MoR West Addis Ababa (ምዕራብ)

@morwestaa


This is official Telegram Channel of Ministry of Revenues West Addis Ababa branch. Join the channel. 0115585348 0114702245

MoR West Addis Ababa (ምዕራብ)

19 Oct, 07:22


ማስታወቂያ ለታክስ ሞጁላር ሰልጣኞች
ውድ የክፍል አንድ ስልጠናን ያጠናቀቃችሁ የ30ኛ ዙር ሰልጣኞቻችን እና በተለያየ አጋጣሚ የክፍል ሁለት ስልጠናን ያቋረጣችሁ፤ የክፍል ሁለት ስልጠና ሰኞ 11/02/2017 ዓ.ም የሚጀመር ስለሆነ ከጠዋቱ 2፡30 ላይ 3ተኛ ፎቅ የስልጠና አዳራሽ በመገኘት ስልጠናውን እንድትከታተሉ እናሳውቃለን፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/profile.php?id=100090259834322
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@morwestaddisababasto

MoR West Addis Ababa (ምዕራብ)

18 Oct, 13:59


ኤክሳይዝ ታክስ አከፋፈል እና ምጣኔ
ኤክሳይዝ ታክስ የሚጣለዉ የቅንጦት እቃዎች ናቸዉ በሚባሉ፤ የኅብረተሰቡን ጤና በሚጎዱ እና የማህበራዊ ችግር በሚያስከትሉ እንዲሁም መሰረታዊ በመሆናቸዉ ምክንያት የገበያ ተፈላጊነታቸዉ በማይቀንስ እቃዎች እና አገልግሎቶች ላይ ነዉ፡፡
የኤክሳይዝ ታክስ ቀደም ሲል በማምረቻ ወጪ ላይ ሲሰላ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ታክሱ በፋብርካ የመሽጫ ዋጋ እንድተካ መደረጉ ታክስ ከፋዮች ሊከፍሉት የሚገባ ታክስ ተገማችነት ረገድ ሲያጋጥማቸዉ የነበረዉን ችግር የሚያቃልል መሆኑ ታምኖበታል፡፡
በኢትዮጵያ “የኤክሳይዝ ታክስ” የሚባለው በሚከተሉት አቅርቦቶች ላይ የሚጣል ታክስ ነው፡-
👉🏿በተፈቀደለት አምራች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚመረቱ የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸው ዕቃዎች፤
👉🏿ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸው ዕቃዎች
በኢትዮጵያ በሚመረቱ ዕቃዎች ላይ የተጣለውን የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፍለው የተፈቀደለት አምራች ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የተጣለውን የኤክሳይዝ ታክስ አስመጪው የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
የኤክሳይዝ ታክስ አስፈላጊነት
👉🏿ገቢ ለማሰብሰብ፤
👉🏿የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ፤
👉🏿ሀብት ለማደላደል፤
👉🏿ለአከባቢ ጥበቃ
የታክሱ ምጣኔ
🖍ኤክሳዝ ታክስ ከ5% እስከ 100 %
🖍በመኪናዎች ላይ ብቻ ግን የአልግሎት ዘመናቸዉን፤ የሲሲ መጠናቸዉን ታሳቢ አድርጎ ከ100% በላይ እስከ 500% ይጣልባቸዋል፡፡ ከ1300 ሲሲ መጠን በለይ ያለቸዉ እና የአገልግሎት ዘመናቸዉ ረጅም የሆነ የታክስ መጣኔያቸዉ በአንፃራዊነት ከፍተኛ እንድሆን ተደርጓል፡፡

MoR West Addis Ababa (ምዕራብ)

16 Oct, 11:24


የንግድ ስራ እና የኪራይ ገቢ ግብር ላይ ስልጠና ተሰጠ
በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት እየተሰጠ የሚገኘው የታክስ ከፋዮች ሞጁላር ስልጠና እንደቀጠለ የሚገኝ ሲሆን ለ30ኛ ዙር ሰልጣኞች በሞጁል ሁለት የንግድ ስራ እና የኪራይ ገቢ ግብር ላይ ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዘነበ አበበ የገቢ ግብር የሚከፈልባቸውን የሰንጠረዥ “ለ“ የኪራይ ገቢ ግብር እና የሰንጠረዥ “ሐ“ የንግድ ሥራ ገቢ ግብሮችን ሰልጣኞች በህጉ መሰረት እንዲረዱ በማድረግ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ማስቻል የስልጠናው ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በስልጠናው የቤት ኪራይ ገቢ ግብር መጣኔ፣ የንግድ ስራ ገቢ ግብር መጣኔ፣ ተቀናሽ ወጪዎች፣ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ፣ በግምት የሚወሰን ገቢ ግብር እና ተያያዥ ጉዳዮች በስፋት ተዳሰዋል፡፡
ተቋምን በልህቀት፣ ገቢን በስኬት!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/profile.php?id=100090259834322
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@morwestaddisababasto

MoR West Addis Ababa (ምዕራብ)

14 Oct, 15:37


የ30ኛ ዙር የሞጁላር ስልጠና መሰጠት ተጀመረ
በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የ30ኛ ዙር የታክስ ከፋዮች ሞጁላር ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል፡፡
በክፍል አንድ ቀጥተኛ የሆኑ የታክስ አይነቶች ላይ በሞጁል አንድ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ እና የወጪ መጋራት ላይ ስልጠና የሰጡት የታክስ ከፋዮች ትምህርት ባለሙያ ወ/ሮ እየሩሳሌም አድማሱ ሠልጣኞች ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ እና ተያያዥ ጉዳዮችን በገቢ ግብር አዋጅ 979/2008፤ በደንብ ቁ.410/2009፤ መመሪያ ቁጥር 1/2011፣ በወጪ መጋራት ደንብ ቁጥር 154/2000 እና መመሪያ ቁጥር 2/2009 ላይ ያሉ ህጎችን አውቀው የታክስ ግዴታቸውን እንዲወጡ ማስቻል የስልጠናው ዓላማ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በቀጥተኛ የታክስ አይነቶች ላይ የሚሰጠው ስልጠና ሶስት ሞጁሎች ያሉት ሲሆን ለተከታታይ አምስት ቀናት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡
ተቋምን በልህቀት፣ ገቢን በስኬት!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/profile.php?id=100090259834322
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@morwestaddisababasto

MoR West Addis Ababa (ምዕራብ)

11 Oct, 12:02


ማስታወቂያ ለ30ኛ ዙር የሞጁላር ሰልጣኞች
ውድ የሞጁላር ስልጠናን በ30ኛው ዙር ለመወሰድ ተመዝግባችሁ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ ግብር ከፋዮቻችን ስልጠናው ሰኞ ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም መሰጠት የሚጀመር በመሆኑ ከጠዋቱ 2፡30 ሶስተኛ ፎቅ የስልጠና አዳራሽ በመገኘት ስልጠናውን እንድትከታተሉ እናሳውቃለን፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/profile.php?id=100090259834322
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@morwestaddisababasto