FastMereja.net2

@fastmerejaa


FastMereja.net

FastMereja.net2

23 Oct, 08:39


የጀርመን ፖሊስ በጎን ኮኬይን እያቀረበ ነው ያለውን የፒዛ ሬስቶራንት ወረረ
https://www.bbc.com/amharic/articles/c30p3pjjj97o

የጀርመን ፖሊስ ለደንበኞቹ ከፒዛ ጋር በጎን ኮኬይን እያቀረበ ነው ያለውን የፒዛ ሬስቶራንት ወረረ።

FastMereja.net2

23 Oct, 08:38


በሱዳን አንድ አውሮፕላን ተመትቶ መውደቁን ተከትሎ ሩሲያውያን ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተነገረ
https://www.bbc.com/amharic/articles/c2k0jd9dl82o

በሱዳን ምዕራብ ዳርፉር አካባቢ አንድ ዕቃ ጫኝ አንቶኖቭ በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ተመትቶ መውደቁን ተከትሎ የሩሲያ የበረራ ሰራተኞች ጭምር ሳይገደሉ እንዳልቀረ ተነግሯል።

FastMereja.net2

23 Oct, 08:37


ትራምፕ የዩኬ ገዢ ፓርቲ በአሜሪካ ምርጫ ጣልቃ ገብቷል ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ
https://www.bbc.com/amharic/articles/c5y583r211ro

የሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩናይትድን ኪንግደም ገዢ ሌበር ፓርቲ ለካማላ ሃሪስ ድጋፍ በማድረግ ጣልቃ እየገባ ነው ሲሉ ለአሜሪካ የፌደራል ምርጫ ኮሚሽን አቤቱታ አቀረቡ።

FastMereja.net2

23 Oct, 04:08


ለዘጠኝ ዓመታት በሐተኛ ማንነት በኢንተርኔት የተታለለችው አፍቃሪ
https://www.bbc.com/amharic/articles/cdd4d7g34n8o

ሁሉ ነገር የተጀመረው በፌስቡክ ጓደኛ እንሁን በሚል ጥያቄ ነበር። ለለንደን ነዋሪዋ ኪራት አሲ የልብ ሐኪሙ እና መልከ መልካሙ ቦቢ ያቀረበላት ጓደኛ እንሁን ጥያቄ ለየት ያለ ነበር። ወዲያውኑም ነበር ማውራት የጀመሩት።

FastMereja.net2

23 Oct, 04:07


አዲስ አበባ፣ ጅማ፣ ጎንደር፣ መቀለ፣ ሲዳማ፣ ድሬ ዳዋ - በጣልያኗ ሮም እንዴት የመንገዶች ስያሜ ሊሆኑ ቻሉ?
https://www.bbc.com/amharic/articles/cd6y6px7v4do

ጣልያን በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛቷ ስር ለማስገባት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ብታደርግም አልተሳካላትም። ነገር ግን በአምስት ዓመቱ የወረራ ዘመኗ በተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች ውስጥ አሁን ድረስ የዘለቀ አሻራዋን ያሳረፈች ሲሆን፣ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ አሻራም በጣልን ከተሞች በጉልህ ይታያል። ጥቂት የማይባሉ የጣልያን የመንገዶች እና አደባባዮች በኢትዮጵያ ከተሞች እና አካባቢዎች ስም ይጠራሉ።

FastMereja.net2

22 Oct, 23:20


የአይ ኤም ኤፍ እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ጉባኤ
https://amharic.voanews.com/a/7832874.html

ዓመታዊው የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤም ኤፍ)ና የዓለም ባንክ ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ ተጀምሯል። 


ኢትዮጵያን ጨምሮ የአባል ሃገራቱ የገንዘብ ሚንስትሮችና የብሄራዊ ባንክ ገዥዎች የሚሳተፉበት ነው።


የኢኮኖሚና ኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ያሬድ ሃይለመስቀል ይህ ጉባኤ የዓለም ኢኮኖሚ በተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ጦርነቶች እየተፈተነ ባለበት ወቅት የሚካሄድ ነው ይላሉ።


/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/ 

FastMereja.net2

22 Oct, 23:19


የሠራተኛ ማኅበራት ድጋፍ በዩናይትድ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ያለው ከፍተኛ ሚና
https://amharic.voanews.com/a/e24-1022-trump-harris-union-voters/7832808.html

በመላዋ ዩናይትድ ስቴትስ ወደ14 ሚሊዮን የሚሆኑት መራጮች መብታቸውን ለማስከበር በተቋቋሙ ማኅበራት የተደራጁ ሠራተኞች ናቸው። ከአጠቃላዩ መራጭ ቁጥር አኳያ ሲታይ ቁጥራቸው አነስተኛ ቢሆንም ፕሬዚደንታዊ ዕጩ ተፎካካሪዎች ድጋፋቸውን በእጅጉ ይፈልጉታል።


የአሜሪካ ድምጿ የምክር ቤታዊ ጉዳዮች ዘጋቢ ካትሪን ጂፕሰን በዘንድሮ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የሠራተኛ ማኅበራት ድምጽ ትልቅ ሚና የሚጫወትባት ከሆነችው ከኔቫዳ ክፍለ ግዛት ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

FastMereja.net2

22 Oct, 19:51


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 11 ፓርቲዎችን በጊዜያዊነት አገደ
https://amharic.voanews.com/a/7832739.html

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ "በጠቅላላ ጉባኤ፣ በኦዲት እና በሴት አባላት አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋራ በተያያዘ፣ 11 የፖለቲካ ፓርቲዎችን በጊዜያውነት ማገዱን ትላንት ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. በጻፈው እና በፌስቡክ ገጹ ይፋ ባደረገው ደብዳቤ አስታውቋል።


ቦርዱ የእግድ ውሳኔ ካሳለፈባቸው ፓርቲዎች መካከል የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የጌዲኦ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የሐረዲ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የገዳ ሥርዓት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ፣ የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ የጋምቤላ ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ኅብረት እና አገው ለፍትህና ዲሞክራሲ ፓርቲ ይገኙበታል። 


ፓርቲው እግዱን አስመልክቶ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋር ምክር ቤት በጻፈው በዚሁ ደብዳቤ፣ ቦርዱ የተለየ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ፣ ፓርቲዎቹ ከማንኛውም ሕጋዊ እንቅስቃሴ ታቅበው እንዲቆዩ ትዕዛዝ አስተላልፏል። 


በመሆኑም የተዘረዘሩት ፓርቲዎች የተጣለባቸው የእግድ ውሳኔ እስከሚነሳ ድረስ፣ በማናቸውም የጋራ ምክር ቤቱ የሚያዘጋጃቸው ጉባኤዎች ላይ ሊገኙ፣ ሊመርጡ፣ ሊመረጡ ወይም በተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ ሊያገለግሉ እንደማይችሉ ቦርዱ ጨምሮ ገልጿል። 


እስካሁን ስማቸው ከተጠቀሰው ፓርቲዎች በኩል የወጣ መግለጫም ሆነ የተሰጠ አስተያየት የለም።

FastMereja.net2

22 Oct, 19:50


ፑቲን የምዕራባውያንን ተጽዕኖ ለመቋቋም የታለመውን ‘የብሪክስ አባል ሃገራት’ ጉባኤ እያስተናገዱ ነው
https://amharic.voanews.com/a/putin-hosts-global-south-leaders-at-brics-summit-meant-to-counterbalance-western-clout/7832663.html

የቻይናው ሺ ጂንፒንግ፣ የሕንዱ ናሬንድራ ሞዲ እና ሌሎች የዓለም መሪዎች በቡድኑ ጉባኤ ለመሳተፍ ዛሬ ማክሰኞ ከሩሲያዋ የካዛን ከተማ ገብተዋል።


በርካታ በመልማት ላይ ያሉ አገሮች በአባልነት የሚገኙበት ‘ብሪክስ’ በሩስያ የሚያካሂደውን ይህን ጉባኤ፤ ክሬምሊን በዓለሙ መድረክ ምዕራባውያን ያላቸውን ተጽዕኖ ለመቋቋም በያዘው ጥረት እንደሚያግዘው ተሥፋ ጥሎበታል።


ለሦስት ቀናት የሚዘልቀው ጉባኤ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ በዩክሬን የፈጸሙትን ወራራ ተከትሎ ሞስኮን ለማግለል ዩናይትድ ስቴትስ መሩ ዓለም አቀፍ ጥምረት ተስፋ ያደረገውን ጥረት ያህል እንዳልሰመረለት በጠንካራ ማሳያነት ይጠቀሙበታል ተብሎ ታምኗል።


የክሬምሊን የውጭ ጉዳይ አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ በሰጡት አስተያየት 36 ሃገራት የሚሳተፉበትን እና ከ20 በላይ የሚሆኑት በመሪዎቻቸው የሚወከሉበትን ጉባኤ "ሩስያ ውስጥ ከተካሄዱ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች ላይ ያተኮሩ መድረኮች ሁሉ ግዙፉ" ብለውታል።


ሲመሰረት ብራዚልን፣ ሩሲያን፣ ህንድን፣ ቻይናን እና ደቡብ አፍሪካን ያቀፈው ሕብረት ኢራንን፣ ግብፅን፣ ኢትዮጵያን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን እና ሳዑዲ አረቢያን ጨምሮ በፍጥነት ወደ ገዘፈ ቡድንነት መሸጋገሩ ይታወሳል። ቱርክ፣ አዘርባጃን እና ማሌዢያም በተመሳሳይ አባል ለመሆን በይፋ ሲያመለክቱ፤ ሌሎች ጥቂት አገሮችም ቡድኑን ለመቀላቀል ያላቸውን ፍላጎት አሳይተዋል።


ታዛቢዎች ጉባኤውን ሩስያ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ያላት ግንኙነት ይበልጥ እየተባባሰ በመጣበት በአሁኑ ወቅት፤ ‘የደቡቡ ዓለም ከተባሉት አገራት’ ያላትን ድጋፍ ለማሳየት የያዘችው ጥረት እና ምጣኔ ሃብታዊ ግንኙነቶቿን ለማስፋት የሚረዳ አድርገው ይመለከቱታል።


ከዋናው ጉባዔ በትይዩ 20 ከሚሆኑ አገራት መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ንግግር እንደሚያደርጉ የተገለጸው ፑቲን፤ እስካሁን ከህንዱ መሪ ሞዲ እና ከደቡብ አፍሪቃው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል። ዘግየት ብሎም ከቻይናው ሺ ጋር ይነጋገራሉ።


ፑቲን ከነገ በስቲያ ሐሙስ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ጋር ተገናኝተው ይነጋገራሉ። ጉቴሬዥ ሩሲያ በዩክሬን እያካሄደች ያለውን ጦርነት በተደጋጋሚ መተቸታቸው ይታወቃል። የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ሩስያ ሲጎበኙ ያሁኑ የመጀመሪያቸው ይሆናል።

FastMereja.net2

22 Oct, 19:49


በመርካቶው የእሳት አደጋ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ
https://amharic.voanews.com/a/addis-ababa-fire/7832585.html

ትላንት ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. አዲስ አበባ መርካቶ ውስጥ በደረሰው የእሳት አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን፣ የከተማዋ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። መርካቶ “ሸማ ተራ” በሚባለው አካባቢ የደረሰውን የእሳት አደጋ ለማጥፋት ስድስት ሰዓታት መፍጀቱን፣ የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ንጋቱ ማሞ ለቪኦኤ ገልጸዋል።


ከአደጋው ጋራ በተያያዘ በሰባት ሰዎች ላይ ቀላልን በሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዛሬ በአወጣው መግለጫ አስታውቋል። የከተማዋ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በእሳት አደጋው የሞተ ሰው እንደሌለ የተናገሩት የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ንጋቱ በበኩላቸው፣ የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ ፖሊስ በማጣራት ላይ መሆኑን አመልክተዋል።


እሳቱ በአካባቢው በፍጥነት በመዛመቱ፣ ጉዳቱን ጨምሮታል ያሉት አቶ ንጋቱ፣ አደጋውን ለመቆጣጠር ስድስት ሰዓታት የፈጀ ጥረት መደረጉን ተናግረዋል፡፡ በአካባቢው የነበሩት ኹኔታዎች የእሳት ማጥፋት ሥራውን አስቸጋሪ እንዳደረጉትም ገልፀዋል፡፡


የእሳት ማጥፋት ሥራው፣ ከአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አቅም በላይ ሆኖ እንደነበር አቶ ንጋቱ ማሞ ጠቅሰው፣ ተቋሙ የሌሎችን ድጋፍ በመጠየቁ በተለያዩ አካላት ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቀዋል፡፡


የአዲስ አበባ ፖሊስ የእሳት አደጋውን መንስኤ ለማጣራት ከፌዴራል ፖሊስ ጋራ በመተባበር የምርመራ ሥራ መጀመሩን ገልፆዋል፡፡ አደጋውን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎችን ይዞ እየመረመረ እንደሆነም አመልክቷል፡፡ የአሜሪካ ድምፅ፣ ወደ አካባቢው ተንቀሳቅሶ፣ ኹኔታውን ለመመልከትና ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ለማነጋገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ ከሰሞኑ የሚመለከታቸውን ኃላፊዎች በማስፈቀድና በአካባቢው ያሉ ተጎጅዎችን በማነጋገር ሰፋ ባለ ዘገባ እንመለሳለን፡፡

FastMereja.net2

22 Oct, 19:48


ብሊንከን በጋዛ እና በሊባኖስ ላለው ግጭት እልባት ፍለጋ ዛሬ እስራኤል ገቡ
https://amharic.voanews.com/a/israel-lebanon-gaza-/7832442.html

የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን የተቀዛቀዘውን የተኩስ አቁም ንግግር ለማነቃቃት፣ የተጠናከረ የሰብአዊ ርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ ለማድረግ እና ብሎም በሊባኖስ በእስራኤል እና በሂዝቦላ መካከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ለማርገብ በታለሙ ውጥኖች ዙሪያ ለመነጋገር ዛሬ ከእስራኤል መሪዎች ጋር ይገናኛሉ። 


ብሊንከን የመስከረም 26ቱን የሃማስ ጥቃት ተከትሎ ጋዛ ውስጥ ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ 11ኛቸው በሆነው የመካከለኛው ምስራቅ ጉዟቸው ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና ከመከላከያ ሚኒስትራቸው ዮአቭ ጋላንት ጋራ ተገናኛተው ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል። 


ከተባሉት ንግግሮች ጥቂት ሰዓታት አስቀድሞ ሂዝቦላ በቴላቪቭ እና ሃይፋ አቅራቢያ በሚገኙ የእስራኤል ጦር ሠፈሮች ላይ ሮኬቶችን መተኮሱን ሲገልጽ፤ እስራኤል በበኩሏ ከሊባኖስ በኩል የተተኮሱትን ተወንጫፊዎች ማምከኗን አስታውቃለች።


ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው ዕለት ቤይሩት ውስጥ ከሚገኘው ዋናው የመንግሥት ሆስፒታል አቅራቢያ እስራኤል በሰነዘረችው ጥቃት 13 ሰዎች ሲገደሉ፤ ሌሎች 57 መቁሰላቸውን የሊባኖስ የጤና ጥበቃ ሚንስቴር አስታውቀዋል።


በአንጻሩ የእስራኤል ጦር የቡድኑን የባሕር ኃይል ማዕከላዊ ጣቢያ ጨምሮ ቤይሩት ውስጥ በርካታ የሂዝቦላህ ዒላማዎችን መምታቱን ይፋ አድርጓል።

FastMereja.net2

22 Oct, 13:05


አውስትራሊያዊቷ የወደቀባትን ስልክ ለማንሳት ስትሞክር በአለት ስንጥቅ መካከል ተቀረቀረች
https://www.bbc.com/amharic/articles/cvgwgjkxexjo

በአውስትራሊያ በአለቶች መካከል የወደቀባትን ስልክ ለማውጣት የሞከረች ሴት ተንሸራትታ በጭንቅላቷ ተዘቅዝቃ በመውደቅ ለሰዓታት ተጣብቃ መቆየቷ ተሰማ።

FastMereja.net2

22 Oct, 13:04


ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎችን የዕውቅና ምስክር ወረቀት ክፍያ ከ200 ብር ወደ 30 ሺህ ብር አሳደገ
https://www.bbc.com/amharic/articles/c8djdy341djo

አዲስ የሚመሠረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተመዝግበው “የሙሉ ዕውቅና” የምስክር ወረቀት ለማግኘት ሲጠየቁ የነበረው የ200 ብር ክፍያ ወደ 30 ሺህ ብር አደገ። በአዲሱ የምርጫ ቦርድ የክፍያ ተመን መሠረት አዲስ የሚቋቋሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጊዜያዊ እና ሙሉ የዕውቅና ምስክር ወረቀቶችን ለማግኘት 45 ሺህ ብር መክፈል ይጠበቅባቸዋል።

FastMereja.net2

22 Oct, 13:03


እስራኤል ኢራንን ለማጥቃት የምታደርገውን ዝግጅት ያጋለጡት ምሥጢራዊ ሰነዶች ምን ይዘዋል?
https://www.bbc.com/amharic/articles/cwyvyl6ze16o

የአሜሪካ መርማሪዎች ሁለት እጅግ ምሥጢራዊ የሆኑ የስለላ ሰነዶች በማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ላይ እንዴት ሾልከው ሊወጡ እንደቻሉ ለማወቅ እየሞከሩ ነው። ባለፈው አርብ በቴሌግራም የመልዕክት መላላኪያ መተግበሪያ ላይ የወጡት እነዚህ ምሥጢራዊ ሰነዶቹ እስራኤል ኢራንን ለማጥቃት እንዳቀደች አሜሪካ ያደረገችውን ግምገማ በዝርዝር የያዙ ናቸው።

FastMereja.net2

22 Oct, 13:02


ኬንያ የቱርክ ስደተኞችን ያለፈቃዳቸው ወደ አገራቸው መመለሷ እንዳሳሰበው የመንግሥታቱ ድርጅት ገለጸ
https://www.bbc.com/amharic/articles/c5ywyey91l8o

የኬንያ መንግሥት በመዲናዋ ናይሮቢ ይኖሩ የነበሩ አራት ጥገኝነት ጠያቂ ቱርካውያንን በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል።

FastMereja.net2

22 Oct, 13:01


የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ለተቀናቃኛቸው ወስነው የነበሩ ሦስት ዳኞችን ከሥራ አባረሩ
https://www.bbc.com/amharic/articles/c3rlrvygq7go

የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሃኪዬንዳ ሂቺሌማ በዳኝነት ሥራቸው ላይ ተገቢ ያልሆነ ተግባር ፈጽመዋል ያሏቸውን የአገሪቱን ሦስት ከፍተኛ ዳኞች ከሥራ አባረሩ።

FastMereja.net2

22 Oct, 04:39


እየዘመኑ የመጡትን ቅንጡ እና አዳዲስ ስልኮችን መያዝ ያስፈልገናል?
https://www.bbc.com/amharic/articles/cd6q01qwz59o

ከዓመታት በፊት “ሃሎ” ለመባባል ብቻ የሚውሉ የሞባይል ስልኮች “እንደ ተዓምር” ይታዩ ነበር።
አንዳንዶቹ ስልኮች ከብረት ቢጠነክሩም፣ ከአሎሎ ቢከበዱም ሰዎች ጎናቸው ላይ “ሸጉጠው” በኩራት አደባባይ ይወጡ ነበር። እነዚህ ስልኮች ለመደወል ግፋ ካለ አጭር የጹሁፉ መልዕክት ከመለዋወጥ የዘለለ አገልግሎት ባይሰጡም ለዓለም ሕዝብ ብርቅ ነበሩ። ዛሬ ስልኮች ሌላ ደረጃ ላይ ደርሰዋል። በብዛትም በዓይነትም ተበራክተዋል።

FastMereja.net2

22 Oct, 04:38


ለሳይንቲስቶች እንቆቅልሽ ሆኖ የዘለቀው በእርግዝና ወቅት የሚከሰተው ከፍተኛ የደም ግፊት
https://www.bbc.com/amharic/articles/cdx93velgnyo

ከፍተኛ የደም ግፊት (ፕሪ ኤክላምፕሺያ) በእርግዝና ወቅት ወይም በወሊድ በኋላ የሚያጋጥም ከባድ የእናቶች የጤና እክል ነው። ፕሪ ኤክላምፕሺያ በዓለም ላይ በየዓመቱ በከፍተኛ ደም ግፊት የተነሳ ከሚመጣ ስትሮክ የተነሳ ከ70 ሺህ በላይ ወላድ እናቶችን እንዲሁም ለ500 ሺህ ጽንሶች ሞት ምክንያት ነው። ይህ ከፍተኛ የደም ግፊት በእርግዝና ወቅት ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቅያ ሊከሰት ይችላል።

FastMereja.net2

21 Oct, 20:35


በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ የእሳት አደጋ ተከሰተ
https://amharic.voanews.com/a/7830703.html

በአዲስ አበባ በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ ዛሬ ማምሻውን እሳት መከሰቱ ታውቋል።


“በተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት እጅግ አዝነናል” ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ “የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ከእሳት አደጋ  እና ስጋት መከላከል እንዲሁም  ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ርብርብ እየተደረገ” መሆኑን  አመልክተዋል። 


አደጋውን ለመቀነስ በመሥራት ላይ ያሉ አካላት ሁሉ ጥረታቸውን እንዲቀጥሉም ከንቲባዋ አሳስበዋል።


አደጋውን በአስቸኳይ ለመቆጣጠር አዳጋች የሆነው የአካባቢው መንገድ ለእሳት አደጋ መኪና እንቅስቃሴ አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት መሆኑን የጠቆሙት ከንቲባዋ፣ በሄሊኮፕተር ለመጠቀም ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑንም ገልፀዋል።

FastMereja.net2

21 Oct, 20:34


አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት በሁለት ቋሚ አባል ሀገራት መወከል እንደሚገባት ጉተሬዥ ተናገሩ
https://amharic.voanews.com/a/7830634.html

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ አዲስ አበባ በሰጡት መግለጫ፣ በፀጥታው ምክር ቤት መሻሻል እና በአፍሪካ ውክልና ላይ በተመድ አባላት መካከል መግባባት መኖሩን ገልጸዋል።


ዓለም አቀፉ የገንዘብ ሥርዓትም አፍሪካን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ መሻሻል እንዳለበት ከስምምነት መደረሱን ዋና ጸሐፊው ጠቁመዋል፡፡


ዋና ጸሐፊው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ በመሆን እድሳት የተደረገለትን የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መቀመጫ የሆነውን የአፍሪካ አዳራሽም መርቀዋል፡፡