Wollo university kombolcha campus student union

@wollostu


ይህ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተማሪዎች ህብረት በኩል መረጃ የሚያገኙበት ቻናል ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇
wollostu@2012

👇👇👇👇👇👇
ለጥያቄ፡ ለአስተያየትወ ይሄን ይጠቀሙ
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻
@Wollouniversitystudentunionbot

Wollo university kombolcha campus student union

21 Oct, 17:14


for all freshman  student final exam scheduled

Wollo university kombolcha campus student union

19 Oct, 08:32


👩‍🎓👨‍🎓👩‍🎓👨‍🎓👩‍🎓👨‍🎓👩‍🎓👨‍🎓👩‍🎓👨‍🎓👩‍🎓
ውድ ተመራቂ ተማሪዎች አንኳን ደስ አላችሁ አንኳን ለዚች ልዩ ቀን አደረሳችሁ እያልን በዛሪው እለት ማለትም 9/02/17 ዓ.ም በወሎ ዩኒቨርስቲ ኮምቦልቻ ካምፓስ አዳራሽ የወሎ ዩኒቨርስቲ የሴኔት አባላት፣የክብር እንግዶች፣ተመራቂ ተማሪዎች እና የተመራቂ ተማሪ ወላጆች በተገኙበት ከወሎ ባህል ቡድን ጋር በደማቅ ሁኔታ በማስመረቅ ላይ ይገኛል።
    ውድ ተመራቂ ተማሪዎች አንኳን ደስ አላችሁ አንኳን ደስአለን💐💐💐

Wollo university kombolcha campus student union

18 Oct, 11:15


🎓🎓🎓🎓🎓
ውድ ተመራቂ ተማሪዎች ከጅማሮው እስከ ፍፃሜው በፈተና ታጅባችሁ ለዚህ ስለበቃችሁ  ክብርና ምስጋና ይገባችኋል እንኳን ደስ አላችሁ!!! ተማሪነት በብዙ ፈተናዎች የታጀበ  መሆኑን ያለፋበት ሁሉ ህያው ምስክር ናቸው በተለይም የዩኒቨረስቲያችን ተመራቂ ተማሪዎች በብዙ ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ ቸግሮት ተፈትናችሁ ለዚህ በቅታችኋል፡፡አዎ ስንኖር ሁሉም የድል አክሊሎች የጀግንነት ኒሻኖች የአሸናፊነት ዋንጫዎች በጠቅላላው የምድር በረከት የሚገኘው ፈተናዎች ሲታለፉ ነው::እናንተም ሁሉንም ውስብስብ ችግሮች አልፋችው ለዚህ ስለበቃቸሁ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ ት/ት ምንጊዜም በየትም ሀገር ቢሆን ከዘመን እና ከቦታ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በአለም መጀመሪያ አደለንም ወይም በስልጣኔ ታሪክ መጀመሪያ ላይ አደለንም፡፡ በአለም መጨርሻም ላይ አደለንም ይልቁንም በመካከል እንጅ በኋላችን ብዙ ዘመናት አልፈዋል በነዚህ ዘመናት ውሰጥ አባቶቻቸን በብዙ ትግል ደከመው ያሰገኙላቸሁ የሰልጣኔ ቅርሶች ይገኛሉ እወ በኢኮኖሚ የደቀቀች ሀገር ተረክባችሁ ይሆናል ፤ የትምህርት ፖሊሲዋ በየግዜው የሚዘበራረቀባት አገር ተረክባችሁ ይሆናል ነገር ግን ለዘመናት በሀገራቸን ላይ ከተደረገው ስውር ሴራ እንጻር የትም የሌለ ነጻነት በማንም ያልተበረዘ ማንነት ተረክባችኋል፡፡ እነሆ ከዚህ በኋላ ስውር የእውቀት አለም መጋረጃ ለእናንተ ተገልጡዋል፡፡ከእውቀት መቅደስ ሚስጢር ተካፋይ ብቁ እጩ መሆናችሁ ተረጋግጡዋል፡፡ስለሆነም ዋናው የእውቀት ፍለጋ ዋናው ትምህርት ቤት ከፊት ለፊታችሁ ይገኛል፡፡ እስካሁን በዩኒቨርስቲአችሁ ቆይታቸሁ ለህይወታችሁ የሚሆን ትጥቅ ይዛችኋል። ለችግሮቸመፈቻ ቁልፍ እውቀት መሆኑን ተረድታችኋል ስለሆነም ይህን ነባራዊ አለም ለመቀበል ልክ በአለት ላይ እንደተሰራ ቤት የጸናችሁ እንጂ የምትሸበሩ አደላችሁም :: የእምዬ ኢትዮጲያ ሀገራችን መጪ ጊዜዎቿ በእናንተ ነው የሚወሰነው ሆኖም ግን በተማራችሁበት የሙያ መስክ ብቻ በመሰማራት ራሳችሁን እና ወገናቸሁን አገልግሉ በሚል ምክር መታሰር የለባችሁም ፡፡ ይልቁንም የልባቸሁን መሻት ተከተሉ እንጂ፡፡የስለጠናቸሁበት ሙያ መነሻቸሁ እንጂ መዳረሻቸሁ ለመሆኑ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፤ ከዩኒቨርሲቲ የቀሰማችሁት አውቀት መስፈንጠሪያ እንጂ መታሰሪያ ገመድ አይሁንባችሁ የሰው ልጅ ሲፈልግ ታምረኛ ሲፈልግ ስበበኛ ይሆናል፡፡ በቆይታችሁ በዩኒቨርስቲያችን ላደረጋችሁት መልካም ስብእና ሁሉ ምስጋናችንን እያቀረብን መልካም የህይዎት ዘመን እንድሆንላችሁ እንመኛለን፡፡
እንኳን ደስ አላችሁ!!!!!

የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
https://t.me/wollostu

Wollo university kombolcha campus student union

18 Oct, 09:41


🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓
ውድ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ
እንኳን  ደስ አላችሁ!!!
ከ9:00 ስዓት ጀምሮ ባይንደር ስለምንሰጥ በተወካይ በኩል ተማሪዎች ህብረት ቢሮ በመምጣት እንድትወስዱ ። በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ
https://t.me/wollostu

Wollo university kombolcha campus student union

16 Oct, 15:49


🔊🔊ማስታወቂያ
ለግቢያችን ፍሬሽ ተማሪዎች
ውድ ተማሪዎች እንኳን ለ2017ዓ.ም የትምህርት ዘመን አደረሳችሁ እያልን በቀጣይ ቀናቶች የትምህርት ክፍል(Department ) የምትመርጡ መሆኑ ይታወቃል ። ስለሆነም ኮምቦልቻ ካምፓስ ውስጥ ከሚገኙ የትምህርት ክፍሎች አንዱ የሆነው የስነ ህንጻ (Architecture ) ትምህርት ክፍልን መቀላቀል የምትፈልጉ ስለ ትምህርት ክፍሉ ማብራሪያ ለመስጠት መድረክ ስለተዘጋጀ ሀሙስ (07/02/2017ዓ.ም )ከምሽቱ 2:00 በትምህርት ክፍሉ ህንጻ ተገኝታችሁ እንድትሳተፉ እናሳስባለን ።

Wollo university kombolcha campus student union

08 Oct, 10:47


ማስታወቂያ
በ2017 የመደበኛ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ

በ2017 የመደበኛ ተመራቂ ተማሪዎች መኖራችሁ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ሁሉም ተማሪ በኦንለይን እስከ 02/02/2017 ዓ.ም ድረስ student detail or admission detail በተለይ በርዝ ዴት በፈረንጆች አቆጣጠር ( SYSTEM ላይ M/D/YEAR FORMAT መሰረት )እንድትሞሉ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለማንኛዉም ተማሪ ድግሪም ሆነ ማንኛዉንም መረጃ የማንሰጥ መሆኑንን እናሳስባለን፡፡

ሪጅስትራር እና አልሙናይ ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

08 Oct, 10:44


ማስታወቂያ
በ2017 ት/ት ዘመን ከኢንተርንሽፕ ለምትመለሱ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

በ2017 ት/ት ዘመን _ ኢንተርንሽፕ ወጥታችሁ የምትመለሱ ተማሪዎች መኖራችሁ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ዉጭ ላይ የነበራችሁበትን የኢንተርንሽፕ ስራ ጨርሳችሁ ወደ ግቢ የምትገቡት እና የኢንተርንሽፕ ኮርሶችን የምትመዘገቡበት ቀን ከ30/01-1/02/2017 ዓ.ም ሲሆን ግቢ ከገባችሁ በኋላ ከትምህርት ክፍላችሁ ጋር የምታጠናቅቁት ስራ ቀድማችሁ እንዲታጠናቅቁ በማለት የ2017 ት/ት ዘመን 5ኛ ወሰነ ትምህርት ምዝገባ እና መማር ማስተማር ጥቅምት 9-10/02/2017 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን እናሳውቃለን።

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

07 Oct, 14:35


ለሁሉም የግቢያችን ተማሪዎች በሙሉ አዲስ እየተሰራ ላለው የወሎ ዩኒቨርስቲ የመመገቢያና የበር ላይ መግቢያ ዲጂታል
መታወቂያ በተመለከተ ከዚህ በፊት በማስታወቂያ  ያሳወቅነ ቢሆንም በሳይበር መጨናነቅ ምክንያት ከA+ የጫናችሁትን መረጃ ከዚህ በታች በላው  ላይ እስከ ቀን 28 /01/2017 ዓ.ም ድረስ እንድትሞሉልን
እናሳስባለን።
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfkg9R5lhgW2htMq28gprwTOAm4T_R4ntSWvAmB_AL8q5BSxQ/viewform?usp=sf_link


ማሳሰቢያ
"ለመመገቢያ ካርድ አገልግሎት የሚውል ስለሆነ በጥንቃቄ ይሞላ፡፡ በጥንቃቄ ጉድለት ለሚፈጠረው ችግር ተማሪው ራሱ ሃላፊነት የሚወስድ መሆኑን አሳውቃለሁ፡፡"



የተማሪዎች ህበረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

07 Oct, 11:02


🔊🔊 ማስታወቂያ
ለተመራቂ ተማሪዎች የመመረቂያ መጽሔት ማሰራትን ይመለከታል 🎓🎓🎓
ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው የመመረቂያ መጽሔት መስራት የምትችሉ አካላትን በተጠቀሱት መስፈርቶች መሰረት አወዳድሮ ማሰራት ስለምንፈልግ
ተማሪዎች ህብረት ቢሮ እስከ ቀን 28/01/2016ዓ.ም ድረስ በአካል በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ።
የተማሪዎች ህብረት

Wollo university kombolcha campus student union

02 Oct, 13:18


አስቸኳይ ማስታወቂያ

ለሁሉም የግቢያችን ተማሪዎች በሙሉ አዲስ እየተሰራ ላለው የወሎ ዩኒቨርስቲ የመመገቢያና የበር ላይ መግቢያ ዲጂታል
መታወቂያ አገልግሎት የሚውል ፓስፖርት ሳይዝ (3*4) ፤ ጀርባው (background) ነጭ የሆነ ሶፍት ኮፒ ፎቶግራፍ
እንድታዘጋጁ እና A+ ድረ-ገጽ (Personal Information) ላይ እስከ ቀን 24/01/2017 ዓ.ም ድረስ እንድትጭኑ በጥብቅ
እናሳስባለን።

ማሳሰቢያ
•  የምታስገቡት ፎቶግራፍ ጀርባው (background) ነጭ መሆን አለበት
•  የምታስገቡት ፎቶግራፍ 3*4 መሆን አለበት
•  የምትጠቀሙበትን ስልክ ቁጥር ማስገባት አለባቹሁ

ይህንን ሳያደርግ የተገኘ ማንኛውም ተማሪ ከቀን 24/01/2017 ዓ.ም ጀምሮ የካፌን ጨምሮ ማንኛውንም የግቢውን
አገልግሎት መጠቀም የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።

የተማሪዎች ህበረት ፅ/ቤት
https://t.me/wollostu

Wollo university kombolcha campus student union

27 Sep, 05:59


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ተማሪዎቻችን እና የአስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ

መልካም በዓል

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

25 Sep, 08:07


ማስታወቂያ
ለ2013 እና 2014 ባች ተማሪዎች በሙሉ
የ2017 ዓ.ም ት/ት ዘመን የ2013 እና 2014 ባች ተማሪዎች ምዝገባ ቀን በ 13/01/17 እና 14/01/17 ዓ.ም መሆኑን በማስታወቂያ መግለፃችን ይታወቃል።

በመሆኑም በዚህ ቀን ምዝገባ ያላካሄዳችሁ ተማሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ እስከ 16/01/17 ዓ.ም ድረስ ምዝገባውን እንድታደርጉ እያልን ከተጠቀሰው ቀን ውጭ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን ።

ለሬጅስትራር እና አልሙናይ ጽ/ቤት

👉የተማሪዎች ህብረት

Wollo university kombolcha campus student union

24 Sep, 18:43


የሐዘን መግለጫ

የምንኖርበት ዓለም ያልተሟላ፣ የርኩሳን ፈተና ያለበትና ስቃይን ያዘለ ከመሆኑም በላይ መጨረሻው በሞት የሚደመደም ነው። “ሞት ማንም እርግጠኛ ሊሆንበት የሚችለው ብቸኛ እውነት ነው”   “የእኛ ሕይወት ማለት ያልተሟላን ኑሮ መኖር ነውን?፤ ሞትስ ልናመልጠው የማንችለው የሁላንችንም ዕጣ ፈንታ ነውን?
መኖር ስትሻ ነው፣ ሞት የሚያሰጋህ
ኑሮ ሲቀልህ ነው፣ መሞት የሚገርምህ!!!!

በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ካምፓስ የ5 ዓመት የቴክስታይል ምህድስና ተማሪ የነበረችው ሽታየ ተፈሪ ባጋጠማት ድንገተኛ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለመላው ቤተሰቦቿ እና ለወዳጅ ጎደኞቿ መፅናናትን እንመኛለን።

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
     👉የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

20 Sep, 15:47


2017 EC kIOT dormitory placement

.
KIOT  STU

Wollo university kombolcha campus student union

19 Sep, 10:04


የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል።

በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ውጤት ተለቋል።

ተማሪዎች ውጤታችሁን በተከታዩ ሊንክ አማካኝነት መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል 👇
https://result.ethernet.edu.et/

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት
https://t.me/wollostu

Wollo university kombolcha campus student union

11 Sep, 15:39


ለሁሉም የሪሚዲያልና የአፓረንት ተማሪዎች በሙሉ የተደረገው የተማሪዎች ጥሪ እናተን የማያካትት ሲሆን የአፓረንት ተማሪዎች በጊዚአዊነት መግቢያ ቀን መስከረም 30/01/2017 መሆኑን እያሳወቅነ የሚቀየር ካለ የምናሳውቅ ይሆናል።

የተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት
https://t.me/wollostu

Wollo university kombolcha campus student union

11 Sep, 08:13


ለዩንቨርስቲያችን ተማሪዎች እና ሰራተኞች በሙሉ እንኳን ለ2017 የዘመን መለወጫ በዓል ዕንቁጣጣሽ በዓል አደረሳችሁ

🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
🌻🌻 መልካም 🌻🌻️
🌻🌻  አዲስ    🌻🌻
🌻🌻  ዓመት   🌻🌻️
🌻️🌹🌾🌻💐🌷🌻
🕊🌻🌻🌻🌻🌻️🕊
🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
🌻🌻 መልካም 🌻🌻️
🌻🌻  አዲስ    🌻🌻
🌻🌻  ዓመት   🌻🌻️
🌻️🌹🌾🌻💐🌷🌻
🕊🌻🌻🌻🌻🌻️🕊

በፈጣሪ ቸርነት 2016 አልፈን ወደ አዲሱ ዘመን ደርሰናል። ፅኑ፣ ብርቱ ህዝብ እና የማይሸነሽ አምላክ ስላለን እዚህ ደርሰናል እኛብንፈልግም ባንፈልግም ዘመን ይለወጣል ያለፈው አመት በመከራ ያለፈንበት አንዱ ገዳይ ሌላው ተገዳይ የሆንበት መሆኑ ይታወቃል ። እነዚህ ወገኖች ወደው የተገኙበት ፈቅደው የዋሉበት አደለም ምን አልባት  መማር ቢፈቀድላቸው ተምረው ለሀገር የሚጠቅሙ ፤መስራት ቢፈቀድላቸው የፋብሪካ ማናጀር፣ የግል ድርጅት ባለቤት፣ አስመጭና እና ላኪ አምራችና አካፋፋይ መሆን ይችሉ ነበር እውነት ነው ያለፈው አመት የምንሻገርበት ነገ እና የምንደርሰበት ተስፋ  ከፊታችን የለም ብለን እንድናስብ፤ ዕጣፈታችን ሠርቶ እና አልምቶ ማደር ሳይሆን ከዚህ በተቃራኒ ነበር። የ2017 አመት ያለፈው ሁሉ እረስተን አሻግሮ የሚያሳየን በማጣታችን የሞት ሸለቆ ዘለን የማንገባበት ፤ነግቶ በመሸ ቁጥር የሀገር ስጋትን ሳይሆን ተስፋን የምናይበት ልክ 2016 አመት ላይ ሁነን 2015 አመት ወይም ትናትን እንደናፈቅነ 2017 አመት ነገን እንጅ ያለፈውን የማንናፍቅበት እንዲሆለን መልካም ምኞታችን ነው።
መልካም በዓል

የተማሪውች ህብረት ፅ/ቤት

Wollo university kombolcha campus student union

10 Sep, 15:26


ማስታወቂያ
05/13/2016 9.
ለወሎ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሁሉም ነባር መደበኛ ተማሪዎች (ቅድመ-ምረቃ እና ድህረ- ምረቃ) የ2017 ዓ.ም የመግቢያ ጊዜ መስከረም 10 እና 11/2017 ዓ.ም ሲሆን መስከረም 13/2017 ዓ.ም ትምህርት የሚጀመር መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ መምጣት አይፈቀድም፡፡
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት