ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

@marakisport34


እንኳን በደህና ወደ ማራኪ ስፖርት የቴሌግራም ቻናል በሰላም መጣችሁ።

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

22 Oct, 19:53


#እረፍት

ሪያል ማድሪድ 0-2 ዶርትመንድ

             ማለን
             ጊቴንስ

አርሰናል 1-0 ሻክታር ዶኔስክ

ሪዝኒክ ( በራስ ላይ )

ጁቬንቱስ 0-0 ስቱትጋርት

ፒኤስጂ 0 - 1 ፒኤስቪ

                ላንግ

አስቶንቪላ 0-0 ቦሎኛ

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

22 Oct, 19:05


የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ውድድር የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ኣርጀንቲናዊው የኢንተር ሚያሚ የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ የሜጀር ሊግ ሶከር የመስከረም ወር ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጥ ችሏል።

አርጀንቲናዊው ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በወሩ ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች አምስት ግቦች አስቆጥሮ አንድ ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

22 Oct, 05:44


ፈረንሳዊው የ ማንችሰተር ዩናይትድ ተከላካይ ሌኒ ዮሮ ከረጅም ጉዳት በኋላ ወደ ልምምድ የተመለሰ ሲሆን አሁን ላይ ለብቻው የተለያዩ ትሬይኒንጎችን እየሰራ ነው::
በቅርቡ ከዋናው ቡድን ጋር ልምምድ እንደሚጀምር ታማኙ ጋዜጠኛ Fabrizio Romano ዘግቧል።

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

21 Oct, 16:55


የሎስ ብላንኮዎቹ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ስለ ነገ ተጋጣሚያቸው ቦርስያ ዶርትመንድ “ ሁሉንም እናውቃለን  መሰለል ኣይጠበቅብንም“ 😂😂

ቦርስያ ዶርትመንድ ሪያል ማድሪድ ይሰልለናል በሚል ፍራቻ በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ልምምድ ላለመስራት መወሰናቸው መገለፁ ይታወሳል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡት አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ “ ስለ ዶርትመንድ ሁሉንም ነገር እናውቃለን እንዴት እንደሚጫወቱ ለማወቅ መሰለል አያስፈልገንም “ ብለዋል።

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

21 Oct, 08:02


X empire ያመለጣችሁ ስሩት በቀን አንዴ ብቻ daily check in ብቻ ነው የሚኖረው

http://t.me/hrummebot/game?startapp=ref389697849

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

20 Oct, 19:08


ሊቩርፑል በ 8 የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ ጨውታዎች 15 ግቦች ሲያስቆጥር 3ግቦች ተቀጥሮበታል::

ሳላህ በፕርሚየር ሊጉ ታሪክ በርካታ የፍፁም ቅጣት ምት ግቦችን ማስቆጠር የቻለ አምስተኛው ተጨዋች መሆን ችሏል።

የደረጃ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?

1⃣ ሊቨርፑል - 21 ነጥብ

2⃣ ማንችሰተር ሲቲ -20 ነጥብ

3⃣ አርሴናል - 17ነጥብ

ቀጣይ የ እንግሊዝ  ፕሪሜየር ሊጌ መርሐ ግብር ?

እሁድ 👉አርሰናል 🆚 ሊቨርፑል

እሁድ 👉 ቼልሲ 🆚 ኒውካስል ዩናይትድ

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

20 Oct, 17:58


ሊቨርፑልን እየመሩ ጥሩ ጊዜን በማሳለፍ ላይ የሚገኙት ኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ አርኔ ስሎት አዲስ ታሪክ መፃፍ ችለዋል።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ከመጀመሪያ አስራ አንድ ጨዋታዎች አስሩን በአሸናፊነት መወጣት የቻሉ የመጀመሪያ የሊቨርፑል አሰልጣኝ መሆን ችለዋል።

ሊቨርፑል ቼልሲን አሸንፎ በዘንድሮው የውድድር አመት ሁሉንም ከሜዳው ውጪ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች ያሸነፈ ብቸኛው ክለብ መሆኑን አረጋግጧል።

1: የፕርሚየር ሊጉ መሪ

2: ማንችስተር ዩናይትድ ፣ ቼልሲ እና ኤሲ ሚላንን አሸነፉ

3: ሁለቱንም የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች አሸነፉ

4:በውድድር አመቱ አንድ ሽንፈት ብቻ አስተናገዱ( ኖቲንግሃም ፎርስት

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

20 Oct, 12:56


ታሪክን የዋሊት

የቀድሞው የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት እና የእግር ኳስ ተጫዋች ጆርጅ ዊሃ ከምንጊዜውም 50 ምርጥ የእግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል በስፖርት ኢሊስትሬት ተመርጧል። የስፖርት ኢላስትሬት የቀድሞዉን ላይቤሪያዊ አጥቂ በ43ኛ ደረጃ ስፖርቱን በመጫወት ከታላላቅ ተርታ አስቀምጧል። ስፖርት ኢለስትሬትድ ለመጀመሪያ ጊዜ በነሀሴ 1954 የታተመ የአሜሪካ የስፖርት መፅሄት ነው።በስቱዋርት ሼፍቴል የተመሰረተ፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስርጭት ያለው የመጀመሪያው መጽሄት ለጄኔራል ልቀት የብሔራዊ መጽሔት ሽልማትን ሁለት ጊዜ አሸንፏል። ከ1964 ጀምሮ በሚታተመው አመታዊ የዋና ልብስ እትም ይታወቃል እና ሌሎች ተጓዳኝ የሚዲያ ስራዎችን እና ምርቶችን አፍርቷል።

https://t.me/marakisport34
https://t.me/marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

20 Oct, 06:31


💥ዋልያዎቹ ከኤርትራ ጋር የሚያደርጉትን የቻን ማጣሪያ አዲስ አበባ እንዲሆን ጠይቀዋል!

🔛 ኢንስትራክተር አብርሃም ወይም አሰልጣኝ ስዩም ቀጣይ አሰልጣኝ?
👇

የ2024 የቻን አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከጥር 24 እስከ የካቲት 21/2017 ዓ.ም ይካሄዳል። የዘንድሮው የቻን ውድድር በኬንያ ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ አዘጋጅነት በአስራ ዘጠኝ ሀገራት መካከል የሚካሄድ መሆኑ ይታወቃል።

ለዚህ የ2024 የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮና ቻን የማጣርያ ጨዋታዎች የመጀመሪያ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ከጥቅምት 15-17 ባሉት ቀናት እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከጥቅምት 22-24/2017 ባሉት ቀናት እንደሚደርጉ
ይሆናል::

በዚህ መሠረት የማጣሪያው የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር አዲስ አበባ ላይ የመልሱ ጨዋታ ህዳር 1 አስመራ ላይ ይካሄዳል። በኢትዮጵያ በኩል የመጀመሪያው፡ጨዋታ አዲስ አበባ ስታዲየም እንዲካሄድ ፌዴሬሽኑ ካፍን የጠየቁ ሲሆን መልስ እየጠበቁ ይገኛል።
የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ከ ታህሳስ 11 - 13 እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከታህሳስ 18-20/2017 ባሉት ቀናት ይካሄዳል።

በሌላ በኩል የአሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ የሃላፊነት ዘመን ጥቅምት 22/2017 የሚጠናቀቅ በመሆኑ ተከትሎ ከኤርትራ ጋር ያለው የቻን የማጣሪያ የደርሶ መልስ ጨዋታ የመጀመሪያው ግጥሚያ አሰልጣኙ ቡድኑን ይዘው ጨዋታውን ያደርጋሉ ተብሎ ቢጠበቅም ከጥቅምት 23 በኃላ ለብሔራዊ ቡድኑ ቀጣይ አሰልጣኝ ለመምረጥ ሂደት ላይ ናቸው:: አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ወይም ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ እንደታሰቡ ተሰምቷል::

© Ethio Kick off

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

20 Oct, 06:31


💥አንዳንድ እድሎች ደግሞ . . .

ትላንት ምሽት በጣሊያን ሴር ኤ ኤሲሚላን በሜዳው ዩድኔዜን ጋብዞ 1 ለ 0 አሸንፏል።
ታዲያ ጨዋታው ተጠናቆ 7 ደቂቃ ይጨመራል፣ በ97ኛው ደቂቃ የዩድኔዜው ቤልጀማዊ ተጨዋች Christian Kabasele ጎል አስቆጥሮ አቻ ማድረግ ችሎ ነበር ።
ነገር ግን ከታች በምስሉ በምታዩት መልኩ ከጨዋታ ውጭ (Off side) ተብሎ ተሽሮበታል።

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

20 Oct, 04:14


💥ለሊት ላይ ኢንተር ማያሚ ከ ኒው ኢንግላንድ ሪቮሊውሽን ጋር በተደረገ የ MLS ጨዋታ እስከ 57ተኛው ደቂቃ 2 አቻ ነበሩ።

ከዚህ በኋላ ሜሲ ተቀይሮ ገብቶ ሶስት ጎል አስቆጥሮ ሀትሪክ ሰርቷል።
ጨዋታውም 6-2 በሆነ ውጤት ተጠናቋል። ሁለቱን ሊዊስ ሱዋሬዝ አንዱን ደግሞ ዮርዲ አልባ አመቻችተውለታል።

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

19 Oct, 19:43


የመድፈኞቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዴክላን ራይስ ቡድናቸው የሚደረግበት ነገር የሚያሳፍር መሆኑን ከጨዋታው በኋላ ሲናገር ተደምጧል።

ዴክላን ራይስ ከጨዋታው በኋላ ለዳኞች ቡድኑ “ በየሳምንቱ እኛ ላይ ይህ ነገር ይፈጠራል በጣም ያሳፍራል “ ሲል መናገሩ ተገልጿል።

በዚህ አመት በሁለት ጨዋታዎች ተመሳሳይ ነገር ተፈጥሮ ከሽንፈት መትረፋቸውን ያስታወሰው ራይስ “ ስህተቶችን መስራት ማቆም አለብን ሙሉ ዘጠና ደቂቃ ሁሉም ተጨዋቾች ያስፈልጉናል “ ብሏል።

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

19 Oct, 19:20


ሰር አሌክስ ፈርጉሰን የቀድሞ ክለባቸውን ለመደገፍ በሴልቲክ እና በአበርዲን መካከል በተደርገው ጫወታ ተገኝተው ነበር።

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

19 Oct, 19:12


ሜሰን ግሪንዉድ ከፍቅረኛው ጋር ሁለተኛ ልጃቸውን እየጠበቁ እንደሆን በማህበራዊ ገፆች ላይ እየተዘዋወረ ነው።

@marakisport34
@marakisport34

2,962

subscribers

1,694

photos

18

videos