GURAGE KINGDOM

@selam_zegurage


ሃሳብ ፣አስተያየት፣ መረጃ ካሎት በዚህ በዚህ bot ያግኙን @Kurat21

GURAGE KINGDOM

22 Oct, 17:04


መርካቶ እንዴትና ለምን እንደተቃጠለ ለማወቅ የፎረንሲክ ምርመራ ማድረግ ሳይሆን የኮሪደር ልማቱ አካል መሆኑ ማወቅ ተገቢ ነው👌

GURAGE KINGDOM

22 Oct, 16:59


መርካቶ በአጋጣሚ ላለመቃጠሉ ለማወቅ መልአክ መሆን አይጠበቅብንም👌

GURAGE KINGDOM

21 Oct, 21:27


መርካቶን እሳት በላው 😰😥
።።።። ።።።።። ።።።
አዲስ አበባ ላይ ለጉራጌ የቀረው መገለጫ መርካቶ ብቻ ነበር እሱንም እንደቀልድ እሳት ሲበላው ከማየት በላይ ህመም ምን አለ 😭

በልማት ስም የስንቱ ጥሪት ሲወድምና ህዝቡንም ተስፋ ቢስ ሲሆን ማየት የእለት ኑሮአችን ባደረግንበት በዚህ ወቅት መርካቶ ላይ የተነሳው እሳት የአጋጣሚ ነው ቢሉን እንዴት ውስጣችን አምኖ ሊቀበለው ይቻለዋል 😭😭

GURAGE KINGDOM

21 Oct, 21:00


የፍልሚያችን ውጤት

         * * *
ጭቆናን ለማክሰም
ያለአንዳች መታከት፥ በብርቱ ብንተጋም
አርነት ለመውጣት
በፅኑ ተጋድለን ፥ጡንቻችን ቢዝልም

ከፍልሚያችን ማግስት፦
የተቀናጀነው፥ የመራብ ነፃነት
ማሳካት የቻልነው ፥የመታረዝን መብት
ሃብታችን የሆነው ፥የህመም ክምችት
የተማርነው ጥበብ፥ ሳይደክሙ መፎከት።

በመፋለም ብዛት፥ ቀድሞ የታነፀው፥ ስለፈራረሰ
ከልብ ምንጫችን ላይ፥ የሚፈልቀው ኹሉ ፥ስለደፈረሰ
ርቱዕ የነበረ ፥አንደበታችንም ፥ባ'ፍረት ተለጎመ
ከልባችን መዝገብ ፥ድል ማድረግ ተፍቆ፥ መሸነፍ ታተመ

GURAGE KINGDOM

21 Oct, 18:35


በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለማጥፋት ሄሊኮፕተር ለመጠቀም እየጣረ መሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ

GURAGE KINGDOM

19 Oct, 19:48


"ጥበብ ስትጠራኝ"
እኩለ ለሊት ላይ ስልኬ ይጮሃል እየተደናበርኩ አነሳዋለሁ::
ከጎረቤቶቼ አንዳቸው ናቸው:: "ውሀ መጥታለች" ማለት ነው:: እነሳና
በጀረኪናዎች: በባሊ:በመዘፍዘፊያ: በሳፋ :ወላ በድስት እቀዳና ለነገ
የሚበቃኝን ያህል ደሞ ጠጥቼ እተኛለሁ::
.
.
.
የቧንቧ ውሐና የተቀቀለ እንቁላል በቀን ካየሁ ቆየሁ::
.
.
.
ሰሞኑን ቀናት ሲያሻት ደሞ ሳምንት አልፋ የምትመጣው ውሀ
መጣች::እንደተለመደው ተነሳሁና ቀድቼ ተኛሁ::
ጠዋት ላይ ግን የቀዳሁት ውሐ ይሄን መስሎ ጠበቀኝ:ሌሎቹንም
እቃዎች አየኃቸው:: የደፈረሰና ቆሻሻ ውሐ ነበረ::
አሁን የቸገረኝ
- ዶ/ር አብይ አልቻለም ልበል?
-ዳውን ዳውን
- ብልፅግናውን ጓደኛዬ(ኩራትን) ጠርቼው የለውጡ ትሩፋት መሆኑን ይንገረኝ?
-ወይንስ ከወያነ ጓደኛዬ ጋ በምርጫ ካርዴ መሪዬን እንድመርጥና ንፁ
ውሃ እንድጠጣ እንማከር?
-ቆሻሻ ውሐ የደረሰን ጎረቤቶቼን ይዤ ክልል እንሁን ልበላቸው እንዴ?
ወይንስ ደሞ
- ጠብቄው ነበረ.....መምጣቱን እናፍቅና እጓጓ ነበረ.....
ሰው እንዴት አንድ ቀን እንኳን እሱን ሳያስብ የሚውልበት ቀን ይጠፋል?
ሲከፋኝ ፣ ስደሰት፣ ዝም ብዬ ብቻዬን ቁጭ ስል፣ ቤተክርስቲያን፣
መጠጥ ቤት፣ ፊልም ሳይ፣ ዘፈን ስሰማ .... በቃ ሁል ጊዜ ስለሱ
አስባለው:: አንድ ቀን ይመጣል ብዬ እመኝ ነበረ.....ሲመጣ ግን.....
ቆሽሾ ነበረ ምናምን ብዬ ጥበብ ትጥራኝ
አረረረረረረ ሼም ኦን ዩ ውሐና ፍሳሽ

GURAGE KINGDOM

16 Oct, 16:34


ታሪክን ወደኋላ
አስካለ ነጋ ቦንገር 

በ 1966ቱ አብዮት የወጣቶች ንቅናቄ ወቅት  የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሳለች ኢትዮጵያ ዜጎቿ በእኩልነት የሚኖሩባት የተሻለች ሀገር ለማድረግ ህልም ቋጥራ መስዋእት የከፈለች የነፃነት ሰማእት ናት።

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች በኢሕአፓ ስር ተድራጅተው ከወንድ ጓዶቻቸው ጋር ጎን ለጎን በመቆም የደርግ ፋሺስታዊ አገዛዝን በመቃወም የስርአትን ለውጥ ለማምጣት ታግለዋል ፤ እራሳቸውንም አሳልፈው ለትግሉ ሰጥተዋል።

ከእነኝህ እንቁና ጀግና ወጣቶች አንዷ አስካለ ነጋ ናት። በ 1966 ዓ.ም አስካለ ነጋ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በአራት ኪሎ ካምፓስ የሳይንስ ፋኩሊቲ ውስጥ በብዙ ጓደኞቿ "አስኩ" በመባል የምታወቀው አስካለ ነጋ ያኔ 2ተኛ አመትን ጨርሳ ወደ 3ተኛ አመት እየገባች ነበር።

የወ/ሮ አበበች ወ/ጊዮርጊስና የአቶ ነጋ ቦንገር ልጅ የሆነችው አስካለ በጓደኞቿ በጣም የምትወደድ፤ ተግባቢ በጣም ደግና እሩህሩህ እንደነበረች ብዙዎች ይናገራሉ።

በትምህርቷ በጣም ጎበዝ የነበረችው አስካለ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርቷን በአፄ ልብነድንግል የ 2ተኛ ደረጃ ትምህርቷን ደግሞ በመድሃኒዓለም ት/ቤት ካጠናቀቀች በኋላ በከፍተኛ ውጤት አልፋ ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እጅ የወርቅ ቀለበት ተቀብላ ፤ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ገብታ ተከታትላለች።

አስካለ በኢሕአፓነት ስትታገል ቆይታ በ 1970 መጨረሻ አካባቢ በአንጃዎች ጥቆማ ተይዛ ለእስር ስትዳረግ የድርጅቷን ሚስጥር ላለማውጣትና ጓዶቿን ለፋሺስት ደርግ አሳልፋ ላለ መስጠት cyanide...(መርዝ) በመዋጥ እራሷን በማጥፋት በጀግንነት ተሰውታለች። አስካለ የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ታላቅ እህት ነበረች።

GURAGE KINGDOM

16 Oct, 16:30


ጉራጌ ሁሉም ቆንጆ እኮ ነው ❤️

GURAGE KINGDOM

25 Sep, 14:49


ጉራጌዎች አባቶቻችን እንደጀመሩት የጉራጌ መንገዶች ስራ ድርጅት ህብረት ጉዞ ቀጥለን ቢሆን ኖሮ፣ ዛሬ ጊቤን በድልድይ ሳይሆን በአየር በተሻገርን ነበር!

መልካም የመስቀል በዓል ይሁንላችሁ!

GURAGE KINGDOM

25 Sep, 11:53


ለመስቀል ሀገር ቤት አይቀርም

የመስቀል በዓልን ለማክበር ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ወደ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ያቀኑ እንግዶች ድባብ

GURAGE KINGDOM

19 Sep, 22:52


አዲሳባ እየፈረሰች ነው። ደሰሳ ቤቶች "አዲሳባን አይመጥኑም" ተብለው እየፈረሱ ነው።

አዲሳባን ዘመናዊ ህንፃ ሳይሆን ደሳሳ ቤት ነው የሚመጥናት። ኢትዮጵያ የደሐ ሐገር ናት። አዲሳባ ደግሞ የድሆች መኖሪያ ነው። ሚሊዮኖ ድሆችን እያስተዳደሩ "የደሀ ቤት ከተማችንን አይመጥንም" ማለት አሳፋሪ ስላቅ ነው።

ደሳሳ ቤቶችን ማስወገድ መፍትሔ አይሆንም። ድህነታችንን የሚመጥነውን የደሐ ቤት ማፍረስ ትርፉ ሌላ መከራ ነው።

መፍትሔው የደሐውን ኑሮ ማሻሻል ነው። የደሐ ኑሮ ሲሻሻል ደሳሳ ቤቶች በራሳቸው ጊዜ በዘመናዊ ቤት ይተካሉ።

ቅድሚያ ለድህነት ቅነሳ ፖሊሲ!

GURAGE KINGDOM

18 Sep, 14:02


ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ (አባ መላ)
።።።።።።።።።።።።።።
ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲናግዴ የትውልድ አገራቸው ጨቦ ጉራጌ ነው፡፡ በአድዋ ዘመቻ ጊዜ በአሽከር ብዛትና በደግነት ሥራ በጣም የተመሰገኑት ሀብተ ጊዮርጊስ በ1889 ዓ.ም. ፊታውራሪ ተብለው የጦር አበጋዝነቱን ተሹመዋል፡፡

ለጃንሆይ አፄ ምኒልክ ታማኝ ነበሩና ዕለተ ሞታቸው ከጃንሆይ ዕለተ ሞት ጋራ በትክክል ስለተጋጠመ፣ ሰው ሁሉ እያደነቀ ተናገረ፡፡ አፄ ምኒልክ የሞቱት ዓርብ ታኅሣሥ ፫ 3 ቀን፲፱፻፮ 1906 ዓ.ም. ነበር፡፡
‹‹አባ መላ›› ፊታወራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ደግሞ በ፲፱፻፲፱(1919) ዓ.ም. አርፈዋል። ዓመታቱ ይለያዩ እንጂ ሁለቱም ያረፉት ዓርብ ታኅሣሥ ፫(3) ቀን ነበር።

ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ‹‹ጥቁር ሰው›› በሚለው አልበሙ ላይ
“ዳኘው ያሉት አባ መላ ፊት ሀብቴ ዲነግዴ፤
ሰልፉን በጦር አሰመረው ፊት ሆኖ በዘዴ።”
እያለ ዘፎኖላቸዋል ፡

" የኋላዉ ከሌለ የለም የፊቱ "

GURAGE KINGDOM

13 Sep, 17:21


#የቤተ-ጉራጌ ቋንቋዎች ለምን በዙ

#ስንትስ_ናቸው ( ደዌቺ ዘርማ)
      
ስለ ጉራጌ ቋንቋዎች ጉዳይ ሳስብ ጭንቅ ይለኛል።በርካታ ጉዳዮችም ያሳስቡኛል።ለሐሳቤ እውነተኛና ታሪካዊ ምላሽ ለማግኘት መፃህፍትን አገላብጥ ጀመር።የማነባቸው መፃህፍትም ከማናደድ ውጪ መፍትሔ ሊሆኑኝ አልቻሉም።
📚እንደሚታወቀው በቁጥር ብዙ የሆነው የኦሮሞ ህዝብ በቋንቋ ዘዬ ቢለያይም በአንድ ቋንቋ ይግባባል።በአንድ ቋንቋ ይተዳደራል።አማራንም ብንወስድ እንደዚሁ ነው።ሌሎችንም እንጠቃቅስ ብንል ከዚህ የተለየ አይደለም።
🗿🗿ጉራጌ ግን በቋንቋና በኃይማኖት ቢለያይም በእደ ጥበብ ስራ፣በቴክኖሎጂና በስልተ-ለማት፣በቤት አሰራር ና በመንደር አመሰራረት፣በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ኑሮ አደረጃጀት ተመሣሣይ ነው።
📡📲ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ በህዝቦች መሐል ያለውን ጥቂት የቋንቋ ዘዬ ልዩነት ተጠቅመው ህዝቡን ለማቃቃርና  ሠላሙን ለመንሳት የሚሰሩ ኃይሎች ተበራክተዋል።ራሳቸውን እንደ ነፃ አውጪ ቆጥረው ህዝቡን ለጦርነትና ለብጥብጥ  ይቀሰቅሳሉ።
💠💠ይሄኔ ነበር ለራሴ "ጉራጌ በታሪኩ ቋንቋዎቹ ለምን ሊበዙ ቻሉ?" ስል የጠየቅኩት።መልስ ፍለጋ ስኳትን ካየኃቸው መፃህፍት ሁሉ በጥቂት ሀሳቦቹ ቀልቤን የገዛው መፅሐፍ አገኘሁ።መፅሐፉ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል ፣ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመሆን ያሳተሙት "የቤተ ጉራጌ ምሳሌያዊ ንግግር " በሚል ርዕስ በ583 ገፅ የታተመው መፅሐፍ ነው።መፅሐፉ ለጥያቄዬ   በጥናት ተመሠረተ መልስ የሰጠ ስለመሠለኝ ላካፍላችሁ ወደድኩ።
🔴መፅሐፉን አግኝታችሁ ለማንበብ እድሉ ያላገኛችሁ እንደሚከተለው አስፍሬዋለሁና እንድታነቡት ገብዣችኃለሁ።


የቤተ ጉራጌ የቋንቋዎችን ሁኔታ ለማያውቅ ሰው ርዕሱ ሊያስገርመው ይችላል።የቤተ-ጉራጌ ቋንቋዎች ጠባይ ምን እንደሆነ ና የጥያቄውንም ተገቢነት ለአንባቢው ለማስጨበጥ ቋንቋውን በሚመለከት ከቀረቡት ጥናቶች የተወሰኑትን መሠረተ-ሃሳቦች ባጭሩ መቃኘት ያስፈልጋል።ጀርመናዊው ማየር ጆሃንስ በ1878 ባሳተመው መፅሐፍ መተሻነት የተጀመረው የቤተ-ጉራጌ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር የቋንቋዎቹን ብዛት የሚጠይቁ ሃሳቦችን አስነስቷል።
ጥናቱ ከተጀመረበት ከ1878 እስከ 1931 ባሉት አመታት የተለያዩ ስሞችን ከመጥቀስ አልፈው ጥያቄውን በቀጥታ ለመመለስ የሞከሩ ፅሁፎች የሉም።በነዚህ አመታት ውስጥ እንደ የቤተ-ገራጌ ቋንቋ ቅርንጫፎች ታስበው በተለያዩ ደራስያን ተጠቅሰው የምናገኘቸው ስሞች አይመለል(ሶዶ)፣ቸሃ ፣ውልባረግ፣ጎጎት፣መስቃንና ወለኔ ናቸው።ስሞቹ የተጠቀሱት በተለያየ ሁኔታና ምክንያት እንደመሆኑ መሠረታዊውን የቋንቋ ብዛት  ጥያቄ ለመመለስ ታስቦ እንዳልሆነ ከፅሁፎቹ እንረዳለን ።በዚህ ግዜ ውስጥ የጥያቄው መልስ ቀርቶ ጥያቄው ራሱ መታሰቡን የምናረጋግጥበት መረጃ የለም።የቤተ-ጉራጌ ቋንቋዎች በምዕራብ፣በምሥራቅና በሰሜን ቅርንጫፎች ሊመደቡ የሚችሉ በርካታ ዝርያዎች ያሏቸው ቋንቋዎች ስለመሆናቸው ለመጀመሪያ ጊዜ  ተጨቅሶ የምናገኘው ፈረንሳዊው ፕሮፌሰር ኮህን መፅሐፍ በመሥኩ ለተሠማሩ አርአያ በመሆኑ ጥያቄው ተገቢውን ትኩረት አግኝቷል።ስለሆነም የኮህን ፈለግ በመከተል ጥያቄውን ለመመለስ የሞከሩ ተመራማሪዎች በርካታ ናቸው።ሁሉንም የሚያስማማ አንድ ማጠቃለያ ላይ መድረስ ቢሳናቸውም በለተይ ከ1950 በኃላ ባሉት አመታት በርካታ ጥናቶች ተካሂደዋል።
ከዋቢ መፃህፍቱ ዝርዝር ማየት እንደሚቻለው ጥናቶቹ በርካታ በመሆናቸው ለአብነት ሮበርት ሄትዝሮንና  ውልፍ ሌስላው በየበኩላቸው የደረሱበት ሀሳብ ብቻ እዚህ ላይ እናቀርባለን።ሁለቱን የመረጥነው በጥያቄው ዙርያ ከፍተኛ የሃሳብ ልዩነት የምናየው በሁለቱ ተመራማሪዎች መካከል በመሆኑ ነው።
ሮበርት ሄትዝሮን ባቀረቡት ሃሳብ መሠረት የቤተ -ጉራጌ ቋንቋዎች አራት ራሳቸውን የቻሉ ቋንቋዎችን ፣ሦሥት የዘዬ ስብስቦችን ና (Dialect clusters)አስራ ሦስት ዘዬዎችን ያጠቃልላል።በቋንቋዎቹ ዝምድና መሠረት በሁለት ዘርፎች የከፈሏቸው የደቡብ ሴም ቋንቋዎች ና ዘዬዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ይሆናል።

ይቀጥላል

GURAGE KINGDOM

13 Sep, 13:30


የጉራጌ ባህልና ስነልቦናው በሰው ልጅ እኩልነት የሚያምን፤ ክፉን የሚፀየፍ፤ በርቸ፣ ድረድግ ፣ኬር እያለ ሰላምን የሚሰብክ ስልጡን ህዝብ ነው ጉራጌ!