KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

@kmuelearning


Kotebe University of Education Community / አዲስ ነገር መረጃ /

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

15 Oct, 13:32


https://www.linkedin.com/posts/saheedkolawole_65-ongoing-fully-funded-scholarships-for-activity-7250823357074489344-HNls?utm_source=share&utm_medium=member_android

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

15 Oct, 13:05


መስማት ለተሳናቸው የሬሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ
****
(ኢ ፕ ድ)

በ2016 ዓም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው በመንግስት ተቋማት የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የማለፊያ ውጤትን ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት፤

👉 የተፈጥሮና ማሕበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከስድስት መቶ 192፣

👉 የተፈጥሮ እና ማሕበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከስድስት መቶ 186፣

👉 በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ እና ማሕበራዊ ሳይንስ ወንድ ከሰባት መቶ 224፣

👉 በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮና ማሕበራዊ ሳይንስ ሴት ከሰባት መቶ 217 እና በላይ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓም

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

12 Oct, 23:51


Channel name was changed to «KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /»

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

12 Oct, 23:45


https://www.linkedin.com/posts/saheedkolawole_it-is-the-application-period-for-fall-2025-activity-7250426640499982336-E-nO?utm_source=share&utm_medium=member_android

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

12 Oct, 11:56


https://www.linkedin.com/posts/scholarshippk_1-mcgill-university-scholarships-in-canada-activity-7249629764339073024-nvOG?utm_source=share&utm_medium=member_android

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

12 Oct, 06:51


https://www.linkedin.com/posts/mitiku-k-kayamo_bmtblhblzbnmbmtbpkbqdbph-bmtblhblzbnmbmtbpkbqdbph-activity-7250594271391539200-7_dX?utm_source=share&utm_medium=member_android

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

12 Oct, 06:49


https://www.linkedin.com/posts/dagemworku_apply-bloblz-scholarship-activity-7249701833223417857-N8c-?utm_source=share&utm_medium=member_android

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

10 Oct, 05:57


https://opswatacademy.com/introduction-critical-infrastructure-protection?utm_source=Facebook&utm_medium=ICIP+-+Free+Course+Program+-+Oct%2724&utm_campaign=TopCount&utm_term=Cybersecurity+related&utm_content=Post+1+-+Urge+users+to+enroll+the+free+course+-+Square+-+Use+existing+post&fbclid=IwZXh0bgNhZW0BMAABHRTORa5Q7RxHE1J1HRLogT2Cj9xYBLFfoXasNGnjWAtHx1McUYHkZQLkLw_aem_gdQzknpsn7f_qSrPLhjIQg&utm_id=120211540502430497

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

10 Oct, 05:54


https://www.facebook.com/share/dLZ7BGTyGJbnGBN4/?mibextid=xfxF2i

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

09 Oct, 23:38


https://www.facebook.com/share/Bg84GajJdYSuMsp4/?mibextid=oFDknk

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

09 Oct, 23:27


በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሚካሄዱ ምርምሮች የዩኒቨርሲቲውን ተልዕኮ ማዕከል ያደረጉ መሆን እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡


“A Training on “Thematic Research: Concepts and Practices” በሚል ርዕስ ዛሬ መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣ ለዩኒቨርሲቲው መምህራን የተሰጠውን ስልጠና በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና፣ በዩኒቨርሲቲው የሚካሄዱ ምርምሮች የዩኒቨርሲቲውን አዲሱ ተልዕኮ እና የሀገራችንን የትምህርት አቅጣጫዎች ማዕከል ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ ምርምሮቹ በተለይ የሀገሪቱን የትምህርት ጥራት ችግር መንስኤዎች፣ ተግዳሮቶች የሚለዩ እና ተጨባጭና ተተግባሪ መፍትሔዎችን የሚያፈልቁ ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ስልጠናውን የሰጡት፣ በትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች ተጠባባቂ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሠራዊት ሀንዲሶ፣ የመንግስትን የጥናትና ምርምር ዋና ዋና ትኩረቶች፣ ለጥናትና ምርምር የተለዩትን ጭብጦች፣ የተቀመጡ ማዕቀፎችን እና አሠራሮችን አብራርተው፣ ከዚህ አንጻር የሚካሄዱት ምርምሮች የሀገሪቱን የትምህርት ችግሮች በሚፈታ መልኩ የተደራጁና ተገቢውን ጥራት ያሟሉ ሊሆኑ እንደሚገባ ጠቁመው፤ ይህንንም ለማሳካት ለምርምር የሚውልን በጀትና ሀብት ሀገራዊ ጠቀሜታ ባላው መልኩ መጠቀም፣ ምርምሮችን በጋራ መስራት እና ከዩኒቨርሲቲው ሀገራዊ ተልዕኮ ጋር ማቀናጀት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

08 Oct, 17:19


https://www.facebook.com/100064682287722/posts/pfbid0BTzWwrpa4FS53Svbk47RNhTEnoiHwnGFguPojVFCvMpcxchkSLu5ogiUojp7vXVQl/?mibextid=CDWPTG

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

08 Oct, 13:42


ትውልድ የሚገነባው እንደዚህ የተሻለ የሠራውን የበለጠ እንዲሠራ፤ የደከመው ቁጭት እንዲፈጥር እየተደረገ ሲኮተኮት ነው። ላለፉት ሙሉ ጊዜያቸውን ሳያባክኑ ዕውቀት ለመሸመት ያዋሉ፣ የትምህርት ቤታቸውን አመራር እና መምህራኖቻቸውን የሠሙ፣ የቤተሰባቸውን ከእነሱ ጋር ዋጋ መክፈል ለውጤት ያበቁ፣ እነዚህ በዕውነት ክብር ይገባቸዋል። ምንም ነገር ሳያዘናጋቸው "ለምን ይሄ " ብለው ተመራምረው ከፊሉን ደፍነው ከፊሉን ሰቅለው በዓመቱ ብሔራዊ ፈተና እጅግ የላቀ ውጤት አስመዝግበው የዩኒቨርሲቲውን ትምህርት ቤት ብሎም የከተማውን ስም ያስጠሩ ናቸውና በመሸለማቸው ደስ ብሎናል ።
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮም ክትትላችሁን፣ ድጋፋችሁን እና የላቀ ውጤት ያመጡ ትጉኃንን መሸለማችሁ ነገ ሺዎች ተሸላሚዎችን ለመፍጠር አነሳሽ ከመሆኑም በላይ የነገን ትውልድ ዛሬ እየተከላችሁ ነውና ሥራችሁ አኩሪ ነው ። ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነችን፣ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱን እና ማናጅመንታቸውን ላደረጉት ሞራል ገንቢ ማበረታቻ በራሴ እና በዩኒቨርሲቲው ማናጅመንት ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር )
ፕሬዚዳንት

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

03 Oct, 10:24


እንኳን ለእሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የመልካ ወይም የሆራ እሬቻ በገዳ ሥርዓት መሠረት ክረምት አልፎ መስከረም ሲጠባ የሚከበር የምስጋና በዓል ነው፡፡ እሬቻ የእርቅ፣ የሰላም፣ የፍቅር፣ የህብረትና የአንድነት ተምሳሌት ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ያለ ምንም ልዩነት ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድም እህቶቹ ጋር በአንድነት ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል
የብዝሃነታችንም መገለጫ ነው፡፡
ስለሆነም ለመላው ህዝባችን እንኳን ለእሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ፤ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ፣ የህብረት እና የአንድነት እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ!

ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር)
የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

Baga Ayyaana Irreechaaf Nagaan Geessan!*
🤝🤝🤝🤝🤝🤝🤝
Irreechi Horaa bu’uura sirna Gadaatiin yeroon gannaa darbee birraan bari’u kan ayyaaneffamu ayyaana galataati. Irreechi Araara,
Nagaa, fakkii gamtaa fi tokkummaati. Uummanni Oromoo garaagarummaa tokko malee Obboleeyyan isaa uummata
Itoophiyaa mara waliin kan ayyaaneffatu ayyaana woliiniiti.

Kanaafuu ummatni keenya marti baga ayyaana Irreechaatiin nagaan isin gahe jechaa, Ayyaanni kun kan naga’aa, kan
jaalalaa, Kan gammachuu, akka nuuf ta'un hawwa.

Dr. Birhaanamasqal Xannaa
Pirazidaantii Yuunivarsiitii Barnootaa Kotobee

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

02 Oct, 08:18


#Dv_ሎተሪ ዛሬ መስከረም 22/2017 ይጀምራል
የአሜሪካ diversity visa ወይንም DV ሎተሪ ይጀምራል።
አንደኛ

ማንኛውንም የሚሞላ ሰው የግድ 12ኛ ክፍል የጨረሰ መሆን አለበት። ወይንም በትንሹ 2 አመት በፈጀ ስልጠና ወይም ትምህርት ካለፉት አምስት አመታት ሁለት አመታት የስራ ልምድ ያለው መሆን ይጠበቅበታል።

12 ያጠናቀቀ እና ያላጠናቀቀ ግን የሆነ ስልጠና ይወስዳል ወይንም ትምህርት ለምሳሌ ላብራቶሪ ተማረ እንበል ትምህርቱን በአንድ አመት ቢጨርስ ለdv አይሆንም። ነገር ግን በትንሹ ሁለት አመት ቢማር መስፈርቱን ያሟላል ይህም ማለት አንድ ሰው ትልቅ ፋብሪካ ጥገና ቢሰራ ጥገናውን ግን ለመማር 6 ወር ወይንም አመት ቢፈጅበት መስፈርቱ በትንሹ 2 አመት የስልጠና እና ትምህርት ጊዜ ስለሚል ውድቅ ይደረጋል።

2 እና ከዛ በላይ አመት የተማረ ከሆነ ደግሞ ባለፉት 5 አመታት ማለትም ከ2011-2016 ባለ ጊዜ ውስጥ ስራ ላይ የነበረና 2 አመት ያገለገለ መሆን አለበት።

የተፈቀዱ የስራ አይነቶችን ለማወቅ በኤምባሲው የተቀመጠውን ጥቆማ

onetonline.org ድህረገፅ ላይ በመግባት Job family ሚለውን ተጭናቹ የስራ ዝርዝሮችን ማየት ይቻላል።

#ሁለተኛ

አመልካቾች የግድ 18 አመት የሞላቸው መሆን አለባቸው። ፎርሙንም አንዴ በትክክል ሞልቶ submit ማድረግ ማስገባት ሲገባ የተደጋገመ ሙሌት በመስሪያ ቤታቸው ቴክኖሎጂ ስርአት ውድቅ የሚደረግ ይሆናል።

እዚህ ጋር submit ብለነው ቀይ ምልክት እና ያልተሟላ መረጃ እንዲሁም እንዳልተቀበለን ካሳወቀን መስፈርቶችን እያሟሉ እና እያስተካከሉ ደጋግሞ መሙላት ይቻላል ያልተፈቀደው ከተቀበለ በውሃላ የሚደረጉ ድግግሞሾችን ነው።

ተቀብሎ submit ካደረገ በውሃላ ራሱ confirmation code ካልተሰጠን ስላልተመዘገብን ጥቂት ከጠበቅን በውሃላ ዳግም መሞከር ይቻላል። ቁጥሩን ካገኘን በውሃላ ግን ዳግም መሞከር ውጤታችን ውድቅ እንዲደረግ ያደርጋል።

#ሶስተኛ

ባለትዳር የሆኑ ሰዎች የግድ ባልም ሚስትም ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ካሟሉ የተለያየ ወረቀት በየግል መሙላት ይችላሉ ካላሟሉ ግን የሚያሟላው ባልም ይሁን ሚስት ቅፁን ከሞሉ በውሃላ ሌላኛውን በጥገኛ ማስመዝገብ ይችላሉ። ሚስትና ልጆች ወይንም ባልና ልጆች የግድ ስማቸው መሟላት አለበት።

ልጆቹ ያላገቡ እና እድሜያቸው ከ21 አመት በታች መሆን አለበት ይህ DV እስከሚሞላበት ቀን ድረስ።

#አራተኛ

አንድ አመልካች በሌላ መንገድ ወደአሜሪካ ለመግባት እየሞከረ ከሆነ በትምህርት ፣ በጤና ፣ በፖለቲካ ጥገኝነት ተመዝግቦ ጉዳዩ በሂደት ላይ ያለም ቢሆን DV መሙላት እና የነፃ እድሉ ተጠቃሚ መሆን ይችላል። DV እድል በነፃ ቢሆንም እድለኞች ከደረሳቸው በውሃላ ወደአሜሪካ ለመሄድ የቪዛ ክፍያ መፈፀም አለባቸው።

ፎርሙንም ማንኛውም ሰው ለሌላ ሰው መሙላት ሲችል ሂደቱ እንደተጠናቀቀ መመዝገቡን ለማረጋገጥ

dvprogram.state.gov ላይ በመግባት check status የሚለውን በመጫን የሚሰጠውን የወረቀት ቁጥር ተጠቅሞ ማረጋገጥ ይችላል።

#አምስተኛ

አሸናፊዎች ከላይ ባለው ሊንክ ማለትም በ dvprogram.state.gov በመግባት የDV አዘጋጅ የሃገሪቱ ስርአተ-ክፍል ሰዎችን በማንኛውም መንገድ ለማግኘት አይሞክርም ( email , facebook , telegram) በመሳሰሉት የእንኳን ደስ አላቹ መልእክት አይልክም።

በመሃል confirmation code ቢጠፋባችሁ ባስገባችሁት email አድራሻ የመለያ ኮዱን እንዲልክላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።

#ስድስተኛ

ፎቶ ፎቶቤት መነሳት የምትችሉ ሲሆን ምንም አይነት ፈገግታ ፣ የፀጉር መገልገያ (ሻሽ መሰል ጨርቆች) ፣ የአይን መነፅር ፍሬም አይንን መከለል የለበትም ፣ የጆሮ ጌጦች የማይፈቀዱ ሲሆን ለdv የምትጠቀሙት ፎቶ አሁናዊ ሁኔታችሁን ለማወቅ እንዲረዳ ቢበዛ ከስድስት ወር ወዲህ የተነሳቹት ፎቶ መሆን አለበት። scan ድደርጋችሁ የምትጠቀሙ ከሆነ ለማስተካከል

123passportphoto.com/upload_photo.php

ድህረገፅን መጠቀም ትችላላችሁ።

ባለፉት አምስት አመታት ከ50 ሺህ በላይ ዜጎቻቸውን በማስወጣት በ2025 የDV ሎተሪ ቻይና ፣ ናይጄሪያ ፣ ፓኪስታን ፣ ባንግላዲሽ ፣ ቻይና ፣ ደቡብ ኮሪያ ፣ ቬትናም ፣ ሜክሲኮ ፣ ቬንዙዌላ ፣ ጃማይካ ፣ ሆንዱራስ ፣ ኮሎምቢያ ፣ካናዳ እንዲሁም ብራዚል ያልተፈቀደላቸው ሃገራት ናቸው።

DV 2026 55,000 ( ሃምሳ አምስት ሺህ) እድለኞችን ይቀበላል

መልካም እድል!

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

26 Sep, 15:11


ኢትዮጵያዊን በአንድነት ተሰብስበው ለሚያከብሩት የደመራ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ !

#መልካም_በዓል

KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /

26 Sep, 10:32


http://t.me/MIDROCINVESTMENT