Freshman and remedial

@freshman_remedials


📌ለfreshman እና ለremedial ተማሪዎች
✔️Freshman module📚
✔️ Remedial module📚
✔️Note📒
✔️ Ppt📑
✔️Mid and final exam📜
✔️Freshman exa📄
✔️Remedial exam🧾
⤵️ ሁሉንም በአንድ ላይ የምታገኙበት ቻናል 👇👇

Freshman and remedial

20 Jan, 23:39


የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል።

በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ውጤት ተለቋል።

ተማሪዎች ውጤታችሁን በተከታዩ ሊንክ አማካኝነት መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል 👇

https://result.ethernet.edu.et/


@freshman_remedials

Freshman and remedial

20 Jan, 23:37


የሪሜዲያል መቁረጫ ነጥብን አስመልክቶ በርካታ ጥያቄዎች ስለቀረቡልኝ ይህን ማለት ፈለኩ

¤ የመቁረጫ ነጥብ የሚወሰነው የተለያዩ ምክንያቶች ላይ መሰረት ተደርጎ ነው። የመጀመሪያው እና ትልቁ የዩንቨርሲቲዎች የመቀበል አቅም ነው። ለምሳሌ የዘንድሮ የዩንቨርሲቲዎች የመቀበል አቅም 100ሺህ ተማሪ ከሆነ ከ50% በታች ውጤት ካላቸው ተማሪዎች ውስጥ እነኚህ 100ሺህ ተማሪዎች በተለያዩ መስፈርቶች ይመረጣሉ።ይህም የመቁረጫ ነጥቡን ከፍ ወይም ዝቅ ያደርገዋል።

📍ሌላኛው ቁልፍ ምክንያት ደግሞ የዘንድሮ ውጤት ላይ የተመሰረተ ነው። ትምህርት ሚኒስቴር በትላንትናው መግለጫው አማካይ የተማሪዎች ውጤት 29 እንደነበር ገልጿል። ይህ ማለት አማካይ የተማሪዎች ድምር ውጤት ከ200 በታች ነው ማለት ነው። ይህ አማካይ ድምር ውጤት ብቻውን የመቁረጫ ነጥቡን ለመገመት አያስችልም። ምክንያቱም የተማሪዎችን ውጤት በዝርዝር አናውቅምና። 300ሺ ተማሪዎች ከ200 በታች ውጤት አላቸው ብንል እንኳ ምን ያህሎቹ ከ40% እስከ 49% ባለው ደረጃ ውስጥ እንደሚገኙ አናውቅም። 

💫 ሌሎች ከላይ ከተጠቀሱት ያነሱ ምክንያቶች ደግሞ በልዩ ድጋፍ የሚደገፉ ተማሪዎች ቁጥር ነው።(ፆታ፣ታዳጊ ክልል፣አርብቶ አደር፣ዓይነ ስውራን፣...)

💫 በእነኚህ እና በሌሎችም ምክንያቶች የተነሳ የዘንድሮ የሪሜዲያል መቁረጫ ነጥብን መገመት አይቻልም‼️

💫 Note:ከላይ የተያያዘው ምስል የአምና የሪሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ሲሆን እሱን አይታቹህ የዘንድሮውን እንዳትገምቱ!



📍Join: @freshman_remedials

Freshman and remedial

20 Jan, 23:27


🏵️ 2017_ያንተ_አመት_ነው 🏵️

👉 ምክንያቱም ቲቪ ላይ ተጥደህ አትውልም
👉 ሶሻል ሚዲያም ትቀንሳለለህ
👉 ንባብ ታበዛለህ
👉 አማራጭ ቢዝነስ ታያለህ
👉 ራስህን ታስተምራለህ
👉 የሚያሳድጉህ ጓደኞች ታፈራለህ
👉 በእምነት ትንቀሳቀሳለህ

= ስኬት ያንተ ይሆናል።

መልካም አዲስ አመት

😴 እንቅልፋም ሳይሆን ንቁ
🗣 የሚያወራ ሳይሆን የሚተገብር
🚫 ሰበበኛ ሳይሆን ተአምረኛ የምንሆንበት አመት ያርገው 💫

Freshman and remedial

20 Jan, 23:26


📮የአዲስ አበባ ዪኒቨርቲ - ምዘገባ ተጀምሯል! ( አይደርሰኝም ብላችሁ እንዳታሰቡ ፣ ዕድላችሁን ሞክሩ)

📚 ለምዘገባ የሚያስፈልገው መቁረጫ ነጥብ - 50 % እና ከዛ በላይ ( የ ዩንቨርስቲው ፕሬዘዳንት እንደ ሁኔታው ታይቶ ከ 60% ወይም 70% በላይ አይተን የመቁረጫ ነጥቡን ከፍ እናረጋለን እንዳሉ የሚታወስ ቢሆንም ፣ ይህ አይነት የመቁረጫ ነጥብ ግን በይበልጥ ይተገበራል ተብሎ የሚታሰበው 100ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች ሊያመለክቱበት በሚችሉበት ሁኔታ ነው! የምዘገባ መቁረጫ የሚቀየር ከሆነ በማህበራዊ ሚዲያ እንደሚያሳውቅ ባሳወቀው መሰረት ፣ የማሻሻያ መረጃዎችን ለማየት ብንሞክርም ሌላ የተላለፈ መግለጫ እንደ ሌለ ነው የተረዳነው! ስለዚህ ዝቅተኛው መቁረጫ ነጥብ ከ 50% ይጀምራል ማለት ነው!

💡 ዩኒቨርስቲው እስከ 5,000 ተማሪዎች የሚቀበል ይሆናል! ግማሹን በመንግስት ወጪ - ግማሹን በራሳቸው ክፍያ የሚከፍሉ ተማሪዎችን ተብሎ የተውሰነ ነገር ባይሮም እንዳመጣጡ 50%- 50 % አካባቢ ምደባ እንደሚካሄድ ተገልጻል!

📮 የመመዝገቢያ ቀናት ፥ ከጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም - መስከረም 8/2017 ዓ.ም ድረስ ነው "

📨የመመዝገቢያ ድህረገፅ :  https://portal.aau.edu.et/

📮 UAT ( Undergraduate Admission Test ፈተና ቀን፡ እስካሁን አልተነገረም [የሚያስፈልጋችሁን Material ) አንድ ላይ አርገን እንልካለን!

👨‍⚕️ Medicine ከፍለን ለመማር AAU ስንት ነው ?
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ - ጥቁር አምበሳ Campus - Doctor of Medicine - የ ስድስት ዓመት ክፍያ -900,000 ብር ነው!

🤲 ለመንግስት Scholarship ማረጋገጫ ከየት እናምጣ?
ስኮላርሺፕ የምትጠይቁ ተማሪዎች ከፍላችሁ መማር እንደማይትችሉ የሚያሳይ ማስረጃ ከሚመለከተው አካል( ለምሳሌ ወላጆቻችሁ ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት ፣ ከቀበሌ ወዘተ ) ማሟላት ይጠበቅባችኋል!

💡ከፍለን የምንማር ተማሪዎች እድል ይኖረናል ወይ?
በሚገባ ፣ ከፍለው መግባት የሚችሉ አመልካቾች በጨመሩ ቁጥር የምደባ ይዘቱ  50%- 50% መሆኑ ይቀርና እንደየ አስፈላጊነቱ ወደናንተ እንዲያመዝን ይደረጋል ፣ UAT ፣ Exam Result እና መክፈል መቻላችሁ ወሳኝ ነገሮች ናቸው



@freshman_remedials

Freshman and remedial

20 Jan, 23:25


የክልሎች መረጃ


1️⃣አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 21%(ከ10ሺ በላይ) ተማሪዎችን አሳልፏል።

2️⃣ሀረሪ 13.3% (337)

3️⃣ኦሮሚያ 3.5%(8520)

ሁሉም ክልሎች ከአምናው የተሻለ ተማሪ አሳልፈዋል።

💥በአጠቃላይ 1663 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም።

ሀረሪ ውስጥ ሁሉም አሳልፈዋል።💥

አዲስ አበባ 4 ትምህርት ቤቶች ምንም አላሳለፉም።

Freshman and remedial

20 Jan, 23:24


የ12ተኛ ክፍል ውጤት ዛሬ ይፋ ይደረጋል

ትምህርት ሚኒስቴር ከሰዓት መግለጫ ይሰጣል። 8:00 ጠብቁን። ትክክለኛው የሚለቀቅበት ሰዓት ይነገራል።

ውጤት የሚለቀቅበት Website እና Telegram ቦት በጊዜው ይነገራል ተብሏል።

ለሁሉም የ12ተኛ ክፍል ተፈታኞች መልካም እድል🙏

           
@freshman_remedials

Freshman and remedial

20 Jan, 22:28


💫 የጂኒየስነት ቁልፍ ክፍል ሁለት 💫



💫 3ቱ typeዎች a.ፈላጭ ( tired one)
                     b. አይናማው (visual) 
                      c. ጋሽ  ዲሹ (auditor)

አይናማው ...!

° ይሄ ያየውን ነገር በፍፁም የማይረሳ አይነት ተማሪ ነው ። አንድ ፊልም አይቶ አነ እንቅስቃሴው copy የሚያረግ ብትገሉት የማይረሳ አላጋጠጠማችሁም ። ማንበብ ለዚ ተማሪ ጥሩ ነው ግን ችክል ብሎ አይደለም concept ከያዘ በኃላ የተለያዮ አጋዥ ቪዲዮችን ማየት .....ከልጆች ጋር በቀልድ ምናምን ለመያዝ መሞከር ....ነው ብሰግጥም አንተ አትይዝም ...አስተማሪ ሲያስተምር በደንብ አዳምጥ እንቅስቃሴውን ተከታተል አንተ የእውቀት መያዥ አይንህ ነው ። ስታነብ ኖት መፅሀፍ ይጠቅምሃል ምክንያቱም በአይንህ ወደ አዕምሮ ስለሚገባ የሚታይ ነገር ያስፈልግሃል....አንዳንድ ተማሪዎች definition  አይናቸውን ጨፍነው ሲያስታውሱ አላያችሁም በአይናቸው ያስገቡትን እየፈለጉ ነው ። አድክም የሆነ ንባብ አያስፈልግም ትንሽ አንብባችሁ ያነበባችሁትን ወደ አዕምሮ moment እየፈጠራችሁ ማስገባት ነው ።


ፈላጩ ...!.

° ይሄ ካልጣረ ካልለፋ በጭራሽ የማይረዳ አይነት ተማሪ ነው ።አንድን ነገር ፈልጎ ማግኘት የሚያስደስተው በጣም ረጅም ሰዓት ማንበብ የሚገባው በጥረቱ የጎበዘ ተማሪ ነው ። በቃ ፍለጥ ነው ....አስተማሪው ሲያስተምር ምን ቢሰማ ፤ ጓደኞቹ ጋር ቢወያይ ቢጠያየቅ እውቀት አያገኝም ቤት ገብቶ የተማረው ካልሸመደደ ካላነበበ ውስጡ አይቀርም ...እነደዚ አይነት ተማሪዎች ካንፓስ በደንብ ማንበብ ይኖርባቹሃል ቶሎ እንደማትረዱ ከገባቹሁ ልጆች ፈተና ሲደርስ እናነባለን ሲሉ ...እነሱ ፈጣን ስለሆኑ ይሆናል እናንተ ግን አንብቡ በደንብ ልፉ .....መሰገጥ ለእናንተ ነው ።

ዲሽ ጆሮ ......

° አንዳንድ ልጆች ቋንቋዉን የማያቁትን ጠዋት የወጣ ዘፈን ከሰዓት አብረው ሲያዜሙ አልሰማችሁም .....ጆሮዎቸው ነው መላቸው ....የሰሙትን በጭራሽ የማይረሱ ግን ሲያነቡ ቢውሉ ብዙ የማይሳካላቸው ናቸው ። እናንተ ማረግ ያለባችሉ አስተማሪው በደንብ መከታተል የሚለውን እያንዳንዱዋን ነገር መስማት ....ነገርየው የሚሸመደድ ከሆነ ደግሞ ... አስተማሪውን ስልክም ቢሆን ቀድታቹ አዳምጡ .... እንደ እናንተ አይነት ተማሪዎች ፈልጋችሁ ተወያዮ ፥ ሲያወሩ ሰግጣችሁ አዳምጡ ...ጆሮዎቹ ነው መላችሁ ... ለራሳችሁ ያነበባችሁትን  መልሳችሁ ንገሩት .....


አመኑኝ የተባባልነው ካረጋችሁ እና በደንብ ከፀለያችሁ ...የግቢው ዋንጫ የእናንተ ነው ።ነቅንቃችሁ  ፥ ሰቃቅላችሁ ነው የምታልፉት አትፍሩ አቦ አብሽር ።

ክፍል 3 ይቀጥላል.........



@freshman_remedials

Freshman and remedial

20 Jan, 22:28


እንዴት አድርገን ብናጠና ነው ፡ ግቢ ላይ ውጤት መስራት የምንችለው🤔?

💠 አንዳንድ መምህሮች ሙሉ chapter ሩን እንድትፅፋ አድርገው ፈተና የሚያወጡ አሉ። ለምሳሌ ፡ List and describe , explain and discuss ምናምን እያለ handout ቱ ላይ ያሉትን ኖቶች እንድትፅፋ አድርጎ የሚያወጣ መምህር አለ።

💠 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ concept ጥያቄ የሚያወጡ አሉ። የ እናንተን የመረዳት ችሎታ የሚጠይቁ ጥያቄዎችን የሚያወጡ መምህሮች አሉ።

💠 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ case ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ። የ case ጥያቄዎች ደግሞ የእናንተን የመረዳት ፡ የማብራራት ፡ እና ተግባራዊነት የሚጠይቁ ናቸው።

ስለዚህ እንዴት እናብብ🤔

🔔 የመጀመሪያው ፈተና ላይ መምህሩ ምን አይነት የፈተና አወጣጥ ስታይል እንዳለው አታውቁም🤷‍♂️

➡️ከመጀመሪያው ፈተና በሗላ ግን የመምህሩን የፈተና አወጣጥ ስታይል ማወቅ ትችላላችሁ። ስለዚህ

🔸 የ ሽምደዳ ጥያቄዎችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በዛው ልክ handout ቱን በ straw ምጥጥ አድርጋችሁ ማንበብ ነው። በርግጥ ሽምደዳ boring ነው ፡ በተለያየ ስልት አንብባችሁ መያዝ ነው።

🔹 መምህሩ የ concept ጥያቄችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በቻላችሁ መጠን የብልጠት አነባበብ መከተል ነው። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ብላችሁ አንብቡ።

🔺 የ case ጥያቄዎች ከበድ ይላሉ ። ስለዚህ ስታነቡ ፡ የምታነቡት ትምህርት ተግባራዊ እውነታውን ማወቅ ፡ የት የት ቦታ apply እንደሚደረግ ፡ advantage and disadvantage ን ማወቅ ። ከዛ በዚህ መሰረት ማብራራት ነው ከእናንተ የሚጠበቀው።

🔸 ስለዚህ የአጠናን ስልታችሁ እንደመምህሩ ፈተና አወጣጥ ቢሆን ብለን እንመክራለን።

     🔺የጊዜ አጠቃቀም

🔻ሌላኛው ና መሰረታዊ ነገር ጊዜያችሁን በአግባቡ የመጠቀም ጉዳይ ነው። ምንድን መሰላችሁ ፡ ብዙዎቻችን ቆይ ነገ አነበዋለሁ ፡ ቆይ ቡሗላ አነበዋለሁ እያልን የመዘናጋት አባዜ አለብን። ይህ ደግሞ የምናነባቸው ትምህርቶች እንዲደራረቡን ያደርጋል። ከ ተደራረቡብን ደግሞ በ tension ልንጨልል እንችላለን። ስለዚህ በተቻለን መጠን ፡ ሳንዘናጋ ፈተናዎች ከመድረሳቸው በፊት ብናነብ መልካም ነው።

      🔸 አለመሰልቸት

🔹ግቢ ላይ ፈተናዎች ፡ አሳይመንቶች ፡ ፕሮጀክቶች ይደራረባሉ። በተለይ በቀጣይ ወደ ግቢ የምትገቡ ፍሬሽ ተማሪዎች ፡ ለ እያንዳንዱ ሴሚስተር የሚሰጣችሁ ጊዜ አጭር ነው። በዚህ ምክንያት ፈተና ቶሎ ቶሎ ነው የምትፈተኑት ፡ አሳይመንት ተደራርቦ ነው የሚሰጣችሁ። ምናልባት ዛሬ ተፈትናችሁ ፡ ነገም ሌላ ፈተና ትፈተናላችሁ ። ከፈተና እንደተመለሳችሁ አሳይመንት ልትሰሩ ትችላላችሁ ምናምን። እና ይኸ መደራረብ መሰልቸን ያመጣል። ስለዚህ ፅኑ መሆን ይጠበቅባችሗል።

   🔸ከመምህር ጋር ሰላማዊ መሆን።

🔻ሁሉንም ማለት ባይቻልም የግቢ መምህሮች ባህሪያቸው አስቸጋሪ ነው። በቻላችሁ መጠን ከመምህራኖቻችሁ ጋር ሰላማዊ መሆን ፡ በትህትና መነጋገር ፡ ለመምህሩ የሚመች ክላስ መፍጠር አለባችሁ። ከመምህር ጋር የምትንገራገጩ ከሆነ ግን ፡ ሆን ብሎ ውጤታችን ያወርድባችሗል። ብዙ ገጠመኝ ስለማውቅ ነው በዚህ ጉዳይ።

  🌐  Google

🔺ለ ግቢ Google በጣም ወሳኝ ነገር ነው። Assignment መስራት ብትፈልጉ ፡ practical education በ video  ማየት ብትፈልጉ ፡ የተለያዩ መፅሀፎችን እና የመፅሀፍ solution ማውረድ ብትፈልጉ ፡ ምናልባት መምህሩ የሰጣችሁ ኖት ካልገባችሁ እና ሳይንሱን መረዳት ብትፈልጉ ፡ Google ለነዚህ ሁሉ በቂ መፍትሔ አለው። ስለዚህ Google ን የቅርብ ወዳጅ አድርጋችሁ ወጤት መስራት ትችላላችሁ ፡ ሳይንሱን መረዳት ትችላላችሁ። በዚሁ አጋጣሚ ለ Google ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ😘

          😊 The End


@freshman_remedials

Freshman and remedial

20 Jan, 22:23


🤓 የጂኒየስነት ሚስጥር ክፍል አንድ.....!

🎓ብዙዎች ካንፓስ መስቀል ይፈልጋሉ ግን እንዴት   መንገዱን አያቁትም🙂  መንገዱ ቀላል ነው ። የእናንተ አነባብ ሰዎች ባረጉት ሳይሆን በግል ሙዳቹሁ መሰረት መሆን አለበት ። መጀመርያ እናንተ የትኛው ተማሪ ነኝ ብላቹሁ ጠይቁ ። ስለ 3ቱ የተማሪ አይነቶች ታውቃላችሁ ...ቀላል ነው ምኖ አይነት ተማሪ ነኝ የሚለው ለማወቅ ቀጣዮቹ 6 ጥያቄዎች በጥንቃቄ አይታችሁ መልሱ ። (እባካችሁ ዝም ብላችሁ አይታችሁ አትለፉ የምር ራሳችሁን ጠይቁና መልሱ ...!🤫)

የሚከተሉትን ጥያቄዎች  ከ a-c ምረጡ እና ወረቀት ላይ ፃፉ ።

1. አንድ ዘፈን አዳምጦ ግጥሙን ለመያዝ ስንት ቀን ይፈጅባቹሃል?

      a.3   b. 2  c .1

2. አንድ ፊልም አይታችሁ ለምን ያክል ግዜ  ሳትረሱ ታስታውሳላችሁ ?

   a.2ቀን   b .ለአመታት   c.ወር

3.ነገሮች እንዴት መሸምደድ ይቀላቹሃል

a.ቀጥታ ነገርየውን መሸምደድ
b ከነገሮች ጋር አያይዞ ምናምን ..(እንደ period tables  ሮኒ ከረባት አርጎ ..ምናምን ..)
c. ሽምደዳ ሚባል አያስደስተኝ መያዝም አልችልም

4.አንድ መፅሀፍ ትረካ ብትሰሙ ፥ ብታነቡት ወይስ በፊልም መልኩ ቢሰራ ለማስታወስ ይቀላቹሃል ..?

a.መፅሀፍ
b.ፊልም
c.ትረካ

5. ከነዚህ ውስጥ የምትወዱት የስራ ዘርፍ የቱ ነው ...?

a.የጉልበት ስራ ...ስፓርት ምናምን ....!

b. ደራሲነት..ጋዜጠኝነት ...

c.ሳይካትሪስት ...ጠበቃ...ዳኛ


ከአምስቱ ምን ያክል a b c አመጣችሁ? 3 በላይ ab c ካመጣችቹ TYpeቹሁን ለማወቅ አሪፍ ነው ። በደንብ መልሱ ።

✌️ክፍል 2 ይቀጥላል.........

@freshman_remedials

Freshman and remedial

20 Jan, 22:14


በጣም ብዙዎቻችሁ እየጠየቃችሁን ስለሆነ ዮኒቨርስቲዎቻችን ከመጀመሪያ ትውልድ ዩኒቨርስቲዎች እስከ 4ተኛው ትውልድ ድረስ  አስቀምጠንላቹሃል ።

ለመሆኑ የዩኒቨርስቲዎች የ ትዉልድ ደረጃ ምንድነው?

የዩኒቨርስቲዎች የ ትዉልድ ደረጃ በ አመሰራርት የጊዜ ሂደት ዩኒቨርስቲዎችን በቅደም ተከትል እንደአንጋፋነታቸው የማስቀምጥ ሂደት ነው።ከተመሰረቱ ብዙ አመታትን ያስቆጠሩ ዩንቨርስቲዎች ብዙ ነገሮችን ያሟላሉ ተብሎ ስለሚታሰብ በብዙዎች ዘንድ ተመራጭ ያደርጋቸዋል


1⃣ኛ_ትውልድ

  ✔️ addis ababa university
  ✔️Arba Minch University
  ✔️Bahirdar University.
  ✔️University of Gondar
  ✔️Hawassa University
  ✔️Haramaya University
  ✔️Jimma University
  ✔️Mekele University


2⃣ኛ ትውልድ ዩኒቨርስቲዎች ፦

   ✔️ Dila University
   ✔️ Dire dawa University
   ✔️Jijiga University
   ✔️ Mede welabo University
   ✔️ASTU
   ✔️Debra Markos University
   ✔️Aksum University
   ✔️Debra Birhan University
   ✔️Wollega University
   ✔️Wollo University
   ✔️Mizan Teppi University
   ✔️Mekdela Amba University
   ✔️Ambo University
   ✔️ Semera University
  ✔️ kotebe motrop. University

  የ 3⃣ኛ ትውልድ ዩኒቨርስቲዎች

  ✔️Adigrat University
  ✔️Mattu University
  ✔️Woldia University
  ✔️Wolkite University
  ✔️Debratebor University
  ✔️Wachamo University
  ✔️Assosa University
  ✔️Aastu University
  ✔️Arsi University
  ✔️ Gambela University
  ✔️ bulehora University
  ✔️ walita sodo university

4⃣ኛ_ትውልድ_

✔️Jinka University
✔️Bonga University
✔️Worabe University
✔️Injibara University
✔️Debark University
✔️Mekdela Amba University
✔️Raya University
✔️Dembidolo University
✔️Selale University
✔️Oda Bultum University
✔️ Borna university

Freshman and remedial

20 Jan, 21:51


🖊 በቀጣይ ዩኒቨርሲቲ የምትገቡ የ ማህበራዊ ሳይንስ(social science) ተማሪዎች የ መጀመሪያው ሴሚስተር ላይ ስለምትወስዷቸው ኮርሶች መረጃ።

🥰 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ አመት የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ የምትወስዷቸው ኮርሶች👇

💠 Communicative English Skill I

💠 Economics

💠 Geography

💠 Maths(Social)

💠 Civics and Moral Education

💠 Global Trends

💠 Physical Fitness

🙌 አሁን ደግሞ ስለ እያንዳንዱ ኮርስ መጠነኛ የሆነ ገለፃ ወይም ጅንጀና እናድርግ።

የተወሰኑት ኮርሶች ከnatural ጋር ተመሳሳይ ስለሆነ ባለፈው ፖስት ያረግነውን ማየት ትችላላችሁ


💻 Economics

📚 ግቢ ላይ ብዙ ሰቃይ ተማሪዎች Economics ን አይሰሩትም🙇‍♂️። 3.7 or 3.8 ያላቸው ልጆች Economics ን B- ምናምን ነው የሚያመጡት። ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው ግቢ ላይ የ Economics ትምህርት ፈተናዎች ወይም ጥያቄዎች conceptual ናቸው። ስለዚህ Economics ን ስታነቡ አትሸምድዱ። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ሞክሩ ፡ ተግባራዊ እውነታውን ተረዱ።ከኛ ጋር ከሆናችሁ ደሞ እመኑን A+ ታመጣላችሁ 😎


💻 Maths (Social)

📚 ከ መጠነኛ ለውጥ ( modification) ውጭ 11 እና 12 የተማራችሁት ነው። 📚 በይበልጥ ፈተና ሲውጣ Basic ነገር ነው የሚያወጡት Module ማንበብ ለዚ ግዜ በጣም ወሳኝ ነው Module በደምብ ሳታነቡ Reference እንዳገልጡ አደራ Defintion , Properties , Exercises ..... module ላይ ያለውን በደምብ ያዙ የሚሰጣቹ Course outline ላይ ያለውንም ነጥብ በደምብ ተመልከቱ ምን ላይ ማተኮር እንዳለባቹ ይረዳቹሀል::

💻 Civics and Moral Education

📚 ዩኒቨርሲቲ ላይ የሚሰጠው የ Civics and Moral Education ኮርስ ፤ Highschool ና pre paratory ከሚሰጠው ኮርስ ጋ በፍፁም አይገናኝም። ግቢ ላይ ያለው የ Civics ኮርስ ለተማሪዎች የሚያስቸግር ከባድ ኮርስ ነው። ይህ ኮርስ በተለይ ስለ Ethics ና Morality ምንነት በስፋት ያትታል። ከ Ethics ጋ የተያያዙ የ ሞራል ፍልስፍናዎችን ና ንድፈሀሳቦችን በስፋት ይዳስሳል። በተለይ ስለ Normative ና non-normative Ethics, Teleological Ethics, Ethical Egoism and psychological Egoism, Altruism, Utilitarianism, Quality over quantity Ethics, Quantity over quality Ethics, Act and Rule Utilitarianism, Virtue Ethics, Meta Ethics በጣም በስፋት ይዳስሳል። እንዲሁም ደግሞ ስለ state, government ና citizenship ምንነት በስፋት ያጠናል በተለይ ስለ pluralist state, capitalist state, Leviathan state, Patriarchal state, minimal state, developmental state,social-democratic state, collectivized state, totalitarian state, religious state ና ስለ Citizenship በጣም በስፋት ያጠናል። አይዞዓቹ እኛ አለንላችሁ 🥸

🥸 የ ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች first semester course እነዚህ ናቸው። በቀጣይ የእነዚህን ኮርሶች መፅሀፍ በ pdf እንለቅላችሗለን።

Freshman and remedial

20 Jan, 21:49


ግቢ ውስጥ Grade እንዴት ነው ሚሰራው 🤔

⭐️ GPA or CGPA ምን ማለት ነው ላላችሁኝ 😍

ጉድ የማያልቅበት ትምህርት ሚንስተር የሚያወጣው አዲስ ህግ እስካልኖረ ድረስ የሁሉም ግቢዎች grading system ተመሳሳይ ነበር

በእያንዳንዱ ሴሚስተር

⏺️ Out of 20 or 30% Test, Quizzes , group work or Assignment

⏺️ Out of 20 or 30 % MID EXAM

⏺️ Out of 50% Final Exam

ለእያንዳንዱ ኮርስ የሶስቱ ድምር ውጤት ሴሚስተር መጨረሻ ላይ ይደመርና ለጠቅላላ ኮርሶቹ ተካፍሎ ግሬድ ይሰራላቹሃል ።

የስድስቱም ኮርሶች ድምር Garde ከተሰራ በኋላ የምታስመዘግቡት ውጤት የትምህርት መስክ ለመምረጥ ትምህርት ሚኒስተር ባወጣው range ልክ value ይኖረዋል ።

GPA ማለት በሁሉም ሴሚስተር የምታስመዘግቡት ግሬድ ማለት ነው

CGPA ማለት Average Grade ማለት ነው።

🔔 በመጀመሪያው ሴሚስተር የተጠቀሱትን አምስት የትምህርት መስኮች join ለማድረግ የምትፈልጉ ተማሪዎች ለውድድር የሚታየው first semister GPA ብቻ ይሆናል ፤ የተቀሩትን የትምህርት መስኮች join ማድረግ የምትፈልጉ ተማሪዎች ግን የሚያዝላቹህ የሁለቱም ሴሚስተር Average or CGPA ይሆናል ማለት ነው።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር አለ የተባለው ወይም ትላንት Post ያደረኩላቹህ 20% entrance , 30% PRE-FEILD ምናምን የተባለውን ነገር በሁሉም ዩንቨርሲቲዎች ላይ በዚህ ዓመት ተግባራዊ ሆነም አልሆነ የመጀመሪያ ሴሚስተር ግሬድ ግን ማንኛውንም የትምህርት መስክ ለመምረጥ ትልቁን ድርሻ ይይዝላቹሃል ፡ ስለሆነም 20%ቷ እውን ከሆነች entrance exam ስለተበላሸብኝ ብላቹህ ተስፋ አትቁረጡ ፤ ሲጀመር 20% ምናምን የተባለው ጉዳይ የሚኒስተር መስሪያ ቤቱ ማህተምና የክብርት ሚኒስተሯ ፊርማ ስላረፈበት አስደንግጦኝ Post አደረኩላቹህ እንጂ እስካሁን 100% እርግጠኛ ሆኖ ለማውራት የሚያስደፍር ማረጋገጫ ከበላይ አካላት አልደረሰንም ፤ ትምህርት ሚኒስተርም ተማሪው ሁለት ልብ ሆኖ እየጨለለ ባለበት ባሁኑ ወቅት ምንም አይነት ማስተባበያ አልያም ማረጋገጫ አለመስጠቱ አስከፍቶኛል ።

ለማንኛውም ግን በውስጥ መስመር ብዙ ተማሪዎች የዩንቨርሲቲ ግሬድ calculation አልገባንም ባላችሁኝ መሰረት ከአራት ወራት በፊት post ያደረኩላችሁን በድጋሚ ለማስታወስ እገደዳለሁ

For instance AAU first semister coursoch እነዚህ ናቸው ብንልና የኮርሶቹም ECTS እንደሚከተለው ቢሆን

♨️Critical thinking......
#5Ects
Psychology...........
#5Ects
♨️ General Physics.
#5Ects
English ..............
#5Ects
♨️Geography ..........
#5Ects
♨️Mathematics......# 6Ects
♨️Physical fitness (pass or fail)
✍️Total credit hours
#31Ects

ተማሪ አለባቸው ደብድባቸው እርገጣቸው😂 የተባለ ተማሪ በመጀመሪያው ሴሚስተር ያስመዘገበው ውጤት

1) Critical thinking-------> 77 🔫B+
2) Psychology ---------->82 🔫A-
3) Gen' Physics --------->59.9🔫C
4) Mathematics---------->42 🔫D
5) English ------------>68 🔫B-
6) Geography ------------->64 🔫C+

ነው ብንል የተማሪ ሙጃን ግሬድ እንደሚከተለው ማወቅ ይቻላል

በቅደም ተከተል calculate ማድረግ
🔍 Credit hour × grade

5×3.5 =17.5
5×3.75 =18.75
5×2 =8
6×1 =6
5×2.75 =13.75
5×2.5 = 12.5

Total sum=76.5
Semister grade = Total sum÷Total credit hour
76.5÷31=2.467GPA
ስለዚህ ተማሪ ሙጃ በመጀመሪያው ሴሚስተር የሰራው ግሬድ 2.46 ነው ማለት ነው ።


Status of first year students in the first semister ፤ የአንደኛ አመት ተማሪዎች በመጀመሪያው ሴሚስተር የሚያስመዘግቡት ግሬድ እንደሚከተለው ወደ ቀጣዩ ሴሚስተር Pass or Fail ያስብላቸዋል


GPA Status
1.75-4.00 ➡️Promoted
1.50-1.75 ➡️Warning
1.00-1.50 🔫Academic dismissal( ለአንድ ዓመት ላግ )

0.00-1.00 Complete dismissal ከትምህርት ዓለም ሙሉ በሙሉ ላግ 😤)

ከዚህ ውጭ ደግሞ በአንድ ሴሚስተር ሶስት ኮርሶች የፈሉበት ተማሪ ሴሚስተር ላግ ይኖርበታል ምናምን የሚባልም ነገር አለ ቢሆንም ግን የኛ ቤተሰቦች ሁሉም ለሜዲስን ስለሚቸክሉ F ምናምን እንደማያሳስባቸው ይሰማኛል 🧛‍♂️

ከላይ የጠቀስኩላቹህ የግሬድ አሰራር ካልገባቹህ ደግማቹህ አንብቡትና በድጋሚ ካልገባቹህ ባቅራቢያቹህ የሚገኙ ነባር ተማሪዎችን refer አድርጉ ።

Join and share

Freshman and remedial

20 Jan, 21:38


#update
#Result #Remedial #Exit_Exam

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና እና የሪሚዲያል ማጠቃለያ ፈተና ውጤቶች መቼ ይፋ ይደረጋሉ?

ቲክቫህ ዩንቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር አመራር አገኘሁት ብሎ ያጋራው መረጃ👇

📌 የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ውጤት ከሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት በጣም ከዘገየ እስከ
#ሰኞ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይፋ ይሆናል።

📌 የመውጫ ፈተና ውጤት በቀጣይ ቀናት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቅ ከመጀመራቸው
#በፊት ይፋ ይደረጋል።

Freshman and remedial

20 Jan, 21:35


#Update

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ውጤት ከመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ይፋ እንደሚደረግ ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል።

የፈተናው ውጤት መቼ ይፋ እንደሚደረግ በርካታ ተማሪዎች ጥያቄያቸውን አድርሰውናል።

የፈተናው ውጤት መቼ ይገለፃል ስንል የጠየቅናቸው የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር፤ "በቅርቡ፥ ከመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት" ሲሉ መልሰውልናል።

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ከሰኔ 3-11/2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።

Freshman and remedial

20 Jan, 21:04


CHEMISTRY FOR PRE REMEDIAL PROGRAM STUDENTS EXAM 💯