ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

@mirttshefoch


ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:26


ከእስራትህ ውጣ!
፨፨፨/////////፨፨፨
ጥፋተኛ ስለሆንክ ላትታሰር ትችላለህ፤ ስለበደልክ፣ ስለጎዳህ ወህኒ ላትወርድ ትችላለህ፤ ነገር ግን ባለማወቅም ይሁን በሃሰት ልትታሰር ትችላለህ፤ የአካል እስራትህ ግን ነፃ የሆነውን አዕምሮህን ሊያስረው አይችልም። የትኛውም ነፃነት ከአስተሳሰብህ ይነሳል፤ ከሁነኛው አቋምህ ይመነጫል፤ ከማንነትህ ይመጣል። አጠፋህ አላጠፋህ፣ ጎዳህ አልጎዳህ ሰዎች ከሚሰጡህ የአጥፊነትና የክፋት ስም ይልቅ አንተ ለእራስህ የምትሰጠው የንፅህናና የመልካምነት ስም ይልቃል። ለእራስህ ባለህ አቋም አንድ ልትወድቅ ትችላለህ፤ ሌላም ከቀድሞ በተሻለ ቀና ብለህ መታየት ትችላለህ። የአስተሳሰብህን ሃይል በመጣህበት የህይወት ጉዞ ውስጥ መመልከት ይኖርብሃል። ብትወድቅ የውድቀትህ መንስኤ ምንድነው? ብትታሰር ያሰረህ ማነው?

አዎ! ጀግናዬ..! ማንም ይሰርህ ማን፣ ማንም ይጣልህ ማን አንተ ግን ጊዜ ሳታጠፋ ከእስራትህ ውጣ፤ እራስህን ነፃ አውጣ። ያለጥፋትህ ላሰሩህ፣ ለጉዳት ለዳረጉህ፣ ጠብቀው ላደቡብህ ከልብህ ይቅር በማለት ከቂም እስራት ነፃ ሁን፤ ከጥፋተኝነት አጥር ውጣ። አስሬ ሰዎች ያደረጉብህን ደጋግመህ ብታስብ ሰዎቹን ከመጉዳት ይልቅ በፍቃድህ እራስህን መጉዳት፣ ማሰርና ማሳዘን ትጀምራለህ። የፈረዱብህ ላይ ለመፍረድ እስካልተጣደፍክ ድረስ፣ ለእራስህ ነፃነት እስካሰብክ ድረስ፣ የይቅርታ ልብ አስከኖረህ ድረስ ባላጠፋሀው መወንጀልህ፣ ባልሆንከው መጠራትህ፣ በማይገልፅህ መወከልህ ምንም አይደለም። ወደኋላ ቢያስቀርህም በንፁው ልቦናህ የተረጋጋና አስደሳች ህይወትን ያጎናፅፍሃል።

አዎ! የነፃነት መሳሪያህ አስተሳሰብህ ነው። በአስተሳሰብህ ከታሰርክ፣ እራስህን ከገደብክ፣ አቅምህን ካሳነስክ፣ በእራስመተማመን ከተሳነክ ብዙዎች ቢደግፉህ፣ ብዙዎች ቢያምኑብህ፣ ብዙዎች ቢያበረታቱህ እንኳን የትም መሔድ አትችልም። አቅምህ በአመለካከትህ ፍቃድ የሚወጣ ነው፤ ትክክለኛው ማንነትህ ካንተ አስተሳሰብ ጋር የተገናኘ ነው። ከምንም ተፅዕኖ ነፃ ለመውጣት ከመታገልህ በፊት እየጎዳህ ካለው ከገዛ አሉታዊ አመለካከትህ ነፃ ውጣ፤ ሃሳብህ ላይ ሰልጥን፤ እራስህን መግዛት ጀምር፤ ትናንትን በይቅርታ የምትሽር፣ ወደፊት ለመራመድ የፈጠንክ፣ እራስህ ላይ የሰለጠንክ ብርቱና ጠንካራ ሰው ለመሆን ሞከር። አንተ ያልፈታሀውን እስር ማንም ቢመጣ ሊፈታልህ እንደማይችል አስተውል።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:26


አማራጭ አይደለም!
፨፨፨፨////////፨፨፨፨
ለዓመታት የምትለፋበት ትምህርትህ የት እንደሚወስድህ፣ የት እንደሚያደርስህ፣ ከምን እንደሚያበቃህ፣ ምን እንደሚያሰራህ ሳታውቅ አትጀምረው። መዳረሻህን የምታውቀው አንድ ቦታ ከደረስክ ቦሃላ ሳይሆን ጉዞህን ሳትጀምር ነው። ብዙ መማርህ አላማው እድሎችን ለማስፋትና የተሻለ ገቢን ለማግኘት ከሆነ ከእርሱ የሚቀድም ጉዳይ እንዳለ አስተውል። አማራጭህን ለማስፋት መጣርህ ክፋት የለውም ነገር ግን ለአማራጭ ብለህ የምታባክነው ጊዜ ግን እጅጉን ወሳኝ ነው። በአጭር ህይወት ለአማራጭ የምትኖረው አመት ሳይሆን የእኔ ብለህ በሙሉ ልብህ አምነህበት፣ ወደሀው፣ መርጠሀው፣ ደስ እያለህ ጊዜህን የምትሰጠው፣ Invest የምታደርግበት ነገር ያስፈልግሃል። ጥረትህ ብዙ አማራጭ ያለው ሰው ለመሆን ሳይሆን በመረጠው ዘርፍ ቁንጮ የሚሆን ሰውን መፍጠር ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! አማራጭ አይደለም! እዚም እዛም ማለትህ አጋጣሚዎች እንዲፈጠሩልህ አይደለም፤ ሁሉም ዘርፍ ላይ መሳተፍ መፈለግህ እረፍት ለማግኘት አይደለም። እዚም እዛም እየረገጥክ አንድ የምተማመንበት፣ የሚያሳርፈኝና የሚያረጋጋኝ ነገር አገኛለሁ ብለህ እንዳታስብ። የምትረጋጋው ብዙ አማራጭ ስላለህ ሳይሆን በአንዱ ምርጫህ ስኬታማ ስትሆን ነው። ምንም አይነት ኮተት ማብዛት አያስፈልግም፤ ህይወትህ ጥራት እንዲኖረው ተለይተህ የምትታወቅበት አይነተኛ ዘርፍ ያስፈልግሃል፤ በእርሱ መንገድ ማደግና ከፍ ማለት ትችላለህ። ነፍስህ ያለው ሌላ ቦታ ሆኖ አንተ የምትማረው ሌላ ከሆነ አንዴት ደስ እያለህ እንደምትማር፣ እንዴት ወደሀው እራስህን እንደምትሰጥለት፣ እንዴት እርግጠኛ እንደምትሆንበት አስበው።

አዎ! የምትፈልገውን ካወክ፣ አላማህን ከተረዳህ፣ የልብ መሻትህን ከለየህ፣ ውስጥህን ካዳመጥክ እዚም እዛም በማለት የምትደክምበት፣ ጀምሮ በመተው የምትሰቃይበት ሁኔታ አይኖርም። ለምትፈልገው ነገር መኖር፣ የምትወደው ስፍራ ላይ መገኘት፣ ወደሚያስፈልግህ አቅጣጫ መጓዝ ከምንም በላይ የውስጥ ሰላም ነው፤ ደስታ ነው፤ በእራሱ ስኬት ነው። አማራጮችህ በበዙ ቁጥር መካከለኛ (mediocre)፣ መደበኛ የመሆን እድልህ በጣም ሰፊ ነው። ብዙ ምርጫ እንዳለህ ማሰብህ ሲጥልህ እንጂ የተሻልክ ሲያደርግህ አተሰመለከትም። በየአቅጣጫው የሚመጣው ትናንሽ ነገር ከአንድ ቦታ በተለየ ሁኔታ ከሚመጣው ጋር አይወዳደርም። በብዙ አማራጭ መከበብ ቀላል ነገር አይደለም። አንዱን አለመያዝህ አንድም ብኩን፣ ሌላም ስሜት አልባ ያደርግሃል። የኔ የምትለውን አንዱን ምረጥ፤ እርሱን እስከ ጥግ ተማር፤ እወቀው፣ ተረዳው፤ ህይወትህን በእርሱ ዙሪያ መስርት፣ እሴትህንም በዛው ዘርፍ ጨምር።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:26


"እድል ነው" ይላሉ!
፨፨፨፨///////፨፨፨፨
ራስን አብቅቶ መታየት፣ አስተሳሰብን ቀይሮ መምጣት፣ ስራን መቀየር፣ ያማረ ተክለሰውነት መግንባት፣ ኩሩ ማንነትን መላበስ፣ ብቸኝነትን እንደ ስጦታ ማጣጣም፣ ትቺትና ዘለፋን መረማመጃ ማድረግ፣ ከናቁት ተሽሎ መገኘት፣ የገፉትን አሸንፎ መገኘት "እድል ነው" ይላሉ። አንዲሁ እንዳጋጣሚ የመጣ፣ እንዲሁ ሳይታሰበ የተፈጠረ፣ እንዲሁ ዱብዳ የሆነ ይመስላቸዋል። ማመን የሚፈልጉት ይሔንን ነውና እስኪሆን ይጠብቁታል፣ ውስጣቸው በእድልና በአጋጣሚ እንደሚያልፍላቸው ያስባልና ተኝተው ደጋግመው እድላቸውን ይሞክራሉ፣ ስንፍናቸውን እያስታመሙ ጥግ ላይ ቆመው ጥሩ ነገር እንዲሆንላቸው ይመኛሉ። ከስራ ይልቅ ምቾት ያንገላታቸው ቢመስላቸውም እውነታው ግን የማይጨበጠው ምኞታቸው እያሰቃያቸው መሆኑ ነው፤ እውነታው ግን ራሳቸውን ከማሻሻል ይልቅ ራሳቸውን ማስነፋቸው ነው። በአድል ማንም ህይወቱን አልገነባም፤ በአንድ አጋጣሚ ብቻ ማንም ሙሉ አካባቢውን አልቀየረም፤ ማንም በአንዲት ቅፅበት ስኬትን አላስመዘገበም። ብዙዎች ባይፈልጉትም ሁሉም የከፍታ ጉዞ ሂደት አለው፣ ሁሉም የለውጥ መንገድ ሂደት አለው፣ ሁሉም የስኬት ጉዞ ረጅም የፈተና ጎዳና አለው።

አዎ! ብዙ መደነቅም ሁነ መደናገጥ አያስፈልግም። አንድ ቦታ ቆመው እድላቸውን የሚጠባበቁትን ተወት አድርጋችሁ እናንተ ግን እድላችሁን አሳዳችሁ ያዙ፣ ስንፍናን ምርጫቸው አድርገው፣ አንድ አጋጣሚ እንዲፈጠርላቸው ከሚማፀኑት ገለል ብላችሁ ያላችሁበትን ሁኔታ ሁሉ እንደ አጋጣሚ መጠቀም ጀምሩ። የቱ ይጠቅማችኋል? የትኛው ያሳርፋችኋል? የቱ ነፃ ያወጣችኋል? ያላችሁበት ቦታ ቆማችሁ እድላችሁን መሞከር ወይስ ጠንክራችሁ ሰርታችሁ በሒደት ራሳችሁን ማሻሻል? ልክ እንደ ሰነፎች በአንዲት አጋጣሚ ህይወታችሁ እንዲቀር መጠበቅ ወይስ በእያንዳንዱ ሁኔታዎች ውስጥ ለእናንተ የተሻለ የምትሉትን አጋጣሚ ለመፍጠር መሞከር? ምርጫችሁን በጥበብ ምረጡ። ጠቢባን የተሰጣቸውን ሁሉ አምነው አይቀበሉም፣ ጠቢባን ብዙዎች ስለመረጡት ብቻ የሚመርጡት ነገር የለም። ጠቢባን የጥበብን መንገድ ይመርጣሉ፣ ጠቢባን በአስተውሎት ወደፊት ይጓዛሉ፣ ጠቢባን የሚበጃቸውን በጥንቃቄ ይመርጣሉ። ምንም ቢፈጠርባቸው ህይወታቸውን በባዶ ምኞት አይሞሉትም፣ ደጋግመው ቢወድቁ እንኳን ቀና በለው እስኪያሸንፉ ድረስ ሙከራቸውን አያቆሙም።

አዎ! ጀግናዬ..! የፊትለፊቱ በር ክፍት ሆኖ ሳለ ከዓመታት ቦሃላ ሊከፈት የሚችለውን የጀርባ በር አትጠብቅ። በህይወት መኖርህን እንደ እድል እየቆጠርክ ለራስህ የሚሆንህን ወደ መፍጠር ተሸጋገር። "በእድል የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው።" የተባለ ይመስል አንድ ቦታ ቆመህ እድለህን እየጠበክ ውይም እያማረርክ አትቀመጥ። ሁሉም ነገር በእጅህ ነው። ፈጣሪም የሚረዳህ የተወሰነ እርምጃ ወደፊት የተራመድክ እንደሆነ ብቻ ነው። በራሳቸው የማይተማመኑ፣ በፍረሃትና በስጋት የተወጠሩ ሰዎች የሚወስኑትን የወደቀ ውሳኔ አትወስን። ለትንሹም ለትልቁም ነገር ምክንያት መደርደር ይሰለቻል። በገዛ ፍቃድህ ራስህን አቅመቢስ ደካማ አታድርገው፤ በምርጫህ ብቻ ህይወትህን ትርጉምአልባ አታድርገው። ምንም ነገር መጠበቅ ከፈለክ ካንተ የሚጠበቀውን ሃላፊነት እየተወጣህ ጠብቅ። መንገዶች ሁሉ ዝግ የሆኑብህ እንዳይመስልህ። ስኬት የአገልግሎትህ ክፍያ እንደሆነ አስተውል። ጊዜህን በጊዜያዊ ነገር ላይ ሳይሆን በዘላቂ ነገር ነገር ላይ አሳልፍ፤ አቅምህን በማይረባ ጫወታ ላይ ሳይሆን በሚረባ ትርፍ ያለው ተግባር ላይ አውለው። ዘወትር በርህን ለሚያንኳኳው እድልህ በርህን ከፍተህ ለማስገባት ደፋር ሁን።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:26


እንዳትቀደም!
፨፨፨/////፨፨፨
ድካምን በብርታት እንጂ በድካም አታሸንፈውም፤ ስልቹነትን በእረፍት እንጂ በእራሱ በስልቹነት አትረታውም፤ ድብርትን በንቃት እንጂ በድብርት አትሻገረውም። ፋታ መውሰድ ካለብህ አጣብቂኝ ሁነት ፋታ ካልወሰድክ በጊዜ ሂደት መመናመንህና በግዴታ ማረፍህ አይቀርም። የሰው ልጅ ድካም አለበት፣ ይታክታል፤ ይሰለቻል፤ ይደብረዋል። እነዚህ ስሜቶች ማንም ብትሆን አይቀሩልህም። ነገር ግን ከስሜቶቹ መምጣት በላይ አንተ የምትሰጣቸው ምላሽ እጅግ ወሳኝ ነው። በየትኛውም ከባድ ሁኔታ ጤናውን የሚያስቀድም፣ እራሱን ለማደስ የሚጥር፣ ካለበት ጫና ለመላቀቅ የሚሞክር ሰው መቼም በእራሱ ስህተት ሊጎዳ አይችልም። ሸክምን በሸክም ላይ፣ ሃሳብን በሃሳብ ላይ እየደራረብክ ሰላም ማግኘት ሳይሆን እራስህንም መሆን አትችልም። የሚያውቁትን መኖርና አውቀው እንዳላዋኪ መኖር የተለያዩ ናቸው።

አዎ! ጀግናዬ..! በአስገዳጁ እረፍት እንዳትቀደም፤ ጊዜውን ጠብቆ በሚመጣው ፈተና እንዳትቀደም። ዛሬ ፋታ ባለመውሰድህ አይቀሬው እረፍት ፈጥኖ መምጣቱ የግድ ነው። ከደከመህ ለማረፍ ጊዜ ይኑርህ፤ ሁኔታዎች ከሰለቹህ ዞር ለማለት አታመንታ፤ ህይወት ካማረረችህ እራስህን ከመንከባከብ ወደኋላ እንዳትል። ከምንም በፊት አንተ እንደምትቀድም አስታውስ። ንብረቱ የመጣው ባንተ ነው፤ ሰዎችን ለማገዝ የበቃሀው አንተ ነህ፤ ህልምህን የምትኖረው አንተ ነህ። አንዳንዴ ለእራስ ቅድሚያ መስጠት፣ እራስን መጠበቅ፣ እራስን መንከባከብ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው። በጣም ብዙ አስጨናቂና አሳሳቢ ጉዳዮች ይኖራሉ ነገር ግን ካንተ ደህንነትና ጤና ሊበልጡ አይችሉም።

አዎ! ባለህ ለማመስገን የብዙዎችን ሰቃይ ማስታወስ አይጠበቅብህም፤ በእራስህ ለመኩራት ብዙዎች ያጡትን ነገር መመልከት አይኖርብህም። ባለህ ደስተኛ የምትሆነው ለእራስህ ሰላምና ጤና ብለህ ነው። ጠንክሮ በሰራ፣ በደከመ፣ ቀን ሌሊት ሳይል ላቡን ጠብ አድርጎ በለፋ አይደለም። ምንም ነገር ብትሰራ ለእራስህ የምትሰጠው ጊዜ በጣም ወሳኝ ነው። ዛሬ እራስህን የምትሰጠው ነገር ነገ አንተንም ሊወስድህ እንደሚችል አስቀድመህ እወቅ። መሮጥህ ብቻ ሳይሆን ያለረፍት መሮጥህ ትንፋሽ አሳጥቶ ለከፋ አደጋ ሊዳርግህ እንደሚችል አስተውል። ስሜቶችህን አዳምጥ፤ በየጊዜው ፋታ ውስድ፤ እራስህን አድሰህ በአዲስ መንፈስ ወደ ስራህ ተመለስ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:26


ዳግም አንፀው!
፨፨፨///////፨፨፨
አፍርሰህ ገንባው፤ እንደገና አስተካክለህ አድሰው፣ ዳግም በንፅህናና በበጥንካሬ አንፀው። አዕምሮህ ትልቁና ዋናው የግል ንብረትህ ነው። የምትመራበትን መርህ ይቆጣጠራል፣ የልማዶችህ መሰረት ነው፣ የአስተሳሰብህ ምንጭ ነው፣ የትላልቅም ሆነ የትናንሽ አቋሞችህ መነሻ ነው። ከድብቁ አዕምሮህ የጅምላና የልማድ ሃሳብ እራስህን ነፃ አውጣ። ለዛሬ ያበቃህ የቀድሞ ልማድህ፣ ያለፈ እምነትህና የበፊቱ አመለካከትህ እንደሆነ አስተውል። በአንድ አይነት የእሳቤ ደረጃ ለተለየ ከፍታ መብቃት አይቻልምና የእሳቤ ደረጃህን፣ አዎንታዊነትህንና ብለሃትህን በማሻሻል መገንባት የምትፈልገውን ህልም መገንባት፣ ልታሳካ የምትመኘውንም ግብ ማሳካት ትችላለህ። ምናልባትም ዛሬ ሰበብ መደርደሩ እንደልማድነቱ ቀላል ሊሆን ይችላል፣ ለነገ ግን ነገሮችን ማክበዱ አይቀርም። እንዲሁ ዛሬ እራስን መግዛት ከባድ ሊሆን ይችላል፣ ለነገ ግን ቀላሉን ህይወት ያጎናፅፍሃል።

አዎ! ጀግናዬ..! እየጣለህ፣ እያሳመመህ፣ እየመረዘህና ወደኋላ እያስቀረህ ከሆነ ጊዜ ሳታጠፋ አዕምሮህን አፍርሰህ እንደገና ገንባው፤ በሚጠቅምህና በሚያሻግርህ መንገድ ዳግም አንፀው፤ እንደገና ሰርተሀው ለእራስህም እንዲሰራ አድርገው። ከአዕምሮህ ጋር ሰጣገባ ውስጥ እየገባህ፣ ከገዛ አመለካከትህ ጋር እየተሟገትክ፣ ለአመታት ከገነባሀው ልማድህ ጋር ፊትለፊት እየተጋጨህ በምንም መንገድ ለታሸንፍና ለድል ልትበቃ አትችልም። በአንዴ በሃይል፣ በቁጪትና በግለት የሚገረሰስ የአመለካከት ክምር፣ የአቋም ስብስብ የለም። ለውድቀት የሰጠሀው ቦታ በአንዴ የመጣ አይደለም፣ ፍረሃትን የምትመለከትበት መንገድ በቀላሉ የተፈጠረ አይደለም፣ ስለቆራጥንት ያለህ እይታ በብዙ አስተምህሮዎችና ተግባራዊ ተሞክሮዎች የተገነባ ነው። እናም በአንዴ የምትቀይረው ወይም አውጥተህ የምትጥለው አይደለም።

አዎ! ሰለዚህ ነገር አታስብ ተብለህ ቢነገርህ ስለምን እንደሆነ ተነግሮሃልና አለማሰብ አትችልም። እንዲሁ አዕምሮህንም ስለገዛው መጥፎ ልማድ ያለማሰብ እድልህ በጣም ጠባብ ነው። እያንዳንዱ የአዕምሮ እድሳትህ፣ የአመለካከት ለውጥህ አሉታዊዎቹንና ጎጂዎቹን ልማዶችህን በሂደት እንደሚቀይሩልህ እርግጠኛ ሁን። የለውጥ ሁሉ መሰረት የአስተሳሰብ ለውጥ ነው፤ የእድገት ሁሉ ቁልፍ ሳያቋርጡ እራስን ደጋግሞ ማስተማር ነው፤ በየጊዜ እራስ ላይ መዋለነዋይን ማፍሰሰ፣ ኢንቨስት (Invest) ማድረግ ነው። ማንኛውም ያስቸገረህ የህይወትህ ክፍል መፍትሔው ለእርሱ ከምትሰጠው ቦታና ከምትመለከትበት አቅጣጫ እንደሚነሳ ተረዳ። አመለካከትህ ላይ ስራ፤ አዕምሮህን በሚጠቅምህ መንገድ ዳግም አንፀው፤ ልማዶችህ እንዲሰሩብህ ሳይሆን እንዲሰሩልህ አድርጋቸው።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:26


ጓደኛ አታብዛ!
፨፨፨////፨፨፨
እውቁ አሜሪካዊ ቦክሰኛና ባለብዙ ድል ባለቤቱ ማይክ ታይሰን (Mike Tyson) እንዲህ ይላል፦ "የሁሉም ሰው ጓደኛ ከሆንክ አስታውስ አንተ የራስህ ጠላት ነህ።" ብዙ ጓደኛ ኖሮት ለራሱ በቂ ጊዜ የሚሰጥን ሰው ፈልግ፣ ያገኘውን ሰው በሙሉ ጓደኛ እያደረገ የተጠቀመን ሰው ፈልግ። በፍፁም አታገኝም። የጓደኛ ብዛት ችግር እንጂ ምንም የሚጠቅምህ ነገር የለውም። ከሰዎች ጋር ያለህን ግንኙነት ገደብ አብጅለት። በሰው ተከበህ ለራስህ ጠላት ከምትሆን ብቻህን ቀርተህ ለራስህ ወዳጅ ብትሆን ይሻላል። ጫወታው ጓደኛ ባበዛ ሳይሆን ጥራት ያላቸው ካንተ ባህሪና ማንነት ጋር የሚሔዱ፣ የሚጠቅሙህና የሚረዱህ ጥቂት የልብ ጓደኞችን ማፍራት ነው። ከራሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍ የማይወድ ሰው የጓደኞቹ ብዛት ተቆጥሮ አያልቅም። ባይፈልግም እንኳን ሁሌም ራሱን የሚያገኘው እነርሱን ለማስደሰት ሲጥር ነው። ብቸኝነትን ይፈራልና እየተጠቀሙበትም ቢሆን ጎጂ ጓደኝነት (toxic friendship) ውስጥ ለረጅም ጊዜ ይቆያል። ጓደኝነት ካልጠቀመህ ብዛቱ ምን ያደርግልሃል? በዙሪያህ ብዙ ሰው ካለ በዋናነት የምታቃጥለው የራስህን ውድ ጊዜ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ራስህን ታደግ! እርግጥ ነው ለብቻ መጓዝ ከባዱ ጉዞ ነው ነገር ግን ከእርሱ በላይ የሚያጠነክርህ ነገር የለም። በጫጫታና በአላስፈላጊ ድራማ በከበብ ማንንም ነፃ አውጥቶ አያውቅም። ብዙ ብዙ ጓደኛ ስላላቸው በሰዎች የሚወደዱ ይመስላቸዋል። ነገር ግን እነዛ ጓደኞቼ የሚሏቸው ሰዎች እንደሚወዷቸው ለማረጋገጥ በደስታቸውና በሃዘናቸው ጊዜ የሚሰማቸውን ስሜት ማስተዋል ቢችል ብዙ ያተርፋል። ምቀኛም ሆነ ሌባ ከሩቅ አይመጣም። አብዝቶ የሚያውቅህ፣ የቅርብ ጓደኛዬ ነው አመነዋለሁ የምትለው ሰው ስለሚቀናብህ ብቻ ከጀርባህ ምን ሊሰራብህ እንደሚችል አታውቅም። ብዙ ጓደኛ ሲኖርህ ችግር አያጣህም። የእያንዳንዳቸውን ችግር ለመቅረፍ ስትሞክር የራስህ ችግር ሊያሰምጥህ ይደርሳል። ለእነርሱ ስትሯሯጥ ራስህን ትረሳለህ፣ ምናልባትም ባላሰብከው መንገድ ልትጠፋ ትችላለህ። በአንድም ሆነ በሌላ የማይጠቅምህ ጓደኝነት እየጎዳህ ነው ማለት ነው።

አዎ! ጓደኛ አታብዛ፣ በዙሪያህ ያሉትን ሰዎች ቀንስ። ከእነርሱ የምታገኘውና ለእነርሱ በምትሰጠው ነገር ላይ ግንኙነትህን መስርት። በፍፁም ትርጉም አልባ ግንኙነት ውስጥ ተሳስተህ እንኳን እንዳትገባ። ግደኝነት የህይወት አቅጣጫህን ሙሉ በሙሉ ይቀይረዋል። በጓደኛህ ትጠፋለህ በጓደኛህ ትድናለህ። በክፉ ቀን የሚደርስህ ጓደኛህ ነው፣ ደስታህንም እንደራሱ ደስታ የሚደሰትልህ እርሱ ነው። ከባድም ቢሆን ጓደኛህን በአግባቡ ምረጥ። ከቻልክ ቁጥራቸውን ቀንስ፣ የጋራ ነገር ከሌላችሁና የማያተርፍልህ ከሆነ ጓደኝነቱ ይቅርብህ። ማንም ትርፍ አልባ ግንኙነት የሚፈልግ ሰው የለም። አንተ ለራስህ ካላወቅክ ማንም መጥቶ የሚጠቅምህን ሊነግርህ አይችልም። በመሰለህ መንገድ ሳይሆን በሚጠቅምህ ትክክለኛ መንገድ ተጓዝ። የይሉኝታ ተጠቂ አትሁን። አንዳንዴ ጓደኛህን ምንም ያህል ብትወድውም ወደ ጥፋት መንገድ እየመራህ ከሆነ አንድም ለራስህ ብለህ ሌላም ራስህን አድነህ ዳግም ተመልሰህ እርሱን ታድነው ዘንድ እያዘንክ ትተወዋለህ። የምታውቀውን ሰው በሙሉ ጓደኛ ለማድረግ አትሞክር ይልቅ በቅድሚያ የራስህ ጓደኛ ሁን።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:23


የምግብ ግብዣው

የባለቤቷን ቤተሰቦች ማክበር የማይሆንላት አንዲት ባልቴት ነበረች። አንድ ቀን ባለቤቷ እንዲህ አላት "ቤተሰቦቼ፣ ወንድም እህቶቼና ልጆቻቸው እጅግ ናፍቀውኛል።  ለነገ የምሳ ማዕድ አዘጋጂና   ለምሳ ፕሮግራም እንዲመጡ እጠራቸዋለሁ። ለበርካታ ጊዜያት ሳንገናኝ ከርመናል።" 
ሚስቲቱም የድካም ስሜት እያንፀባረቀችና በንቀት ዓይን እየተመለከተች " ኢን ሻ አላህ  ጥሩ እሺ" አለች። ባል ወዲያው ንግግሯን እንዳበቃች "እንግዲያውስ ቤተሰቦቼን በሙሉ ልብ እጠራቸዋለሁ" አለ። ፊቱ በደስታ የፈካ፣ ልቡም በፈንጠዚያ የተወጠረ ይመስላል።

ጊዜ ይተካካልና ትናንት አልፎ ቤተሰቦቹ የተጠሩበት ቀን ደረሰ። ባል በማለዳ ተነስቶና ተጣጥቦ ወደ ስራ ቦታው አቀና።  ብዙም ሳይቆይ ወደ ቤቱ ተመለሰ። ለባለቤቱ "የምሳውን ማዕድ አዘጋጅተሻላ? ቤተሰቦቼ  ከአንድ ሰዓት በኋላ ብቅ ይላሉ"  አላት።  ሚስት " አይ! ምንም የተለየ ምግብ አላዘጋጀሁም። ቤተሰቦችህ እንግዳ ስላልሆኑ ቤት ያፈራውን ይመገባሉ። ምንም ችግር የለውም።" አለች ቀለል አድርጋው። ምን ያልነካው ምን አያውቅም አሉ። ባል ድምፁን ንዴት ዋጠው። ትንሽ ዝምም አለና "ፈጣሪ ይቅር ይበልሽ! ትናንት ስንስማማ አላዘጋጅም፣ አልችልም ብለሽ አትነግሪኝም ነበር? አሁን ከ 1 ሰዓት በኋላ እዚህ ይደርሳሉ። ታድያ ምን ላደርግ ነው እሺ?" አላት። ፊቱ ላይ የሀዘን ዳመና አጥሎበታል። አንገቱን ወደታች አቀርቅሮ በሀሳብ ተውጧል። "በቃ ደውልላቸውና ምንም እንዳልተዘጋጀ አሳውቀህ  ይቅርታ በላቸው።  እነርሱ እንግዶችኮ አይደሉም ቤተሰቦችህ ናቸው።" አለች። 

ባል ልቡ በሀዘን ተሰብሮ ከቤት ወጣ። ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ  የቤቱ በር መንኳኳት ጀመረ። ሚስት ተነሳችና በሩን ከፈተችው።  አይን ለአይን ይተያዩ ጀመር። ድንጋጤ ውስጧን ገፈፈው። እንደ ድንገት በሩን የከፈተቻቸው ሰዎች የርሱ ቤተሰቦች ሳይሆኑ የርሷ ቤተሰብ፣ ወንድም እህቶቿና ልጆቻቸው ነበሩ።  "ባለቤትሽ የት ነው?" ሲል ጠየቃት አባቷ። እሷም "እ… አሁን ቅርብ ሰዓት ወጥቶ ነው" አለች።  "ትናንትኮ ለዛሬ የምሳ ግብዣ ጥሪ እንዳለ ነግሮን ነበር። እንዴት ጋብዞን እሱ ይጠፋል?" አላት።  ሚስት የምትሆነው ጠፋት። አንዳች ይሆናል ብላ የማታስበው ከባድ ዱብዳ የወረደባት መሰላት።  ነገሩ ግር አሰኝቷት እጆቿን ቆላለፈች።
ይገርማል! ቤት ያፈራው ምግብ ለሷ ቤተሰቦች የማይመጥን ለርሱ ቤተሰቦች ደግሞ ተገቢ መሆኑ ነው።  ሞባይሏን አንስታ ደወለች። ስልኩ ተነሳ።

"ሄሎ…  ቤተሰቦቼ የምግቡ ግብዣ ላይ እንደሚመጡ ለምን አላሳወቅከኝም?" አለች ጭንቀት በተሞላበት ቀጭን ድምፅ። "ያው ያንቺ ቤተሰቦች ማለት የኔ ቤተሰቦች ናቸው። ልዩነት አለው እንዴ?" አላት ባል።
  "እባክህን ከሆቴል የተዘጋጀ ምግብ ይዘህ ና!  ቤት ውስጥ ምግብ የለም።" አለች። ሳይታወቃት  የመርበትበት ነፋስ ስሜት ውስጥ የሰጠመች ይመስላል።
"እኔ አሁን ሩቅ ቦታ ነው ያለሁት።  እነዚህኮ እንግዶች አይደሉም ቤተሰቦችሽ ናቸው። ለኔ ቤተሰቦች ልትመግቢ የነበረውን ቤት ያፈራውን ምግብ አቅርቢላቸው። እሱን ይመገቡ። ይህም ቤተሰቦቼን ለማክበር ትምህርት ይሁንሽ" ስልኩ ተዘጋ!

"ሰዎች እንዲያደርጉልህ በምትፈልገው ነገር ሰዎችን አስተናግድ!

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:21


ገደብህ እራስህ ነህ!
፨፨፨፨//////////፨፨፨
በእድሜህ ብዙ አይተሃል፤ ምድር ላይ በቆየህባት ዘመን ብዙውን እተውለሃል። ከሁሉ በላይ የፈተነህ ግን የደስታህ ጉዳይ እንደሆነ እርግጥ ነው። የሁሉም ሰው የመጨረሻ ግብ ደስታና የሙላትን ህይወት መኖር ነውና ያንተም ከአርሱ አይለይም። ብዙዎች ግን ይህን ህይወት ፍለጋ የአሁን ደስታቸውን ያጣሉ፤ አንድ ቀን ለመደሰት ለዘመናት ይለፋሉ፤ አንድ ቀን ሰዎችን ለማስደሰት እራሳቸውን መሱዓት ያደርጋሉ። ደስታ ግባቸው የሆነ ሰዎች የሚጠብቁትን ደስታ እስኪያገኙ ቀን ከሌሊት ይተጋሉ፣ ይለፋሉ፣ ይደክማሉ። ትጋታቸውንም እየተመለከቱ ያ ቀን የቀረበ ይመስላቸዋል ነገር ግን ጊዜው በሄደ ቁጥር የመደሰቻ ጊዜውም እንዲሁ እየራቀ ይመጣል። ከረፈደም ቦሃላ ከሩቅ እንደሚመጣ ሲጠብቁት የነበረው ደስታ ከጉያቸው ተቀምጦ፣ አይናቸው ስር ሆኖ ከአይናቸው እንደተሰወረ ይገነዘባሉ።

አዎ! ጀግናዬ..! ገደብህ እራስህ ነህ! የደስታህ፣ የመረጋጋትህ፣ የውስጣዊ ሰላምህ ገደብ እራስህ ነህ። ከእራሳችን መምጣት የነበረበትን ነገር ከሰዎች ስንጠብቅ ጊዜያት ነጎዱ፤ አንድን ቀን በደስታ ለመኖር ለዘመናነት ስንታገል ዘመናት ነጎዱ፤ በሰዎች ዘንድ ስማችንን ልንተክል፣ ቅቡልነትን ልናገኝ፣ ተወዳጅነትን ልናተርፍ፣ ከብርን ልናገኝ ስንዳክር እራሳችንን ጣልነው። አንተ ለውጫዊው አለም እየደከምክ ውስጥህን ማን እንዲጠግን ትፈልጋለህ? በምታየው ነገር ብቻ እየተደመምክ ማን ባንተ ይደመም? ማንስ ላንተ ድካምና ትጋት እውቅና ይስጥህ? ደስታን ከውጭ ፍለጋ ስትጦዝ ያገኘሀው ሲመስልህ አላገኘሀውም፤ አገኘውት ብለህ ማጣጣም ስትጀምር ዳጋም ስታሳድደው እራስህን ታገኛለህ፤ ከአንዱ አንዱ የተለየ መልክ ይዞ ትመለከተዋለህ፤ ነገር ግን የትኛውም መልክ ካንተ ጋር እንደማይሔድ እያደር ይገባሃል።

አዎ! እራስህን ገድበህ ደስታህ ኬት ይመጣል? ውጪውን እያማተርክ ውስጥህ እንዴት ይዳን? ውዳቂ ተደግፈህ እንዴት ለእራስህ ብቁ መሆን ትችላለህ? ስልጡን መሪ አስቀድሞ የሰለጠነ ነው፤ ጎበዝ መምህር መጀመሪ እራሱን ያስተማረ ነው፤ የሰዎች የደስታ ምክንያት የሚሆን ሰው ቀድሞ በእራሱ የተደሰተ፣ ከማንነቱ እርካታን ያገኘ፣ በአምላኩ ፀጋ መሞላቱን ያወቀና ያሳወቀ ነው። ውጫዊ ፍለጋ መቋጫ የለውም፤ ውጫዊ አሰሳ መጨረሻው አይታወቅም። የምትፈልገውን ሰው ያገኘህ ሲመስልህ ከቆይታ ቦሃላ ጠፍቶ ታገኘዋለህ፤ በውጫዊ ነገር ለማረፍ ስትፈልግ በስተመጨረሻ ከንቱ ድካምህ ይታወቅሃል። ውጫዊ ሩጫህን ገታ አድርገው፤ ከባቢህን ከማሰስ መለስ በለ፤ እርጋታህን እራስህ ፍጠር፤ ሰላምህን አንተው ለማረጋገጥ ሞክር፤ ለእግዚአብሔር የበረከት ልጁ እንደሆንክ መገንዘብ ጀምር። ለአመታት ሮጠህ ካልሆነልህ ለትንሽ ጊዜ አድፍጠህ ለሰላምህ ዘብ፣ ለደስታህም ዋስትና ሁን።

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:21


እኛ እንደዚህ ነን!
፨፨፨////////፨፨፨
ይሔ የጋራ አቋማችን ሊሆን ይገባል፦ "አስተሳሰባችን ከወትሮው በተለየ መንገድ ተቀይሯል፣ ምቾትን ከማሳደድ እምቅ አቅማችንን ወደማሳደድ ተሸጋግረናል፣ በትንሽ ነገር ከመረበሽ ዲሲፕሊንድ መሆንን መርጠናል፣ ቆሞ ካሰብ እያደረግን ማሰብ ጀምረናል። ብዙዎች ላያምኑበት ይችላሉ እኛ ግን ወደ እውነታው እንጓዛለን፤ ለሁላችንም የወጣችውን ፀሃይ እንሞቃለን፣ በራችን ላይ ያለውን እድል እንጠቀማለን፣ እለት እለት ራሳችንን እናሳድጋለን፣ በየቀኑ ወደፊት እንራመዳለን። ከአሉታዊ ሀሳቦች በብዙ ማይል እንርቃለን፣ እይታችንን እናሻሽላለን፣ አስተሳሰባችንን እናስተካክላለን፣ አመለካከታችንን ከብዙ አቅጣጫ እንቃኛለን፣ እኛን ፈልገው ሊረብሹን የሚመጡ ሁኔታዎች እንዲቆጣጠሩን አንፈቅድም።" ከፈጣሪ ቀጥሎ የሰው ልጅ ትልቁ ደጋፊው እራሱ የሰው ልጅ ነው። ምናልባት ሰዎች የውድቀታችን መንስኤ፣ የህመማችን ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን በስተመጨረሻም ለከፍታችን የሚያግዙን፣ በጥረታችን ከጎናችን የሚቆሙት፣ ወደምንፈልገው ስፍራም እንድንሔድ የሚደግፉን እነርሱ ይሆናሉ። ፈጣሪ ለሰው ልጅ የሰጠው ትልቅ አቅም ራሱ ብቻ የሚፈልገውን ህይወት እንዲኖር እንዲያስችለው አይደለም። ይልቅ ከራሱ በላይ ብዙዎችን ይዞ እንዲያድግና ለሰው የሚተርፍ ህይወት እንዲኖረው የሚያደርግ ነው።

አዎ! እኛ እንደዚህ ነን! ከአቋምም አቋም አለን፣ ከእውቀትም እውቀት አለን፣ ከድፍረትም ድፍረት አለን። እየተደጋገፍን የት እንደምንደርስ እናውቃለን፣ አብረን ሆነን ምን መፍጠር እንደምንችል ይገባናል፣ ተረዳድተን ወዴት እንደምንቀየር እናውቃለን። ከብዙዎች የተነጠልነው ምርጫችንን ስለምናከብር ነው፤ ምቾትን የምንሸሸው እድገትን አጥብቀን ስለምንፈልግ ነው፤ እንቅልፍና ድካም፣ ድብርትና ስንፍና የማያሸንፉን የሚንቀለቀል ውስጣዊ ፍላጎት ስላለን ነው። እንዴትም አንዘናጋም፣ ማንም ከጀመርነው የታላቅነት ጉዞ አያስቆመንም፣ ለብዙዎች ይሔን መቀበል ቢከብዳቸውም ለራሳችን ነፃነት ማንም እንዲዋጋልን አንፈልግም። እራሳችን ተዋግተን እራሳችንን ነፃ እናወጣለን። እስከዛሬ ከሰው ስንጠብቅ የባከነው ጊዜ ይበቃል፣ እስከ አሁን የኖርነው የበታችነትና የፍረሃት ህይወት ይበቃል። ከአሁን ቦሃላ ቁጭ ብለን የምንመኘው አስደሳች ህይወት የለም፤ ሰርተን እንኖረዋለን፣ ከአሁን ቦሃላ በግርድፉ የምናሳልፈው ውድ ጊዜ አይኖርም፣ ከፋፍለን በአግባቡ እንጠቀመዋለን።

አዎ! ጀግናዬ..! አቋማችን ግልፅ ነው። የራሳችንን ቤተመንግሥት የምንገነባው እኛው ነን፤ እስከ ተራራው ጫፍ የምንጓዘው እኛው ነን፤ በፍቅርና በፅናት የምናሸንፈው እኛው ነን። ሰዎች አሳክተው የምንመለከተውን ትልቅ ነገር የማሳካት አቅሙ እንዳለን ያመንን እለት የህይወት ዘይቤያችን በሙሉ እየተቀየረ ይመጣል። ድልድያችንን አፍርሰናል፣ ምንም ወደኋላ የሚመልሰን ነገር አይኖርም፣ ማሳካት የምንፈልገውን ነገር ከማሳካት ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም። ወደፊት የምንጓዘው ማንም ገፍቶን ሳይሆን ፈልገን ነው፤ ጠንክረን የምንሰራው ተመችቶን ሳይሆን ስቃይ ወዳጃችን ምቾትም ጠላታችን እንደሆነ ስለገባን ነው። የምናውቀውን እናውቃለን ባወቅነው ልክም ለመኖር እንጥራለን፤ የገባን ገብቶናል በገባን ልክም ሁሌም ልናሳካው እንሞክራለን። ከባዱን መንገድ ስንመርጥ በዋናነት ከባዱን ማሳካት የሚችል ማንነት እግዚአብሔር እንደሚሰጠን ስለምናምን ነው፣ ሌላም ውስጣችን ያለው እምቅ አቅም ከባዱንም ነገር መቋቋም እንደሚችል ስለምናምን ነው። አሁን ጉዞ ጀምረናል እስክናሸንፍ አናቆምም፤ አሁን ሂደቱ ውስጥ ነን ሂደቱን ሳናጠናቅቅ ወደኋላ አንመለስም። በእርግጥም የተጠማነውን ስኬት በእጃችን አስገብተን በጋራ የምንኮራበት ጊዜ ሩቅ አይደለም።
እንበርታ ቤተሰቦች!
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:21


ፍቅርም ይባክናል!
፨፨፨፨//////፨፨፨፨
ስንት ያለቦታው ሲገባ፣ የማይመጥነው ስፍራ ሲገኝ፣ ለማይመጥነው ሲሰጥ የሚባክን ነገር ታውቃላችሁ? ገንዘብ፣ እውቀት፣ ጊዜ ሌላም ሌም። እንዲሁ ፍቅርም ከሚባክኑ ስጦታዎቻችን ውስጥ አንዱ ነው። የማይገባችሁን ሰው አፍቅራችሁ ስትሰቃዩ ፍቅራችሁን ለማይገባው ሰው ሰጥታችኋልና በሌላ መንገድ እያባከናችሁት ነው፤ ምናቹንም ለመቀበል ዝግጁና ፍቃደኛ ያልሆነ ሰው ፍላጎታችሁን በግድ እንዲቀበል እራሳችሁንና ሰውዬውን ስታስጨንቁ ፍላጎታችሁ ያለምንም ምክንያት እየባከነ ነው። የትኛውም ትግል ብክነት ባይሆንም ትርፍ አልባው፣ አስጨናቂውና ዋጋ ቢሱ ትግል ግን ብክነት ነው። ሰው ፍላጎቱን ሊያሳካ ላይ ታች ይላል፣ ይወጣል ይወርዳል፣ እራሱን አሳልፎ እስከመስጠትም ይደርሳል። ለማን እራሱን አሳልፎ እንደሚሰጥ ካላወቀ ግን ውድቀቱ የማይሆን ይሆናል።

አዎ! ጀግናዬ..! ፍቅርም ይባክናል፤ የተቀጣጠለው፣ ገደብ አልባው፣ የታፈነው መውደድም ዋጋ ያጣል፣ ይንኮታኮታል፣ ትርፍ አልባ ይሆናል። ከሶስቴ በላይ አከታትለህ ደውለህ የማይነሳን ስልክ ለማስገደድ ብትጥር ሸክሙ የእራስህ ነው፤ ለረጅም ጊዜ ደጇ ስትጠና፣ ፍላጎትህን ስታሳያት፣ ስሜትህን ስታስረዳት ሰንብተህ ትኩረት ከተነፈክ፣ ችላ ከተባልክ፣ ፍቅርህ ምላሽ ካጣ በጊዜ መንገድህን መቀየሩ የእራስህ ሃላፊነት ነው። ምንም የሚሰጥ ነገር ሊኖርህ ይችላል፣ ምንም እፁብ ድንቅ የምታጋራው ስጦታ ሊኖርህ ይችላል፣ የትኛውንም ዓለምን የሚያስደምም እንቁ በእጅህ ሊገባ ይችላል ያለቦታው ሲቀመጥ ግን ከምንም አንሶ መና የሆነ ብክነትን ብቻ የሚያስከትል የሚሆንበት ጊዜ ይኖራል። ንጉስ በሃገሩ ንጉስ ነው በሰው ሃገር ግን መደበኛ የሀገሬው ነዋሪ ነው። ፍቅርህም ለሚገባው ሰው ሲሰጥ የምድራዊ ገነትህ መፍጠሪያ መሳሪያ ነው፤ ለማይገባው ሲሰጥ ግን ምድራዊ ሲዖል ውስጥ የሚከትህ ይሆናል።

አዎ! አንዳንድ መልካም ነገሮች በደፈናው መልካም ይሆናሉ እንዳንዶች ግን በቦታና በሁኔታ ይገደባሉ መልካምነታቸውንም ያጣሉ። የፍቅር መጥፎ የለውም፣ ምንም እንኳን የፈለገውን ምላሽ የመስጠት ምርጫ ቢኖረውም የሚፈቀረው ሰው ግን መጥፎ ሊያደርገው ይችላል። ያለምንም ጥርጥር አብዝተህ ደጅ ፀንተህ በጎና ፍፁም እንከን አልባ ምላሽ ሊሰጥህ የሚችለው እግዚአብሔር አምላክህ ብቻ ነው። የሰጠሀውን ለመቀበል እራስህን ብታዘጋጅ ስብራቱ ለእራስህ ነው። ፍቅርህ ሲባክን፣ መውደድህ ትርጉም ሲያጣ፣ እንክብካቤህ ከንቱ ልፋት ሲሆን ማንነትህን ያሳንሳልና፣ ዋጋህን ያወርደዋልና ከሚባክን ፍቅር እራስህን ጠብቅ። ለብክነት የሚሆን ጊዜም ሆነ ስሜት እንደሌለህ ለእራስህ አስምረህ ንገረው።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:21


//•• Mastering Your mind & Thought ••//

ተመስጦህን አሳድግ !!!

የተመስጦ  ዋናውን ገጽታ የበለጠ እያሰላሰልክ ስትሄድ፤ አንተ አለቃ፣ አእምሮህ ደግሞ ባሪያ ይሆናል፤ ሁልጊዜም መሆን ያለበት እንደዚህ ነው። አእምሮ ማለቂያ በሌለው መከራ ውስጥ የሚያሳልፍህ አስፈሪ ጌታ ቢሆንም፣ በተወሰነ መንገድ ከያዝከው ግን የምትፈልገውን ማንኛውንም - ነገር ልታደርግበት የምትችል ድንቅ ባሪያ ይሆናል። በዚህ ጊዜ በደንብ ልትቆጣጠረው ትችላለህ
ማሰብ ከፈለግክ ማሰብ ትችላለህ፧ ማሰብ ካልፈለግክ ደግሞ አታስብም፡፡ መሆን የሚገባውም እንደዚህ ነው፡፡

አሁን እጄን ማንቀሳቀስ ከፈለግኩ እጄን አንቀሳቅሳለሁ፤ ካልፈለግኩ ደግሞ አላንቀሳቅስም፡፡ ሰውነትህ ሁልጊዜ ዝም ብሎ የሚንቀሳቀስ ፡ ከሆነ፣ እብድ እየሆንክ ነው ማለት ነው። በአእምሮህ ላይም ተመሳሳይ ነገር እየሆነ ከሆነ ማለትም ማሰብህን ማቆም እየፈለክ ደጋግመህ በማይረቡ ሀሳቦች ውስጥ የምተዘፈቅ ከሆነ ፣ ሰዎች ሊያዩት በቀላሉ ስለማይችሉ እብድ ሆኗል አትባልም እንጂ ፣በበቂ  ሁኔታ ራስህን  ስትመለከት  ግን እያበድክ እንደሆነ ትገነዘባለህ።


አእምሮህ ተመስጦ አይወድም። መቀመጥና ማሰላሰል ስትፈልግ አእምሮህ ያንን እንዳታደርግ ሁሉንም ነገር ያደርጋል። በመጀመሪያ" ነገ ታደርገዋለህ” ይልሃል። “ነገ” የአእምሮ ጥልቅ ማታለያ ነው።ነገ ደግሞ በፍጹም አይመጣም፡፡ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ብዙ ነገሮችን “ነገ” ብለዋል፡፡ ለራሳቸው ደስታ ሳይቀር “ነገ” ይላሉ፡፡

ለተመስጦ ወይም ለማሰላሰል ስትቀመጥ የአእምሮ “ነገ” የሚለው  ዘዴ ካልትሳካና “አይ፣ ነገ አይሆንም፤ ዛሬ ለማድረግ ቆርጫለሁ” ካልክ፣ ሁለተኛ ዘዴውን ይሞክራል፡፡ ሳምንቱን ሙሉ ለማስታወስ ስትሞክር የነበረው የስልክ ቁጥር ድንገት ብልጭ ይልልህና ወደ  ስልክህ ትሮጣለህ ተመስጦውም ያበቃል፡፡

ይህንንም - ከተቋቋምክና ወደ ስልኩ ሳትሮጥ ተመስጦህን ከቀጠልክ፣ በሁለት እና ሶስት ደቂቃዎች ደርዘን የሚሆኑ የተለያዩ የሰውነትህ ክፍሎች በድንገት ያሳክኩሀል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ አእምሮ ሰውነት ከተረጋጋ እርሱም እንደሚረጋጋ ስለሚያውቅ ነው፡፡ አእምሮ ይህ እንዲሆን ከፈቀደ ደግሞ ባርያ እንደሚሆን ያውቃል፡፡

ራስህን ብታስተውል፤ ስትቆም፣ ስትቀመጥና ስትናገር ሰውነትህ ምን ያህል አላስፈላጊ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያደርግ ታያለህ። ሕይወትህን ስትመለከት ምናልባት ከግማሽ በላይ ጊዜ የወሰዱት እነዚህ ነገሮች እንደሆኑ ትገነዘባለህ፡፡ በሰውነትህ ውስጥ አንተ  ግድ የማትሰጣቸው ብዙ አላስፈላጊ ሀሳቦችና እንቅስቃሴዎች አሉ። ነገር ግን ሰውነት መረጋጋት ከቀጠለ፣ አእምሮም ቀስ በቀስ መርገብ ይጀምራል።

ይህን ማድረግ ከቻልክ፣ አእምሮ የሚያደርገውን  የማያቋርጥ ሩጫ ገታህ ማለት ነው።እናም አእምሮ በድንገት የተለየና ድንቅ ባሪያ ይሆናል።

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍
YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:21


ማን ይምጣ?
፨፨፨////፨፨፨
ያንተን የግል ችግር ለመፍታት ማን ይምጣ? ያንተን ጭንቀት ካንተ በላይ ለመጨነቅ ማን ይምጣ? አንተን በሌሊት ሊቀሰቅስህ፣ ስፖርት ሊያሰራህ፣ ስራህን በአግባቡ እንድትሰራ ሊያደርግህ፣ ወደፊት እንድትጓዝ ሊያደርግህ ማን ይምጣ? አንተ የተሻልክ ሰው ትሆን ዘንድ ምን ይፈጠር? አንተ ህይወትህን ትቀይር ዘንድ መንግስት ድጎማ ያዘጋጅልህ ወይስ ቤተሰቦችህ ስር ስርህ እየሔዱ ይለምኑህ? አንተ ደስተኛ ስኬታማ ትሆን ዘንድ ወዳጅ ጓደኞችህ የራሳቸውን ህይወት ትተው ያንተ ረዳት ይሁኑ ወይስ በየጊዜው የሚያስፈልግህን ነገር ያሟሉልህ? ለራሱ የማያውቅ ሞኝ አትሁን። ላንተ ህይወት ካንተ በላይ ሃላፊነት የሚወስድ ሰው የለም። ዛሬ ተነስተህ አንተ ብትወድቅ፣ ብትጎዳ፣ ብትከስር፣ ብትገፋ፣ ብትሰቃይ ካንተ በላይ ሁኔታው ሊያስጨንቀው የሚችል ሰው ልታገኝ አትችልም። "ቤተሰቤ የምፈልገውን አላደረገልኝም፣ ጓደኞቼ አይረዱኝም፣ ፍቅረኛዬ ጊዜ አትሰጠኝም፣ መንግስት ደሞዝ አልጨመረልኝም" እያልክ ብታለቃቅስ ትርፍህን እዛው ከጎንህ ታገኛለህ። ሰው እየወቀሰ አንድ ያለፈለትን ሰው ፈልግ፣ ለውድቀቱ ሌላ አካል ላይ እያሳበበ ዳግም ራሱን ያገኘን ሰው ፈልግ ኬትም አታገኝም።

አዎ! ጀግናዬ...! ራሱን የሚያጃጅል ጂል አትሁን፣ ራሱ ላይ የሚበላውን ቁማር የሚቆምር ሰነፍ ቁማርተኛ አትሁን።  ብታምንም ባታምንም ያንተ ህይወት 100% ያንተ ሃላፊነት ነው። ማንን በምን ላይ ተስፋ ማድረግ እንዳለብህ ጠንቅቀህ እወቅ፣ ማንን ተደግፈህ ወዴት እንደምትሔድ አስተውል። ለሆነብህ ነገር ዙሪያህን ከመውቀስ ራስህን መውቀስ እስካልጀመርክ ድረስ አንድ እርምጃ ወደፊት ልትራመድ አትችልም። በአላፊ አግዳሚው መረበሽህን፣ የመጣው የሔደው ላይ አይንህን ማንከራተትህን፣ በቀላሉ እጅ መስጠትህን፣ የማይመለከትህ ጉዳይ ተንታኝ መሆንህን፣ በማያገባህ መግባትህን፣ ሳይጠሩህ አቤት ሳይልኩህ ወዴት ማለትህን አቁም። እውቀትህ የማትፈልገውን ህይወት መቀየር እስኪችል ድረስ መማርህን እንዳታቆም፤ ከራስህ በላይ በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ባንተ ተፅዕኖ ስር መውደቅ እስኪችሉ ድረስ ጠንክረህ መስራትህን እንዳታቆም። "ሊታደጉኝ ይመጣሉ፣ አሁን ካለሁበት አስከፊ ህይወት ያወጡኛል፣ ችግሬ ይገባቸዋል፣ ፍላጌትን ይረዱታል፣ ጥረቴን ያግዛሉ፣ ከጎኔ ይቆማሉ" ብለህ የምትጠብቃቸው ሰዎች አይመጡም ተስፋ ቁረጥ፣ እነርሱም የራሳቸው ብዙ ጣጣ አለባቸው አትጠብቃቸው።

አዎ! ከፈጣሪ ውጪ ከሰው መጠበቅን አሁን በቃኝ ካላልክ መቼ በቃኝ ልትል ነው? አሁን ሌላውን አካል መውቀስ ካላቆምክ መቼ ልታቆም ነው? ዛሬ ለራስህ ህይወት ሃላፊነት መውሰድ ካልጀመርክ መቼ ልትጀምር ነው? ዓለም በምታሳይህ ጊዜያዊ ብልጭልጭ አትሸወድ፣ ለምታጠምድህ የፈጣን እርካታ ሱስ ራስህን አትስጥ። ወደፊት መጓዝ የምትፈልግ ከሆነ መራር ቢሆንም እውነታውን ለመቀበል ደፋር ሁን። አንተ የሌለህበት ህይውት ባዶ እንደመሆኑ፣ ያንተ ጥረት የሌለበት ነገርም ትርፍ ሊያመጣልህ አይችልም። የሁሉም መጀመሪያ፣ የሁሉም መጨረሻ አንተ ነህ። ይሔ እውነታ ዛሬ ባይገባህ ነገ ይገባሃል፣ ነገም ባይሆን ከጥቂት ጊዜያት ቦሃላ በተግባር ይገባሃል። አሁን የጀመርከውን ነገር አቋርጠህ ከሆነ ተመልሰህ ጀምረው፣ አሁን ከሚጠቅምህ ሙድ ወጥተህ ከሆነ ድጋሜ ተመለስ፣ አሁን በብዙ ጅምሮች ተከበህ ከሆነ ሁሉንም በየተራ ጨርሳቸው። ሰውን ትልቅ ሰው የሚያደርገው መጀመር ሳይሆን የጀመሩትን መጨረስ እንደሆነ አስታውስ። ከማንም ምንም አይነት ግፊት አትፈልግ፣ ራስህን ወደፊት ግፋው፣ የሚጠበቅብህን ስራም በፍጥነት ጀምር።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:21


አያውቁኝም!
፨፨፨///፨፨፨
ከራስ ጋር ንግግር፦ "አንተ ማነህ ብለው ቢጠይቁኝ ምላሼ "እኔ እኔ ነኝ" ነው። ማንም ጠንቅቆ ሊያውቀኝ የሚፈልግ ካለ እስከዛሬ የተጓዝኳቸውን ጉዞዎች አብሮኝ መጓዝ አለበት፣ እስከዛሬ ሳስባቸው የነበርኩትን ሀሳቦች አብሮኝ ማሰብ አለበት፣ እስከ ዛሬ የሞከርኳቸውን ስራዎች አብሮኝ መሞከር አለበት፣ እስከዛሬ በገፉኝ ሰዎች መገፋት አለበት። ካለዛ በፍፁም እንዴትም እኔን ሊያውቀኝ አይችልም። ምንያህል ርቀት ብቻዬን ከፈጣሪዬ ጋር ብቻ ስጓዝ እንደነበር ማንም አያውቅም፤ ምንያህል አስፈሪና አስጨናቂ ቀናንትን ፊት ለፊት ስጋፈጥ እንደነበር ማንም አያውቅም፤ ምንያህል እንቅልፍ አልባ ምሺቶችን ሳሳልፍ እንደነበር ማንም አያውቅም፤ ምንያህል ሰዓት ወገቤ እስኪጎብጥ፣ እጆቼ እስኪዝሉ፣ አዕምሮዬ እስኪደነዝዝ ስሰራ እንደነበር ማንም አያውቅም። ሁሉም የሚያውቀው ውጤቴን ብቻ ነው፣ ሁሉም የሚያየው የደረስኩበትን ደረጃ ብቻ ነው። ብዙዎች የስኬታማ ሰዎችን ህይወት ይመኛሉ ነገር ግን ስቃይና ድካማቸውን በፍፁም አይመኙም፤ ብዙዎች በዓለም አደባባይ ስማቸው ተጠርቶ የአሸናፊነት ሜዳልያን ማጥለቅ ይፈልጋሉ ነገር ግን አሸናፊ የሚያደርገውን የዘመናት ልምምድ አይፈልጉም።

አዎ! ስሜንና ስራዬን ሲያውቁ ያወቁኝ ይመስላቸዋል ነገር ግን በፍፁም አያውቁኝም፤ ውሎዬንና ንግግሬን ስላወቁ ማንነቴንም የተረዱት ይመስላቸዋል ነገር ግን በፍፁም አልተረዱትም። ማንነቴን እኔና ፈጣሪዬ በሚገባ እናውቀዋልን። ምን እንደዚህ እንደ አለት እንዳጠነከረኝ፣ እነማን ወደዚህ ከፍታ እንገፉኝ፣ ማንን ለማስደሰት ትልቅ ዋጋ እንደከፈልኩ ከእኔና ከፈጣሪ በቀር ማንም አያውቅም። ከብዙ ድካምና ስቃይ ቦሃላ ቢገባኝም አንዴ ከገባኝ ቦሃላ ግን አንድም ቀን ዓለምን ለማሸነፍ ታግዬ አላውቅም፤ ለደቂቃዎች ከአቅሜ በላይ በሆነ ጉዳይ እራሴን ለማስጨነቅ ሞክሬ አላውቅም። ጥረቴ ራሴን ለማሸነፍ ነው። አንዳንዴ እላለሁ "ፈተናዎቼ ጌጦቼ ናቸው፣ መሰናክሎቼ ሰሪዎቼ ናቸው።" በእነርሱ ብኮራ እንጂ በፍፁም አላዝንም፤ በእነርሱ ብመካ እንጂ በፍፁም አላፍርም። ምክንያቱም ብርቱውንና ጠንካራውን ማንነት ገንብተው ሰጥተውኛልና፤ ምክንያቱም የዛሬውን እኔ በሚገርም ሁኔታ ገንብተው አስረክበውኛልና። ራሴን በሚገባ ካወቅኩት፣ የመረጥኩትን ምርጫና የምጓዝበትን መንገድ ከተረዳው በሰው ለመታወቄ ግድ የለኝም። በሰው ለመታወቅ ብቁ ስሆን ያኔ ሊያውቀኝ የሚፈልግ ሁሉ ያውቀኛል። እስከዛ ግን ሁሌም ራሴን ለማወቅ እጥራለሁ፣ ጥበቡንም ፈጣሪ እንዲያድለኝ ዘወትር እማፀነዋለሁ።"

አዎ! ጀግናዬ..! እያንዳንዳችን ብዙ ብዙ ሰው የማያውቀው፣ ለሰውም የማይነገሩ እንዲሁ በጓዳ ጎድጓዳው የተደበቁ አያሌ ነገሮች አሉን። እኚህ ነገሮች ፈልገነውም ሆነ ሳንፈልገው ሰርተውናል ወይም አፍርሰውናል። ማንም የማያውቃቸው የብችኝነት ፈተናዎች ዛሬ ቀና ብለህ በኩራት እንድትራመድ አድርገውሃል። ለአፍታም ቢሆን ጥረትህና ድካም ለሰው እይታ እንዳይሆን። ሰው ከውጭ ባየህ ሊለካህ ቢሞክርም አንተ ግን ማን እንደሆንክ፣ ወዴት እንደምትሔድ፣ ምንስ ማሳካት እንደምትችል አንተ ታውቃለህ። እንደ አምላክ ፍቃድ እነዛን አስፈሪ ጊዜያት አልፈሃል፣ በፅናትና ትዕግስትህ ልክ ጠንካራውን ማንንትህን ገንብተሃል። አሁን ላይ ራስህን ታውቀዋለህ፣ ውስጥህን ትረዳለህ፣ ዙሪያህን ትቃኛለህ፣ እንኳን ሊሸጡህ ይቅርና ሲያስማሙህ ታውቃለህ። እነዛ የሚያሴሩብህ ላይ ቆቅ ሁንባቸው፣ እነዛ ያወቁህ ለመሰላቸው ድብቅ ሰው ሁንባቸው። መገለጥ ስትፈልግ ብቻ በልክ ተገለጥ፣ አስፈሪውናና ባለግራማሞገሱን ማንነትም ራስህ ጋር አቆየው። 
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:21


ለመናገር ጊዜ አለው!
፨፨፨፨//////////፨፨፨፨
አስተዋይ ሰው አስተውሎቱ የሚታወቀው ከንግግር ዝምታን የመረጠ እለት ነው። ለዘመናት አውርታችሁ ምንም ካላመጣችሁ አሁን ተራውን ለዝምታ ሰጥታችሁ ሞክሩት፣ ለረጅም ጊዜ ብዙ በማውራታችሁ እውቅና አግኝታችሁ ተፅዕኖ መፍጠር ካልቻላችሁ ለዝምታም ጊዜ ሰጥታችሁ ተፅዕኖውን አስተውሉ። በህይወታችሁ እንደማትችሉት የሚሰማችሁ ትልቅ ነገር ምንድነው? እንደ ተራራ አልገፋ ብሎ ያስቸገራችሁ አበይት ጉዳይ ምንድነው? ለዓመታት አልፋታ ያላችሁ ችግር ምንድነው? እርሱ ምንም ይሁን ነገር ግን እርሱን ላገኛችሁት ሰው ሁሉ ማውራት መፍትሔ እንደማያመጣላችሁ እወቁ። ለሁሉም ጊዜ አለው እንደሚል ቅዱስ መፅሐፍ ለመናገርም ጊዜ አለው፣ ለዝምታም እንዲሁ ጊዜ አለው። ዝምታን ወይም ንግግርን የምትመርጡበት ሁኔታ መፃኢውን የህይወት አውዳችሁን ይወስነዋል። ዝም ማለት ባለባችሁ ሰዓት ብትናገሩ ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል? መናገር በሚኖርባችሁ ጊዜስ ዝም ብትሉ ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል? ነገሮች በሁኔታዎች ላይ ይመሰረታሉ። በቅፅበታት ውስጥ የሚወሰኑ ውሳኔዎችም ቀጣዩን የህይወት መንገድ የሚወስኑ ይሆናል።

አዎ! ለመናገር ጊዜ አለው፤ ቃላትን ለማውጣት ጊዜ አለው፣ ስሜትን ለመግለፅ፣ ሁኔታዎችን ለማስረዳት፣ ጥፋትን ለመጠቆም፣ ሀሳብን አደባባይ ለማውጣት ጊዜ አለው። አንዳንዴ በቃላት ከምታስረዱት በላይ ዝምታችሁ ነገሩን በግፅ ሊያስረዳ ይችላል። ቃላት አውጥቶ መናገር፣ ጮክ ብሎ ማውራት፣ ምንም ነገር በግልፅ ማድረግ ለአንዳንዶች የጥንካሬና የአስፈሪነት ምልክት መስሎ ይታያቸዋል። እውነታው ግን ማንም ጮክ ብሎ ቢያወራ፣ ማንም በሃይለ ቃላት ቢናገር፣ ማንም ያለውን ነገር በሙሉ ለሰው ቢያሳይ ከዛ ዝምታን ከመረጠው፣ ከተረጋጋውና ነገሮችን በፀጥታ ውስጥ ከሚከታተለው ሰው በላይ ሊያስፈራና ሰውን ሊያሸብር አይችልም። ብታውቁት ዝምታና ጊዜ ማንም የማይሰጣችሁን ሃይል ይሰጧችኋል። ምንምያህል በእርሱ አሻግራችሁ የምትመለከቱት ነገር ውብና አጓጉዊ ቢሆንም የሚጎዳችሁን መስኮት መዝጋት ይኖርባችኋል። ምናልባት በንግግራችሁ ብዙዎችን እያስደሰታችሁና ለብዙዎች እየጠቀማችሁ ቢሆንም ንግግራችሁ ግን ለእናንተ እንደ እሾህ ተመልሶ እየወጋችሁና ለራሳችሁ የምትሰጡትን ቦታ እያሳነሰ ከሆነ መናገራችሁን አቁሙና በዝምታ ነገሮችን ማስተዋል ጀምሩ። እድሉን ስላገኛችሁ ብቻ አትናገሩ፣ የመናገር እድል ስለተነፈጋችሁም ብቻም ዝም አትበሉ። ምርጫችሁን ምክንያታዊ አድርጉት።

አዎ! ጀግናዬ..! ማንም የማይቀማህን አደገኛ ትጥቅ ታጥቀሃል። እርሱም አንደበትህ ነው። ዝም ሲልም ሆነ ሲናገር ተፅዕኖ መፍጠር ይችል ዘንድ አጠቃቀሙን በሚገባ እወቀው። ያለጊዜው ብትጠቀመው ያጠፋሃል፣ በጊዜው ብትጠቀመው ግን ከምታስበው በላይ ከፍታ ላይ ያስቀምጥሃል። መናገር እንደሚችሉ እያወቁ ጊዜው ስላልሆነ ብቻ ዝም የሚሉ፣ ዝም ማለት እንደሚችሉ እያወቁ ጊዜው እንዳልሆነ ስላወቁ የሚናገሩ ሰዎች ህይወት ምነኛ የገባቻቸው ሰዎች ናቸው? አስተዋይ ዝም ይላል፣ ብልህ ሰውም የንግግሩን ጊዜ ጠንቅቆ ያውቃል። ጊዜ ስላለህ ብቻ በአንዴ ብዙ ስራ ልትሰራ አትችልም፣ ስለፈለክ ብቻም እንደፈለክ የመናገር መብቱ የለህም። የቅጣትና የፀፀት ናዳ ሳይወርድብህ ልብህን ግዛ፤ የማንም መሳቂያና መሳለቂያ ከመሆንህ በፊት ለአንደበትህ ስረዓት አብጅለት። የእውነት አዋቂ፣ የምርም ጠቢብ ትሆን ዘንድ ለምታደርገው የትኛውም ነገር ጊዜ አስቀምጥለት። ሃይልና ብርታትህን በገዛ ፍቃድህ ለሰዎች አሳልፈህ አትስጥ። ቁጥብ ሁን፣ ራስህን ግዛ፣ ምንም ከመናገርህ በፊት ጊዜው መሆኑን ተረጋግተህ አስብ።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:21


አትዋከቡ!
፨፨////፨፨
አንድ ቀን ቆም ብላችሁ ወደኋላ ትመለከታላችሁ። በሰዓቱም ፈጣሪ እያንዳንዱን የህይወት ጉዟችሁን አብሯችሁ እንደተጓዘ ታስተውላላችሁ። አሁንም ቢሆን ብቻችሁን የሆናችሁ ቢመስላችሁም ብቻችሁን እንዳልሆናችሁ እወቁ፤ ውጤት አልባ ጥረት ላይ እንዳላችሁ የሚሰማችሁ ቢመስላችሁም እስካላቆማችሁ ድረስ ግን ጥረታችሁ አንድ ቀን እንደሚከፍላችሁ እወቁ። ሁሌም ቢሆን ይሔንን አስታውሱ፦ የፈጣሪ ጊዜ ከእናንተ ጊዜ የፈጠነና የተሻለ ነው። ስለቸኮላችሁ የፈለጋችሁትን አታገኙም፣ ስለሮጣችሁ ከሁሉም ቀድማችሁ አትደርሱም፣ ያለማቋረጥ ስለለፋችሁም የምትመኙትን ህይወት አትኖሩም። እግዚአብሔር ካለው ጊዜ የተሻለ ፈጣንና ትክክለኛ ጊዜ የለም። ሁሌም ቢሆን የመጨረሻ ተስፋችሁም ሆነ ምርኩዛችሁ ፈጣሪ እንደሆነ እወቁ። ብቸኝነትን የመረጡ የፈጣሪን አብሮነት ያስተዋሉ ናቸው፤ ተገፍተው ብቻቸውን የሆኑ ግን የፈጣሪን አብሮነት ሊያስታውሱ አይችሉም። በምርጫ ውስጥ እውቀት አለ፣ በግፊት ውስጥ ግን ጭንቀትና ብሶት አለ።

አዎ! ከትክክለኛው የፈጣሪ ጊዜ ለመቅደም አትዋከቡ፤ እርሱ ካሰበላችሁ በተሻለ ለማግኘት ራሳችሁን አትሰዉ። ሰውን ተከራክራችሁ እንደምትረቱት ከፈጣሪ ጋር ተከራክራችሁ ለማሸነፍ አትሞክሩ። እናንተ አሁን ላይ ጥሩ ሁኔታ አይደላችሁም ማለት፣ እናንተ ተበድላችኋል ማለት፣ ደጋግማችሁ ወድቃችኋል ማለት፣ ብቸኝነት ጎድቷችኋል ማለት ፈጣሪ ለእናንተ ሲሆን ተሳስቷል ማለት እንዳልሆነ አስተውሉ። የእርሱ ስራ አንዳች ስህተት ጥቂት ግድፈት የለባትም። እርሱ ይሁን ካለው የማይሆን አንዳች ነገር የለም። ከአቅማችሁ በላይ በሆነው የፈጣሪ ስራ ገብታችሁ ራሳችሁን ከልክ በላይ አታስጨንቁ። ይልቅ የሆነው መሆኑ አይቀርምና የሆነውን ለመቀበል ራሳችሁን አዘጋጁ፣ ራሳችሁን አጠንክሩ፣ ፈጣሪ ብርታቱን እንዲሰጣችሁ ተማፀኑ። ምድር ላይ የሰው ልጅ ሳይቀር የትኛውም ነገር ማለፉና ታሪክ መሆኑ አይቀርም። ማለፉ ለማይቀር ጊዜያዊ ስሜትና ክስተት ራሳችሁን መውቀስ አቁሙ።

አዎ! ጀግናዬ..! የምትፈልገው ነገር ሁሉ ፈጣሪህ ጋር አለ። ቀን ከሌሊት የምትደክምለት ገንዘብ፣ እንቅልፍ አጥተህ የምትጨነቅለት አስደሳች የፍቅር ህይወት፣ ያለማቋረጥ ለዓመታት ዋጋ የምትከፍልለት ዝናና እውቅና፣ ዛሬ ላይ የምትተችበት የራስህ የህይወት መንገድ ሁሉ አምላክህ ጋር አለ። ህይወትህን ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ አታድርገው። ፈጣሪህን ሳታገኘው፣ የእርሱን ፍቃድ ሳትጠይቅ፣ ህግጋቱን ሳትጠብቅ ምንም ነገር ለማግኘት ብትለፋ ትርፉ ድካም እንጂ ምንም አይነት ውጤት አይኖረውም። ንቁዎች በመንገዳቸው ሁሉ ስኬትን ይጎናፀፉ ዘንድ ፈጣሪያቸውን ያስቀድማሉ፤ ልባሞች የተረጋጋና ደስተኛ ህይወትን ይኖሩ ዘንድ ለእያንዳንዱ ተግባራቸው የአምላክን ይሁንታ ይጠብቃሉ። የእውነት በፈጣሪያቸው ፍቅር የተማረኩ፣ እገዛውን የሚያሰተውሉ፣ አብሮነቱ የገባቸው፣ ለእነርሱ ያደረገውን ያወቁ ሰዎች ለአፍታ ከእርሱ ፈቀቅ አይሉም፣ ለደቂቃዎች ህግጋቱን ለመሻር አያስቡም። የተገዙት በፍቅር እንጂ በፍረሃት አይደለም፤ የሚተማመኑበት በሰው ስለተከዱ ሳይሆን አስቀድመው መርጠውት ነው። ሀሳብህ ሁሉ በፈጣሪ መንገድ ይከናወንልህ ዘንድ ታጋሽ ሁን፣ የፈጣሪን ጊዜ ጠብቅ፣ ፅናትና ብርታቱንም እርሱ እንዲሰጥህ ራስህን አዘጋጅ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:21


ራሳችሁን አትናቁ!
፨፨፨////////፨፨፨
ክቡሩ የሰው ልጅ መቼም ሙሉ ህይወት ኖሮ አያውቅም፤ ምርጡ የሰው ልጅ መቼም ያፈለገውን ሁሉ እያደረገ ኖሮ አያውቅም። በእርግጥ ደካማ ነው፣ አቅመቢስ ነው፣ ልፍስፍስ ነው። ነገር ግን አንድ ብርታት አለው እርሱም ፈጣሪው ነው። ፈጣሪው በእርሱ ላይ ተዓምራትን ያደርጋል፣ የተወሰነ ማንነቱን በፀጋና በበረከት ያትረፈርፈዋል፣ የተገደበ አቅሙን በሃይሉ ገደብ አልባ ያደርገዋል። ራሳችሁን ከሰዎች ጋር እያስተያያችሁ የበታችነታችሁን አታጉሉት፣ የሌላችሁን እየቆጠራችሁ ራሳችሁን አትናቁ፣ ድክመታችሁ ላይ እያተኮራችሁ ተነሳሽነታችሁን አትግደሉት። የተሻለው ሁሉ እንደሚገባችሁ ከልባችሁ እመኑ፣ ጥሩ የተባለው ነገር በሙሉ በእጃችሁ መግባት እንደሚችል እወቁ። ራሱን የሚንቅ ሰው ፈጣሪውን እንደሚንቅ ሰው ነው፣ በራሱ የሚያፍር ሰው በአምላኩ እንደሚያፍር ሰው ነው። ማንም ያልሰጣችሁ ሰውነታችሁ ብቻ ያጎናፀፋችሁ ክብር እንዳለ አስተውሉ። ዝቅታና ትህትናችሁ ራስን በመናቅና በመጥላት ሳይሆን በእውቀትና በእምነት ይሁን።

አዎ! ራሳችሁን አትናቁ፣ ራሳችሁን አትግፉት። ራስን እየበደሉ የሚመጣው ፅድቅና ከፍታም ይቅርባችሁ። ከቻላችሁ ከነሙሉ ማንነታችሁ ቀና በሉ፣ ለእያንዳንዱ ፍላጎታችሁ ራሳችሁን ስጡ። ለራስ የሚሰጥ ቦታ በሔዳችሁበት ሁሉ እንደሚከተላችሁ እወቁ። ሰው ስለእናንተ ከሚያስበው በላይ የህይወት አቅጣጫችሁን የሚወስነው እናንተ ስለራሳችሁ የምታስቡት ነገር ነው። በምናባችሁ የሳላችሁ ሰው ይዋል ይደር እንጂ በገሃድ መገለጡ የማይቀር ጉዳይ ነው። በአንዴ ብዙ ነገር ይደራረብባችሁ ይሆናል፣ ችግር ከየአቅጣጫው ፈተናም ከየመንገዱ ይመጣባችሁ ይሆናል። ነገር ግን ራሳን ያለልክ ዝቅ ማድረግና መናቅ በፍፁም ለመጡት ችግሮች መፍትሔ ሊሆን አይችልም። ራሳችሁን ለማዳን ስትሉ የግድ ፊት ለፊት ተጋፍጣችሁ ማለፍ የሚኖርባችሁ ሁኔታዎች ይኖራሉ። ፍረሃት ቆልፎ ውስጣችሁን አሳስሮ እንዲያስቀምጥ አትፍቀዱ። ከአቅማችሁ በላይ የሆነ ነገር ቢገጥማችሁ እንኳን ፈጣሪ ብርታትና ድፍረቱን እንዲሰጣችሁ ተማፀኑት። ምንም ብታደርጉ ከራሳችሁ በላይ በአምላካችሁ መመካትን አስቀድሙ።

አዎ! ጀግናዬ..! በሰዎች እንኳን ሲደረግብህ ክፉኛ የሚያሳምምህን መጥፎ ተግባር በፍፁም ራስህ ላይ አታድርግ። ራስህን በጥሩ አይን ተመልከት፣ ያለህበትን ሁኔታ በአዎንታዊነት አስተውለው። ልብህን በቅንነት ክፈተው ነገር ግን አስቀድሞ ለራሱ ቅን እንዲሆን አድርገው፣ ምርጫህን አክብረው ነገር ግን ጉዳት አልባ እንደሆነ እንዳታስብ። ብዙ ጊዜ የነገሮች መበላሸት የሚከሰቱት የምንጠብቃቸውና የሚሆኑት ነገሮች መሃል ትልቅ ልዩነት ሲፈጠር ነው። ከራስህ የምትጠብቀው ትልቅ ቢሆንም ነገሮች ከጠበቅከው በታች ሲሆኑ ለራስህ የሰጠሀውን ስፍራ አታሳንስ። መውደቅ መነሳት፣ ማግኘት ማጣት፣ መደሰት ማዘን የሰው ልጆች ሁሉ የህይወት አካል እንደሆኑ አስታውስ። ከራስህ ጋር ሰጣገባ ውስጥ አትግባ። የሆንከውን ማንነት ተቀበል፣ ያለህበትን ደረጃ አክብር፣ አሁን በህይወትህ እየተከናወኑ ላሉ ጉዳዮች እውቅና ስጥ። የምትወዳቸውን አስቀጥል፣ የማትወዳቸውንም ለመቀየር ተንቀሳቀስ። ለራስህ ቀና ሁኑ፣ ለራስህ የዋህ ሁን። ለሰው ማሰቡም ውጤታማ ይሆን ዘንድ ለራስህ ከማሰብ ቦሃላ አድርገው።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:21


ስራቸው ነው!
፨፨፨///፨፨፨
ሳቄን ምን ሊቀማኝ ይችላል ብለህ ብታስብ በቅድሚያ ወደ አዕምሮህ የሚመጡት ሰዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች እነማናቸው ብለህ ብትጠይቅ ደግሞ እነዛ አንተ በሌለህበት ከጀርባህ የሚያወሩብህ፣ አንተን አጀንዳ ማድረግ የማይሰለቻቸው፣ አንተ ፊት ወዳጅ ከጀርባህ ግን ጠላት የሚሆኑብህ፣ በምላሳቸው የሚማርኩህ በድርጊታቸው የሚያቆስሉህ ሰዎች ናቸው። ምናልባት ልታውቃቸውም ላታውቃቸው ትችላለህ ነገር ግን ስለመኖራቸው አንዳች ጥርጣሬ የለህም። እነዚህ ሰዎች ከጀርባህ የሚያወሩትን ሁሉ ብትሰማ ህይወትህ ምን ያህል ደስታ የራቀው፣ የጨለማ ጥላ ያጠላበት፣ በትንሽ ኮሽታ የሚደነግጥ፣ ስብራቱን መጠገን የማይችል፣ በቅዠትና በተስፋቢስነት የተሞላ እንደሚሆን አስበው። ከጀርባችን የሚወራውን አለመስማት፣ ስንታማም ከስፍራው አለመገኘታችን ምናልባትም ዛሬ በጤና ለመኖራችን ትልቁ ምክንያት ሊሆን ይችላል። እነማን ስላንተ ምን እንደሚያወሩ አንተ ታውቃለህ፣ እነማንም ለውድቀትህ ጉድጓድ እንደሚምሱልህ ታውቃለህ። ያወሩብኛል ብለህ ውስጥህን አታስጨንቅ፣ ያሙኛል ብለህ ከራስህ እምነት አትጉደል።

አዎ! ጀግናዬ..! ተዋቸው እነርሱ ስራቸው ነው፤ እርሳቸው እነሱ መገለጫቸው እርሱ ነው። ምንም ያውሩ ምን አንተ የምታውቀው እውነተኛ ማንነት አለህ። ማንም ሰው ተገዶ ያለምንም ምክንያት ሰውን ከጀርባው አያማውም፣ የሰውዬውን ክፉ ክፉ ነገርም ደጋግሞ አያነሳም። ብዙ ጠላት ይኖርሃል አንተ ግን ለጠላትህ ብለህ ሳይሆን ለራስህና ለወዳጅህ ላለህ ፍቅር ብለህ በራስህ ተማመን፣ ለሚሸረብብህ ሴራ እጅ አትስጥ፣ የሚወራብህን ወሬ አትስማ፣ በምትገፋው ልክ ለውድቀት አትቅረብ። አንዳንድ የጀርባ ግፊቶች ለተጠቀመባቸው አርቀው ወደፊት የሚያስወነጭፉ ናቸው። ለጤናህ፣ ለደህንነትህና ለደስታህ ስትል ስላንተ የሚወራውን ክፉ ነገር ብትሰማ እንኳን እንዳልሰማህ ሆነህ እለፈው፣ ውስጥህን እየከፋህ ቢሆንም ለያዝከው አላማ ብለህ ችላ ብለህ እለፈው። የማንም ንግግር የሚያደናቅፍህ ልፍስፍስ ሰው አለመሆንህን ለራስህ ንገረው፤ ያሰብከውን እንጂ የታሰበልህን የማታደርግ ኩሩ ሰው መሆንህን ለራስህ አሳይ። አቅም አለህ አቅምህ ግን የሚፈትነው መሰናክል ይኖረዋል፤ ፅኑ አቋም አለህ አቋምህ ግን ልብን በሚሰብሩ አሉታዊ ንግግሮች ይፈተናል።

አዎ! የተሻሉና ጥሩ ደረጃ ላይ የደረሱ ሰዎች በፍፁም ስላንተ መጥፎ ነገር እንደማያወሩ እወቅ። የሚቀኑብህና እንደምትበልጣቸው የሚያስቡ ሰዎች ግን ሁሌም አጀንዳቸው አንተ ነህ። አንድ መራር እውነት አለ፦ "ማንም መበለጥን አይፈልግም።" ስለዚህ እነዚህ ከኋላህ ስምህን የሚያጠፉ ሰዎች በተግባር ስላልቻሉህ በወሬ ሊጥሉህ የሚጥሩ ከበታችሁ ያሉ ሰዎች ናቸው። በእርግጥ ከጀርባህ የሚወራብህን ሁሉ ብትሰማ ከማንም ጋር መኖር አትችልም ነበር። ሰምትህ እንዳልሰማህ፣ አውቀህ እንዳላወቅክህ፣ ገብቶህ እንዳልገባህ እንዳልገባህ የምትሆነው የሚበጅህን በሚገባ ስለምታውቅ ነው። የትናንሽ ሀሳብ ባለቤት የሆኑ ሰዎች ንግግራቸውም ተግባራቸውም ትንንሽ ነው። ለመውደቅ የሚንገዳገዱ ሰዎች በሚወረውሩብህ ቃል ከጥረትህ አትስተጓጎል፤ አዋቂነት ባወራ ለሚመስላቸው ሰው መልስ ለመስጠት አትቸኩል። በልብህ የያዝከው አላማህና ወደፊት የሚነዳህ ህልምህ መሰረት ሰው ሳይሆን አንተ እንተ ነህ። ለራስህ የሚያዳላ፣ አንተን ጠብቆ ለብዙዎች ሊያበቃህ የሚገባ ደንዳና ልብ እንደሚያስፈልግህ አትርሳ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:21


"ያማረ ነገህ የሚፈጠረው ዛሬ በምትሰራው ነገር እንጂ፤ ነገ በምታደርገው አይደለም !"
                    
ብዙዎቻችን ሂወት ተደጋጋሚ ሆነችብኝ ፣ለውጥ ያስፈልገኛል፣ ጥሩ ደሞዝ የሚከፍል ስራ ማግኝት አለብኝ፣ የራሴን 'ቢዝነስ' መጀመር  እፈልጋለሁ የመሳሰሉትን እንላለን:: ለውጥ መፈለጉና የተሻለ ነገን መመኘቱ  መልካም ሆኖ ሳለ፤ እነዚህ ነገሮች ወደኛ እንዲመጡ ከኛ የሚጠበቅብንን ነገር አድርገናል ወይ ዋነኛው ጥያቄ ነው??

በአንድ ወቅት አንድ ፀሀፊ እንዲህ ብሎ ነበር...

"በቀን 5 ገፅ እንኳን የማንበብ ‘ዲሲፕሊን’ ሳይኖርህ/ሽ፤ እንዴት የተሻለ ስራ አላገኘሁም ብለህ/ሽ ታማርራለህ/ለሽ?
በቀን ለ30 ደቂቃ ስፖርት መስራት አቀበት ሆኖብህ/ሽ ሲያበቃ፤ ጤናዬ ተዛባ ብለህ ለምን ታዝናለህ/ለሽ?
ለሰዓት እና ለስራ ያለህ/ሽ አመልካከት ግድ የለሽ ሆኖ፤ የሚከፈለኝ ብር በቂ አደለም ብለህ/ሽ ትቆዝማለህ/ለሽ..." የመሳሰሉት...

ይሄ ይገባኛል ከማለታችን በፊት ፤ከትላንት የተሻለ ማንነትና ብቃት እንዲኖረን እራሳችን ላይ ምን ያህል  'ኢንቨስት' አድርገናል ሚለውን መጠየቅ ተገቢ ነው::

በሂወታችን እንዲመጡ የምንፈልጋቸውን ለውጦች እኛው እንፍጠራቸው:: 'ስኬት' በኛ 'ዲሲፕሊን' ላይ የተመሰረተች ናትና::

በህይወት የምንፈልገውን ማወቅ፣ ቀድመን ማቀድ  ፣ ላመንበት ነገር ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆን፣ እራሳችንን ከአልሆነ ምቾት ውስጥ በማውጣት አዲስ ነገር መሞከርና ነገ እሰራዋለሁ የማለት ስንፍናን በማቆም፤ ይምንፈልገውን ነገ  ዛሬ እንስራ!

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:18


አንድ ሰው ሲመጣ..!
፨፨፨፨///////፨፨፨፨፨
አንድ ሰው ሲመጣ፣ ወደ ህይወትህ ሲገባ የወደድክለትንንና የተማረክበትን ማንነት ብቻ ይዞ አይመጣም። ልታከብርለትና ልትቀበለው የሚገባ ሌላ የእራሱ አመለካከት፣ የእራሱ አቋም፣ የእራሱ ባህሪ አለው። የምትወድለት እንዳለ ሆኖ የማትወድለትንና የማይመችህን ባህሪውንና ስብዕናን የመቀበል ግዴታ አለብህ። አንድ ሰው አንድ ነው፤ ደስ የሚለ ስብዕና፣ ማራኪ ውበት እንዳለው ሁሉ አንዳንዴ ተቀባይነት የሌለውና መልካም የማይባል ባህሪም ሊኖረው ይችላል። ለዚህ ግድፈትና ህፀፅ ምክንያትም በፍፁም ልትተወውና ከህይወትህ ልታስወጣው አትደፍርም። ፍሬውን ለመብላት አንዳንዴም ቢሆን በእሾሁ መወጋትህ ግድ ነውና።

አዎ! ጀግናዬ..! አንድ ሰው ሲመጣ፣ አንተም ስትሔድበት፣ ስትመርጠው እርሱም ሲመርጥህ መምጣቱን ብቻ አትመልከት። ይዞልህ የሚመጣው እንደመኖሩ ይዞብህ የሚመጣውም ጉዳይ ይኖራል። የምትቀበለው እርሱን ብቻ ሳይሆን የእርሱ የሆነውንም ጭምር ነው። አንድን ሰው ለይቶ መውደድ፣ ለይቶ መቀበል አይቻልም። ወደህ የእራስህ ማድረግህ ካልቀረ የማትወዳቸውን እያንዳንዱን ባህሪውን፣ ከቻልክ የምትወደው ሰው ላይ ስለሆኑ ብቻ ልትወዳቸው ትሞክራለህ፣ ካልቻልክ ግን ልታሻሽላቸው፣ ልትቀይራቸው ትሞክራለህ፣ ካልሆነም አክብሮ መቀበሉን ትመርጣለህ።

አዎ! የወደድካትን፣ ያፈቀርካትን፣ የመረጥካትን ሴት አንተ አልሰራሃትም። ይህም እርሷ አንተ የምትፈልገውን ነገር ብቻ አላት ማለት አይደለም። የማትፈልገውም ነገር ሊኖራት ይችላል፤ በፈጣሪዋና በሰሪዋ ፊት ግን እንከን አልባ፣ ምንም የማይቀነስባት የማይጨመርባት ፍፁም ነች። ፍፅምናዋን መቀበል ባይቻልህ ባንተ ፊት ጉድለት መስሎ የታየህን ማክበር እንዲሁም ለመሙት መጣር ግን ትችላለህ።
አዎ! ባንቺ መነፅር፣ ባንቺ እይታ ፍፁምና እንከን አልባ የነበረው ምርጫሽ በሂደት የጎደለው ነገር እንዳለ ሊታይሽ ይችላል። ጅማሬሽ ላዩን ቢያይም ቆይታሽና ሂደቱ ግን ውስጡን በጥልቀት እንድትመለከቺ ያደርግሻል። የእውቀት ልኩም ሽፋን ሳይሆን ውስጥ ነውና ባወቅሽው ልክ አክብሮትን፣ ፍቅርን፣ እንክብካቤን መለገስ ልመጂ። የታየሽ ልዩነትና ክፍተት ስላወቅሽው ነውና እውቀቱን አትጠይው፤ ተቀብለሽ በመቻቻልና በመከባበር ወደፊት መጓዙን ሁነኛ ምርጫሽ አድርጊ።

ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

21 Jan, 00:18


ሳይደጋገምብህ..!
፨፨፨፨//////፨፨፨፨
የተቃራኒ ሁነቶች አስተማሪነት እጅግ አስገራሚና ተመጋጋቢ ነው። በዚህም ዙሪያ ቱርኮች አንድ አባባል አላቸው "የመጥፎውን አፕል ጠዓም ካላወክ በጣፋጩ አትደነቅም።" ይህም ማለት ልክ እንደ ህይወት፣ ተጀግረህ እስካላየህ ከችግር ነፃ መሆን ስሜት አይሰጥህም፣ ታመህ እስካላየህ በጤንነትህ አታመሰግንም እንደማለት ነው። የውሃን ጥም ሲጠማህ ታውቀዋለህ፣ የረሃብን ስሜት ስትራብ፣ የፍቅርን መልካምነት በጥላቻ ክፋት፣ የሰላምን ዋጋም ሰላም ስታጣ ይገባሃል። ሳትኖረው፣ ሳታልፈው፣ ሳታሳልፈው የሚገባህ የህይወት ልምድ አይኖርም። ባንተ ላይ ባይከሰት ሰዎች ላይ ተከስቶ ታየዋለህ፣ ባንተ ባይደርስም ሌሎች ላይ ደርሶ ትመለከታለህ። ፈልገህ ሳይሆን ተገደህ የህወትን ክፉ ጎን ተመለከታለህ፣ የሰውን ልጅ ተንኮልና ሴራ ረቂነት ታያለህ፤  የጭካኔው ጥግ ይገባሃል። ያለማሰብን ውርደት ማሰብና ማገናዘብ ስትችል ታውቀዋለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ከሰውነት መውጣት የሚታወቅህ ሰው ስትሆን ብቻ ነው፤ የሚራራ ልብ፣ አዛኝ ልቦና የሚኖርህ ሰው ስትሆን ብቻ ነው። ህይወት የጠቃሚውን ነገር ጥቅም ለማስረዳት የመጥፎውን ጉዳት ታቋድስሃለች፣ በመነሳት እንድትገረም ደጋግማ ትጥልሃለች፤ በስኬትህ እንድትደነቅ በስኬት አልባ አዙሪት ታሽሃለች፤ የእቅድ ዋጋ እንዲገባህ በእቅድ አልባነት ታባክንሃለች፤ የመኖር አላማህን እንድታገኘ በተለያዩ መንገዶች ታዳክርሃለች። ስንፍናን ስታሸንፍ የብርታ፣ የጥንካሬ ዋጋ ይገባሃል፤ ከውድቀትህ ስታገግም ወድቆ መነሳት ትልቅ ድል አድራጊነት እንደሆነ ትረዳለህ። በህይወት መንገድ ተቃራኒ መንገዶች አሉ። ከተማርንባቸውና ከተረዳናቸውም ከእነሱ የሚበልጥ የህይወት ዘመን አስተማሪ የለም። የመጥፎ ሁኔታዎች መብዛት፣ የአስከፊ ገጠመኞት መደጋገም፣ የአጣብቂኝ አጋጣሚዎች መደራረብ የበጎውን፣ የመልካሙንና የጠቃሚውን ሁነት ዋጋ በሚገባ እንድናስበው ሊያደርገን ይገባል።

አዎ! ሳይደጋገምብህ፣ ሳይደራረብብህ ከመራራው የህይወት መንገድ እራስህን ግታ። አንድ ሁለቴ በተመሳሳይ ችግር ውስጥ ከተገኘህ ይበቃሃል፤ አንድ ሁለቴ ለከባድ ሁኔታ እራስህን ካጋለጥክ ይበቃሃል፤ ለተወሰነ ጊዜ ተመሳሳይ ስፍራ ከተገኘህ ይበቃሃል። መንቀሳቀስ ለአካልም ሆና ለአዕምሮ አስፈላጊ ነውና ካለህበት ስፍራ ቀስቀስ በል፤ ዞር ዞር በል፤ ዙሪያህን ተመልከት፤ ስፍራህን ጎብኝ። በማጣት አረንቋ ዘወትር አትሰቃይ፣ በችግር ብሶት ታስረህ አትቀመጥ፣ በህመም ውርጅብኝ እራስህን አትቅጣ። ህይወት የምታስተምረው ለሚማር ብቻ ነውና ሁሌም በተመሳሳይ የህይወት ውጣውረድ እራስህን አታድክም፣ በተመሳሳይ መራር ጠዓም አታሰልቻት። በቶሎ ተማር፣ በቶሎ ዞር በል፣ የተማርከውንም በቶሎ መኖር ጀምር።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/@mikre_aimro2
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪