ቅን አመለካከት

@betyfekadu2024


🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
💛 አብረን እንደግ ተቀላቀሉን !!
አስተያየት ለመስጠት እና ጥያቄ ለመጠየቅ
@Negabeti
https://t.me/Betyfekadu2024
0977717378 ቤቲሻ ነኝ

ቅን አመለካከት

22 Oct, 12:22


ትልቁ የህይት ጥያቄ?
ለምን ተፈጠርኩ ለተፈጠርኩለት አላማስ እየኖርኩ ነው?📥
ይህን ጥያቄ የመለሰ ሰው ስኬትን ተጎናጽፈዋል

ቅን አመለካከት

21 Oct, 08:12


አስር ጠቃሚ አባባሎች ለመልካም ሳምንት ጅማሬ💯 🆕🆕

1. አንተ የምርጫህ ውጤት እንጂ በአንተ ላይ የሚደርሱት ነገሮች ውጤት አይደለህም፡፡
-ካርል ጉስታቭ

2. ባለትላልቅ አእምሮ ሰዎች በሃሳብ ላይ ይወያያሉ ፣ መካከለኞች በ ድርጊት / ሁኔታዎች ላይ ይወያያሉ ባለትናንሾች ቁጭ ብለው ሰው ያማሉ፡፡
-ሪያኖር ሮዝቪልት

3. እስካልቆምክ ድረስ በምንም ዝግታ ብትጓዝ መድረስህ አይቀርም ፡፡
-ኮንፊሺየስ

4. ችሎታ ያለው ሰው ምንም ስራ እስካልሰራ ድረስ ችሎታ በሌለው ጠንካራ ሰራተኛ ይበለጣል ፡፡
-ቲም ኖትኪ

5. ከውድቀት ይልቅ ጥርጣሬ የነገ ህልምን ይገላል፡፡
-ሱዚ ካስም

6. እውቀት ብቻ አይበቃም ተግባራዊ ካልተደረገ በስተቀር ፣ ፍቃደኛነት ብቻ አይበቃም ካልተሰራ በስተቀር፡፡
-ብሩስ ሊ

7. የዛሬ አመት በዚህ ሰአት ምናለ ምናለ ከአመት በፊት በጀመርኩ የምትላቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፡፡
-ካረን ላንብ

8. ጀማሪዎቹ ለመስራት ከሞከሩት ጊዜ በላይ አለቃቸው ብዙ ጊዜ ወድቋል፡፡
-ስቴፈን ማክክሬን

9.ብዙ ጊዜ ላለመስራት የምትተዋቸው ስራዎች በውስጣቸው ብዙ እድልን የያዙ ናቸው፡፡
-ሮቢን ሻርማ

10. መተንፈስ እንደምትፈልግ ያህል ለስኬታማ ሕይወት ጥልቅ ፍላጎት ካለህ ይሳካልሀል፡፡
-ኤሪክ ቶማስ

የተዋበ የስራ ሳምንት ይሁንላችሁ 👋

ባለራዕይ፣ቅን፣ጤናማና ባለፀጋ ትውልድ ማፍራት!

ቅን አመለካከት

20 Oct, 20:35


አልኝ ብለህ አትኩራ
የለኝም ብለህ አትፍራ
አይታወቅ የእግዚአብሔር ስራ

ቅን አመለካከት

19 Oct, 08:38


#ሌሎች. . .

1- ሌሎች ሲተኙ- አጥና
2- ሌሎች ሲያመነቱ-  ወስን
3- ሌሎች ሲያልሙ- ተዘጋጅ
4- ሌሎች ዛሬ ነገ ሲሉ- ጀምር
5- ሌሎች ሲመኙ- ስራ
6- ሌሎች ሲያባክኑ- ቆጥብ
7- ሌሎች ሲያወሩ- ስማ
8- ሌሎች ሲያኮርፉ- ፈገግ በል
9- ሌሎች ሲያቋርጡ- ጽና

ይህ ነው ቢዝነስ ጥበብ!!!

ቅን አመለካከት

19 Oct, 06:34


#እንዳታቆም#

1-እንደ አለት ቢከብድህ
2-ገንዘብ ባይኖርህ
3-ቢደክምህ
4-ብቸኛ ብትሆን
5-ብትፈራ
ሕልምህን ማሳደድ መቼም እንዳታቆም!!
አንድ ቀን ራስህን ታመሰግነዋለህ።

ቅን አመለካከት

18 Oct, 06:41


#የወርቅ_ጉድጓድህ

ሰዎች የሚፈልጉትንና የሚያስፈልጋቸውን ነገር አጥንተህ ሥራ፤

ሳይጠገን የቆየ ስብራት መፍትሄ ሲያገኝ የሚጨምረው እሴት የላቀ ነው።

ብዙ ሰዎች የተሰበረባቸው፣ አንተ ግን ልትጠግነው የምትችለው ነገር ካለ...

ያ የወርቅ ጉድጓድህ ነው!!

ውብ ቀን ተመኘሁ😍😘🌹

ቅን አመለካከት

16 Oct, 10:54


#ታላቅ_መሪ፦

1- በምሳሌ የሚመራ
2- ግልጽ ገደቦች የሚያስቀምጥ
3- ሌሎች እንዲያድጉ የሚያበረታታ
4- በስሜት ብልህ የሆነ
5- ጠንካራ ራእይ የያዘ
6- ራሱ ላይ የሚሰራ
7- ከስህተቶቹ ቶሎ የሚማር

ነውና! ያን ዓይነት መሪ ያድርገን!

💐💐💐💐💐

ቅን አመለካከት

13 Oct, 07:51


#ማንንም_አትጠብቅ!!

የአንተ ድርሻ፣ ከራስህ አልፈህ፦

ተስፋ ላጡት 👉 ተስፋ መስጠት
የተዘናጉትን👉 ማነሳሳት
የደከሙትን👉 ማበርታት
ግራ የገባቸውን👉 መንገድ ማሳየት

ነው!! እወቅ መሪው አንተ ነህ!!

ቅን አመለካከት

13 Oct, 03:58


አይሆንም አይሳካም ይቅርብህ የሚሉህ ሌሎች ናቸው ነገር ግን ዋናው ያንተ እምነት ነው ነገ ደርሰህ እንደምታሳያቸው ማመን አለብህ ይቅርብህ ያሉህ በእራሳቸው እይታ እንጂ እውነታው እሱ ሳይሆን ያንተ የስኬት ረሃብ ነው

No, it won't work, there are others who will say , but the main thing is your faith, you have to believe that you will show them tomorrow.

ሃይሌ ገ/ስላሴ

ቅን አመለካከት

12 Oct, 06:51


#3ቱ_ጥበቦች፦

👉 ትናንት እንዲህ ይልሃል፦

እርሳኝ ግን ከእኔ መማር ያለብህን ተማር!

👉 ዛሬ እንዲህ ይልሃል፦

ተቀበለኝ፤ የምችለውን ያህልም ተጠቀምብኝ!

👉 ነገ እንዲህ ይልሃል፦

ተስፋ አድርገኝ፤ ከዛም ለእኔ ተዘጋጅ!

#የሰሎሞን_ጥበብ መጽሐፍ

መልካም ቀን😍😘

ቅን አመለካከት

10 Oct, 08:05


#ከእነዚህ_ሰዎች_አምልጥ_ብሮ!

1- መወደድ የማትችል እንዲመስልህ ከሚያደርጉ
2- በትናንትህ ሊቀጡህ ከሚፈልጉ
3- አብዝተው ከሚፈርዱብህ
4- ከሚቀልዱብህ
5- ለሌሎች ሐዘኔታ ከሌላቸው
6- የማይጠቅምህን ከሚመክሩህ

አዲሱ #ልማድህን_ ነህ

ቅን አመለካከት

07 Oct, 08:58


#ውረድ!

የተሳሳተ አውቶብስ ውስጥ እንደተሳፈርክ ብታውቅ ምን ታደርጋለህ?

በቀጣዩ ፌርማታ ላይ ትወርዳለህ አይደል?

በሕይወትህም ላይ በተሳሳተ አቅጣጫ ውስጥ በቆየህ መጠን ከመዳረሻህ በጣም እየራቅክ ትመጣለህ፣ _ በቶሎ ውረድ



መልካም ቀን🌹🌹🌹😍😘

ቅን አመለካከት

05 Oct, 10:58


#እውነተኛ_ራስህን_ለመሆን

1) ማስመሰልህን አቁም
2) ፍጹም አለመሆንህን ተቀበል
3) ዋጋህን በሌሎች እይታ አትመዝን
4) ራስህን አትደብቅ
5) ጥሩ ያልሆኑ ገጾችህንም ተቀበል
6) በተቻለህ መጠን ራስህን እወቅ

😍😍😍😍

ቅን አመለካከት

04 Oct, 14:33


Baga Ayyaana Irreechaa Nagaan Geessan!

እንኳን ለኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ!

ቅን አመለካከት

04 Oct, 08:51


#ያለ_ሰበብ_የጀመርከውን_ጨርስ!

1) አንድ ስራ ላይ አተኩር
2) ረብሻዎችን ችላ በል
3) ጊዜው አሁን ብቻ ነው
4) በፍጹም ከመንገድህ አትውጣ
5) እንዳይሰለችህ አዳዲስ አሰራር ሞክር
5) በምታደርገው ሁሉ ደስ ይበልህ

አዲሱ #ሰበብ_አታብዛ መጽሐፍ በገበያ ላይ

😴 እንቅልፋም ሳይሆን ንቁ
🗣 የሚያወራ ሳይሆን የሚተገብር
🚫 ሰበበኛ ሳይሆን ተአምረኛ. . . መሆን ለሚሹ ሁሉ የቀረበ

ቅን አመለካከት

03 Oct, 08:42


#በመሬት_ልብ_ውስጥ_ያለው_ወርቅ

በአንተ አእምሮ ውስጥም አለ!

ሀሳብ የመፍጠር ኃይል ነው ወይም የፈጠራ ኃይል እንዲንቀሳቀስ ማድረግ የሚችል ተጽዕኖ ፈጣሪ ኃይል ነው፡፡

በተወሰነ መንገድ ማሰብ ሀብትን ወደ እናንተ ያመጣል፡፡ ነገር ግን ለተግባራችሁ ትኩረት ሳትሰጡ በሀሳባችሁ ላይ ብቻ መተማመን የለባችሁም፡፡

ብዙ ሳይንሳዊ ሜታፊዚክስ አሳቢዎች የሚሰናከሉበት አለት ይህ ነው፡፡ ሀሳብን ከግለሰባዊ ተግባር ጋር ማገናኘት አለመቻል፡፡

ካለ ተፈጥሯዊ ሂደቶች ወይም ካለ ሰው ልጅ ጣልቃ ገብነት ነገሮችን ከቅርጽ አልባው ንጥረ ነገር መፍጠር ይቻላል ብለን ብንል እንኳን የሰው ልጅ እንደዚህ አይነቱ የእድገት ደረጃ ላይ አልደረሰም፡፡

#ሰው_ማሰብ_ብቻ_ሳይሆን_ያለበት፣ የግል ተግባሩም ሀሳቡን የሚያሟላ መሆን አለበት፡፡

በመሬት ልብ ውስጥ ያለውን ወርቅ በሀሳባችሁ ኃይል ወደ እናንተ እንዲመጣ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ወርቁ እራሱን ከመሬት አውጥቶ፣ አጣርቶ፣ ቅርጽ ያለው ሳንቲም አድርጎ በጎዳናዎች ላይ እየተሽከረከረ ወደ ኪሳችሁ አይገባም፡፡

ይህ #የሀብት_ሳይንስ መጽሐፍ፦

ቅን አመለካከት

02 Oct, 10:30


#ትነግሳለህ!

እነዚህ ካሉህ በሕይወት ላይ
ትነግሳለህ!

1- ፈጠራ
2- ሐቀኝነት
3- መነቃቃት
4- በራስ መተማመን
5- ይቅር ማለት
6- ሰላማዊነት
7- ደስታ
8- እምነት
9- ጀግንነት
10- እርዳታ

ንጉስ ሆይ ሺ አመት ይንገሱ😁😁😁😍😘

ቅን አመለካከት

02 Oct, 06:46


#3ቱ_ጥበቦች፦

👉 ትናንት እንዲህ ይልሃል፦

እርሳኝ ግን ከእኔ መማር ያለብህን ተማር!

👉 ዛሬ እንዲህ ይልሃል፦

ተቀበለኝ፤ የምችለውን ያህልም ተጠቀምብኝ!

👉 ነገ እንዲህ ይልሃል፦

ተስፋ አድርገኝ፤ ከዛም ለእኔ ተዘጋጅ!

#የሰሎሞን_ጥበብ መጽሐፍ

መልካም ቀን😍😘

3,303

subscribers

3,265

photos

400

videos