የስብዕና ልህቀት

@human_intelligence


በዚህ ቻናል
ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።

#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

የስብዕና ልህቀት (Amharic)

የስብዕና ልህቀት ላይ የሚያንፁ ስነ-ልቦና ምክሮች እና ፍቅር ታሪኮችን እና ወጎችን በተመሳሳይ እና ገና ያቀረጥነው የጥበብ ድግስ ሆኖ ነው። ይህ በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ሳይሆን የሚታዘዝና መስራት ላይ እያንዳንዳቸው መከላከያዎችን በመከታተል ተማሪዎችን ይመልከቱን። ወደ ሳተላይ ስለ መደብ ማሰናጋን ወደዚህ ቻለ ስለ ተመረተበት ግለሰብ ቻናሎችን ማድረግ በማድረግ ለዘላቂ ውበት እና ፍቅር የተመከረውን ህይወት በቀን እና አንድም ዛፍ አንዳንዶቹ ብቻ እንደሚጠቀሙ እና የቻሌ ስለሆነ ይጋብዙ።

የስብዕና ልህቀት

22 Oct, 07:01


ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም!!

በጃፓን ጦርነት ወቅት የወንድሙን ሬሳ (አስክሬን) በጀርባው አዝሎ በጥልቅ ስሜት ሊቀብር ይሄድ የነበረውን ታዳጊ ሕጻን ያስተዋለ አንድ ወታደር!

"ለምን እራስህን ታደክማለህ የሕጻኑን እሬሳ ጥለኸው ብትሄድ እኮ ድካምህ ይቀንስልህ አልነበር?" ሲል ጠየቀው::

ሕጻኑም ሲመልስ እንዲህ አለ:- "ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም" አለው::

ያን ጊዜ ጥያቄውን ያቀረበው ወታደር ራሱን መቆጣጠር አልቻለም ... ስሜቱ በጣም ተነካ ... ዓይኖቹ በዕንባ ታጠቡ::

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በጃፓን ይህ ምስል ... የወንድማማችነት፣ የአንድነት ተምሳሌት ሆነ::

እናም ... የሕይወት መርሃችን እንዲህ ቢሆንስ:-

ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም !
እህቴ ናት እኔን አትከብደኝም !
ወንድምህ ቢወድቅ አንሳው !
እህትህ ብትደክም ከጉኗ ቁም !
ወንድምህ ቢስት በቅን መንፈስ አቅናው !
እህትህ ስህተት ብትሰራ ይቅርታህን አትንፈጋት!

የስብዕና ልህቀት

የስብዕና ልህቀት

22 Oct, 06:13


የፍልሚያችን ውጤት
(ተስፋኣብ ተሾመ)
* * *

ጭቆናን ለማክሰም
ያለአንዳች መታከት፥ በብርቱ ብንተጋም
አርነት ለመውጣት
በፅኑ ተጋድለን ፥ጡንቻችን ቢዝልም

ከፍልሚያችን ማግስት፦
የተቀናጀነው፥ የመራብ ነፃነት
ማሳካት የቻልነው ፥የመታረዝን መብት
ሃብታችን የሆነው ፥የህመም ክምችት
የተማርነው ጥበብ፥ ሳይደክሙ መፎከት።

በመፋለም ብዛት፥ ቀድሞ የታነፀው፥ ስለፈራረሰ
ከልብ ምንጫችን ላይ፥ የሚፈልቀው ኹሉ ፥ስለደፈረሰ
ርቱዕ የነበረ ፥አንደበታችንም ፥ባ'ፍረት ተለጎመ
ከልባችን መዝገብ ፥ድል ማድረግ ተፍቆ፥ መሸነፍ ታተመ


@Tfanos

የስብዕና ልህቀት

17 Oct, 16:51


ጊዜህን በርካሽ ዋጋ አትሽጥ!!

"ሴኔካ አካላዊ ንብረቶቻችንን መጠበቅ ላይ ጥሩ የሆንነውን ያህል፣ አእምሯዊ ድንበሮቻችን ማስመር ላይ ግን ግድ የለሽ መሆናችንን . ያስታውሰናል። ማንም እንዳሻው ድንበራችንን አልፎ ሲገባ አንቃወመውም: ንብረት ተመልሶ ሊገኝ ይችላል፤ እንዲያውም ገና ብዙ የምድር ሃብቶች በሰው አልተነኩም። ጊዜ ግን? ጊዜ ፈጽሞ ሊተካ የማይችል ሀብታችን ነው፤ ተጨማሪ መግዛት አንችልም፡፡ ማድረግ የምንችለው በተቻለ መጠን ለመቆጣጠር ጥረት ማድረግ ብቻ ነው፡፡"

"በሕይወታችን ውስጥ ሌሎች ጣልቃ እንዲገቡ በቀላሉ እንፈቅዳለን፤ የከፋው ነገር ደግሞ በአብዛኛው ጊዜያችንን ሊያጠፉት ለሚችሉት ሰዎች መንገድ የምናመቻች መሆናችን ነው። ማንም ሰው ለአላፊ አግዳሚው ገንዘቡን አይሰጥም፤ ግን እያንዳንዳችን ለምን ያህል ሰዎች ሕይወታችንን ሰጥተናል!ለንብረትና ለገንዘብ እጃችን አይፈታም፣ ሁላችንም እጅግ ስስታሞች መሆን ለሚገባን ለሚባክን ጊዜ ግን የምናስበው እጅግ ትንሽ ነው።”
- ሴኔካ

"የሕይወታችንን ቀናት ልክ እንደ ገንዘባችን አንመለከተም? በትክክል ለምን ያህል ቀናት በሕይወት እንደምንቆይ ስለማናውቅ፣ አንድ ቀን የምንሞት የመሆኑን ሀቅ በቻልነው ሁሉ ላለማሰብ ስለምንሞክር፣ ጊዜያችንን በነጻነት ለማባከን ፍቃድ የተሰጠን ይመስለናል። እዚህ ላይ እኔ በምትኩ የማገኘው ምንድነው?” ብለን እምብዛም ሳንጠይቅ በዚያችው ባለችን ጊዜ ላይ ሰዎችና ክስተቶች ጊዜያችንን እንዲሰርቁን እንፈቅድላቸዋለን፡፡"


"እንዴት እንደምትጠቀምበት ካወቅክ፣
ሕይወት ረጅም ነው ነገሩ፣ ለመኖር ያለን ጊዜ አጭር ስለመሆኑ ሳይሆን ብዙውን ያባከንነው ስለመሆናችን ነው። በደንብ ከተጠቀምንበት ሕይወት በበቂ ሁኔታ ረጅም ነው ብዙ ታላላቅ ነገሮችን ለመስራት በበቂ ሁኔታ ተለክቶ የተሰጠ ነው። በድሎትና ችላ በማለት ውስጥ ካባከንነው፣ መልካም ፍጻሜ ለማግኘት ካልሰራን፣ በመጨረሻ ማለፉን እንኳን ከመረዳታትን በፊት አልፎ እናገኘዋለን። ስለዚህ የተቀበልነው ሕይወት አጭር አይደለም፤ አጭር ያደረግነው እኛ
ነን።”
-ሴኔካ

ስለዚህ ዛሬ ራስህን ስትጣደፍ ወይም “በቂ ጊዜ የለኝም፡፡” የሚሉትን ቃላት ስትናገር ብትሰማው፣ ቆም በልና ጥቂት ሰከንዶች ውሰድ፡፡ ይህ እውነት ነው? ወይስ ብዙ አላስፈላጊ ነገሮች በመስራት ተጠምደህ ነው? በእርግጥ ውጤታማ ነህ፣ ወይስ በሕይወትህ ውስጥ ብዙ የባከነ ነገር እንዳለ ትገምታለህ? በህይወታችን አብዛኛውን ጊዜ  የምናባክነው በማይጠቅሙን ሀሳቦች እና በማይረቡ ነገሮች ላይ ነው። እያንዳንዱን ደቂቃ የምንጠቀም ቢሆን ምን ያህል ጊዜ ሊተርፈን እንደሚችል አስቡ!!


"እንዲህም እላለሁ እንዲት ቀንም ቢሆን አልሰጥም - ማንም ቢሆን አንድ ቀኔን ሊመልስልኝ አይችልምና!!

እንዲህም እላለሁ እያንዳንዷ ሰከንድ የእኔ ናት በባለቤትነት እና በስልጣን አስተዳድራታለሁ:: አልፋኝ የምትሄድ ሽርፍራፉ ሰከንድ አትኖርም!!"

የእለት ፍልስፍና


የስብዕና ልህቀት
Share : @Human_Intelligence

የስብዕና ልህቀት

16 Oct, 10:56


የመሪ ያለህ !
(ተስፋኣብ ተሾመ)


ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ችግር እያለ ሕዝቡ ዝምታን መምረጡ ስንፍና አልያም ግድ የለሽነት የሚመስላቸው ሰዎች አሉ። ይህ ስህተት ነው።

ሕዝብ እንዴት መተባበር እንዳለበት አያውቅም።

ፖለቲካ የሙሉ ጊዜ ስራቸው የሆኑ አካላት ካልመሩት በቀር ህዝብ መንግስታትን ለመጋፈጥ ቢሞክር ችግር ይከሰታል። ባንክና ታንክ ካለው አካል ጋር ሕዝብ ቢጋፈጥ የእሳት እራት ከመሆን አይተርፍም።

ይልቅ ፖለቲካ የሙሉ ጊዜ ስራቸው የሆነላቸው ሰዎች ቸልታ አሳሳቢ ነው። የፓርቲዎች ስንፍና የሚወቀስ ነው።

ሕዝብ መሪ ይፈልጋል።

ሚሊዮን ሰዎች እንዴት ይግባባሉ? ሚሊዮን መረጃዎች እንዴት ይተነተናሉ እንዴትስ ይተገበራሉ?፥ ህዝብ መረጃን እንዴት ይቀባበላል?፥ ግብ ላይ ለመድረስ የሚረዳው ስትራቴጂ ምንድነው?

ለጥያቄዎቹ መልስን ማበጀት የሚችለው መሪ ነው።

የፖለቲካ መሪ የጠፋው ለምንድነው?

የደርግ ዘመን እሳት ሙህራንን በላ፥ መምራት የሚችሉትን አኮላሸ። የኢህአዴግ ዘመን በተደራጀ መንገድ ድንቁ*ርናን አመረተ። ፖለቲካ እውቀት መሆኑ ቀርቶ ተራ ነገር ሆነ። ጥቂት አዋቂዎች የቀደሙትን የበላው እሳት እንዳይበላቸው "ፖለቲካን በሩቁ" አሉ።

መሪ የለንም። መተማመን የለም። የአንዱ መሪ ለሌላው ጠላ*ት ነው። የጋራ መሪም የጋራ አላማም የለም።

ለምንድነው መሪ አልባ የሆንነው? ሕዝባችን መሪ ለመውለድ መክነ ወይስ የተወለዱ መሪዎች ተጨናገፉ?


@Tfanos

የስብዕና ልህቀት

15 Oct, 13:55


ፍቅርና ጋብቻ

“ፍቅር ምንድን ነው?” ሲል ተማሪው ለመምህሩ ጥያቄ አቀረበ፡፡ “ለጥያቄህ መልስ ለመስጠት በቅድሚያ በአንድ የስንዴ ማሳ ሂድና ትልቁን ስንዴ መርጠህ ይዘህ ናና መልሱን እነግርሃለሁ፡፡

ነገር ግን ልብ አድርግ የአሰራር ሕጉ የሚፈቅደው በስንዴው ማሳ አንድ ጊዜ ብቻ በማለፍ የስንዴውን ዛላ ይዘህ ትመለሰላህ እንጅ በማሳው ውስጥ መመላለስ አይቻልም አለው” መምህሩ፡፡

ተማሪው እንደተባለው ወደ ስንዴው ማሳ ገባና የመጀመሪያውን ሽና (መደዳ) ይዞ ሲጓዝ አንድ ትልቅ የስንዴ ዛላ አገኘ ነገር ግን ይሄን አድንቆ ሌላ ከዚህ የላቀ ትልቅ ይኖራል በማለት ፍለጋውን ቀጠለ እንዳሰበውም ከበፊቱ የተሻለ ትልቅ አገኘ፡፡

ምን አልባትም እስካሁን ካየሁት የበለጠው እየጠበቀኝ ይሆናል በማለት ፍለጋውን ቀጠለው፡፡

የስንዴውን ማሳ ከግማሽ በላይ ካደረሰ በኋላ ከዚህ በፊት ካገኛቸው የስንዴ ዛላዎች የበለጠ እንደማይኖር ተረዳና ቀደም ብሎ አግኝቶት በነበረውና ባመለጠው ትልቅ የስንዴ ዛላ እየተቆጨ ባዶ እጁን ወደ መምህሩ በተመለሰ ጊዜ “ፍቅር ማለት እሱ ነው፡፡

የተሻ ፍለጋው አልገታ ብሎህ ፍለጋውን ቀጠልክ ነገር ግን የተሻለውን እንዳጣህ ዘግይተህ ተገነዘብክ” አለው መምህሩ፡፡

“ታዲያ ጋብቻ ማለትስ ምንድን ነው?” ሲል ሁለተኛ ጥያቄውን አቀረበ

መምህሩም “አሁንም ጥያቄህን ለመመለስ ባንድ የማሽላ ማሳ ሂድና ትልቅ ነው ያልከውን ማሽላ ይዘህ ተመለስ፡፡

ታዲያ አሁንም እንደበፊቱ የአሰራር ሕጉ የሚፈቅድልህ አንድ ጊዜ ማለፍ እንጅ ተመልሶ መፈለግና ማንሳት አይቻልም” አለው፡፡

ተማሪው ወደ ማሽላው ማሳ በደረሰ ጊዜ ከበፊት ስህተቱ ተምሮ ስህተቱን ላለመድገም ከማሳው ግማሽ እንደደረሰ አንድ በቂ ነው ብሎ ያሰበውን መካከለኛ ማሽላ ይዞ ወደ መምህሩ ተመለሰ፡፡

መምህሩም “አሁን ጥሩውን ፈልገህና የተሻለ ነው ብለህ ያሰብከውንና ምርጡንም እንዳገኘህ አምነህ በእምነት ይዘህ መጠሀል ይህ ማለት ጋብቻ ነው” በማለት ጥያቄዎቹን መለሱለት፡፡


የስብዕና ልህቀት
Share; @Human_Intelligence

የስብዕና ልህቀት

14 Oct, 08:05


አእምሮአችን በሰው ልጅ የአፈጣጠር ታሪክ ውስጥ ልዩ የሆነ የእግዚአብሔር ስራ ነው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠራቸውን ነገሮች ሁሉ አንድ በአንድ ብንፈትሽ የፀሀይን መጥለቅና መውጣት፣ የውቅያኖሶችን ስጥመት እና መሰል አስደናቂ የተፈጥሮ ምስጢራት ብንመረምር፤ እንደሰው አእምሮ ረቂቅ የሆነ ነገር ግን አናገኝም፡፡ አእምሮአችን በህይወታችን ጉዞ ሁሉ የሚከተለን ጠባቂያችን ግን ደግሞ ልንከተለው ያልፈለግነው ዋነኛ የእኛነታችን አሻራ ነው፡፡

አእምሮአችን ራሱን የቻለ ሰፊ ውቅያኖስ ቢሆንም እኛ ግን ከዚያ ሁሉ ማዕበል የምንጠቀመው የአንድ ማንኪያ ጠብታ ያህሉን ብቻ ነው። ምርጫችንም የምናደርገው የውቅያኖስ ያህል ስፋት ካለው አቅማችን ይልቅ በዚህችው ጠብታ ላይ ነው፡፡ በዚህ ኢምንት ጉዳይ ላይ መመርኮዝ ደግሞ አንድ መሠረታዊ እውነታ እንዲያመልጠን ያደርጋል። አብዛኛው ጊዜያችንና ገንዘባችን ሰውነታችን ለማስዋብ የሚጠፋ ነው፡፡ እዚህ ላይ የምናጠፋውን እሩብ ያህል ጊዜ አእምሮአችንን ለመሞረድ ብናጠፋ ግን ጥቅማችን ዘርፈ - ብዙ ይሆናል፡፡ በዚህ ዘመን በህይወት ያለ ሰው ሶቅራጥስን፣ ኮንፊሺየስን፣ ሼክስፒርን ወይም ቤትሆቨንን በአካል የሚያቃቸው አይገኝም፡፡ ነገር ግን የአእምሮአቸው ውጤት የሆነው ስራቸው በክፍለዘመናችን ሁሉ ገናና ሆኖ እየኖረ ነው፡፡

ቪጄ ኤስዋሪን

የስብዕና ልህቀት
Join: @Human_Intelligence

የስብዕና ልህቀት

08 Oct, 17:45


ድንቅ ትረካዎች
ተራኪ -አንዱአለም ተስፋዬ
@Human_Intelligence

የስብዕና ልህቀት

08 Oct, 12:04


ማራኪ የፍቅር ታሪክ
ተራኪ- ግሩም ተበጀ

@Human_Intelligence

የስብዕና ልህቀት

07 Oct, 11:20


በጨዋታ መሃል ፦

<<በራስህ አትተማመንም አይደል>> አለቺኝ ?

እንዴት ልበ ሙሉነት የተጠናወተኝ ሰው እንደሆንኩ ከራሴ ጋ እየተሻማው አወራሁ... አብራራሁ... ዘበዘብኩ

በእርጋታ ከሰማቺኝ በኃላ
<<እንዴት እንደዚህ አልሽ ብትለኝ እና ያስተዋልኩትን ብነግርህ  አይሻልም?>> አለቺኝ

<<ቀጥይ>> አልኳት ደስ ባላለው ፊት እያየኃት

<<ስላለህ፣ ስላስደመምከው  ፣ስላደረከው ነገር ብዙ ሰአት ሁል ግዜ ታብራራልህ ።  የተጣላኸውን የጠላኸውን ያናደደህን  ሰው ስህተት እና ያንተን ቅድስና ታስረዳለህ ፣

ሰው ስለራሱ ሲያወራህ ቀጥለህ እኔ.. እኔም.. ብለህ ስለ ራስ ታወራለህ ምንም ነገር ስትሰማ ከራስህ ጋ እያወዳደርክ ነው መሰለኝ ።

ሰው ሲቃወምክ ስለምታወራው ነገር ሳይስማማ ሲቀር ቅር ይልሃል... ብዙ ታብራራለህ ። ያመንከው እና የሆንከውን እንዲመሰከርልህ እንዲጨበጨብልህ ጉንጭህ እስኪዝል ታስረዳለህ  ።

ስላደረከው እና ስለሆንከው ነገር አስተያየት ትጠይቃለህ ደስታህ የሰው አስተያየት ላይ ተንጠልጥሎል።

እምቢ ማለት ይከብደሃል ። እምቢ ከማለት መዋሸት ትመርጣለህ ። ባላሳቀህ ነገር ትስቃለህ ፣

የአዲስ ሰው ቀልብ ለመሳብ እሱ የሚወደውን ነገር ለማውራት ለመሆኑ ጥረት ስታደርግ ብዙ ግዜ ያስተዋልኩ ይመስለኛል ።

ሰው እንዳይቀየም ስትል መጠየቅ ያለብህን አጠይቅም ።

ያበደርከውን ብደር እንኳን ስትጠይቅ ችግር እንዳጋጠመክ አብራርተህ ነው ።

ራስህን አታከብርም መሰለኝ እራስን አለማክበር  አንደኛው  በራስ ያለመተማመን ውጤት ነው !!

ከጠላት ሁሉ ጠላት  የሚከፋው የውስጥ ጠላት ነው ። ከራስህ ጋ የታረክ  ግዜ አለም ቢጣላህ እንኳን አትሸበርም ።

ስታወራ ረጋ ብለህ  ተናገር !
ለመወደድ ስቃይ አትብላ !
ሰው አክብር  እንጂ አክብደህ አትይ !
ሁሉንም እቅድህን ለሁሉም አታውራ!
የተሰማህን ሁሉ አትናገር !
እምቢ አልችልም ማለት ልመድ !
ስለተሳካልህ ነገር ሂደት በየሜዳው አታብራራ !

ያልተቀበልከው ማንነት ካለ የበታችነት ስሜት የሚያሰማህ ሁነት ካለ ረጋ ብለህ አጥናውና መላ ፈልግለት ።

ብቻህንም መሆን ልመድ ሁሌ አብሮ ሰው እንዲሆን አታስስ

ዝም ብዬ አየኋት ።

ልክ ካልሆንኩ፣ ያልኩት እውነት ከሌለው እንደቀባጠርኩ ከተሰማህ አፉ በለኝ
ካወራውት ፍሬ ነገር ካገኘህበት ደሞ ደግ >>

አሁንም ዝም አልኳት ።  ዝምታዬ ውስጥ ግን መደነቅ እና ድብርት  ነበረበት

የስብዕና ልህቀት

05 Oct, 05:28


"የተከፈለ ዋጋ " ስህተት
ያለፈውን መርሳት የሚገባን ለምንድ ነው?

ልናየው የጀመርነው ፊልም መጥፎ ነበርና ከግማሽ ሰዓት በኋላ ሚስቴን ‹እንሂድ› አልኳት። እሷ ግን ‹‹በጭራሽ፣ 30 ዶላራችንንማ ዝም ብለን አንጥልም›› አለቺኝ፡፡ ‹‹ይህ ለመቆየት ምክንያት አይሆንም›› ብዬ ተቃወምኳት፡፡ ገንዘቡ አንድ ጊዜ ወጥቷል - ይህ የተከፈለ ዋጋ ስህተት የሚባል የአስተሳሰብ ስህተት ነው፡፡ ሎሚ የገመጠች ይመስል ፊቷን አኮሳተረችብኝ፡፡ ‹‹ከመቆየታችንና ካለመቆየታችን ጋር ሳይያያዝ 30 ዶላሩን አንድ ጊዜ ወጪ አድርገናል ፤ ስለዚህ ይህ ነገር ለውሳኔያችን መሰረት መሆን አይችልም›› ብዬ ሁኔታውን ለማብራራት ሞክርኩ፡፡ ጥረቴ አልተሳካም፣ ተመልሼ ተቀመጥኩ፡፡

በቀጣዩ ቀን በአንድ ስብሰባ ላይ ተቀመጥኩ፡፡ የማስታወቂያ ዘመቻችን ላለፉት አራት ወራት እየተካሄደ ቢሆንም አንዱንም ግቡን እንኳን አላሳካም ነበር፡፡ እኔ ማስታወቂያው እንዲቀየር ፍላጎት ስለነበረኝ ይሄው እንዲፈፀም ሃሳብ አነሳሁ፡፡ የማስታወቂያ ክፍል ሃላፊያችን ግን አጥብቃ ተቃወመች፡፡ ‹‹ብዙ ገንዘብ አውጥተንበታል፤ አሁኑኑ ከተውነው የከፈልነው ገንዘብ መና ቀረ ማለት ነው›› የሚል ነበር መከራከሪያዋ - ሌላ የተከፈለ ዋጋ ስህተት ሰለባ፡፡

አንድ የሴት ጓደኛ ያለችው ወጣት በተረበሽ ግንኙነታቸው ውስጥ ለመቀጠል ብዙ ታገለ፡፡ የሴት ጓደኛው እየደጋገመች ከእሱ ውጪ ትማግጥበታለች፡፡ ይሄን ችግሩን ለእኔ የገለፀልኝ እንደዚህ ብሎ ነበር። ‹‹በዚህ ግንኙነት ውስጥ ብዙ ኃይል አባክኛለሁ፤ ብዙ ዋጋም ከፍያለሁ፡፡ አሁን ላይ ግንኙነቱን ማቋረጥ አልችልም፤ ልክ አይመስለኝም፡፡» - የተከፈለ ዋጋ ስህተት አይነተኛ ሰለባ፡፡

ይህ የተከፈለ ዋጋ ስህተት የበለጠ አደገኛ የሚሆነው ደግሞ ብዙ ጊዜ፣ ገንዘብ፣ ጉልበትና ፍቅር የከፈልንበት ነገር ላይ ሲሆን ነው፡፡ - ይዘነው ልንቀጥለው እየታገልንለት ያለው ጉዳይ የሞተ ነገር ቢሆን እንኳን እንዳንጨክንበት ያደርገናል፡፡ ነገሩ ምንም እንደማይጠቅመን እያወቅን ከነገሩ ጋር ጊዜያችንን እና ገንዘባችንን እናባክናለን።

በአንድ- ነገር ላይ ከፍተኛ ጥረት ካደረግክና ብዙ ጊዜያት ከከሰከስክበት ለውጤቱ የምትሰጠው ዋጋ የተጋነነ ይሆናል። የምትሰራቸውን ስራዎች ሁሉ በምክንያት  እንምትሰራቸው አስተውል። በአንድ ነገር ላይ ብዙ ጊዜ እና ጉልበት ባባከንክ ቁጥር ወደ ኋላ እየተመለስክ ውጤቱን ተመልከት - ውጤቱን ብቻ። አምስት አመታትን ለፍተህ የተማርከው ትምህርት (ዲግር) ተግባራዊ እውቀት ካልሰጠህና ጥሩ የስራ እድል ካልፈጠረልህ  ተወው!! አምስት አመታትን ወስደህ ያዘጋጀው መጽሐፍ ጠያቂ ከሌለው መጽሐፉ ላይረባ እንደሚችል አስብ። አምስት አመት ሙሉ ለፍቅር የለመንካት ሴት ከዚያ በኋላ በጥቂት ወራት ውስጥ ተዋውቀሃት ካገባሃት ሴት ትበልጣለች? አስተውል አንድን ነገር ብዙ ደክመህበታል ማለት ነገሩ ጥሩ ነው ማለት አይደለም!!

ነጋዴዎቸና ኢንቨስተሮች በዚህ ስህተት ተጠቂዎች ይሆናሉ።  የከፈልነው ዋጋ እና ኢንቨስትመንት ከፍ ያለ በሆነ ቁጥር ከጉዳዩ ጋር ለመቀጠል ያለን ፍላጎትም ከፍ እያለ ይሄዳል፡፡ብዙውን ጊዜ የንግድ ውሳኔዎቻቸውን በከፈሉት ዋጋ ላይ የሚንጠለጠል ያደርጉታል፡፡ ‹‹በዚህ ቢዝነስ ውስጥ ብዙ ገንዘብ ከስክሻለሁ ስለዚህ ስኬታማ ሊሆን ባይችልም አሁን ልተወው አልችልም›› ይላሉ፡፡  ይህ ኢ ምክንያታዊነት ባህሪ ወጥ በመሆን ፍላጎት የሚመራ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ወጥነት የታማኝነት (credibility) ማሳያም ይመስለናል። ሃሳብ መቀያየር እንደነውር ነው የሚታየው፡፡ በግማሽ የሄደ ፕሮጀክትን መተው መሸነፍን እንደማመን ይቆጠራል። ይህ ስህተት ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል፣ አንዳንድ ጊዜም የተሳሳተ ውሳኔ ላይ እንድንደርስ የሚያደርግ ነው። አሜሪካ የቬትናም ጦርነት ውስጥ መቀጠልን የመረጠችው በዚህ የተነሳ ነው። ‹‹ለዚህ ጦርነት ብዙ ዋጋ ከፍለናል፤ አሁን ማቆም ስህተት ነው የሚሆነው›› በሚል አረዳድ በመታጠር፡፡


በእርግጥ አንድ ነገር እስኪጠናቀቅ መስራትና መጨረስ ውስጥ ብዙ ጥሩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ለተሳሳቱ ምክንያቶች አንድን ነገር ይዘህ እየቀጠልክ አለመሆንህን ግን እርግጠኛ ሁን፡፡ ለምሳሌ ተመልሰው ለማይገኙ (non recoverable) ወጪዎች ሲባል አንድን ነገር ይዞ መቀጠል አግባብ አይደለም፡፡ ምክንያታዊ ውሳኔ ሰጪነት እስከእለቱ ድረስ የወጡ ወጪዎችን እንድንረሳ ያስገድደናል፡፡ ምን ያህልም ግን ያፈስስክበት ነገር ቢሆን አሁን ላይ ውሳኔ ለመስጠት ከግምት ውስጥ ልታስገባቸው የሚገቡህ ነገሮች የወደፊት ወጪዎችና ጥቅሞችን ብቻ ናቸው።

✍️ሮልፍ ዶብሊ

የስብዕና ልህቀት
Share&Join
@Human_Intelligence

የስብዕና ልህቀት

04 Oct, 14:10


ውብ ታሪኮች-1
ድንቅ አጫጭር ትረካዎች በአንድ ላይ

ተራኪ-ግሩም ተበጀ

የስብዕና ልህቀት
Join: @Human_Intelligence

የስብዕና ልህቀት

29 Sep, 05:38


ድፍረት ማለት ያለ ፍርሀት መኖርና እየደነፉ ማውራት ማለት ሳይሆን ፣ከሚገባው በላይ ብንፈራና ብንደነግጥም እንኳን ያሰብነውን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አለማለት ነው ።

በአስቸጋሪ ጊዜና ሁኔታ ውስጥ ተረጋግቶ መውጫ ቀዳዳ በመሻት  መውጣት የድፍረት አንድ አካል ነው

ድፍረት ማለት የፍርሀት አለመኖር ሳይሆን ፍርሀት ላይ የምንቀዳጀው ድል እንደሆነ ተማርኩ፤ ጀግና የሚባለው ፍርሀት የማይሰማው ሳይሆን ፍርሀትን መማረክ የቻለው ነው!

----ኔልሰን ማንዴላ

የስብዕና ልህቀት

29 Sep, 05:08


የሁላችንም ጥንካሬ ያለው በተመቻቸው ስፍራ ሳይሆን ሁኔታዎች ፈር ሲለቁ ጨለማ ሲከበንና ህይወት መውጫ የሌላት መስላ ስታስጨንቀን በምንወስነው ውሳኔ ውስጥ ነው። የማንነታችን ትርጉም የሚለካው ነን ብለን የምናስበው ማንነታችን ፈተና ሲገጥመው በምንወስደው እርምጃ ነው። እራሳችንን የፍቅር ጥግ አርገን የምንይ ከሆነ የፍቅር ጥግ መሆናችንን የሚረጋገጠው ጥላቻ ግድ የሚሆንበት ቦታ ላይ የፍቅርን ፀዳል መልቀቅ ስንችል ነው። የይቅርታ ሰው መሆናችን የሚታወቀው ይቅርታ ለማረግ በሚያስቸግርበት ሁኔታ ላይ ይቅር ማለት ስንችል ነው።

የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence

የስብዕና ልህቀት

27 Sep, 16:43


"ሞት ሰራቂው ሞተ" በጣም የሚደንቅ ታሪክ!

በአንድ ወቅት አንድ ሰው የፈጣሪን ተአምር ለመመስከር እሩቅ አገር ለመሔድ ከተሳፋሪዎች ጋር በአውቶብስ ጉዞ ይጀምራል። ጉዞ ከተጀመረ በኋላ ግን መንገድ ላይ አንድ ከተማ ውስጥ ተሳፋሪው በሙሉ ምሳ ለመብላት ይወርዳል።

......ከተሳፋሪዎቹ መሐከልም አንዱ ወደ አንድ ምግብ ቤት ይሔድና ምሳውን ከበላ በኋላ ለመክፈል ቦርሳውን ሲፈልግ ያጣዋል።

......መሰረቁንም ከተረዳ በኋላ ለምግብ ቤት ባለቤቱ የደረሰበትን ስርቆት አስረድቶ በነበረበት ከተማ የሚያውቀው ዘመድ ስለነበር ገንዘብ አምጥቶ እንደሚከፍል ተናግሮ ገንዘብ ይዞ መጥቶ ይከፍልና ወደ አውቶብሱ ሲሔድ አውቶብሱ ለካ ጠብቆ ጠብቆ የደረሰበትን ነገር ስላላወቀ ትቶት ሔዷል።

........ ሠውየውም ገንዘቡም ተዘርፎ አውቶብሱም ጥሎት መሔዱ እየገረመው
"#ይሄ_ፈተና_ነው_ሰይጣን_እፈር እኔ እንደሆነ ከአገልግሎት አልቀርም ብሎ ብዙ ከተንከራተተ በኋላ በሌላ አውቶብስ ተሳፍሮ ጉዞ ይጀምራል።

. ...... በመንገድ ላይም  አንድ ትልቅ ገደል ውስጥ የገባ አውቶብስ ያያል። ከተሳፋሪዎቹም የተረፈ ሰው አለመኖሩ ይመለከታል። ደነገጠ።

....በጣም አዝኖ እያለም ወርዶ አውቶብሱን በደንብ
ሲያየው እርሱ ተሳፍሮባት የነበረችውና ጥላው የሔደችው አውቶብስ መሆንዋን ይረዳል።

....በጣም ገርሞት ለካ አውቶብሱ ጥሎኝ የሔደው #ለበጎ_ነው በሚል ፈጣሪውን እያመሠገነ ጉዞ ይጀምራል። የሚያገለግልበት ቦታ ደርሶም ስለተደረገለት ነገር ለአንድ ሣምንት እዛው ፈጣሪውን ሲያመሰግን ሰንብቶ ወደ ቤቱ ሲመለስ መኖሪያ ቤቱ ድንኳን ተተክሎ ያያል።

.....ምን ተፈጥሮ ይሆን? በሚል ጠጋ ብሎ ሲመለከት ለቅሶ ነው። ጎረቤቶቹ በሙሉ ደንግጠው እርሱን ሲያዩት ያያል። ሠውየውም "ማን ነው የሞተው?" ብሎ ይጠይቃል።
እነርሱም "አንተ" ይሉታል።

እርሱም እንዴት እኔማ ይሄው አለሁ አይደል። ይላል። የእርሱን በሕይወት መምጣት የሰሙ ቤተሰቦቹም ማመን አቅቷቸው እየመጡ ይጠመጠሙበታል።

ሐዘኑም ወደ ደስታ ይለወጣል። ሰውየውም ቤተሰቡም ጎረቤቱም ረጋ ብለው ስለተፈጠረው ሁኔታ ያወራሉ።
...ለካ አውቶብሱ ሲገለበጥ አደጋው የከፋ ስለነበር የሰዎቹ ማንነት በመልክ መለየት ስላልተቻለ የሟቾች ኪስ ፓሊስ እየበረበረ ማንነታቸውን መለየት ሲጀምር የሰውየውም የጠፋው ቦርሳ አንዱ የሰረቀውና አንዱ ሟች ኪስ ውስጥ ይገኛል።

...ፓሊስም በመታወቂያው መሠረት ለሰውየው ቤተሰቦች መርዶ ይነገራል። ለቤተሰቡም በቤ/ክን በተዘጋጀ አዲስ የመቃብር ቦታ ይቀብሩታል።
ለካ ሠውየው ነው ተብሎ የተቀበረው #ሌባው ነው። ሁሉም ሠው ይህን ሲሰማ ይገረማል።

ከሰወችም መካከል አንዷ ልጁ "የአንተ አዲሱ መቃብር የተቀበረው ሌባው ነው። አንተ መቃብር ላይ ሌባ አይቀበርም። #ይውጣ።" ስትል

....ሠውየው አንድ አስገራሚ ነገርተናገረ "
አይሆንም ሌባውን #እወደዋለሁ ሞቴን የወሰደልኝ ሞቴን የሰረቀኝ ባለውለታየ ነው። እርሱ ቦርሳየን ሰርቆኝ ለምሳ መክፈያ ብር ፍለጋ ባልሔድ ኖሮ አውቶብሱ አያመልጠኝም ነበር። እኔም ሟች ነበርኩ። አትንኩት።" ነበር ያለው።

ፈጣሪ ሲፈቅድ ለካ ሞትም ይሰረቃል። አይገርምም?
የሰውየው ንግግር በጣም ይገርማል። "ነገር ሁሉ ለበጎ ነው።'' ሁሌም በመንገዱ ፈጣሪውን ያስቀደመ አያፍርም!

የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence

የስብዕና ልህቀት

27 Sep, 05:24


ለክርስትና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!!

መልካም በዓል!!

የስብዕና ልህቀት

24 Sep, 16:37


አዋዋልህ ሕይወትህን ይወስናል!!

አዋዋልህ የህይወትህ መገለጫ ነው፡፡ አንዲቷን ቀን የምታሳልፍበት መንገድ የዘመናት ሕይወትህን ይወስናል፡፡ ዛሬ የምትሠራው ነገር የወደፊት ሕይወትህን ይፈጥራል፡፡ የምትናገራቸው ቃላት፣ የምታፈልቀው ሐሳብ፣ የምትመገበው ምግብ እንዲሁም የምትወስዳቸው እርምጃዎች እጣ ፈንታህን ይወስናሉ፣ ማንነትህንና ሕይወትህን ይቀርፃሉ፡፡ ትናንሽ ውሳኔዎች በጊዜ ሂደት ግዙፍ ውጤት ያስከትላሉ። ‹‹ትርጉም አልባ» እለት የሚባል ነገር የለም፡፡

እያንዳንዳችን ለታላቅነት የሚያበቃ ጥሪ አለን፡፡ እያንዳንዳችን በውስጣችን ታላቅ ኃይል አለ፡፡ እያንዳንዳችን በዙሪያችን በሚገኙ ሰዎች፣ ሁናቴዎችና ነገሮች ላይ ተጽእኖ ማድረግ እንችላለን። በውስጣችን የሚገኘውን ይህን ኃይል ለማጎልበት ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ ይበልጥ ተግባራዊ ስናደርገው የበለጠ ይጎለብታል፤ ብርቱ ይሆናል። ይሄን ኃይል ይበልጥ ስትጠቀምበት ይበልጥ ልበ-ሙሉ፤ በራስህ የምትተማመን ትሆናለህ፡፡

ከእኛ መካከል ይበልጥ ስኬታማ የሆኑት ሰዎች ከተቀረነው የተለየ ስጦታ ያላቸው አይደሉም፡፡ ወደ ታላቁ ሕይወት ሲጓዙ በየእለቱ ጥቂት ደረጃዎችን በትክክለኛው አቅጣጫ የሚራመዱ ናቸው፡፡ . ቀናት ወደ ሳምንታት፣ ሳምንታት ወደ ወራት ይሸጋገራሉ. . . ሳይታወቃቸው የተለየ» ተብሎ ከሚታወቅ ሥፍራ ይደርሳሉ፡፡

✍️ሮቢን ሻርማ

#share
የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence

የስብዕና ልህቀት

20 Sep, 15:48


አዲሳባ እየፈረሰች ነው። ደሰሳ ቤቶች "አዲሳባን አይመጥኑም" ተብለው እየፈረሱ ነው።

አዲሳባን ዘመናዊ ህንፃ ሳይሆን ደሳሳ ቤት ነው የሚመጥናት። ኢትዮጵያ የደሐ ሐገር ናት። አዲሳባ ደግሞ የድሆች መኖሪያ ነው። ሚሊዮኖ ድሆችን እያስተዳደሩ "የደሀ ቤት ከተማችንን አይመጥንም" ማለት አሳፋሪ ስላቅ ነው።

ደሳሳ ቤቶችን ማስወገድ መፍትሔ አይሆንም። ድህነታችንን የሚመጥነውን የደሐ ቤት ማፍረስ ትርፉ ሌላ መከራ ነው።

መፍትሔው የደሐውን ኑሮ ማሻሻል ነው። የደሐ ኑሮ ሲሻሻል ደሳሳ ቤቶች በራሳቸው ጊዜ በዘመናዊ ቤት ይተካሉ።

ቅድሚያ ለድህነት ቅነሳ ፖሊሲ!


@Tfanos

የስብዕና ልህቀት

16 Sep, 08:54


የሹፌሩ ማስታወሻ
በእወቀቱ ስዩም

@Human_intelligence

የስብዕና ልህቀት

15 Sep, 13:38


የማይረቡ ወይም የማይጠቅሙ ነገሮችን ከሕይወትህ ቆርጠህ አስወግዳቸው

በሕይወትህ መንገድ ላይ ምን እንዳጣህ ሳታውቅ፤ ስንት መሆን ያለባቸው ነገሮች ሳይሆኑ ቀሩ? በማይረቡ ሃዘኖችህ፣ በሞኝ ደስታዎችህ፣ በሥሥታም ፍላጎቶችህ እና በማህበር ፍንደቃዎችህ ውስጥ ምን ያህል አጣህ? ምን ያህልስ ለራስህ አስቀረህ? የመሞቻ ቀንህ ከመድረሱ በፊት እየሞትክ እንደ ሆነ ታውቆሃል?”
-ሴኔካ

በሕይወት ውስጥ ካሉ ከባድ ነገሮች ውስጥ አንዱ “#አይ #አይሆንም”  ማለት ነው። ለግብዣዎች፣ ለጥያቄዎች፣ ለግዴታዎች እና ሁሉም ሰው ለሚያደርጋቸው ተለምዷዊ ነገሮች “እምቢ” ማለትን ልመድ። እነዚያን ለማልፈቅደው ነገር እሺ በማለት ያጠፋኋቸውን ጊዜያቶች እንዴት ልመልሳቸው እችላለሁ ብለህ ታውቃለህ? ያልተጨናነቀ እና በስራዎች ያልተወጠረን ጊዜ ማሳለፍ ትፈልጋለህ?.. “እምቢ!” የማለትን ኃይል መማር ጀምር:: እንዲህ በል “አይ አይሆንም አመሰግናለሁ” ፧ “አሁን ላይ ይህን ላደርግልህ አልችልም” ፤ “በፍጹም ይህን ማድረግ አልችልም::”

ምናልባትም የአሉታ መልስህ ሰዎችን ሊጎዳ ይችላል፤ ምናልባትም ሰዎችን ካንተ ሊያርቅ ይችላል። ይህን ማድረግ በእጅጉም ሊከብድህ ይችላል። ሆኖም በሕይወትህ ውስጥ ያሉ እና የማይጠቅሙህን ነገሮች , “እምቢ” ስትል፤ ለሕይወትህ አስፈላጊ ነገሮችን “እሺ” ማለት , ትጀምራለህ። እሺ ያልካቸውም እንድትኖር እና ሕይወትን . እንድታጣጥማት ያደርጉሃል። እንደፍቃድህም ትኖራለህ።

✍️ርያን ሆሊደይ
የስብዕና ልህቀት
@Human_intelligence

የስብዕና ልህቀት

15 Sep, 11:02


ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለ1 ሺህ 499ኛው የነብዩ መሀመድ ልደት (መውሊድ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!