አርሰናል daily fans page🇪🇹

@arsenaldailyfanspage


🔻|| ወቅቱ የዝውውር ነው ይህንንም አስመልክቶ የትም መሄድ ሳይጠበቅብዎት
ካሻዎት በፌስ ቡክ ፔጅ ወይም በመወያያ ግሩፓችን ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች ደሞ በቴሌራም ቻናላችን ሥለ ተወዳጁ ክለባችን አርሠናል 👇👇👇👇👇👇👇👇

➡️|| ዜናዎች
➡️|| የዝውውር ጭምጭምታዎች
➡️|| የተረጋገጡ ዝውውሮችን
➡️|| ሰበር ዜናዎችን [Breaking news]
➡️|| ትንታኔዎችን እና
➡️|| ቀጥታ ሥርጭት

አርሰናል daily fans page🇪🇹

24 Jul, 14:31


🚨Breaking𝗟𝗔𝗧𝗘𝗦𝗧  🇮🇹 𝐂𝐀𝐋𝐀𝐅𝐈𝐎𝐑𝐈 𝗧𝗥𝗔𝗡𝗦𝗙𝗘𝗥 𝗡𝗘𝗪𝗦

ሪካርዶ ካላፊዮሪ ወደ አርሰናል ለመዘዋወር ስምምነቱ ተጠናቋል።

የ22 አመቱ ተከላካይ ሜዲካሉን ማድረግና ኮንትራቱን መፈረም ይኖርበታል ነገርግን ስምምነቱ ተፈፅሟል።

ሁሉም ነገር በታቀደው መሰረት ከሄደ ሪካርዶ ካላፊዮሪ የአርሰናልን ስብስብ በአሜሪካ ይቀላቀላል።
[David Ornstein]

አርሰናል daily fans page🇪🇹

23 Jul, 15:09


🗣️ 🇫🇷𝗥𝗼𝗹𝗹𝘀-𝗥𝗼𝘆𝗰𝗲.🌟 William Saliba⚡️ "በሚቀጥለው የውድድር አመት የተሟላውን አርሠናል ትመለከቱታላችሁ ።"🔥
ዊልያም ሳሊባ: ይናገራል

🗣🔸️" ባሳለፍውነው የውድድር ዘመን ድንቅ የውድድር አመት ማሳለፍ ብንችልም የውድድር አመቱም ያለ ዋንጫ መጨረሳችን በውጤታችን በምንም መሥፈርት መደሰት አንችልም ነገር ግን ጥሩ ነገር ሁሌም እየተማርን መቀጠላችን ነው በዚህ ሲዝን ትልቅ ሥኬቶችን ለማሥመዝገብ ካለፈው የውድድር ዘመን ብዙ ነገሮችን ተምረን እንመለሳለን።

🗣🔸️"ባሳለፍነው የውድድር አመት ጠንካራ ቡድን ነበርን በእያንዳንዱ ጨዋታ ሜዳ ላይ ቡድናችን ተጋጣሚዎችን ማሸነፍ ቢያቅተው ቢያንስ አንሸነፈም ነበር ይህ ትልቅ ለውጥ ነው። ባለፈው የውድድር ዘመን እንደ ቡድን ጥሩ ሠርተናል ጥሩም ተፎካካሪ መሆን ችለናል ይህ ዝም ብሎ የመጣ አይደለም ጠንክረን በመሥራት ያመጣነው ለውጥ ነው እሥከ ውድድር አመቱ የመጨረሻ ሳምንት ድረሥ እልህ አሥጨራሽ ፉክክር አድርገናል  ማንቸስተር ሲቲ የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግን ከእኛ በ2 ነጥብ በልጦ ዋንጫውን አሸንፏል ነገርግን በዚህ ውጤት በሊጉ 2ኛ በመውጣታችን  እኛ በፍጹም አልረካንም።"

🗣🔸️በሚቀጥለው የውድድር አመት እራሳችንን አሻሽለን እንመለሳለን ይህን ቡድን ማሻሻላችንን እንቀጥላለን ካለፈው የውድድር አመት የነበሩብንን ድክመት አሻሽለን የነበረንን ጥንካሬ አሻሽለን እንመለሳለን በአዲሡ የውድድር አመት ሁሉንም የEpl ቡድኖችን ስንገናኝ የፍጻሜ ያህል እየተመለከትን እያንዳንዱን ጨዋታ በድል መወጣት ይጠበቅብናል  በዚህ አመት ክለባችን አርሠናል ካለፉት አመታት ጋር ሲወዳደር በእርግጠኝነት ከየትኛውም አመት የበለጠ የተሻሻላ እና በሁሉም ረገድ የተሟላ አርሰናልን ትመለከቱታላችሁ በእግርጠኝነት የተሟላ ቡድን ይዘን እንመጣለን።"

እናምናለን! 🇫🇷𝗥𝗼𝗹𝗹𝘀-𝗥𝗼𝘆𝗰𝗲.🌟 William Saliba⚡️ 🔥

አርሰናል daily fans page🇪🇹

30 Jun, 13:04


በዩሮ 2024 አንዳንድ ቁጥራዊ መረጃ ...

☑️ ብዙ ሙከራ ያደረገ

= ካይ ሀቨርት 🥇

☑️ ብዙ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ

= ካይ ሀቨርት 🥇

☑️ በተቃራኒ የግብ ሳጥን ውስጥ ብዙ ኳስ የነካ

= ካይ ሀቨርት 🥇

☑️ ከፍተኛ xG ያለው

= ካይ ሀቨርት 🥇
👉  የኛዋ ተወካይ 👉 ከይ ሉካስ ሀቨርትዝ በዚ የውድድር አመት ለክለቡ እና ለሀገሩ በአጠቃላይ 19 ጎል አስቆጥሯል 👉በአጠቃላይ ለሀገሩ ጀርመን ያለው እስታት

                        38 Starts
                        🛑 30 G/A
                        ⚽️18 Goals
                        ✍️12 Assists
💪     The    king strikes again 🎯
👑 kai is on 🔥

አርሰናል daily fans page🇪🇹

30 Jun, 12:53


"ቡካዮ ሳካ ከኮል ፓልመር የተሻለ ፈጣን እና ልምድ ያለው ተጫዋች ነው።" 🇬🇬󐁿😃

            🗣 ይህንን የተናገረው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሠልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት ነው

🗣️ ጋሬዝ ሳውዝጌት ለምን ከፓልመር ይልቅ ሳካን በቋሚ አሰላለፍ  እንደሚመርጥ ተናግሯል፡-

🗣“ሰካ እና ኮል ፓልመር ትንሽ የተለያዩ ተጫዋቾች ናቸው ፣ ነገር ግን ሁለቱም የግራ እግር ተጫዋቾች ናቸው  የግራ እግር ተጫዋች በመሆናቸው ሚናቸው አንድ አይነት ቢሆንም  ሁለቱም ከመስመር እየተነሱ ወደ ሳጥን ውስጥ እየገቡ የቀኝ ክንፍ መሥመሩን ይጠቀሙበታል የሁለቱም ሚና አንድ ቢሆንም የተወሰነ ጥቂት ልዩነት አላቸው።"

🗣" ቡካዮ ሳካ ምናልባት ከፓልመር የበለጠ ቀጥተኛ ፣ የበለጠ ፍጥነት ያለው ከኳስ ጋርም ያለ ኳስም የበለጠ ፍጥነት ያለው  እና ከእሡ [ፓልመር] የበለጠ ልምድ ያለው ተጫዋች መሆኑ ግልጽ ነው።"

🗣"ኮል ፓልመር በዚህ የውድድር ዘመን የመጀመሪያ የውድድር አመቱ ከፕሪሚየር ሊጉ ጋር በጥሩ ሁኔታ እየተላመደ ነው እና ከእኛ ጋርም  ህይወትን ይሰጣል። ስለዚህ በሁለቱም ተጫዋቾች በቡድናችን በመኖራቸው በጣም ደስተኞች ነን።"

🗣"ሁለቱም ጥሩ ለቡድናችን ጥሩ አስተዋፅዖ አበርክተዋል እያበረከቱም ይገኛሉ እናም ቡድናችን ላይ ያላቸውን ብቃት ሠጥተው ቡድኑ ላይ የተለየ ለውጦችን ማምጣት ይፈልጋሉ።"
👉 እሥኪ እናንተም ሀሳብ ስጡ ከደጋፊነት መንፈስ ውጡና ለእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን በቋሚነት መጀመር ያለበት ማን ነው ?
ቡካዮ ሳካ 😘
ኮል ፓልመር ❤️

አርሰናል daily fans page🇪🇹

20 Jun, 16:43


🚨 ሰበር ዜና 🇹🇷ፈርዲ ካዶዮግሉ ወደ አርሰናል?

↘️አርሰናል ለቱርኩ ኮከብ  20 ሚሊዮን ይሮ ይፋዊ ጥያቄ ለፌነርባቼ አቅርቧል !🇹🇷
🔥ፌነርባቼ ለተርካዊ ጥበበኛ 35 ሚሊዮን ይሮ ይፈልጋል!
Aygun Ozipek ( ታማኛ የቱርክ ዘጋቢ )
ስለ ቱርካዊው 🇹🇷ፈርዲ ካዶዮግሉ ሌላው መረጃ ደሞ 👇
🚨 ታዋቂው ቱርካዊው ጋዜጠኛ ሳቻ ታቮሊሪ እንዳለው ቱርካዊው የፊነርባቼ የግራ ፉልባክ ተከላካይ እና ሁለ ገብ ተጫዋች ወደ አርሰናል ሊቀላቀል መቃረቡን የፈርዲ ካዲኦግሉ የቅርብ ምንጮች ሹክ ብለውኛል በማለት ታዋቂው ጋዜጠኛ  ሳቻ  ታቮሊሪ አረጋግጠዋል።

🔸️አርሰናል ቱርካዊውን የ24 አመት ሁለገብ ተጫዋች ወደ ኤምሬትስ ለማዘዋወር ከተጫዋቹ ጋር በሁለቱ ወገኖች መካከል ረዥም ግዜን የፈጀ ውይይት ማድረጋቸውን እና በግል ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ በሁለቱም ወገኖች መካከል የተካሄደው ውይይት ሥኬታማ እንደነበረ የዘገበ ሲሆን ። ዘገባው አክሎም  አርሠናል ከተጫዋቹ እና ከወኪሉ ጋር ሥምምነት ላይ መድረሳቸውን ነገር ግን ከክለቡ ከፌነርባቼ ክለብ ጋር ምንም አይነት ቀጥተኛ ውይይት እንዳልተደረገ ዘግቧል።

🔸️ከአንድ ወር በፊት ሥለዚህ ዝውውር ያልተረጋገጠ ምንጭ ከወደ ቱርክ 🇹🇷  የአገሪቷ ከፍተኛ ተነባቢ እና የፊነርባቼ የቅርብ መገናኛ አውታሮች መረጃው የተሰራጨ ሲሆን በተጨማሪም የካዲኦግሉ አባት ልጁ መድፈኞቹን በክረምቱ ዝውውር እንደሚቀላቀል ተናግሯል። ከዚህ ቀደም አርሰናል ይህን ተከላካይ እንደሚያነጋግረው ብዙ ወሬዎች ነበሩ።

🔸️ፌርዲ ካዲዮግሉ የ24 አመቱ ወጣት ሲሆን በዋናነት የሚጫወተው በግራ ተከላካይነት ነው ነገርግን በቀኝ በኩል እና በመሀል አማካዩ ጥሩ መጫወት ይችላል።

🔸️ይህ በቴክኒክ ላይ የተመሰረተ በማጥቃት ላይ ያተኮረ ተከላካይ ነው ኳስን የመቆጣጠር እና የማዞር ዝንባሌ ያለው እና በጥሩ ሁኔታ መጨረስ ይችላል።

🔸️ፌርዲ ካዲኦግሉ በቱርክ ብሄራዊ ብሄራዊ  ሻምፒዮና ሊግ ውሥጥ ከክለቡ ጋር የተሳካ የውድድር አመት ማሳለፍ የቻለ ሲሆን ይህ ቱርካዊ ሁለገብ ኮከብ በቱርክ ሊግ ውሥጥ በርካታ የተሳኩ ፓሶች በማድረግ እና ኳስ ለጎል አመቻችቶ በማቀበል የሚቀድመው አንድም ተጫዋች የሌለ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የኋላ መሥመር ተከላካዮችን በማገዝ እና ኳሥ በማሠራጨት ኳሥ ከቡድን አጋሮቹ ተቀብሎ በማቀበል ይመራል በተጨማሪም የመልሶ ማጥቃትን በማቋረጥ  እና የተሳኩ ታክል በመውረድ እግር ኳስ ላይ የተመሰረተ ብቃት ያለው በሁሉም ቁጥሮች ይህ ኮከብ በሊጉ አናት ላይ ይገኛል።

↪️ይህን ልጅ አይቶ ለአርሰናል አለመመኘት ሀጥያት ነው....

↪️እውነት ለመናገር ስለዚህ ልጅ የሰማውት እና መከታተል የጀመርኩት ፕሪሚየር ሊጉ የመጨረሻ ሳምንት አካባቢ ነበር...ትክክለኛ የአርሰናል ተጫዋች ቀለም ያለው ፤ ቴክኒካሊ ጊፍትድ የሆነ ፤ ድሪብል በደምብ ማድረግ እሚችል፤ ከሳጥን ውጪ ሹት አርጎ የሚያገባ  ፤ በሁለቱም እግሩ መጫዋት ሚችል ፤ የተለያየ ቦታ መጫወት የሚችል ፋልባክ መሀል ክንፍ ፤ ገና ወጣት ሁሉም ነገር ያለው ድንቅ ተጫዋች ነው። ለማንኛውም ዝውውሩ የሚሳካ ከሆነ ብዙ ትንታና ሠርተን እናጋራችኋለን  ለጊዜው ግን የልጁን ድንቅ ብቃት አጭር ቪዲዮ ኮሜንት ላይ  ከስር ችሎታውን በቪዲዮ ተመልከቱት

አርሰናል daily fans page🇪🇹

03 May, 18:39


😳ስፐርስ በትናት ምሽቱ ጨዋታ በቼልሲ ከተሸነፈ በኋላ የዋንጫ ተፎካካሪዎቹ በተለይም የማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎች ከትናንቱ የቶትንሃም ሽፈት በኋላ

"ይህ ቶትንሃምን ነው የአርሰናል ደጋፊዎች ሲቲን እንዲያሸንፍ  የሚጠብቁት ከወዲሁ እርማችሁን አውጡ ተስፋ ያረጋችሁት በዚህ ቶተንሃም ከሆነ፣ እንግዲያውስ ማንችስተር ሲቲ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ አሸንፈናል እያሉ ነው  😁🙌"

😳የሲቲ እና አንድ አንድ አርሰናል ጠል ለሆኑ ክለቦች የተወሠነ ነገር ላስታውሳቸው ወደድኩኝ በትናንቱ የቶትንሃም ሽንፈት ሲቲ በቃ ዋንጫውን በላው ለሚሉ የረሡትን ነገር ላሥታውሳቸው ተከተሉኝማ 👀👇

↪️ባለፈው የውድድር ዘመን ኒውካስል ቶተንሃምን 6-1 በሆነ ሠፊ ውጤት ከጨዋታ ብልጫ ጋር አሸንፎት ቶትንሃም ከዚህ መራራ ሽንፈት ለማገገም ግዜ ሳይወሥድበት በሜዳው ማንችተር ሲቲን አሥተናግዶ ስፐርስ ማን ሲቲን 1-0 ማሸነፉን የሲቲ ደጋፊዎች እና አንድ አንድ አርሰናል ጠል የክለብ ደጋፊዎች ያለፈውን አመት ቢረሡትም ፔፔ ጋርዲዮላ እና የሲቲ ተጫዋቾች ግን መቼም አይረሡትም

↪️በዚህ ሲዝን  ኒውካስትል ቶተንሃምን 4-0 አሸንፏል ??????

😳ባለፈው የውድድር አመት አርሰናል ቶተንሃምን 2-0 አሸንፎታል  ነገር ግን ስፐርስ አሁንም በአርሰናል ሽንፈት ሳይደናበር  ማን ሲቲ አሸንፏል 💁🏾‍♂️

🤞በዚህ ሲዝን; አርሰናል ስፐርስን 3-2 አሸነፈ ??????

ቼልሲ እና ሊቨርፑል ሁሌም የቶተንሃም ቅዠት እንደሆኑ ሁላችንም እናውቃለን መለስ ብላችሁ የቸልሲ እና የቶትንሃምን ያለፉ ጨዋታ ውጤቶችን መመልከት በቂ ነው ሊቨርፑልም ስፐርን በገጠመበት ጨዋታ ያን ያህል ሲቸገር አንመለከተውም ስለዚህ ቶተንሃም በቸልሲ አልያም በአርሰናል በተከታታይ መሸነፍ ከሲቲ ውጤት ጋር ምንም አይገናኝም በቸልሲ እና አርሠናል መሸነፍ ለእነሱ ትልቅ ነገር አይደለም።

😳ይህ ሲዝንም ካለፉት ሲዝኖች  ያን ያህል የተለየ አይደለም ቶትንሃም በአርሰናል ተሸነፈ በቸልሲ ተደገመ ስፐርሶች ሁሌም ለፔፔ ጋርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ ቅዠት የሆነ ቡድን ስፐርስ ነው ቀልድ ሊመስላችሁ ይችላል አርሰናል ቀሪውን ጨዋታ የራሱን የቤት ሥራ በአግባቡ ይወጣ እንጂ ማንችስተር ሲቲ ነጥብ መጣሉ አይቀርም ሌላው ቢቀር  ማን ሲቲ በቶተንሃም ሆትስፐር ስታዲየም ሶን-ሄንግ-ሚን  በአንድ እግሩ ቢጫወት እንኳን ቶትንሃም ስታድየም ላይ ሲቲ ይሸነፋል 😂 🤳

አርሰናል daily fans page🇪🇹

03 May, 16:56


🇬🇬ቤን ዋይት - 26 ዓመቱ
🇩🇪Kai Havertz - 24 ዓመት
🇬🇬Declan Rice - 25 ዓመት
🇳🇴ካፒቴን ማርቲን Ødegaard - 25 አመቱ
🇧🇷ገብርኤል ማርቲኔሊ - 22 ዓመቱ
🇹🇯Jakub Kiwior - 24 Ars
🇬🇬ቡካዮ ሳካ - 22 ዓመት
🇫🇷ዊሊያም ሳሊባ - 22 ዓመቱ
🇧🇷Gabriel Magalhaes - 26 ዓመቱ
🇳🇱Jurrien Timber - 22 ዓመቱ
🇵🇹ፋቢዮ ቪዬራ - 23 ዓመቱ
🇬🇬ሪስ ኔልሰን - 24 ዓመቱ
🇬🇬ኤዲ ንከቲያ - 24 አመቱ
🇪🇸ዴቪድ ራያ (ከፈረመ) - 28 አመቱ
🇬🇬ስሚዝ ሮው 22 አመቱ
🇯🇵Takehiro Tomiyasu - 25 ዓመት
🇬🇬አሮን ራምስዴል (ከቆየ) - 25 ዓመቱ

ልምድ ጠገቦቹ
🇮🇪ጆርጂኒሆ
🇧🇷ገብርኤል ጂሰስ
🇹🇩ሊዮ ትሮሳርድ
🇬🇭 ቶማስ ፓርቴ
🇺🇦 ዚንቼንኮ

ልምድ ጠገቦቹን ትተን ከላይ ያሉት የአርሰናል የመጪው ዘመን የስኬት ቁልፎች እነዚህ ተጫዋቾች አሁንም በአርሰናል ቤት ቢያንስ 3 አመት የሚያቆያቸው ኮንትራት አላቸው።

↪️ከዴቪድ ራያ በስተቀር እሡም ቢሆን ለበረኛ 28 አመት ገና ወጣር እንደሆነ ይቆጠራል ከዛ ውጪ ሁሉም ከ22-26 አመት እድሜ ክልል የሚገኙ ሮጠው ያልጠገቡ በክህሎት የዳበሩ እርሥ በእእሥ የሚተሳሰቡ እና የሚዋደዱ ተጫዋቾች ናቸው።

በዚህ በመጪው ክረምት ወጣቱ አለቃ ለሚመራቸው ወጣት ክዋክብቶቹ ከፊት መሥመር ላይ ሻርፕ የሆነ አጥቂ የዴክላን ራይስ አጣማሪ እና የሳካ ሁነኛ ቤንች የምናሥፈርም ከሆነ እዚህ እምቅ ሃይል እና ባለክህሎት ወጣት ሥብሥብ ላይ ጥቂት አዲስ ተጨማሪ ተጫዋች ብናመጣ ፣

💪አርሰናል በቅርብ በእርግጠኝነት ፕሪሚየር ሊጉን (እና አውሮፓ ሻምፒዮንሥ ሊግን ) ለመቆጣጠር ማንም ሃይል አያግደውም

↪️አርሰናል በዚህ ስብሥብም ዘንድሮ ለሊጉ ዋንጫ እየተፋለመ ይገኛል ለዚህ ሥብሥብ ከፍተኛ ክብር እና ፍቅር ይገባቸዋል
💯 T R U S T T H E P R O C E S S💯

አርሰናል daily fans page🇪🇹

02 May, 14:15


🇧🇷ብራዚላዊው ኮከብ ጋብርኤል ጄሱስ ከአርሰናል ኦፊሻል ቲቪ ጋር አጭር ቆይታ አድርጎ ነበር ጋቢ በዛሬው ቃለመጠይቅ የተናገራቸው ዋና ዋና ነጥቦችን እናጋራችሁ

🗣ጋብሪኤል ጄሱስ በአርሰናል ቤት ደስተኛ ነው ፤ እናም ጄሱስ ለቦታው መፋለም እና በአርሰናል ቤት ተጨማሪ አመታትን መቆየት እንደሚፈልግ ተናግሯል ።

🗣ጋብሪኤል ጄሱስ ለአርሰናል ደጋፊዎች መልዕክት አስተላልፏል !

" እባካችሁ ደጋፊዎቻችን እኛን መደገፍ እና በእኛ ማመናችሁን ቀጥሉ ፤ አንዳንድ ጊዜ ነገሮች ባይሳካ እንኳን መደገፋችሁን ቀጥሉ ፤ ምክንያቱም እግርኳስ ውስጥ ማሸነፍ እና መሸነፍ ያጋጥማል።

" እኛ እናንተን ለማስደሰት ጠንክረን እየሰራን ነው ፤ ዋንጫውን ለማሸነፍ እየታገልን እንገኛለን ፤ ያለፈው አመት አሳዛኝ ነበር ፤ በዚህ አመት ዋንጫውን ለማሸነፍ እንፋለማለን ፤ ዘንድሮ ባይሳካ እንኳን የሚቀጥለው አመት ለማሳካት እንሰራለን ፤ በጣም አስፈላጊው ነገር የናንተ ድጋፍ ከእኛ አለመለየቱ ነው።" ሲል ተናግሯል ።

🗣ጋብሪኤል ጄሰስ ስለ ካይ ሃቨርትዝ፡

“እዚህ ሁሉም ሰው ብቃት እና መጫወት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ያውቃል፣ እና ካይ ብቃት ያለው እና ጥሩ እየተጫወተ ሲሆን ጎሎችንም አስቆጥሯል።

አሰልጣኙ በእሱ ያምናል እና ይህ ለተጫዋቹ  በጣም አስፈላጊ ነው መጀመሪያ ላይ ለእሱ ቀላል አልነበረም ነገር ግን ደግፈነዋል እና አሁን ፊቱ ላይ በፈገግታ እየተጫወተ ነው።

🗣ጋብሪኤል ጄሱስ ስለ ማርቲኔሊ

🗣“ጋቢ [ማርቲኔሊ] ገና 22 ዓመቱ ላይ የሚገኝ ተጫዋች ቢሆንም እድገቱ አሥገራሚ ነው ጋቢ በዚህ እድሜው አገሩን ወክሎ በአለም ዋንጫው በትልልቅ ደረጃዎች ተጫውቷል እናም ጠንክሮ እየሰራ እና አሁን ካለው ብቃት እየተሻለ እንደሚያሳይ  ተስፋ አደርጋለሁ። እሱ ማሽን ብለው ይቀላል ከኳስ ጋርም ያለ ኳስም ፈጣን ነው ከቡድን ጓደኞቹ ጋር ተናቦ መጫወት ተክኖበታል አሁን ያለበትን መንገድ እንደማይለውጥ ተስፋ አደርጋለሁ።"

🗣ገብርኤል ጄሱስ ስለ ሚኬል አርቴታ፡

🗣“እሱ የትለየ ሰው ነው ኦህ ከቦስ ብዙ ነገር  ተምሬአለሁ ከእሱ ጋር ላለፉት ሰባት ዓመታት በላይ አውቀዋለሁ። ማንቸስተር ሲቲን ለቆ ከእኔ በፊት ወደ አርሰናል ሲመጣ ሶስት አመት የተለያየን ቢሆንም በእሱ ትልቅ እምነት ስላለኝ ዳግም አብረን አርሰናል ቤት አብረን እንገኛለን ከማይክል ብዙ ተወርተው የማያልቁ ጥሩ ትምህርቶችን ተምሬያለው።"

🗣“ከእሱ ጋር በሲቲ ቤት ለሶስት ሲዝኖች አብረን ነበርን  ከእኔ ጋር ብዙ ስራዎችን ሰርቷል፣ ከዚያም እዚህ መጣሁ። እሱ ያውቀኛል እኔም በደንብ አውቀዋለሁ። ከዚህ በፊት ብዙ ረድቶኛል እና አሁን እየረዳኝ ነው።"

🗣ገብርኤል ጄሱስ በአርሰናል ቤት ከሳካ ማርቲኔሊ ጋር ሥላለው ጥምረት

🗣 በራሱ፣ ቡካዮ ሳካ እና ገብርኤል ማርቲኔሊ መካከል ስላለው ኬሚስትሪ፡

🗣“እንደ እድል ሆኖ በዚህ የውድድር ዘመን አንድ ላይ ብዙ ጨዋታዎች ላይ አልተጫወትንም፣  በዋናነት እኔ ያጋጠመኝ የተወሰነ የጉዳት ችግሮች እንዲሁም በተወሰነ መልኩ  ጋቢ አንዳንዴም እንዲሁ በጉዳት ምክንያት እንደ እንድል ሆኖ ብዙ ጨዋታዎች ላይ አልተጫወትንም።"

🗣"ያለፈው የውድድር ዘመን አብረን በርካታ ጨዋታዎች ላይ አንድ ላይ ተጫውተናል የሶስታችን ጥምረት እና ግንኙነቱ በጣም ጥሩ ነበር ያለፈው ሲዝን ብዙ ነገር ማሳካት ነበረብን እውነት ለዚህ ደጋፊ ብዙ ክብሮች ይገባቸዋል ይህንን  ባለማሳካታችን ሁሌም ይጸጽተኛል።"

🗣" አንድ ላይ ሥንሠለፍ በብዙ ነፃነት እና እንቅስቃሴ ተጫውተናል፤ ይህ ጥምረት ተመልሰን አብረን መጫወት እንደምንችል ተስፋ አደርጋለሁ ምክንያቱም ሜዳው ላይ ሶስታችንም በተለየ መልኩ እንግባባለን እንረዳዳለን ወደ ፊት ዳግም  የምንጣመርበት በርካታ ጨዋታዎች ይኖሩናል።"

አርሰናል daily fans page🇪🇹

29 Mar, 14:38


🔜 | ቀጣይ ጨዋታ | 🔛

🔥የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ 🤌

 🔴 ማንችስተር ሲቲ  🆚  አርሰናል

የጨዋታው ቀን ፦ | እሁድ

የጨዋታ ሰአት ፦⌚️| 12:30

የጨዋታ ሜዳ ፦ 🏟️ | ኢትሃድ ስታድየም

መልካም እድል ለታላቁ ክለባችን አርሰናል !

👉 ክለባችን አርሰናል እሁድ በኢትሃድ ስታድየም ላይ የሳምንት ታላቅ  ጨዋታ ከሲቲ ጋር ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ይጫወታል ከእሁዱ ወሳኝ ጨዋታ በፊት አለቃ ሚካኤል አርቴታ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል ቦሥ በዛሬው መግለጫ ካነሳቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል ይዘንለችሁ ቀርበናል እናንተም እንደተለመደው አብሮነታችሁን በላይክ ሀሳብ አሥተያየታችሁን በኮሜንት እንዲሁም ይህ መረጃ ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ማረጋችሁን አትርሱ 🖐

👉 አለቃ አርቴታ በዛሬው መግለጫ

ስለ ቡድናችን የጤና ሁኔታ
ሥለ ማጋሌሽ
ሥለ ሳካ
ስለ ማርቲኔሊ
ሥለ ቤን ዋይት
ስለ ተጫዋቾቹ
ስለ ጨዋታው አሥፈላጊነት
ስለ ፔፔ ጋርዲዮላ
ስለ ነገው ተጋጣሚው
   🎤 ዛሬ በሠጠው መግለጫ ላይ ከተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች መካከል ይገኛሉ እኛም ለእናንተ በሚመች መልኩ ብለን የአሥልጣኛችንን መገለጫ እንደሚከተለው ይዘንላችሁ ቀርበናል 👇👇

🗣አርቴታ ስለ ማጋሌሽ ሳካ እና ማርቲኔሊ

ጋብሬል ማጋሌስ ፣ ሳካ እና ማርቲኔሊ ትናንት ከቡድኑ ጋር ልምምድ አልሰሩም ፤ ቢሆንም ግን ለእሁዱ ጨዋታ እንደሚደርሱ ተስፋ አለኝ ። ሲል ተናግሯል ።

🗣• || ሚኬል አርቴታ ስለ ቤን ዋይት :-

"ሀገሩን በተቻለው መንገድ ለመወከል አንድ ቀን ዝግጁ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።"

🗣አርቴታ ስለ ጋርዲዮላ

" ፔፕ ጋርዲዮላ የአለማችን ምርጡ አሰልጣኝ ነው።" ሲል ተናግሯል ።

🗣◾️• ||ሚኬል አርቴታ ሥለ አርሰናል ተጫዋቾች

"በተጫዋቾችን ላይ ሙሉ እምነት አለኝ በሜዳ ላይ ማሳየት ያለብን ነገሮች አሉ።"

🗣◾️|| አርቴታ ስለጨዋታው አስፈላጊነት :-

"ለሁለቱም ቡድኖች ትልቅ ጨዋታ ነው እዚያ ሄደን ካሸነፍን እንደገና ትልቅ መነቃቃትን ይሰጠናል ጨዋታውን  ለማሸነፍ  ብዙ መንገዶች አሉን።"
አርቴታ በጨዋታው አስፈላጊነት ላይ: "ለሁለቱም ቡድኖች ትልቅ ጨዋታ ነው. ወደዚያ ሄደን ካሸነፈን እንደገና ትልቅ መነቃቃትን ይሰጠናል.

🗣አርቴታ ካለፈው ጊዜ በተሻለ አርሰናል ወደ ሲቲ ሲያመራ የበለጠ በራስ መተማመን ስሜት ካለው "በተጫዋቾቼ ላይ ሙሉ እምነት እና ምን ለማድረግ እየሞከርን እንደሆነ። በሜዳ ላይ ማሳየት ያለብን ነገር ነው"

🗣አርቴታ ከአለም አቀፍ ቡድኖች ጋር ስላለው ግንኙነት፡ "ከብሄራዊ ቡድኖች ጋር የተቻለንን ግንኙነት ለማድረግ እንሞክራለን ነገርግን በመጨረሻ ተጫዋቾቹን የመምረጥ እና የመጠቀም አቅም አላቸው።ሁልጊዜም ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ይሰማኛል።

👍         📝          📌       👉
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳ