BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

@burhan9


ብሩህ እሳቤ ለብሩህ ነገ!

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

05 Sep, 18:15


ማሰብ ጉዞ ነው፡፡ እምነት ግን በእኛ ሐገር ማረፊያህን ካገኘህ በኋላ የምታደርገው ጉዞ ነው፡፡ አምነህ ስለምትጀምር ብዙ ጊዜ አምላክን አታገኘውም፡፡ በሕይወትህ ውስጥ የሆነ ጥያቄ ሲመጣብህ ሮጠህ የሀይማኖት አባትህን ትጠይቃለህ እንጂ ለራስህ አታስበውም፡፡ ስትወለድ ተወልደሀል፡፡ አድገህበታል፡፡ ስሙን (ክርስቲያን ወይም ሙስሊም የሚለውን) ሰጥተውሃል፡፡ አምነሃል፡፡ የትም አትሄድም፡፡ ፍለጋ አታደርግም፡፡ “አንብበው እስቲ” ተብሎ የእምነት መጽሐፍ ቢሰጥህ እንኳን የምታነበው መልስ ለመስጠት እንጂ ለማመንና አለማመን አይደለም፡፡ ያመንከውን አምነሃል፡፡ እምነት ውስጥ ለምሳሌ “አምላክ አለ-የለም” የሚለው አይነት ሐሳብ አለ፡፡ ሐሳብ ውስጥ ግን እምነት የለም፡፡

ሐሳብ ጉዞ ነው፡፡ ሁሌ ታስባለህ፡፡ ፍፁም አይደለሁም” ነው የሚለው የሚያስብ ሰው፡፡ የሚያስብ ሰው ከሚያምነው በጣም የሚለይበት ጥሩ ጐኑ አሳቢው “ጐዶሎ ነኝ” ሲል አማኙ “ፍፁም ነኝ” ይላል፡፡ ትልቁ ልዩነታቸው ይህ ነው፡፡ አንድን አማኝ ስለ ኳንተምን ፊዚክስ አንሳና ጠይቀው እስኪ፡፡ “ሁሉም ነገር እኮ መጽሐፉ ላይ ተጽፏል፡፡ ምንም ያልተጻፈ ነገር የለም” ነው የሚልህ፡፡ ግን ምናልባትም መጽሐፉን አላነበበው ሁሉ ይሆናል፡፡ ቢያነብም አልመረመረውም ይሆናል፡፡ አምኖ መጀመር ማለት ይኼ ነው፡፡ የሃይማኖት መጽሐፉን በጥልቀት አንብቦ መፈተሽን እንደ ሐጢአት ነው የሚወስደው፡፡ አምኖ መጀመር ችግሩ ይሄ ነው፡፡ ካመንክ አምነሃል በቃ፡፡ ፍተሻ አያስፈልግህም፡፡ ስለዚህ ባታነብም፣ አንብበህ ባይገባህም “ልክ ነው” ብለህ ትወስዳለህ፡፡ አሳቢ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ ሁሌም አዲስ ሐሳብ እንዳለ ያስባል፡፡ አስር ገፅ እንዳነበበ ይጠይቃል፡፡ በሐሳብ በየቀኑ እያደግህ ትሔዳለህ፡፡ በኛ ሀገር በእምነት ውስጥ ግን በየቀኑ እያነስክ ነው የምትሄደው።

ቡርሃን አዲስ ነው ይህንን የነገረን

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

30 May, 15:43


ሀቅ ነው!!!

የማይኖረውን ከሚዘምር ሰባኪ ... የሚኖረውን የሚያምን ሌባ ብርሀን ይሰጠኛል ...

ከሚያስመስል .... ዳኢ

ፓስተር ወይም ቄስ

ያመኑትን የተናገሩትን የሚኖሩ የገጠር ሽማግሌዎች .... ብርሃን ያሳዩኛል፤
ከተማሩ ጥቅመኞች ያልተማሩ ወላጆቼ ያፈኩኛል፤

#መሀመድ አሊ ብርሀን

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

30 May, 10:41


ወደ ማወቅ መጓዝ ጥድፊያን ይከላል። በጥድፊያ የሚደረስ እውቀት የለም። ማዝገም ነው ማወቅ። በሩጫ ማስተዋልን ጸጋ ማድረግ አይቻልም። አዝጋሚ ነው ጉዞው፥ የረጋ ጥሞና የሚያደምቀው ልምላሜም እንዲሆን የሰከነ ልብ ይፈልጋል።
እየሮጡ ማወቅ ማወቅን መካድ ነው። ቅጽበቶች ሁሉ ሰፊ የእውቀት ምዕራፎች ይወልዳሉ የተረጋጋ ነፍስ ላለው አእምሮ። ስሜቶቻችን ሲያሮጡን አእምሯችን ሊያረጋጋን ይሞክራል። በውስጣችን ያለው በላጭ ኃይል እኛን የሰራው ነው። ስንኖር የሚመራን ወይ ከስሜታችን ወይም ከማሰባችን ካንዱ ይበልጥ ይጎላል።
ይሔም በምናጸባርቀው የየእለት ጠባያችን ይገለጣል። የታየው የስሜታችን ወይም የማስተዋላችን ገሃድ ስለሚሆን በምንኖረው ህይወት አዋቂነት ወይም የስሜት ሰውነታችን ፍንትው ብሎ ለሌሎች የሚታይ ይሆናል። በአካባቢያችን የሚሰጠን ስምም ከዚሁ አመላችን አይርቅም።

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

15 May, 18:06


ሰው ጊዜውን ይሆናል፣ የሚኖረው ከሰው ጋ በህብረት ነውና ስለሚጠበቁበት ኃላፊነቶች ማስተዋል ሲጀምር የጊዜውንና ጸጋውን ውድነቶች ይረዳል። ጊዜውን መሆንን ይንከባከባል፣ የተቸረውን የምናብ አቅም ለህይወቱ እርካብ እንዲጸናበት የኑሮው ግምበኛ ይሆናል።

ይህን መድረስ ለመበቃት ግን ሰው መብቴ ከሚለው የማረጠ አፍላ ሀሳቡ አልፎ መገኘት አለበት። ግዴታየ ብሎ ሲያስብ፣ ከኃላፊነቱ ማሰብን ሲደርስ ያኔ ጥሩ የህይወት ልክ ይደርሳል። ሊበቃም ንጋቱን ያያል።

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

10 May, 21:00


የደጋገምናቸው ስሜቶች ጥቅል ስብእናን ይሰራሉ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የምንብሰለሰልባቸው ቃላትና ሀሳቦች በድግግማቸው ልክ ባህሪዎቻችን ላይ ሂድታዊ ለውጥ ይፈጥራሉ። የደጋገምናቸውን ስሜቶች እንሆናለን። ባህሪያችን ቅርጸ መልኩ ከየቅጽበቶቻችን መብሰልሰል የተንጸባረቀ ነው። ምንግዜም ወደ በጎነት ብቻ ተዘንባይ ውጤት ያለውን በመፈለግ ላይ መገንባት ይልቃል ።

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

06 May, 18:33


ከመንታ ትናንቶች ወደ አንዱ መንጋት አለ፣
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

እድሜያችን ሲያሸቅብ የትዝታ ዜማ አፍቃሪ እንሆናለን፡፡ የጋሽ ማህሙድን ዘፈን አብዛኞች እንሰማለን፤ ትዝታዎቹን እየመረጥን እንኮመኩማለን፡፡ ሌሎች የትዝታ ቅኝት ዜማዎችም ይስቡናል፡፡ ትዝታና ኢትዮጵያዊነት ብዙ ትስስር አላቸው፡፡ ትናንትን ሳያወሳ ዛሬን የሚናገር እጅግ ጥቂት ነው፡፡

የጋሽ ማህሙድን ሙዚቃዎች በየአጋጣሚው እየሰሙ ራስን ማከም ከወጣት እስከ አረጋዊው የሚታይ ነው፡፡ ያለፉ ትናንቶች የየራሳቸው ሰመመናዊ ወጎች ናቸው።

የሰዎች ውሎ በሙዚቃዎቹ ዉስጥ የተጠቀለለም ይመስላል፡፡

ስለአሁኑ ትናንትን የሚያንጎራጉር፣ ሞትን እንኳ በዜማ አልቅሶ የሚሸኝ ህብረት አለን፡፡ ስራና ደስታውን፣ ሰርግና ሞቱን በዜማ አጅቦ የሚሞቀው ኢትዮጵያዊ ዛሬውን ከትናንቱ አበው አጣብቶ ይኖራል፡፡

ዘፈኑ፣ ልብ-ወለዱ፣ ግጥሙ፣ ታሪኩ፣ ምሳሌው ሁሉ ትናንትን ያማክላል፡፡ ትናንትን መሰረት ያደርጋል፡፡ በትናንት ጡብ የተካበ ስሪተ-ወግ የመሰረትን ህዝቦች ነን፡፡ ኢትዮጵያዊነት ከትናንት የመነሳት ሱስ የተጣባ ስሜትም አለው።

ጥሩም አለው። መነሻውን ባልዘነጋ፣ ትናንቱን እየተደገፈ ዛሬን ለመስራት ይውላል። ዋና አቅም ግን አይሆንም ዋናችን አሁን ነው፣ ከዛሬ ቅንጥብ ያለች አሁንነት።

ወደ ነገ የመፈንጠር አቅም ሲሰጥ ለስሜት ያህል ያግዛል። ጽሞና ያለው፣ በፍሬ የጎመራ ትናንት ሲኖረን ማለት ነው። ያልጎመራ፣ ያልተሳካ ትናንት ደሞ የዛሬ አረም ይሆናል፣ መለየቱ ላይ ነው ጥበበኝነት ያለው።


ከትናንት መነሳቱ በጎ ነው። አነሳሱ አረም ለበስ ሜዳ ከነበረው ግን ዛሬን ይበላል። የጎመራ ትናንትን ለይቶ ዛሬን ለማብዛት መገበር የበሰለ ማጤን ነው።


በትናንት ዋሻ ገብቶ ለመኩራራት በሆነ ጊዜም እንዲሁ ዛሬን ይዘርፋል። ስለ ትናንት ያለን አርምሞ፣ ለዛሬ የፍሬያማነት ማረፊያ እንዲሆን ነው፣ አመክኒዮ፣ ሳይንሳዊ ሰውነትና የጥበብን ቀለም በመዛመድ፣ ትናንትን ለዛሬ አገልጋይ ማድረግን ይበስሏል።

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

21 Mar, 15:24


ማሰብ ጉዞ ነው፡፡ እምነት ግን በእኛ ሐገር ማረፊያህን ካገኘህ በኋላ የምታደርገው ጉዞ ነው፡፡ አምነህ ስለምትጀምር ብዙ ጊዜ አምላክን አታገኘውም፡፡ በሕይወትህ ውስጥ የሆነ ጥያቄ ሲመጣብህ ሮጠህ የሀይማኖት አባትህን ትጠይቃለህ እንጂ ለራስህ አታስበውም፡፡ ስትወለድ ተወልደሀል፡፡ አድገህበታል፡፡ ስሙን (ክርስቲያን ወይም ሙስሊም የሚለውን) ሰጥተውሃል፡፡ አምነሃል፡፡ የትም አትሄድም፡፡ ፍለጋ አታደርግም፡፡ “አንብበው እስቲ” ተብሎ የእምነት መጽሐፍ ቢሰጥህ እንኳን የምታነበው መልስ ለመስጠት እንጂ ለማመንና አለማመን አይደለም፡፡ ያመንከውን አምነሃል፡፡ እምነት ውስጥ ለምሳሌ “አምላክ አለ-የለም” የሚለው አይነት ሐሳብ አለ፡፡ ሐሳብ ውስጥ ግን እምነት የለም፡፡

ሐሳብ ጉዞ ነው፡፡ ሁሌ ታስባለህ፡፡ ፍፁም አይደለሁም” ነው የሚለው የሚያስብ ሰው፡፡ የሚያስብ ሰው ከሚያምነው በጣም የሚለይበት ጥሩ ጐኑ አሳቢው “ጐዶሎ ነኝ” ሲል አማኙ “ፍፁም ነኝ” ይላል፡፡ ትልቁ ልዩነታቸው ይህ ነው፡፡ አንድን አማኝ ስለ ኳንተምን ፊዚክስ አንሳና ጠይቀው እስኪ፡፡ “ሁሉም ነገር እኮ መጽሐፉ ላይ ተጽፏል፡፡ ምንም ያልተጻፈ ነገር የለም” ነው የሚልህ፡፡ ግን ምናልባትም መጽሐፉን አላነበበው ሁሉ ይሆናል፡፡ ቢያነብም አልመረመረውም ይሆናል፡፡ አምኖ መጀመር ማለት ይኼ ነው፡፡ የሃይማኖት መጽሐፉን በጥልቀት አንብቦ መፈተሽን እንደ ሐጢአት ነው የሚወስደው፡፡ አምኖ መጀመር ችግሩ ይሄ ነው፡፡ ካመንክ አምነሃል በቃ፡፡ ፍተሻ አያስፈልግህም፡፡ ስለዚህ ባታነብም፣ አንብበህ ባይገባህም “ልክ ነው” ብለህ ትወስዳለህ፡፡ አሳቢ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ ሁሌም አዲስ ሐሳብ እንዳለ ያስባል፡፡ አስር ገፅ እንዳነበበ ይጠይቃል፡፡ በሐሳብ በየቀኑ እያደግህ ትሔዳለህ፡፡ በኛ ሀገር በእምነት ውስጥ ግን በየቀኑ እያነስክ ነው የምትሄደው።

ቡርሃን አዲስ ነው ይህንን የነገረን

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

13 Mar, 16:15


https://youtu.be/C61TEDLQxrc?si=hnmfPnIRpsXo7F-Y

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

12 Mar, 21:35


በህይወት ስትኖር የምታርፍበት ብዙ ፌርማታ አለ፡፡ በየፌርማታህ ያለህን ለውጥ መመዘን እንጂ በመጨረሻ ልትደርስ ያሰብከውን ተቻኩለህ መድረስን አትመን፡፡

በየማረፊያዎችህ ጥቂት ጥቂት እድገቶች ካሉህ እያጣጣምካቸው እለፍ፡፡

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

24 Feb, 21:22


እየኖርክ ብትሳሳት እያደክም ነው። ካላስረገጥከው ግምትህ የምታገኘው ስሜትህን መረበሽና ስህተት እንዳይሆን አስተውል። በእጅህ ካለ እውነት በመነሳት መልካምን ትሆናለህ።

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

21 Feb, 16:52


https://youtu.be/dB05iXi8Knw?si=5vsGzb1dP8sf4ZuB

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

08 Feb, 02:34


የጨበጥነውን አንፈራም፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።

የያዝነው መዳፋችን ላይ ያለ ሁሉ የኛ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ የምንጋፈጠው የፊት ለፊት ጦር አያስፈራንም፡፡ እስክንጀምረው ብንብረከረክ እንኳ አንዴ ላንመለስ ከእሳቱ ከጠለቅን የሞት ሽረት ይሆናል ጉዳዩ… ፡፡

የምንፈራው ያልያዝነው ወይም ከኛ ቁጥጥር ውጪ የሆነውን ነው፡፡ ወደ ኋላ ያለ ታሪካችንን እንፈራለን፤ እኛ ከምንቆጣጠረው ልክ ውጪ የመሆን አቅም ስላለው ነው፡፡ ወደ ነገም ስለሚመጣው ቀን እንፈራለን፤ እንደርስ ይሆን እንዳሰብነው እንሆንበት ይሆን ብለን ስንጠይቅ እርግጠኛ መሆን ሲሳነን ነው፡፡


ፍርሀት የእምነት ትጋትን ይነፍጋል፡፡ አቋምን ያከሳል፤ የዛሬን መኖር ይወስዳል፡፡ ፍርሃት በለውጥ አቅም ጥረታችን ሁሉ ጣልቃ እየገባብን ብርታታችንን ያጎላል፡፡

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

01 Feb, 12:04


ከሚወዱት ሰው ጥቂት ደስታ ማየት ብዙ እፎይታ ነው።

ቡርሐን አዲስ

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

26 Dec, 22:10


https://youtu.be/k2X041slCHI?si=TjlO9CsTcCtAV99O

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

16 Dec, 11:37


በማስተዋል መታገስንና በህይወት ግብግብ ልምድን መካበትን አስረግጠህ ተላመድ። በተፈተንክበት ጉዞህ በላቀ ትማራለህ። ከሀሳባዊ ግንዛቤህ በበለጠ የኖርከው ውሎ አዳር እርግጥ የሆነ ምሳሌህ ነው። ኑሮህን ከንባብህ አቻ ስፈርና በምትኖረው ተገንባ፣ የኖርከውን መማሪያ ስለ ማድረግ ፈንጥቅ።

ውሃን ውሃ ስለተባልክ ብቻ አትረዳውም በውሃ በዝናቡ ርሰህ ወይም ጠጥተህ ወይም ዋኝተህበት ማለፍ አለብህ፡፡ ነገሮች ስለተነገሩህ ብቻ አይሞሉህም፤ ስታልፍባቸው የልምድህ አካል ሲሆኑ ነው ይበልጥ የሚገለጡህ።

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

11 Dec, 02:31


https://youtu.be/3F-uwO75cxA?si=kXibQuSK8xCwJivJ

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

20 Oct, 21:15


https://youtu.be/COG4qUWXPD4?si=HZADFlvPoOSqOBGl

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

07 Oct, 11:00


https://youtu.be/7_EilgkGCjg?si=hW0Y_8lIct5Z4kuj

BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት)

30 Sep, 17:40


BURHAN-ADDIS (የሀሳብ ንጋት) pinned «ሰውን መረዳት እንቆቅልሹ አያባራም፡፡ ራሱን የሚያጠና ፍጡርም ነው ሰው፤ ሰውን እንዴት እንረዳው? ራስን መረዳት እንደግልና እንደሀገር እንደእምነት አባል ወይም እንደዓለም ህብረት በምንና በምን ይታያል? እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ በተከታታይ ክፍሎች የጀመርነው የሀሳብ ጉዞ ነው፡፡ https://youtu.be/gyOFG6sa1JI?si=anjr2AZ-K9IuJn3x»

7,691

subscribers

37

photos

5

videos