Mayal Info World️

@mayalinfoworld


ይህ የቴሌግራም 'ቻናል' በዓለም አቀፍ ደረጃ ታላቅ መነጋገሪያ የሆኑ መረጃዎች-በተለይም በምዕራባውያኑ የዜና አውታሮች እምብዛም ሽፋን ያላገኙና እጅግ ወሳኝ የተባሉ ወቅታዊ መረጃዎችን የምንጋራበት ገጽ ነው።

በዚህ ቻናል ላይ በሚቀርቡ መረጃዎች ላይ ተመሰርቶ ስድብና ዘለፋ መሰንዘር አይቻልም።

ከዚህ መገኛችን በተጨማሪ የፌስቡክ አድራሻችን
https://www.facebook.com/MayalInfo

Mayal Info World️

22 Oct, 15:43


የሩሲያ ኢኮኖሚ በ 3.6% በማደግ ላይ ይገኛል !!
#IMF

ምንም እንኳን ከሀያላኑ ስብስብ ጋር የዓለማችን አስከፊውን ጦርነት በማድረግ ላይ የምትገኘው ሩስያ ዛሬም ለምዕራባውያኑ ራስ ምታት መሆኗን እንደቀጠለች ትገኛለች !

ዓለም አቀፉ ተቋም የሩሲያን የዕድገት ግስጋሴ #አስደናቂ ሲል ገልፆታል !

እ.ኤ.አ. በ 2024 የሩሲያ ኢኮኖሚ እድገት ቀደም ሲል ከተገመተው በላይ ሆኗል- ይህ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የደረሰበት መደምደሚያ ሲሆን ባሳለፍነው የሐምሌ ወር የሩስያ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ አቅርቦት የነበረውን የ3.2% ግምቱን እንዲያሻሽል አስገድዶታል።

በዚህም መሰረት ተቋሙ እ.አ.አ በ2024 በበርካታ ሀገራት ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ግምገማ በሚከተለው መልኩ ይፋ አድርጓል፡-

🇮🇳 +7.0% - ህንድ
🇨🇳 +4.8% - ቻይና
🇷🇺 + 3.6% - ሩሲያ
🇧🇷 +3.0% - ብራዚል
🇺🇸 +2.8% - አሜሪካ
🇨🇦 +1.3% - ካናዳ
🇬🇧 +1.1% - ብሪታንያ
🇫🇷 +1.1% - ፈረንሳይ
🇮🇹 +0.7% - ጣሊያን
🇯🇵+ 0.3% - ጃፓን
🇩🇪 +0.0% - ጀርመን

አይ.ኤም.ኤፍ እ.አ.አ በ2024 በበርካታ ሀገራት የነፍስ ወከፍ እድገትን በተመለከተ ባስቀመጠው ግምት፡-
🇮🇳 + 6.0% - ህንድ
🇨🇳 +4.9% - ቻይና
🇷🇺 + 3.8% - ሩሲያ
🇧🇷 +2.6% - ብራዚል
🇺🇸 +2.3% - አሜሪካ
🇫🇷 +0.8% - ፈረንሳይ
🇯🇵+ 0.8% - ጃፓን
🇮🇹 +0.7% - ጣሊያን
🇬🇧 +0.6% - ብሪታንያ
🇩🇪— 0.4% - ጀርመን
🇨🇦 —1.5% - ካናዳ

በተጨማሪም የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ብሎ ካስቀመጣቸው መካከል ምስራቅ አፍሪካዊቷ 🇪🇹 #ኢትዮጵያን በ13ኛ ደረጃ ላይ ያሰፈረ ሲሆን የዕድገት መጠኗንም በ6.2% አድርጎ አስፍሯል።

Mayal Info World️

22 Oct, 14:56


የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን በ #BRICS የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ሩስያ ( ካዛን ) መግባታቸውን የአገሪቱ የፕሬስ አገልግሎት አስታወቀ።

video credit #TASS

Join us 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

22 Oct, 14:52


🇱🇧🇮🇱የእስራኤል አየር ኃይል አውሮፕላኖች በምሥራቃዊ ቤይሩት በሚገኙ አካባቢዎች ላይ ጥቃት በመሠንዘር ላይ ይገኛሉ።

በአሁኑ ሰዓት የአየር ድብደባው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በዚህም ጥቃት የሊባኖስ አጠቃላይ የደህንነት መምሪያ አቅራቢያ የሚገኝ ህንጻ ተመትቶ በርካቶች በፍርስራሹ ስር ተቀብረው እንደሚገኙ ታስ የዜና ወኪል ከስፍራው ባሰራጨው ቪዲዮ አመልክቷል።

Join 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

22 Oct, 14:44


#Breaking

🇮🇱🇱🇧 የእስራኤል ጦር በፈፀመው የአየር ድብደባ በቤሩት የሚገኝን ባለ 10 ፎቅ ህንጻ አፍርሶ የ20 አባውራዎች ቤቶችንና ውስጥ የነበሩ ጥቂት ኗሪዎችን ሙሉ ለሙሉ አወደመ።

Join 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

19 Oct, 18:45


የኢራን ፕሬዝዳንት ቢሮ፥ " ፕሬዝዳንት ፔዜሽኪያን በቀጣዩ ሳምንት (ማክሰኞ) ወደ ሩሲያ በመጓዝ በ16ኛው የብሪክስ+ ጉባዔ ላይ ንግግር ያደርጋሉ " ሲል አስታወቀ።

Join👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

19 Oct, 18:38


የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ በቂሳርያ የሚገኘው ቤታቸው ጥቃት ከተፈፀመበት በኋላ ባስቀረፁት የ24 ሰከንድ ቪድዮ ባሰራጩት መልዕክት ላይ ለጥቃቱ በሰጡት የመጀመሪያ ምላሽ ምላሻቸው " ወደፊት መግፋታችንን እንቀጥላለን - እናም በምድር ላይ ምንም ኃይል ሊያስቆመን አይችልም " ብለዋል።

Join 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

19 Oct, 08:10


#BREAKING

ሄዝቦላህ የሰው አልባ አውሮፕላን በመጠቀም የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር #ኔታንያሁን ለመግደል ሙከራ አድርጓል፡ - በጥቃቱም የኔታንያሁ የግል መኖሪያ ቤት የተመታ ( የተቃጠለ ) ሲሆን በወቅቱ ግን ጠቅላይ ሚንስትሩ በቤት ውስጥ አልነበሩም ተብሏል።

ይህንንም ተከትሎ የሊባኖሱ ታጣቂ ሄዝቦላህ በሰጠው መግለጫ የትም የሁን የትም ነፍሰ በላውን ሚንስትር አድንን እንገላቸዋለን ብሏል።

Join us 👇🏽
https://whatsapp.com/channel/0029Va5lw25ATRSnWUnJpp1Y

Mayal Info World️

19 Oct, 04:25


— በተናጠል የ #BRICS ምንዛሪ ለመፍጠር ጊዜው አሁን አይደለም - ይህ ከግምት ውስጥ አልገባም። #የBRICS አገሮች በራሳቸው መንገድ የስዊፍት ተተኪ የሆነ የገንዘብ የዝውውር ስርዓትን ለመፍጠር በርትተው እየሰሩ ነው።

— በሩሲያ፣ በቻይናና በሕንድ አዎንታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ቢጠበቅም በአፍሪካና በደቡብ ምሥራቅ እስያ አገሮች ግን ፈጣን ዕድገት እንደሚኖር አመላካች ፍንጮችን እያየን ነው።

—በአሁኑ ጊዜ ብሪክስ የምድሪቱን 33% ይዞታ እንዲሁም 45 በመቶ የሚሆነውን የፕላኔቷን ሕዝብ የያዘ ነው ! ብሪክስ "የፀረ-ምዕራባውያን ማኅበር አይደለም፣ ነገር ግን በቀላል አገላለፅ የምዕራባውያን ማኅበር አይደለም።

— ዩናይትድ ስቴትስ የቻይናን ዕድገት ማስቆም አትችልም፤ ይህንን ማድረግ ከሚችሉበት 15 ዓመት ያህል ዘግይታለች። በተመሳሳይም ዩናይትድ ስቴትስ አውሮፓውያንንና ኔቶን እንደ ትንንሽ ውሾች ከቻይና ጋር ወደሚያላትም ግጭት እየጎተተች ትገኛለች።

— የሩሲያና የቻይና ትብብር በዓለም ላይ የተረጋጋ ሁኔታ እንዲከሰት ከሚያደርጉት ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ ነው። በአገሮች መካከል በዓይነቱ ልዩ የሆነ የመተማመን ግንኙነት የዳበረ ሲሆን የንግድ መጠኑም ይህን ያረጋግጣል። በቻይና የንግድ ልውውጥ ላይ የሩሲያ ድርሻ እያደገ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በአራተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።

— ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ሁለት መንግስታት - (እስራኤል እና ፍልስጤም) - እንዲፈጠሩ ያሳለፈው ውሳኔ ተግባራዊ መሆን አለበት ከሚለው እውነታ ጋር ሁሌም ቀጥላለች። እናም ፍልስጤማውያንም ከዚያ አይወጡም። ይህች ምድራቸው ናት። ይህን መረዳት አለብን። ፍልስጤማውያን በምድራቸው ላይ የመጡባቸውን ወራሪዎች መመልከትና ታግለው ነፃነታቸውን የማስከበር ሙሉ መብት አላቸው።

— ዩክሬን በምንም ዓይነት ሁኔታ የኒውክለር መሣሪያዎችን እንድትሰራ ሩሲያ አትፈቅድም !!

— በዩክሬን ውስጥ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን ለመፍጠር ለሚወሰዱ እርምጃዎች "ተገቢው ምላሽ" ይሰጣቸዋል። በተመሳሳይም ሩሲያ በዩክሬን ያለውን ግጭት በተቻለ ፍጥነት ለማስቆም ፍላጎቱ አላት። ይሁን እንጂ ግጭቱን ለማስቆም የሚያስችል የጊዜ ገደብ ማውጣት ውጤታማ አይደለም።

—ዘመናዊው የጦርነት መንገድ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚደረግ ግጭት ነው ፣ ይህም የሂሳብ ሊቃውንቶች ጦርነት ነው።

—ሩስያ በዩክሬይን ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ በማቆም ላይ ውይይት ለማድረግ ዝግጁ ናት። ሆኖም ግን በኢስታንቡል ስምምነቶች መሰረት ብቻ ከሆነ ነው።

— ድል የኛ ይሆናል !

Mayal Info World️

19 Oct, 04:25


⚡️ ዘመናዊው የጦርነት መንገድ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚደረግ ግጭት ነው ፣ ይህም የሂሳብ ሊቃውንቶች ጦርነት ነው።

ቭላድሚር ፑቲን
የሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት

ፕሬዚዳንቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቆፍጠን ብለው እንዲሁ ደግሞ ፈታ ብለው ታዳሚውን እያዝናኑ ፣ እያሳቁ ፣ እያስገረሙም በርካታ የሆኑ የዓለም አቀፍ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸው ውስጥ ያለው በራስ የመተማመን መንፈስ ከሌላው ጊዜ ለየት ያለ ሆኖ ተመልክተነዋል።

ፑቲን የብሪክስን ወቅታዊ ቁመና አስመልክተው በተናገሩት ንግግር ምዕራባዊያኑን " እንቁልልጭ " ከማለት በማይተናነስ ሁኔታ ምራቃቸውን ለማስዋጥ ሞክረዋል።

ፑቲን በሞስኮ እየተካሄደ ባለው የብሪክስ የአገራት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ከየአገራቱ የሚዲያ ኃላፊዎች ጋር ተነጋግረው ነበር። ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከልም የሚከተሉት ይገኙበታል:- በቀጣዩ ይዘት እነሆ !
👇🏽👇🏽👇🏽