የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

@gibigubaye


ይህ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባዔ መንፈሳዊ ትምህርቶች እና መልዕክቶች እንዲሁም ወቅታዊ መረጃዎችን የሚያስተላልፍበት ይፋዊ(Official) የቴሌግራም ገጽ ነው።

ማንኛውንም አስተያየት ፥ ሀሳብ እና ጥያቄ ካለዎት @AstugibigubaeBot ላይ ያድርሱን::

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

23 Oct, 03:50


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
“ከብር ይልቅ ትምህርትን፥ከተፈተነ ወርቅም ይልቅ ዕውቀትን ተቀበሉ።”
      ▬ ምሳሌ 8፥10 ▬

ሁላችንም በናፍቆት ስንጠብቀዉ የነበረዉ የ2017 የኮርስ መረሀ ግብር እንሆ ተጀመረ

◊ 2ኛ ዓመት ➩ ክርስቲያናዊ ሕይወት እና ሥነ-ምግባር

◊ 3ኛ ዓመት ➩ ነገረ ማርያም

◊ 4ኛ ዓመት ➩ የቤተክርስቲያን ታሪክ

◊ 5ኛ ዓመት ➩ነገረ ቅዱሳን

⚠️ ለአንደኛ አመቶች ሀሙስ የተዘጋጀ የስልጠና መርሀ ግብር ስላለ በዛሬው እለት ኮርስ የማይኖር ይሆናል።

⛪️ ቦታ :-ደብረ አሜን አቡነ ተክለ ሃይማኖት
🗓 13/02/2017 ዓ/ም
🕰 11፡40

📲 ለማንኛዉም ጥያቄ :     +251973671282
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
➣የአ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
➣ባች እና መርሐግብራት ማስተባበሪያ

🏷 @gibigubaye◀️ተከታተሉን

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

22 Oct, 02:15


የዕለቱ ስንቅ

ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤

ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል፡፡

                  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ሠናይ ዕለተ ሠሉስ

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

21 Oct, 10:30


🗣🔊🗣🔊ደረሰ ደረሰ ደረሰ 🗣🔈🗣🔈

ለአንደኛ አመቶች የተዘጋጀ ልዩ የስልጠና መርሃግብር
በዚህ መርሃግብር ላይ፦
በዩኒቨርስቲው ሊኖረን ስለሚገባ ማህበራዊ ኑሮ

ጓደኝነት
የካፌ ሰአት አጠቃቀም
የክበባት ተሳትፎ ና
ስለ መገልገያ ስፍራዎችና

👉በተማሪዎች በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች ላይ ጥልቅ ገለጻ ይሰጣል

📌እርስዎም ከወንድምና እህቶቻችሁ ጋር በመሆን ይህን የመሰለ መርሐግብር ፈፅሞ እንዳያመልጣችሁ ስንል በእግዚአብሔር ስም ጠርተንዎታል።

🗓ሰኞ 11/02/2017
11፡30 - 1:30 LT ማታ
📍ደብረ አሚን አቡነ ተ/ሐይማኖት ግቢ ጉባኤ አዳራሽ

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

21 Oct, 03:54


የዕለቱ ስንቅ


ኑና፡እንዋቀስ፡ይላል፡እግዚአብሔር፤

ኀጢአታችኹ፡እንደ፡ዐለላ፡ብትኾን፡

እንደ፡ዐመዳይ፡ትነጻለች፤

እንደ፡ደምም፡ብትቀላ፡

እንደ፡ባዘቶ፡ትጠራለች።

ዕሺ፡ብትሉ፡ለኔም፡ብትታዘዙ፥የምድርን፡በረከት፡ትበላላችኹ፤

ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ፡1:18-19

ሠናይ ዕለተ ሰኑይ

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

20 Oct, 12:30


✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ውድ የጊቢ ጉባኤያትን የኪነጥበብ ክፍል አባላት  ሳምንታዊው የኪነጥበብ ጥናት መርሃግብር ዛሬ በእለተ እሁድ ጥቅምት 10 ቀን እንደተጠበቀ ነው። በመርሃግብሩም :-
# የእለቱ የወንጌል ንባብ
# እኔ ማነኝ ?
# ካነበብኩት ላካፍላችሁ
# የቃለ-ተውኔት(ሞኖሎግ) እና የድምጽ ልምምድ (ቮካል )
# ቅጽበታዊ  ተውኔት
# የስነ-ጽሑፍ ስራዎች እና ሌሎችም .......

ታዲያ እኛም ይህንን መልዕክት ለጓደኞቻችን በማጋራት ላልሰሙት በማድረስ ተሰባስበን በሰዓቱ ሳናረፍድ  በጥናት መርሃግብሩ ላይ እንገኝ ዘንድ ኪነጥበብ ክፍሉ በአክብሮት ጋብዞናል ። አይቀርም !!!!


ሰዓት :- 11:30 ላይ መርሃግብሩ በጸሎት ይጀመራል
ቦታ :- በናዝሬት ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን

ኑ አብረን የዕለተ ሰንበት ማምሻን በስነጥበብ እናሳልፍ !!!!
✝️✝️✝️መልካም ዕለተ ሰንበት ✝️✝️✝️

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

20 Oct, 05:53


የዕለቱ ስንቅ

"ሔሮድስ የማይዘዉን ይይዝ ዘንድ ተነሳ አዉሎ ነፋስንም በቤቱ አስገብቶ ሊዘጋ ታገለ"

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ


"በማይጠቅመኝ ነገር ጊዜዬን እንዳላጠፋ ድንግል እናቴ ሆይ እርጂኝ" :- የኅሊና ፀሎት



ሠናይ ዕለተ ሰንበት

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

19 Oct, 09:55


🌹🌷🌹 ማኅሌተ ጽጌ 🌹🌷🌹

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ጸዐዳ ወቀይሕ።
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ።
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፥
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ፡፡

ትርጓሜ

ነጭና ቀይ መልክ ያለው አበባ የሚባል ልጅሽን ታቅፈሽ፤
ወደ ቤተመቅደስ እንደገባሽበት ተአምርና ንጹሕ ጊዜ ሁሉ፤
ደስ ካለው ከገብርኤልና እንደ አንቺ ርኅሩህ ከሆነው ከሚካኤል ጋር ከኀዘን ታረጋጊኝ ዘንድ ነዪ።

እያልን የምናመሰግንባት 🌹🌷🌹ሥርዓተ ማሕሌተ ጽጌ (3ኛ ሳምንት)🌹🌷🌹ደረሰ ከ 12:00 ሰዓት  ጀምሮ ሁላችንም የግቢ - ጉባዬ  ልጆች  ተሰባስበን በአንድነት ወደ ደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት  በማቅናት ምሽቱን ማህሌተ ጽጌ በማጥናት ሌሊቱን በማህሌት በአንድነት ሆነን እናመስግን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏


📍መሰባሰቢያ ቦታ:እስታዲየም መግቢያ

  12:00- 1:00LT ምሽት
📍ደብረ አሚን አቡነ ተ/ሃይማኖት

እንዲደውልላችሁ የምትፈልጉ:
       ለወንድሞች: 0935359134
       ለእህቶች: 0900680333
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
®የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
       📲 Join and Share 🤳
               @gibigubaye
               @Astugibigubae

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

18 Oct, 15:37


https://t.me/+e_o_IDe9P9lkOGVk

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

18 Oct, 07:10


🔊🔊እንዳያመልጥዎት! እንዳያመልጥዎት! 🔊🔊

በእውነት ከቀሩ የሚቆጩበት፣
ትልቅ ቁም ነገር የሚያገኙበት፣
የመርሐግብር ድግስ ተደግሶ፣
እየጠበቆ ነው ሐሙስ ተኮፍሶ፣
ታዲያ ቢመጡ ተክልዬ እርሶ፣
ይመለሳሉ የልብዎ ደርሶ።


በመርሐግብሩም ላይ:

✝️አጠቃላይ ስለ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ማለትም
           👉እንዴት ማጥናት እንዳለብን እንዴት የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል፣
           👉 በጥቅሉ በአካዳሚክ ሕይወታችን እንዴት ስኬታማ መሆን እንደሚቻል፣
           👉 እንዲሁም ስለማህበራዊ ህይወት ማለትም ግቢ ውስጥ ካሉ ማንኛውም ተማሪዎች ጋር የሚኖረን ግንኙነት ምን ይመስላል የሚለው ይዳሰሳል፤

✝️ ሌላው ስለ ግቢ ጉባኤ
           👉ግቢ ጉባኤው በአካዳሚክሱ ለመርዳት ያዘጋጀውን ፕሮጀክት ገለጻ ይሰጣል
           👉በግቢ ጉባኤ ውስጥ ያሉ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ዙሪያ ጥልቅ የሆነ ገለፃ ያገኛሉ።

📌እርስዎም ከወንድምና እህቶቻችሁ ጋር በመሆን ይህን የመሰለ መርሐግብር ፈፅሞ እንዳያመልጣችሁ ስንል በእግዚአብሔር ስም ጠርተንዎታል።

🗓አርብ 08/02/2017
11፡30 - 1:30 LT ማታ
📍ደብረ አሚን አቡነ ተ/ሃይማኖት ግቢ ጉባኤ አዳራሽ

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

18 Oct, 03:00


የዕለቱ ስንቅ

ወዳጄ ሆይ እንደ ሳምራዊቷ ሴት መመላለስ የሰለቸህ መንገድ የለም ?

ስትጠጣዉ አሁንም ጨምር የሚያሰኝህ የማይቆርጥ ጥም የለህም

ልትቀዳ የምትመላለስበት ጉድጓድ የለም?

ሁለተኛ አልመለስበትም ብለህ ዝተህ የምትሄድበት ቦታ

ሁለተኛ አልጠጣውም ብለህ የምጠጣው ዉኃ ምንድን ?

መላቀቅ አየፈለግህ ያልተወከዉ ዞረህ የምትሄድበት

ታጥቦ ጭቃ አድሮ ቃርያ ከርሞ ጥጃ የሆንህበት ልማድ የለህም ?

ክርስቶስ ቦታዉንም ዉሃዉነም ያዉቀዋል!!!

ከዚህ መገላገል ከፈለግህ እንደ ሳምራዊተዋ ሴት እንዲ በለዉ :-


"ጌታ ሆይ እንዳልጠማ ዉኃም ልጠጣ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ዉሃ ስጠኝ"
       
                ቅምሻ ከ የኤፍራጥስ ወንዝ

ሳምራዊትዋን ሴት ታግሶ የጎደላትን እንደ ሞላላት የኛንም በልምድ ሀጢያት የቆፈርነዉን ጎዶሎአችንን በምህረቱ ይሙላልን!!!

ሠናይ ዕለተ ዐርብ

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

17 Oct, 16:13


የአርብ_ጸሎት
  ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
📖 "የልመናዬን ቃል አድምጥ ንጉሴ እና                    
         አምላኬ ሆይ አቤቱ ወደ አንተ 
        እፀልያለሁ" መዝሙር 5፥2

     እህት እና ወንድሞች በአንድነት የሚሳተፉበት መደብኛ የጸሎት መርኃግብር። ጠዋት እስቴዲየሙ ጋር ያለው በር አከባቢ ተገናኝተን 11:30 ላይ ከግቢ የምንወጣ ይሆናል።


🗓 ሁሌም በየሳምንቱ አርብ ዕለት
  12:00- 1:00 LT ጠዋት
📍ደብረ አሚን አቡነ ተ/ሃይማኖት ግቢ ጉባኤ አዳራሽ

እንዲደውልላችሁ የምትፈልጉ:
       ለወንድሞች: 0940640089
       ለእህቶች: 0994251129
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
®የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
       📲 Join and Share 🤳
               @gibigubaye
               @Astugibigubae

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

17 Oct, 05:27


የእለቱ ስንቅ

ደሃዉ ወደ አንተ ሊለምን ሲመጣ

"ራቁቱን ሆኖ የሚለምነዉ ሲያስመስል ነዉ" ትላለህ::

እርሱን አታላይ ያደረገዉ ግን የአንተ ጭካኔ ነዉ::
ርኅሩኅ ብትሆንለት ኖሮ አንተን ለማራራት ሲል እንዲህ ባልደከመ ነበር::

እሱ እኮ በየቀኑ እየመጣ ይለምነኛል ብለህ አትበሳጭ

በየቀኑ የሚለምንህ እርሱ እንደ አንተ በየቀኑ ሰለሚበላ ነዉ።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

"ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤

እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል።

 እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፥

ሕያውም ያደርገዋል፥

በምድር ላይም ያስመሰግነዋል፥

በጠላቶቹም እጅ አያሳልፈውም።

እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤

መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል።
"

መዝሙረ ዳዊት 41:1-3

ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ልብ ያድለን

ሠናይ ዕለተ ኅሙስ

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

16 Oct, 08:25


እድሉ ላመለጣቹ (ላልተመዘገባቹ) ብቻ በድጋሚ እስከ ማታ 2:00


2 ቀን የሚቆይ ስልጠና ከስራ እድል ጋር ለተማሪዎች


https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSf_NPQV1u9iYqCcVCwN-gsv_w7-M595lVmpaahyOlX9QNvejw/viewform?usp=pp_url

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

16 Oct, 05:30


የእለቱ ስንቅ

"የምንቆጥረው ሬሳዎች አይደለም።

ሰማዕታትን ነዉ።

ሙታንን ሳይሆን ሙሽሮችን ነዉ።

ሰማዕታት ሆይ ሰለ እኛ ማልዱ"

ከአኃዉ አንዱ

ሠናይ ዕለተ ረቡዕ

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

15 Oct, 13:29


https://www.instagram.com/astu_gibi_gubae?igsh=YzljYTk1ODg3Zg==

ይህ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባዔ መንፈሳዊ ትምህርቶች እና መልዕክቶች የሚተላልፍበት የInstagram official ገጻችን ነው። ሁላችንም follow ና share በማድረግ ተደራሽ እናድርግ

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

15 Oct, 03:42


እንኳን አደረሳቹ

ጥቅምት 5-ኑሮአቸው እንደሰው ያይደለ በምድረ በዳ እንደመላእክት የኖሩትና በዝቋላ ተራራ ባለው ባሕር ውስጥ 100 ዓመት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ሰዎች ምሕረትን የለመኑት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታላቅ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ነው፡፡ 

አባታችን አራት ሺህ እልፍ እየሰገዱ፣ 300 ጊዜ የቀኝ 300 ጊዜ ደግሞ የግራ ፊታቸውን በድንጋይ እየመቱ፣ መዝሙረ ዳዊትን እየደገሙ፣ 15ቱን መኅልየ ነቢያት፣ መኀልየ ሰሎሞንንና ውዳሴ ማርያም እየጸለዩ ለኃጥአን ምሕረትን ሲለምኑ ዕንባቸው እንደ ውኃ ይፈስ ነበር፡፡ ጌታችንም ‹‹በተወለድሁባት፣ በተጠመቅሁባትና ከሞት በተነሣሁባት ዕለት እልፍ እልፍ ነፍሳትን እምርልሃለሁ›› የሚል ቃል ኪዳን ሰጣቸዉ

አምላካችን በቃል ኪዳናቸው ይማረን