ጣና ሚዲያ Tana Media

@tanamedia2


ጣናዊነት አዳማዊነት ኖኃዊነት!!!

ጣና ሚዲያ Tana Media

22 Oct, 17:56


የአማራ ክልል  ሕዝብ የናፈቀው ሰላምን እንጂ የጤፍ ሰብል ፎቶ አይደለም።

ጣና ሚዲያ Tana Media

22 Oct, 17:56


ድሮን በያይነቱ የምትገዛ ሀገር አንድ እንኳን ደህና የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር የላትም!😢😭

ጣና ሚዲያ Tana Media

22 Oct, 17:49


በ 2017 አ/ም መስከረም እና ጥቅምት ላይ የድሮን ጥቃት ከተፈፀመባቸው ትምህርት ቤቶች በከፊል፦

ጎንደር ፡

- ሚካኤል ደብር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
/አዲስ ዘመን/

ጎጃም :

- ድማማ ትምህርት ቤት
/ፋግታ ለኮማ ወረዳ/

- አፈሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
/ዳንግላ ዙሪያ/

- ቅድስ ዮሐንስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት
/ሜጫ ወረዳ/

- ንዋዬ ማርያም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
/እናርጅ እናውጋ ወረዳ ፈለገ ብርሃን ከተማ/

- ቀጋት ትምህርት ቤት
/ደብረ ኤልያስ/

እነዚህ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ተማሪዎችም በጥቃቱ ሞተዋል።
አብይ አህመድ የትምህርቱን ዘርፍ ርካሽ ፖለቲካ ከሰራበት በኋላ እንዲህ ነው የሚያደርገው።
ለዚህ ነው ትምህርት ነፃነታችንን እስክናረጋግጥ ይቆይ የምንለው።

ታድያ ወንድም እህቶቻችን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ እያሉ የእኛ የአማራ ፋኖን መመሪያ ተላልፎ በትምህርት ቤቶች መገኘት የድሮን እሳትን ያስገኝ እንደሆነ እንጂ እውቀትን መቅሰም በዚህ ሁኔታ የማይታሰብ ነው።

ቀጣይ ለሚኖረን ጥሪ ዝግጁ ሁኑ!

ጥቅምት ፲፪ ቀን ፪፻፲፯ ዓ.ም | ባ/ዳር
የግዮን አጠቃላይ ፪ኛ  ደረጃና ከፍተኛ ት/ም መሰናዶ ት/ቤ የተማሪዎች ንቅናቄ
"ትምህርት ከነፃነት በኋላ!!"

ጣና ሚዲያ Tana Media

22 Oct, 07:05


ለ12 ቀን ሲካሄድ የነበረውን ስብሰባ ሙሉ ለሙሉ ስከታተለው ነበር። እናም በተስፋ መቁረጥ ደምደውታል!

የመጨረሻ ውሏቸው፦
የስብሰባ አዳራሽ- አድዋ 00 ሙዚዬም

ውሎ ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን!

ጠ/ሚ እስካሁን የሰነበቱባቸውን የ10 ሰነዶችን ዋና ዋና የሚላቸውንና አዳማ ያቀረበውን ቪዲዮ ሙሉ ሳይሆን ሰሞኑን በሶሻል ሚዲያ ሲነሱ የነበሩትን ጉዳዮች ተቆርጦ እንዲቀርብ ተደርጓል። ከተቆረጡት ንግግሮች መካከል (ኤርትራን እንደጋዛ)  በዚሁ ውስጥ አጠቃላይ ሀገራዊና አለማቀፋዊ ሁኔታ አንስቷል። ከአንሳቸው ነጥቦች መካከል "አመራሩ የፅንፈኛ ምሽግ ናችሁ፣ እናንተ ሰርታችሁ ለውጥ አታምጡ፣ የሆነ ነገር ሲነገራችሁ አንገት መነቅነቅና ከንፈር መምጠጥ ሆኗል ስራችሁ" ብሏቸዋል።

ቀጥሎም "አጠቃላይ እኛ አሁን ባለው ሁኔታ ከንጉሱ ጀምሮ እስከ ኢህአዴግ ድርስ በምስለኔ እንጅ ሶማሌ በራሱ ተወላጅ ክልሉን መርቶ አያውቅም፣ አፋር በራሱ ተወላጅ ተመርቶ አያውቅም፣ ክልሎች አሁን ያላቸውን ያክል ነፃነት ኖሯቸው አያውቁም።" እያለም ቀባጥሯል። ታሪክ ስለማያውቅ ከዚህ የተለዬ ሊናገር አይችልም።

#ስለDiplomacy፦ ዙሪያችን ብዙ እድገታችንን የማይወዱ በክፉ አይን እየተመለከቱን ነው። የባህር በር ጥያቄ ጉዳይ ነገም የማንተወው ጉዳይ ነው ብሏል። በቪዲዮ ላይ ባለፈው ናዝሪት ላይ በተካሄደው ስብሰባ ኤርትራን እንደ ጋዛ እናደርጋታለን ያለውን ቆርጠውታል።

አብይ አህመድ ከፋኖ ጋር እየተካሄደ ስላለው ጦርነት ምንም ያለው ነገር የለም፤ ግን ንግግሮቹ ሁሉ የተስፋ መቁረጥ ይመስላል።

#####################

ከአብይ አህመድ ማጠቃለያ በመቀጠል ከንቲባ ተብዬዋ በአካል መጥታ የስራ መመሪያ ልሰጥ ነው በሚል ደስኩራለች።

በንግግሯም "እናንተ የምንሰራውን ስራ ጠላት ሲያራክሰው እያያችሁ ምንም አይመስላችሁም፣ እኛ ከተማዋ እየቀየርናት ነው፣ ማንም ቢጮህ እኛ ከጉዟችን የሚያግደን ነገር የለም።" የሚል እረጅም ሰዓት ወስዳ እጅና እግር የሌለው ማጠቃለያ ነበር።

በንግግሯ ተስፋ መቁረጧን መረዳት ችያለሁ። አዳነች ከተናገረቻቸው ነጥቦች "እስኪ የምር ብልፅግና ሁኑ፤ መጀመሪያ እናንተ የምር መሆን ብትችሉ የሚያቅተን ነገር የለም፣ ሌብነት ተንሰራፍቷል። አሁን ባለው ሁኔታ ተቋማዊ ሌብነት ባይኖርም ከወዲሁ ማስተካከል ካልቻልን ወደ ተቋማዊ ሌብነት መሄዱ አይቀርም። በየቡድኑ ስለ ሌብንት ብዙ አንስታችኃል ግን ማነው ሌባው? ማነው የእጅ መንሻ የሚቀበለው? ለምን መታገል አቃታችሁ ብላ ጥያቄውን ወደ ተሳታፊው መልሳዋለች።" ቀጥላ ግን ይሄኛውን ከላይ ያነሳችውን ነጥብ የሚያፈርስ ሀሳብ ሰንዝራለች። ይህ ሀሳብም እንዲህ ይላል:-  "ፊርማ አትፍሩ እኛ የኮሪደር ልማቱን ለማፋጠን ስንል አንዳንድ አሰራሮች ላንጠብቅ እንችላለን፤ የፋይናስ አሰራር እንጠብቅ ካልን በአሰብነው ጊዜ መጨረስ አንችልም፤ ስለዚህ የወረዳ አመራሮች በእኛ በኩል የመጣ ከሆነ 'ለለውጥ' ስለሆነ ያለምንም ፍርሃት የሚፈረም ነገር ካለ አትሸማቀቁ ፈርሙ እኛ ሀላፊነት እንወስዳለን" ብላለች።

ከፋኖ ጋር እየተደረገ ስላለው ጦርነት አለቃው አብይ አህመድ የፈራውን ሀሳብ እሷ አንስታዋለች።

"አማራ ክልል የተፈጠረውን ችግር ማስተካከል ያልቻልነው፤  ሕዝቡ በተግባርም በአመለካከትም የፋኖ ተባባሪ ስለሆነ ነው እንጅ ከመከላከያ አቅም በላይ ሆኖ አይደለም።" ብላለች።

አጠቃላይ የሁለቱም ማጠቃለያ በተስፋ የተሞላ ሳይሆን በተስፋ መቁረጥ የተደረግ ማጠቃለያ ነው ያደረጉት!

ስብሰባው ሲጠናቀቅ ተኝተው የነበሩት ተቀስቅሰው ወደ ቤታቸው ሂደዋል!

አንበርብር!

ጣና ሚዲያ Tana Media

21 Oct, 19:54


እስከ አሁን አልጠፋም።
#Update

መርካቶ ' ሸማ ተራ ' የተነሳው ከባድ የእሳት አደጋ እስካሁን አልቆመም።

እሳቱን መቆጣጠር አልተቻለም።

የፋሽስቱ አገዛዝ ሹም የሆነችው የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ " አደጋውን ቶሎ ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለዉን ጥረት  አዳጋች ያደረገዉ የአካባቢው መንገድ የእሳት አደጋ መኪና በተሟላ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት ነው " ብለዋል።

አሁን ላይ " በሄሊኮፕተር ለመጠቀም እየጣርን  ነው " ሲሉ የሴራው ባለቤቶች በህዝብ ሀብት ውድመት አላግጠዋል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

21 Oct, 18:38


መርካቶን አንድደው ሞቋት! እየበለጠጋችሁ 🤔🤔

ጣና ሚዲያ Tana Media

21 Oct, 18:35


“የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ ቀዳሚው የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ነው፡፡ እኛ እንደ ኦነግ አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ስር መሆን አለባት ነው የምንለው! የፌደራሉ መንግስት መሬት የለውም፤ ከፈለገ ባህርዳርን ዋና ከተማው ማድረግ ይችላል፡፡”
ቀጀላ መርዳሳ ከአዲስ ማለዳ ጋር ካደረጉት ቆይታ የተወሰደ

ጣና ሚዲያ Tana Media

21 Oct, 18:34


መርካቶ ሸማ ተራ

መርካቶ ሸማ ተራ ከጃቡላኒ የንግድ ማዕከል ጀርባ ወይም ሽንኩርት በረንዳ የሚባለው ሥፍራ ላይ ከበድ ያለ የእሳት አደጋ ተከስቷል ።

Via: ጌች ሐበሻ

ጣና ሚዲያ Tana Media

21 Oct, 07:48


የDK ነገር

እነዚያ በረሮ እንዳሉ እነዚህ ጊንጥ እያሉ ወገን ሊጨርሱ!

የዘር ፍጅት ጥሪ ነው

ውነቃ ዳንኤል "ጊዜ ተሰዓቱ ማን ተገኝ አለሽ?" በቅኔ መምህራን ቤት የሚነገረውን ተጠቅሞ ያስተላለፈው የዘር ፍጅት ጥሪ ነው።

ሲጀመር ስለ ጊንጥ ሳይኾን የተነገረው ስለ ትል ነው። ጊንጥ በአመዛኙ በአሸዋማ በረሃ አካባቢ የምትኖር ሲኾን በዛፍ ቅርንጫፍ ቅጠል ለቅጠል የሚሳበው ደግሞ ትል ነው። ጊንጥና ቅጠል የማይመስል ነገር። ጊንጥ የቱንም ያኽል ትንሽ ብትኾን ትጎረብጣለች። ትል ግን ከቅጠል ልስላሴ ወይም መሻከር የመመሳሰል ዕድሉ ሰፊ ነው።

ባሕታዊው ሠዓታቸው ሲደርስ አፋቸውን ለመሻር (ለማደፍ) የላመ የጣመ ስለሌላቸው የተገኘውን ቅጠል ይሸመጥጣሉ። በዚያ ሠዓት ከቅጠሎቹ መኻል ተወሽቃ ሳያዩአት ወደ አፋቸው የገባች ትል ድምፅ ታሰማለች። እርሳቸውም ጊዜ ተሰዓቱ ማን ተገኝ አለሽ? ብለው "አስተናግደዋታል"።

ይኽንን ጠቅሶ የብልጽግና ሠራዊት ፋኖን እዋጋለሁ በሚል ሰበብ ሕፃናትን፣ ንጹሐንን፣ ከብቶችን፣ ሰብሎችን፣ አብያተ እምነትን እና ተቋማትን በነጭ ፎስፈረስ ቦምብ መግደሉንና ማፈራረሱን ትክክለኛ ርምጃ ነው ሲል ተከላክሏል።

ባሕታዊው ትሊቱን የተመገቡት ዐውቀው ኾን ብለው ሳይኾን ስላላዩአት ነው። ውነቃ ዳንኤል ግን የተገኘ ሁሉ ይጨረገዳል፣ እዚያ አካባቢ የምንጨነቅለት ሕይወትም ተቋምም የለም በማለት የዘር ፍጅት ቀስቅሷል።

የባሕታዊው ድርጊት ያጣ የነጣ የሚያደርገው ፍትሐዊ ሲኾን የውነቃ ዳንኤል መልእክት ግን የዘር ፍጅት ዐቅዶ መሥራትን ቅቡል አድርጎ ለማንበር የተነገረ ነው።

አኹንም ያገኘነውን ከመጨፍጨፍ የሚያግደን የለም። ከተፈጃችሁ በኋላ ለሌላ ፍጅት ተዘጋጁ የሚል አደገኛ ቅስቀሳ ነው። እነዚያ በረሮ እነዚህ ጊንጥ እያሉ ወገን ሊጨርሱ ተነሥተዋል።

ዲ/ን አባይነህ ካሴ

ጣና ሚዲያ Tana Media

20 Oct, 18:24


#ሰበር_የድል_ዜና
ጊራና ከተማ በአማራ ፋኖ በወሎ እዝ ስር ገብታለች ..‼️‼️

በዛሬው እለት በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ አካባቢ በጀግናው ኮለኔል ፋንታሁን ሙሃባ በሚመራው አማራ ፋኖ በወሎ እዝና እና በብርሀኑ ጁላ አራዊት ሰራዊት መካከል ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ መዋሉን የገለፁት ምንጮቻችን የአማራ ፋኖ በወሎ እዝ ስር የሚገኙት ባለሽርጡ ክፍለጦር፣ልጅ እያሱ ክፍለጦርና መቅደላ ክፍለጦር አንድ ላይ በመሆን በሶስት አቅጣጫ ከመጣው የጠላት ሀይል ጋር እልህ አስጨራሽ ውጊያ ሲያካሄዱ ውለዋል።
▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️
በስተመጨረሻም ዛሬ ከመሸ የጊራናን ከተማን ጀግኖቹ  የኮለኔል ልጆች በቁጥጥር ስር ማስገባታቸውን ለማወቅ ተችሏል ። ጊራና ከተማ ሰርጎ ገብቶ የነበረው የጠላት ሀይልም ጀግኖቹ አፈር አብልተው አከርካሪውን በመምታት ሙትና ቁስለኛ የቀረውን ሃይል ደግሞ በፍርጠጣ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች እንዲፈረጥጥ አድርገውታል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

20 Oct, 18:17


ዜና ጎንደር‼️
ጎንደር ከተማ ፈንጠር በሚባል ቦታ የአድማ ብተና ሀላፊ ከአጃቢዎቹ ጋር
እርምጃ ተወስዶበታል::
ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም

ጣና ሚዲያ Tana Media

20 Oct, 18:16


የድል ዜና ጎንደር❗️

የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት ተጨማሪ ኃይል ከባሕር ዳር ወደ ደብረ ታቦር ከተማ ለመግባት  በምድር ዙ- 23፣ BM-107፣ ዲሽቃና ሞርታርን እንዲሁም በሠማይ በሄሊኮፍተር የታገዘ ጉዞን ሢያደርግ ውሏል። በተመሣሣይ ከባሕር ዳር የተነሳውን ጦር ለመቀበል ከደብረ ታቦር ወደ አለም በር  የአገዛዙ ጦር በከባድ መሣሪያ ታግዞ ዘምቷል።

ድልን እሥትንፋሳቸው ያደረጉ የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር እና የጉና ክፍለ ጦር አካል የሆነችው ጣይቱ ሻለቃ በጥምረት የአገዛዙን ጦር የተለያዬ ቦታ ላይ ደፈጣ ጥለውበታል። በደፈጣ የታጨደው የአገዛዙ ጦር ወደ ሁለቱም አቅጣጫ እግሬ አውጭኝ ካለ በኋላ ራሱን አደራጅቶ ተመልሷል።

ድንጋጤን መለያው ያደረገው የአቢይ ጦር በምድር ውጊያ እንደተሸነፈ ሢያረጋግጥ በሠማይ በሄሊኮፍተር ታግዞ ከእንደገና ውጊያን አድርጓል። ነገር ግን አሸናፊነት ከአባቶቻቸው የወረሱት፣ ሥነ ልቦናቸው በዕውነት የጸናው፣ ትግላቸው ሕልውናን ማሥቀጠል እንደሆነ ያመኑት የአሥቻለው ደሤ ቀኝ እጆች፣ የውባንተ አባተ ልጆችና የናሁሰናይ ወንድሞች በአገዛዙ የጦር ጋጋታ አልተረበሹም።

የአማራ ፋኖ በአለም በር ላይ የልብ ትጥቅን በደምብ ታጥቆ በውሥን ጦር አገዛዙን ሲለበልብ ውሏል። አለም በርና ዙሪያ ገባው ላይ በነበረው ውጊያ የአገዛዙ አመራሮችም ጭምር ሢደመሰሱ ደብረ ታቦር ሆሥፒታል በዚህ ሠዓት በአገዛዙ ቁሥለኞች ተሞልቷል። የአገዛዙ ከፍተኛ የጦር መሪም እንደቆሰለና ታቦር ሆሥፒታል እንደገባ አረጋግጠናል።

ሕልውናችን በተባበረ አማራዊ ክንዳችን
via:የአማራ ፋኖ በጎንደር የሚዲያና ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ