትሰማ ታመመች ለ አልጋ እስክትዳረግ ድረስ ታመመች። እንደማትድን ስታውቅ አባትህን አስጠርታ ቤት ውስጥ ያሉትን ከብቶች እና እህል አውጥቶ እንዲሸጥ ነገረችው እሱም እንደታዘዘው ሸጦ መጣ ለሁሉም ሰራተኞች ደሞዛቸውን እየከፈለች ሸኘቻቸው።

አሰግድ ግን ምንትዋብን ትቼ የትም አልሄድም ልጄን ለማን ጥዬ ብላ እንቢ አለች እናቴ ግን አይሆንም አሷን ሁነኛ ሰው ገር ነው የማሳርፋት አትስጊ ብላ ሸኘቻት።

በመጨረሻ እኔ እና አባትህን አንድ ላይ ጠርታ በሉ ልብ ብላችሁ አዳምጡኝ አውርቼ እስክጨርስ ድረስ እንዳታቋርጡኝ ብላ ወሬዋን ጀመረች

አንተ እንደምትወዳት ባታሳያትም እንደምትወዳት አቃለሁ አንችም ልብሽ ለሱ እንደከጀለ አቃለሁ በሉ ይሄ አባትሽ በህይወት ዘመኑ የቆጠበው ገንዘብ ነው ይህ ደሞ ከብቶቹ እና አህሉ ተሽጦ ለሰራተኞቹ ከፍዬ የተረፈ ገንዘብ ነው አዲስአበባ ደሟ አባትሽ በአጎትሽ አማካኝነት በስምሽ የገዛ ባዶ መሬት አለ በዚ ገንዘብ ቤት ስሩበት እና አብራችሁ ኑሩ እኔ ከዚ በላይ አብሬ አችሁ ልቆይ አልችልም ልጄን ጠብቃት አደራ ብላ አረፈች።

ይቀጥላል.....




🔻ክፍል 5️⃣1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔

የልብ ቋንቋ

22 Oct, 16:22


ቤተሰብ እንዴት አመሻችሁ መራራው እውነት ክፍል 4 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?

የልብ ቋንቋ

21 Oct, 19:06


የመርካቶ ገበያ ማዕከል እስከዚህ ሰዓትድረስ በምታዩት መልኩ እየነደደ ነው። ከተማ አስተዳደሩ እሳቱን ለማጥፋት መኪና መጠቀም ስላልቻልኩ በሂሊኮፕተር ለማጥፋት ልሞክር ነው ብሏል። ያሳዝናል!

የልብ ቋንቋ

21 Oct, 19:00


    🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

                 
💙  መራራው እውነት   🌹🔸


❤️  ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ❤️



                       #ክፍል_ 3️⃣


እየውልህ ቅዱሴ እኔ ያው እንደምታውቀው የወሎ ልጅ ነኝ እና ቤተሰቦቼ በጣም ሀብታም እና የተከበሩ ነበሩ በዛ ላይ ለቤተሰቦቼ ብቸኛ ልጅ ነኝ ሀብት ወራሽ ስም አስጠሪ የቤተሰቤ መኩሪያ ነበርኩ አይ ነበርኩ ምን ያደርጋል ቁጭት ብቻ በል ወደ ታሪኬ ልመለስልህ ልጄ።

እኔም እንደ ገጠር ልጅ ከብት ጥበቃ በጎች እረኝነት አልወጣሁም አባቴ እረኛ ቀጥሮ ነበር ከብት የሚያስጠብቀው ከቤት የምወጣበት ምክንያት የለኝም ከእኩዮቼ ጋር እንድጫወትም አይፈቀድልኝም ጭቃ ሳቦካ ገደል ለገደል ስሮጥ ውሀ ስረጫጭ መታየት አልችልም ጓደኛም መያዝ አልችልም አባቴ ትልቅ የተከበረ ባለሀብት ስለሆነ የ አየለ ልጅ እኮ ወንዝ ውሀ ስትረጫጭ ጭቃ ስታቦካ ታየች ከ እንትና ልጅ ጋር ከ እገሌ ልጅ ጋር እዛ መንገድ ዳር ቆማ ታየች  መባልን አይፈልግም ይልቅስ እሱ ሚፈልገው የ አቶ አየለ ልጅ እኮ  ቤት ውስጥህ በክብር የተቀመጠች እራሷን የምጠብቅ የቤተሰቧንም ክብር የምታስጠብቅ ቆንጆ እዩኝ እዩኝ የማትል መልከመልካም ልጅ ናት በዛ ላይ ፀባይዋ መባልን ስለሚፈልግ ነበር ነፃነቴን ያጣሁት።

ታድያ ቅዱሴ ቤት ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ እንዴት ይእወዱኛል መሰለህ በልቼ ምጠግብ አይመስላቸውም ነበር በተለይ አሰግድ ምትባል ሰራተኛ ነበረችን እሷ ደሟ ለእኔ ያላት ፍቅር እና እንክብካቤ ይለያል ከእናቴ በላይ ነበር ምትንከባከበኝ መሀንም ስለነበረች ይመስለኛል ለኔ ያላት ፍቅር ያየለው።

እናም እኔ 14 አመት ሲሟላኝ አባትህ እኛ ቤት አራሽ ሆኖ የተቀጠረው አስታውሳለሁ እኛ ቤት ሲገባ ከእኔ ጋር ምንም አይነት ቅርበት አደለም ቅርበት እኔ በማልፈበት እንዳያልፍ ቀና ብሎ እንኳን እንዳያየኝ አስጠንቅቆ ነበር አባቴ የቀጠረው ።

እሱም በታዘዘው መሰረት አጠገቤ ሳይደርስ እኔ ባለሁበት ሳይገኝ ስራውን መስራት ጀመረ እኔ ግን እንዴት አያየኝም እንዴት ችላ ይለኛል እዚ የተቀጠሩት በሙል እኮ አባቴ የሰጣቸውን ትዛዝ ትተው እኔ ያለሁበት አይጠፉም በዚ ምክንያት ከ አንድ ሳምንት በላይ የቆየ ወንድ ሰራተኛ አልነበረም አባትህ ግን ሳምንታትን አለፎ ወራት በታዛዥነት ስራውን አክብሮ ኖረ።

አባቴም በጣም የሚመካበት ሰራተኛው ሆነ ላገኘው ሰው ሁላ ታማኙ አገልጋዬ ነው እያለ ያስተዋውቀዋል እኔ ደሟ ሲወጣም ሲገባም ጠብቄ እወጣለሁ እሱ ግን ዞሮም አያየኝ ይሄ ነገር እልህ እያስያዘኝ መጣ እንዴት 1 አመት ሙሉ ተሳስቶ እንኳን አያየኝም እዚ ቤት ከነበሩት ሌሎች ሰራተኞች በምን ይለያል አያልኩ መብከንከን ጀመርኩ ጭራሽ እንደውም ፍቅር አስዤ ባላሳብደው እኔ ምንትዋብ አይደለሁም ብየ ዛትኩ በቃ ከዛን ቀን በኋላ እሱ ለእኔ ስሜት እንዲኖረው እንዴት ማድረግ እንዳለብኝ የነረ ሚሆንበትን መንገድ እሱ እንዲያየኝ እንዲቀርበኝ ለማድረግ ማሰብ እና ማውጠንጠን ጀመርኩኝ።



ይቀጥላል.....




🔻ክፍል 4️⃣1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔

የልብ ቋንቋ

21 Oct, 18:56


አላችሁ ክፍል 3 ይለቀቅ?

የልብ ቋንቋ

21 Oct, 18:10


የዛሬው ክፍል አጭር ስለሆነ ክፍል 2ን በፍጥነት 1ዐዐ Like ሙሉትና አንድ ክፍል ይለቀቃል

የልብ ቋንቋ

21 Oct, 17:56


    🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

                 
💙  መራራው እውነት   🌹🔸


❤️  ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ❤️



                       #ክፍል_ 2️⃣


እሽ ምሳ እየበላን ብናወራስ የኔ ልጅ ምን ትላለህ ብላ ወሬ ጀመረች
አይ አይሆንም እህቴ እና ወንድሜ እቤት ብቻቸውን ናቸው ገና ከማለቴ ከአፌ ቀምታ ቶሎ ብላ ማማ እና ባባ ናቸው ይዘሀቸው ና አብረውን መሄድ ይችላሉ አለችኝ የዚች ሴትዮ ነገር ይበልጥ ግራ እያጋባኝ መጣ አንደኛ ነገር የግቢውን በር ማን እንደከፈተላት ሳላቅ ገባች።
ምን አልባት ከተከራዮቹ ውስጥ አንድሰው ከፍቶላት ይሆናል ብዬ አለፍኩት  ቀጥላ እናቴ አንድም ቀን እንኳን ጓደኛ ይቅር እና እህት ወንድም ኖሯት አያቅም ዛሬ የእናትህ ጓደኛ ነኝ ብላ መጣች እሺ የድሮ ጓደኛዋ ነች ይባል ለምን ስትሞት ጠብቃ መጣች ጭራሸ ደሞ ስለ እነ ማማ ማወቋ  ብቻ ግን ትንሽም ቢሆን ሁኔታዋ አልጣመኝም።

እሺ እንዳልክ ይሁን ስሜ አመለ እባላለሁ ነብሷን ይማረው እና የእናትህ የረጅም ግዜ ጓደኛዋ ነኝ ጥሩውንም ደጉንም አብረን አሳልፈናል ከእናትህ ጋር አብረን ነው የተማርነው ይገርምሀል እናትህ እንዴት ያለች ጎበዝ ተማሪ ነበረች መሰለህ ደሞ በዛ ላይ መልካም ሰው ነበረች እያለች መቀባጠር ጀመረች ከሰማኋት ያልሰማኋት ይበልጣል ።

ብዙ እውነት የማይመስሉ ነገሮችን ቀባጣጥራ ስጨርስ እና አሁን ለምን መጣሽ ምን ፈልገሽ መጣሽ ብዬ ጠየኳት

እሷም እየውልህ ቅዱሴ እናትህ ትምህርትቤት እያለን ትልቅ ውለታ ውላልኝ ነበር ብላ ማውራት ስጀምር ወሬዋ ውሸቷ ሰለቸኝ በቃ ከምችለው በላይ ሆነችብኝ ውሸት በትልቅ ሰው እንደዚ ያስጠላል ኸረ በስማም  ቀላ ታየች ድምጿ እራሱ አስጠላኝ በቃሽ በሚል ቁጣ በታዘለበት ጬኸት ወሬዬን ጀመርኩ ከዚ በላይ ውሸትሽን መስማትም ሆነ ላዳምጥሽ አልፈልግም በቃ ድጋሜ በስህተት እራሱ ላይሽ አልፈልግም ደሞ ከእህቶቼ እራቂ እነሱ ስር ባገኝሽ አጠፍሻለሁ ተግባባን ብዬ እጮኩ የምታወራው እስኪጠፍት ተደናግራ እስክትርበተበት ድረስ ጮኬ ተናግሪያት ከመኪናው ወርጄ በሩን ወርውሬ ዘጋሁት።

ቤት ከገባሁ በኋላ እናቴ ስለ እሷ የነገረችኝን ታሪክ ፎቶዋን እያየሁ ማስታወስ ጀመርኩ አስታውሳለሁ ቡና እያፈላች ነበር የነገረችኝ በዛው ቅፅበት ስለ እሷ እያሰብኩ እንባዬ ግጥም ብሎ ያለችኝን ማስታወስ ጀመርኩ።





ይቀጥላል.....




🔻ክፍል 3️⃣1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔

የልብ ቋንቋ

21 Oct, 17:32


ቤተሰብ እንዴት አመሻችሁ መራራው እውነት ክፍል 2 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?

የልብ ቋንቋ

21 Oct, 05:10


የዚህ ቻናል admin መሆን እሚፈልግ  @ethio1226 inbix አዋሩኝ:

channel link
https://t.me/+Qb4RnEBZgx4yZTM8

የልብ ቋንቋ

20 Oct, 17:31


    🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

                 
💙  መራራው እውነት   🌹🔸


❤️  ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ❤️



                       #ክፍል_ 1️⃣



በህይወቴ ካሳለፍኳቸው ቀናቶች እንደ ዛሬ ቀን ከባድ አስቀያሚ ክፉ ቀን ፍፁም ባዶነት የተሰማኝን ወቅት አላስታውስም።

ለምን እንደሆነ ታቃላችሁ የሕይወቴ አካል የሆነችውን ለኔ መኖር ለኔ መደሰት ለኔ ሰላም የእኔ እዚች ምድር መፈጠር ምክንያት የሆነችውን እናቴን እያየኋት 🚐 መኪና ቀማኝ ለ ልጆቼ እንጂ ለእኔ የማትለው ለኛ ስትኖር ለራሷ ሳትኖር የእኛን ሆድ ለመሙላት ስትል ሞልቶ የማያቀውን ህይወቷ እንደጎደለ ደርሼ እሞላላታለሁ ስል ሳልሞላላት ሞት ቀደመኝ።

ፈጣሪ ግን ምንበደልኩት እና ነው እኛን ትታን እንድትሄድ ፈጣሪ የፈረደብን እኛ እኮ ካለ እሷ ማንም የለንም ብቻችንን እኮ ነን ለምን ወሰድካት ለምን ለምን እኛ አናሳዝንህም እኛ በብቸኝነት ኑሮ ስንባዝን ይሁና አንተ ካልከው አይቀየር።

እማዬ ከሞተች ዛሬ ሳምንት ሞላት እኔ አሁን ታናሽ እህቴን እና ወንድሜን ማስተዳደር ሀላፊነት የኔ ነው ምን እንደማደርግ ምንሰርቼ እንደማኖራቸው አላቅም እናቴ ናት የውጭውንም የቤቱንም እሷ ነበረች የምትሰራው እኔ ትምህርቴ ላይ ብቻ እንዳተኩር ብቻ ነበር ምትፈልገው ግን ምንያደርጋል የኔም ትምህርት ቀረ እሷም ቀረች ብቻ አሁን የማቀው ነገር ቢኖር የዩንቨርስቲ ትምህርቴን እንደማቆም ብቻ ነው ምን ሰርቼ እንደማኖራቸው ግን አላቅም ግራ ግብት ብሎኛል ደሞ በዛ ላይ ማማ እና ባባ እማዬ እያሉ እያለቀሱ ነው ደሞ መንታ ስለሆኑ ስሜታቸው ተቀራራቢነት አለው።

የእነሱን ለቅሶ ላቁም ወይስ ጭቅላቴ ውስጥ የሚመላለሰውን ጬኸት ላቁም እራሴን ማረጋጋት ጭራሽ አልቻልኩም ማሰብም ጭምር ብቻ በሰአቱ ምፈልግ የነበረው የነሱን ለቅሶ ማቆም ነበር።

እንደምንም ብዬ እራሴን አረጋግቼ አባብዬ አስተኛኋቸው እኔም ለካ እነሱን ሳስተኛ በዛው እንቅልፍ ወስዶኝ ነበር ከንቅልፌ የነቃሁትም ቅዱስ ቅዱሴ እያ ለ በተደጋጋሚ  ስሜን የሚጣራ የማላቀው የሴት ድምፅ ነበር ያባነነኝ።
አቤት ብዬ ወጣሁ ሰላም ቅዱስ አለችኝ እኔም አፀፋውን በሰላምታ መለስኩላት ሲያዩአት እድሜዋ ከእናቴ እድሜ እኩል ትመስላለች ቀይ እና ጥሩ አቋም ላይ ያለች ትመስላለች አለባበሷ በጣም ያማረ ነው በእጇ ቦርሳ እና የመኪና ቁልፍ ይዛለች አነጋገሯ እረጋ እና ሰከን ያለ ነው ሳስበው ሴትየዋ ሀብታም ቢጤ ትመስለኛለች።

እ እየውልሕ የኔ ልጅ በማለት ንግግሯን ጀመረች እኔ የእናትህ የረጅም ጊዜ ጓደኛ ነኝ አይተኸኝም ስለ እኔ ሰምተህ ስለማታውቅ ትንሽ ግር ሊልህ ይችላል ስለዚ ቅድሚያም እራሴን ላስተዋውቅህ ግን የኔ ልጅ ብዙ መቆም ስለማልችል መኪና ውስጥ ገብተን እናውራ ብላ ውጭ የቆመ አንድ ጥቁር range rover መኪና ጠቁማ አሳየችኝ እኔም እሺ ብዬ በሩን ዘግቼ ከግቢው አብረን ወጣን





ይቀጥላል.....




🔻ክፍል 2️⃣1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን!
😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔
💔 https://t.me/yefkr_tube 💔

የልብ ቋንቋ

20 Oct, 17:25


መራራው እውነት የተሰኘ አደዲስ ታሪክ ሊለቀቅ ነው ዝግጁ ናችሁ?

የልብ ቋንቋ

20 Oct, 17:02


ፖሉ እየሰራ ባለመሆኑ ሀሳባችሁን comment ላይ አሳውቁን

ቤተሰብ ዛሬ በዋናው ቻናል አዲስ ታሪክ እንጀምራለን ። ስንቶቻችሁ ናችሁ  በሌላ ቻናል የተጀመረውን ጥቁር ልብ የተሰኘ ታሪክ ከዚህ በፊት ያነበባችሁት?

የልብ ቋንቋ

20 Oct, 14:36


ቤተሰብ እንዴት ናችሁ ዛሬ ምሽት 2:30 አዲስ ታሪክ እንጀምራለን
100 like እንጠብቃለን ፈጠን አድርጉት

የልብ ቋንቋ

20 Oct, 07:14


Guys በዚህ ወር መጨረሻ list እሚደረግ $cross የተባለ  አዲስ   project ተጀምሯል

❗️ብዙ ሰው እየሰራው አደለም ፈጥኖ የጀመረ ትርፋማ ይሆናል

❗️pre market ላይ  1$cross=0.2$ እየተሸጠ ነው

❗️Task ብቻ ሰርታችሁ ከ25ሺ point በላይ ታገኛላችሁ 
❗️task ስተሰሩ  ስልካችሁን እንዳይሞላባችሁ  እያንዳንዱን የግድ join ማድረግ  አይጠበቅባችሁም  ከፍታችሁት ስትመለሱ  task point ይሰጣችዃል(✔️)

❗️0.2$  የpre marketun price እንተወውና  በ 0.02$ list ቢደረግ  Task ብቻ ሰርተን ያገኘነው 25ሺ point   ወደ 500$ አካባቢ ይመጣል

❗️አስታውሱ list እሚደረገው በዚህ ወር መጨረሻ ነው 10ቀን ይቀረናል

❗️verify የሆነ Bitget acount ሊኖራችሁ ይገባል የሌላችሁ  ቀላል ነው  በመታወቂያችሁ መክፈት ትችላላችሁ


☄️አሰራሩ
1.Emial address አስገቡ 
2.Bitget UID አስገቡ
3.Bitget $cross address አስገቡ
4.task ጨርሱ 

❗️ከላይ የፃፍኩት ቅደም ተከተል አደለም bitget acount የሌላችሁ   emial  አስገብታችሁ task መጨረስ ትችላላችሁ ነገር ግን  connect ለማድረግ የግድ Bitget acount መክፈት ያስፈልጋል

❗️ task ከጨረሳችሁ በዃላ በቀጣይ እንዴት ከ Bitget acount  ጋ connect ማድረግ እንደሚቻል post እናደርግላችዃለን


ለመጀመር.  
👇👇👇👇👇👇
https://swee.ps/CmqCiF_vUAtLla

የልብ ቋንቋ

19 Oct, 11:31


‼️Guys wcoin እየሰራችሁ ነው አደል
october 27 list ይደረጋል

‼️ያልጀመራችሁ  8 ቀን አላችሁ task ሰርታችሁ ብዙ point መሰብሰብ ትችላላችሁ አሁን ጀምሩ


https://t.me/wcoin_tapbot?start=NTkzODg4ODA1Nw==

የልብ ቋንቋ

18 Oct, 17:40


🔸🔸🔺🔺🔹🔸

       ❤️ጥቁር   ልብ❤️

ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ
💟

          ክፍል
1️⃣

እናቴ በገጠሪቷ የሀገራችን ክፍል ነው ተወልዳ ያደገችው አባቴም እንደዛው የአንድ ሀገር ልጆች ናቸው።

እናቴ የሷ እኩዮች ባል ሲመጣላቸው ሲዳሩ እናቴ ግን አንድም ባል ሳይመጣላት ቀረ ታናናሽ እህቶቿም ታላቋም ወንድሟም በትዳር ሲጣመሩ
........

ሙሉውን ከታች ያለውን ቻናል join ብላችሁ ተከታተሉ
👇👇👇👇👇

https://t.me/yefikirtelegramet
https://t.me/yefikirtelegramet

የልብ ቋንቋ

17 Oct, 18:58


ቤተሰብ እንዴት አመሻችሁ በዋናው ቻናል አዲስ ታሪክ ሰሞኑን እንጀምራለን እስከዛው ጥቁር ልብ የተሰኘ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በሌላ ቻናል ልናቀርብላችሁ ነው

ይጀመር ካላችሁ 100like ከሞላ አሁን እንጀምራለን

የልብ ቋንቋ

16 Oct, 20:34


#Alert🚨

ከደቂቃዎች በፊት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ለሰንከንዶች የቆየ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዘረት እንደሰሙ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል።

" በተለይም ፎቅ ላይ በደንብ ይታወቅ ነበር ' ብለዋል።

ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት በቀናት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።

ሰሞኑን በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል።

ይህም የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች ድረስ እየተሰማ ነው።

tikvahethiopia