Skyline media

@skyline7777


Skyline media

21 Oct, 09:43


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት መተግበር ለኢትዮጵያ ምን ያስገኛል?
የናይል ተፋሰስ አገራት ለሚያስተሳስራቸው የዓለም ረጅሙ ወንዝ፤ የትብብር እና አጠቃቀም ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ሂደት የጀመሩት ከ27 ዓመት በፊት እ.አ.አ በ1997 ነበር። ሦስት አስር ዓመታት ገደማን የፈጀው ስምምነት የማርቀቅ፣ የድርድር እና የማፅደቅ ሂደት ባለፈው ሳምንት እሁድ ጥቅምት 3/2017 ዓ.ም. የመጨረሻውን ደረጃ አጠናቅቆ ተፈጻሚ መሆን ጀምሯል። ኢትዮጵያ ለዓመታት ስትጥርበት የነበረው የዚህ ስምምነት ተግባራዊ መሆን ምን ጥቅም ያስገኝላታል?
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

Skyline media

18 Oct, 17:10


https://www.youtube.com/live/sc7Bw7pdhrM?si=ncslK8hRzPj7Xo3u

Skyline media

18 Oct, 09:36


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ለሦስት ከፍተኛ ኃላፊነቶች ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡

በዚሁ መሠረት ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ሰላማዊት ካሳ የቱሪዝም ሚኒስትር እንዲሁም ሃና አርዓያሥላሴ የፍትሕ ሚኒስትር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመዋል፡፡

በቅርቡ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው በተሰየሙት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ቦታ የተተኩት ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) የፍትሕ ሚኒስትር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

በሌላ በኩል ሰላማዊት ካሳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ እንዲሁም ሃና አርዓያሥላሴ ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

Skyline media

18 Oct, 02:18


ከቡና ወጪ ንግድ 519 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ
*************

በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሶስት ወራት ወደ ውጭ ከተላከ ቡና 519 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ።

በሩብ ዓመቱ 115 ሺህ 851 ቶን በላይ የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት ወደ ውጭ በመላክ 522 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ መገኘቱን ባለሥልጣኑ ገልጿል።

ከተገኘው ገቢ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘው የቡና ምርት መሆኑም ተጠቁሟል።

በተጠቀሰው ጊዜ 115 ሺህ 174 ነጥብ 75 ቶን ቡና በመላክ 519 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መገኘቱም ነው የተገለጸው።

በ2016 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተላከው ጋር ሲነጻጸር የዚህ ዓመቱ በመጠን 69 በመቶ እና በገቢ የ46 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Skyline media

17 Oct, 17:29


#ኢትዮጵያ  #ሶማሌላንድ

የኢትዮጵያ መንግሥት ራስ ገዟ ሶማሌላንድ አዲስ አበባ ላይ ኢምባሲ እንድትገነባ በነጻ ቦታ ሰጥቷል።

የሶማሌላንድ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኢሳ ካይድ፣ ለግዛቲቷ በተሰጣት ቦታ ላይ ትናንት የኢምባሲውን የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

መንግሥት ለኢምባሲ መገንቢያ ቦታ መስጠቱቱ፣ በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ መካከል ያለውን የኹለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ እንደሚጠናክረው የግዛቲቷ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ገልጧል።

Skyline media

17 Oct, 17:15


የፓን-አፍሪካ የመከላከያ ኃይሎች ትብብርን እውን የሚያደርግ ስትራቴጂ ያስፈልጋል - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን


የፓን-አፍሪካ የመከላከያ ኃይሎች ትብብርን እውን የሚያደርግ ስትራቴጂ እንደሚያስፈልግ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተር ጄኔራሉ በአዲስ አበባ በተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ መከላከያ ሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ “በአፍሪካ የመከላከያ ኃይሎች መካከል ያለውን ትብብር” የተመለከተ የመወያያ ጽሑፍ አቅርበዋል።

ባቀረቡት ገለፃም "ዓለም በአሁኑ ወቅት አንዱ ሌላውን ጥሎ የሚያልፍበት የበይ እና ተበይ አውድ ውስጥ ይገኛል" ብለዋል፡፡

የዓለም ነባራዊ ሁኔታ የፓን-አፍሪካ የመከላከያ ኃይሎች ትብብርን እውን የሚያደርግ ስትራቴጂ ቀርፆ ወደ ተግባር መግባትን የግድ እንደሚልም ጠቁመዋል፡፡

በዚህ ዓለም አቀፋዊ አውድ ውስጥ አፍሪካ አንድነቷን ካላጠናከረች ልክ እንደ በፊቱ የሌሎች የመጫወቻ ሜዳ የመሆን ዕጣ እንደሚገጥማትም አንስተዋል፡፡

Skyline media

17 Oct, 15:12


አዳኒ ኢትዮጵያ በሽግግር ወቅት ላይ ነች እና ጊዜ ሰጡኝ ብሏል።

"ጊዜ ሰጥተነዋል፣ ኢትዮጵያ በሽግግር ወቅት ላይ ነበረች፣ የሥርዓት ለውጥ ተካሂዶ አዲስ አገዛዝ መጣ።ስለዚህ ይህ ግምገማ ከቀደምቶቹ ውስጥ አንዱ ቢሆንም በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ወደሚገኝበት ወሳኝ ወቅት አልፏል። እኛን የሚነኩ ሁኔታዎች ናቸው ስለዚህ ዓይኖቻችንን የምንከፍትበት ደረጃ ላይ ነን ሲሉ የአዳኒ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

በዚህ አመት መስከረም ወር ላይ ከኢትዮጵያ ወታደራዊ አዛዥ ብርሃኑ ጁላ ለቀረበለት መግለጫ ኦብነግ ምላሽ ሰጥቷል።

በመግለጫው የኢትዮጵያ መንግስት የአዛዡን መግለጫ ለማብራራት እና ለማብራራት እየጠበቀ መሆኑን ተናግራለች።

በወቅቱ ለቢቢሲ ያነጋገራቸው የኦብነግ ቃል አቀባይ ጉዳዩ አስገራሚ መሆኑን ተናግሮ ሊቀበለው አልቻለም።

አብዱልቃድር ሀሰን ሂርሞጌ (አዳኒ) ኦብነግ ያንን አባባል እንደ ቅስቀሳ እንደሚቆጥረው ጠቁመዋል።

"ለእኛ እንግዳ እና አዲስ ነገር ነው የዛፎቹ እግር እየተረገጠ የኢትዮጵያ ሃይሎች ጠላት ሆነው ከኋላችን እንዳሉ ተጠቁሟል።

የኦብነግ መግለጫ በቅርቡ በኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ብርሃኑ ጁላ የተሰጠ መግለጫን ተከትሎ ነው።

Skyline media

17 Oct, 15:10


የእነዚህ ድንጋጌዎች ውጤት ምንድን ነው?

"በሰላም አብረን እንድንኖር እና በአጠቃላይ ለስድስት አመታት ለሰላም ስንታገል የቆየው ብቸኛው ነገር ስለ ሰራዊቱ የተፃፉት ፅሁፎች አልተተገበሩም ፣ የተጎዱትን ህዝቦች መልሶ የማቋቋም ፅሁፎች። ጦርነቶቹ አልተተገበሩም፣ ውይይቱ ሊቀጥል የሚገባቸው ኮሚቴዎች ለችግሩ መሰረት እና ከየት እንደመጣ መፍትሄ የማፈላለጉ ሂደት ትንሽ ተጀምሯል እና አልቀጠለም ብለዋል አብዲቃድር ሀሰን

Skyline media

17 Oct, 15:08


እ.ኤ.አ. በ2018 ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተፈራረሙትን የሰላም ስምምነት በፓርቲዎቹ መካከል የረዥም ጊዜ ጦርነት ያስቆመውን ኦብነግ በድጋሚ እየገመገመ ነው ብሏል። ድርጅቱ ከ6 አመት በፊት የተስማሙባቸው አንዳንድ ድንጋጌዎች ተግባራዊ እንዳልሆኑ ገልጿል።

በኢትዮጵያ እና በኦብነግ መካከል የተደረገው ስምምነት ምን ነበር?

ለቢቢሲ ልዩ ቃለ ምልልስ የሰጡት የኦብነግ ቃል አቀባይ አብዲቃድር ሀሰን ሂርሞጌ (ነጭ) እንደተናገሩት ስምምነቱ የኦብነግ አላማ የህዝቡና በጦርነት የሚፈልገው መሬት ሰላም እንዲፈልግ ነው ብለዋል።

"በተጨማሪም በሶማሌና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ችግር ወይም "በኦጋዴንያ የሚኖሩ የሶማሌ ህዝቦች" ችግር ከግጭቱ መንስዔ ተነስቶ መፍትሄ ፈልጎ ለአካባቢው፣ ለፌዴራል እና ለኦብነግ ኮሚቴዎች የችግሩን ምንጭ በማጣራት መላክ እንዳለበት ጠቁመዋል። ቆይ አንዴ።"

"በጦርነቱ የተጎዱ ወገኖቻችን ወደ ሶማሊያ፣ኬንያ እና ጅቡቲ እና ሌሎች ሀገራት ጎረቤት ሀገራት እንዲመለሱ እና እንዲሰፍሩ እና የኦጋዴን ነፃ አውጪ ሰራዊት በድርጅቱ ውስጥ እንዲገባ" የኦብነግ ቃል አቀባይ አብዲቃድር ሀሰን ተናግረዋል። ሂርሞጌ (ነጭ)።

Skyline media

16 Oct, 17:27


የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ከተፋሰሱ ሀገራት ጋር ለ13 ዓመታት ውይይትና ድርድር የተደረገበት ነው፡- ኢንጅነር ተፈራ በየነ
****

በቅርቡ ወደ ተፈፃሚነት የገባው የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ለ13 ዓመታት በሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት መካከል ውይይትና ድርድር የተደረገበት መሆኑን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አማካሪ ኢንጅነር ተፈራ በየነ ገለፁ፡፡

ኢትዮጵያ የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ እንዲረቅ እና ድርድር እንዲደረግበት ከዚህ ቀደም በነበሩ ትብብሮች አባል ባትሆንም በታዛቢነት በነበራት ተሳትፎ ያነሳችው ሃሳብ መሆኑን ኢንጅነሩ ይገልፃሉ፡፡

እ.ኤ.አ በ1997 ተቀባይት ያገኘውን ጥያቄዋን ተከትሎ የተጀመረው የትብብር ማዕቀፍ ከመቅረፅ እና መደራደር ጀምሮ የተለያዩ ደረጃዎችን ማለፉን ተናግረዋል፡፡
በቀዳሚነት ከተፋሰሱ ሀገራት 3 አባላት ያሉት ፓናል ተቋቁሞ ድንበር ተሻጋሪ ውኃዎችን የሚጋሩ ሀገራትን በመመልከት እና ያሉ ሃሳቦችን በመገምገም ዛሬ ላይ መድረሱን አንስተዋል፡፡

በድርድር ልዑካን አማካኝነት የነበሩ የልዩነት አንቀፆች እየጠበቡ መምጣታቸውን ኢንጅነሩ ይጠቅሳሉ፡፡

ይህን ተከትሎ የውኃ ካውንስሉ እ.ኤ.አ በ2005 ያቀረበውን ሪፖርት መሰረት በማድረግ በሚንስትሮች ደረጃ እ.ኤ.አ ከ2006 እስከ 2010 ድርድር መደረጉን ያስረዳሉ፡፡

በእነዚህ ሁሉ ጊዜያት ኢትዮጵያ ድርድሩን ስትመራ የቆየች ሲሆን፣ስምምነት ላልተደረሰባቸው ነጥቦች አማራጭ የረቂቅ ሰነዶችን በማቅረብ እና ንግግር በማድረግ ለጋራ ተጠቃሚነት ያላትን ቁርጠኝነት ያሳየችበት መሆኑን አንስተዋል፡፡

ስምምነቱን ተከትሎ የሀገራቱን የሕግ ባለሙያዎች ያካተተ የናይል የትብብር ማዕቀፍ ኮሚሽን በሕግ መቋቋሙን ገልፀዋል፡፡

በዚህም በሚኖር የሽግግር ጊዜ በናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ በኩል የተደረጉ ስምምነቶች እና ስራዎችን ጨምሮ ለኮሚቴው የማስተላለፍ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

የናይል ተፋሰስ ሀገራት የትብብር ማዕቀፍ ሥምምነትን ከተፋሰሱ ሀገራት ስድስቱ ፈርመው በፓርላማዎቻቸው ማጽደቃቸውን ተከትሎ ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ተፈጻሚነት ገብቷል። ይህም ለታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት የባለቤትነት መብትን የሰጠ ሆኗል።

ስምምነቱን ያልፈረሙ ሀገራት እንዲፈርሙ እና ተጠቃሚነታቸውን እንዲያስጠብቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

በአፎሚያ ክበበው

Skyline media

16 Oct, 10:11


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት መተግበር ለኢትዮጵያ ምን ያስገኛል?
የናይል ተፋሰስ አገራት ለሚያስተሳስራቸው የዓለም ረጅሙ ወንዝ፤ የትብብር እና አጠቃቀም ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ሂደት የጀመሩት ከ27 ዓመት በፊት እ.አ.አ በ1997 ነበር። ሦስት አስር ዓመታት ገደማን የፈጀው ስምምነት የማርቀቅ፣ የድርድር እና የማፅደቅ ሂደት ባለፈው ሳምንት እሁድ ጥቅምት 3/2017 ዓ.ም. የመጨረሻውን ደረጃ አጠናቅቆ ተፈጻሚ መሆን ጀምሯል። ኢትዮጵያ ለዓመታት ስትጥርበት የነበረው የዚህ ስምምነት ተግባራዊ መሆን ምን ጥቅም ያስገኝላታል?
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

Skyline media

13 Oct, 12:15


ከተባበርን ጠንካራ ቀጣና መፍጠር እንችላለን - ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተባበርን እና ከተደጋገፍን ሁላችንም በጋራ በመልማት ጠንካራ ቀጣና መፍጠር እንችላለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡

የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ከዛሬ ጀምሮ ወደ ተፈጻሚነት ገብቷል፡፡

ይህን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በናይል ወንዝ ተፋሰስ ላይ የተደረገው የማዕቀፍ ስምምነት ወደ ተፈጻሚነት መግባት ለጋራ ብልጽግናችን የጀርባ አጥንት ነው ብለዋል፡፡

በናይል ወንዝ ተፋሰስ ላይ የተደረገው የማዕቀፍ ስምምነት (ሲ ኤፍ ኤ) ወደ ተፈጻሚነት መግባት የአባይ ወንዝ ውኃን በፍትሐዊነትና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የተሄደበትን ረጅም ጉዞ የቋጨ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ስምምነቱ ወደ ተፈጻሚነት የገባበት የዛሬው ቀንም ለተፋሰሱ ሀገራት ታሪካዊ መሆኑን ገልጸው÷ እውነተኛ ትብብርን ለማጎልበት በጋራ ለምናደርገው ጥረት መሰረት ነው ብለዋል፡፡

የማዕቀፍ ስምምነትቱ ወደ ተፈጻሚነት መግባቱ እንደ ናይል ወንዝ ተጠቃሚ ሀገራት ያለንን ትስስር ያጠናክርልናል ሲሉም አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም የጋራ ሃብታችን የሆነው የናይል ወንዝ ለሁላችንም ጥቅም እንዲውል ያስቻለ ነው ብለዋል።

ይህ የማዕቀፍ ስምምነት እውን እንዲሆን ላስቻሉ አካላትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

በሌላ በኩል ስምምነቱን ያልፈረሙ አካላት እንዲፈርሙ ጥሪ አቅርበው÷ ከተባበርን እና ከተደጋገፍን ሁላችንም በጋራ በመልማት ጠንካራ ቀጣና መፍጠር እንችላለን ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

Skyline media

13 Oct, 12:04


በተጨማሪም ስምምነቱ ለሁሉም የናይል ተፋሰስ ሀገሮች ሕጋዊ መብት ዕውቅና እንደሚሰጥ ገልጸው÷ ሁላችንንም ለውኃው ፍትሐዊ ክፍፍልና ለዘላቂ አጠቃቀም ተገዥ ያደርገናል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
እያንዳንዱ ሀገር የሌላውን መብት ሳይጋፋ በጋራ የሚያድግበትና የሚበለጽግበት የሁሉንም መጻኢ ተስፋ እንደሚወክልም አመላክተዋል፡፡
ዘላቂ ልማት የትብብር ስምምነቱ ማዕከል ነው ያሉት ሚኒስትሩ÷ የናይልን የውኃ ሀብት ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ከእኛ በኋላ ለሚመጡት ትውልዶችም እንዲሆን አድርገን መጠቀም የሚያስችል ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ስምምነቱ ናይልንና ከባቢውን እንድንጠብቀው፣ ውኃውን የወደፊቱን ተጠቃሚ በማይጎዳ መልኩ እንድንጠቀም ያስገድደናል ሲሉም ነው የገለጹት፡፡
ሁሉም የተፋሰሱ ሀገሮች ስምምነቱን  እንዲቀላቀሉትና መርሆዎቹን በታማኝነት እንዲፈጽሙ ጥሪ ያቀረቡት ሚኒስትሩ÷ የናይል ወንዝ የተስፋ ምንጭ የሚሆንበትን፣ ተግዳሮቶችን በጋራ የምናቃልልበትና ለራሳችንና ለመጪው ትውልድ የተሻለ  ዓለም የምንፈጥርበትን መጻኢ ጊዜ ለመገንባት በጋራ እንሥራ ብለዋል፡፡
የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም በትብብር ጉዟቸው ላደረጉት አስተዋጽኦ አመሥግነው÷ ወደ አዲስ የትብብር ምዕራፍ በምናደርገው ጉዞም አጋርነታቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

Skyline media

13 Oct, 12:04


የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ከዛሬ ጀምሮ ወደ ተፈጻሚነት መግባቱን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሐብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሩ ስምምነቱ ወደ ተፈጻሚነት መግባቱን አስመልክተው የናይል የትበብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈጻሚነት ማብሰሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም÷ የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ከዛሬ ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ  ወደ ተፈጻሚነት መግባቱን አስታውቀዋል፡፡
ይህን ተከትሎም የዛሬው ቀን በናይል ተፋሰስ ታሪክ ልዩ መሆኑን አንስተው÷ መላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ የተፋሰሱ ሀገራት መንግሥታትና ሕዝቦች ለዚህ ታሪካዊ ስኬት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
ለዚህ ስምምነት ከጥንስሱ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በተለያየ መንገድ አስተዋጽዖ ላበረከቱ  ኢትዮጵያውያንም ሚኒስትሩ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
የናይል የትብብር ስምምነት ተፈጻሚ መሆን የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽንን መመስረት እንደሚስችል ጠቅሰው÷ ኮሚሽኑ ለሁሉም ተጠቃሚነት የናይል ወንዝን የማስተዳደርና የመጠበቅ ኃላፊነት ይወስዳል፤  የትብብሩም የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ ያገለግላል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ የሕግ ማዕቀፍ፣ የናይልን ወንዝ ለሁላችንም ጥቅም ለማዋል የጋራ ቁርጠኝነታችን ምስክር እንዲሁም የውኃ ሀብቱን በእኩልነትና ፍትሐዊነት የመጠቀም መብት ማረጋገጫ የሚሆን ስምምነት ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት የናይል የውኃ አጠቃቀምን በተመለከተ የነበረውን  ኢ-ፍትሐዊነት ያስተካክላል፤ የሁሉንም የናይል ሀገሮች የጋራ ሀብት ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል ብለዋል በመግለጫቸው፡፡

Skyline media

10 Oct, 17:16


https://www.youtube.com/live/fCDUw5B_3Rk?si=jeNa1tCesOkIxbhR

Skyline media

09 Oct, 17:54


ወ/ሪት ሰሎሜ ታደሰ የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቃባይ እያሉ ስለ ኤርትራ ወደቦች የሰጡት ምላሽ

Skyline media

08 Oct, 22:08


የአዲስ አበባ የሁለተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ስድስቱ ኮሪደሮች እና ሁለቱ የወንዝ ዳርቻ ልማት ኮሪደሮች የትኞቹ ናቸው?
***

• 
ካዛንቺስ፣ መስቀል አደባባይ፣ ሜክሲኮ፣ ቸርችል፣ አራት ኪሎ፣ እስጢፋኖስ


•   ሳውዝጌት፣ መገናኛ ፣ ሃያሁለት፣ መስቀል አደባባይ


•  ሲኤምሲ፣ ሰሚት ጎሮ፣ ቦሌ አየር ማረፊያ ቪአይፒ ተርሚናል፣ አዲስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚብሽን ማዕከል

•  ሳር ቤት፣ ካርል አደባባይ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ አቦ ማዞሪያ፣ ላፍቶ አደባባይ፣ ሃና ፉሪ ኮሪደር


•  አንበሳ ጋራዥ፣ ጃክሮስ ጎሮ

•  አራት ኪሎ፣ ሽሮ ሜዳ እንጦጦ ማርያም፣ ጉለሌ እጸዋት ማዕከል


•  የቀበና ወንዝ ዳርቻ ኮሪደር ልማት

•  እንጦጦ፣ ፒኮክ ፓርክ የወንዝ ዳርቻ ልማት ኮሪደር ልማት


   በአጠቃላይ በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት 2817 ሄክታር የቦታ ስፋት ሲኖረው 132 ኪሎሜትር ርዝመትን የሚሸፍን ነው።

Skyline media

06 Oct, 18:07


በአዲስ አበባ ከተማ በበርካታ ቦታዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ተሰምቷል።

ከምሽት 2 ሰዓት በኃላ በርካታ ቦታዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ነበር።

ህፃዎች ላይ የነበሩ ሰዎችም በደንብ ንዝረቱ የተሰማቸው ሲሆን በተለይ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉ ነዋሪዎች ከስጋት አንጻር ወደ መሬት ወርደው ተሰባስበው ነው የሚገኙት።

ከአዲስ አበባ ውጭም በሌሎች ከተማዎች / ቦታዎች መሰል ሁኔታ እንደነበር ከቤተሰቦቻችን በሚላኩ መልዕክቶች ተረድተናል።

Skyline media

03 Oct, 05:43


#አማራ

መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ ኦፕሬሽን መጀመሩን
የመከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኮለኔል ጌትነት አዳነ ተናግረዋል።

ሰሞኑን በርካታ የመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ወደ አማራ ክልል ገብተዋል።
የክልሉ ሰላም ሙሉ ለሙሉ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እስኪመለስ ድረስ መከላከያ ሰራዊት ከክልሉ እንደማይወጣ ገልፀዋል።

በአማራ ክልል በፋኖ ሀይሎች እና በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች መካከል ከአንድ አመት በላይ ውጊያ ውስጥ እንዳሉ ይታወቃል።

በዚህም ጉዳዩ እስካሁን በድርድር ይፈታል በሚል ብዙ ጥረት እንደተደረገ ገልፀው መከላከያ ሰራዊት ከዚህ በኋላ አይታገስም፣እርምጃ ወደ መውሰድ ገብቷል ብለዋል።

በዚህም ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ ከፋኖ ሀይሎች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ በርካታ ሰዎች እና አመራሮች መታሰራቸውን ገልፀዋል። ኦፕሬሽኑ ይቀጥላል ብለዋል።

በተመረጡ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ከትናንት በስተያ ጀምሮ የስልክ አገልግሎት እንዲቋረጥ ተደርጓል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የፋኖ ሀይሎች ከነገ ጀምሮ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲቆም ትዕዛዝ እያስተላለፉ ይገኛሉ።