Lemi kura Communication

@lemikuracom


Lemi kura Communication

24 Jul, 12:19


በ2ኛ ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ጥናት ላይ ውይይት ተካሄደ

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በምዕራፍ ሁለት የኮሪደር ልማት ጥናት ላይ ከክፍለ ከተማ አጠቃላይ እና ከወረዳ የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ከሚመለከታቸው አመራሮች ጋርም ውይይት አካሄዷል።

ጥናቱ በተመረጡ አምስት ኮሪደሮች ላይ የተከናወኑ ሲሆን እነሱም
👉 ከጎሮ አደባባይ እስከ 72 አካባቢ
👉ከሲሚት ለስላሳ ፋብሪካ እስከ ፍየል ቤት
👉ከሲ ኤም ሲ አደባባይ እስከ ከፍየል ቤት
👉ከፊጋ እስከ ሳሊተምህረት እንዲሁም
👉 ከሲ ኤም ሲ አደባባይ እስከ ደራርቱ አደባባይ እንደሆነ በውይይቱ ተገልጿል።

ይህን የውይይት መድረክ የመሩት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ገመቹ እንዳሉት በመጀመሪያው የኮሪደር ልማት ስራ የተሠሩ በርካታ ስኬታማ ስራዎችን እንደ ምርጥ ተሞክሮ በመውሰድ አመራሩ በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ውይይትም ከህብረተሰብ እንዲሁም ከተቋማት ኃላፊዎች ጋር በተናጥልም ሆነ በጋራ ማድረግ እና መግባባት ያስፈልጋልም ሲሉ ተናግረዋል። የቀጣይ አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ /ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር በበኩላቸው ከላይ የተሠጡ አቅጣጫዎችን ተቀብሎ ወደ ተግባር በመግባት የተሻለ የስራ አፈፃፀም ማስመዝገብ ያሻል ሲሉ አያይዘውም አመራሩ በቁርጠኝነት ወደ ስራ ገብቶ ተግባሩን እውን ማድረግ አለበት ብለዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስጨንቅ ብርሃኑ እንዳሉት በመጀመሪያው ምዕራፍ ያገኘናቸውን ልምዶችና ተግባራት በላቀ ትጋት በሁለተኛው ምዕራፍ በመድረገም ውጤታማ ስራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የለሚ ኩራ ኮሚኒኬሽን
ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም

Lemi kura Communication

24 Jul, 09:36


አስደማሚ ውበት በለሚ ኩራ የኮሪደር ልማት