ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

@segno_des_sil

ሰኞ የሳምንቱ የመጀመሪያ የስራ ቀን ነው!
ካለፈው ተምረን ሳምንቱን እንደ አዲስ የምንጀምርበት ቀን ነው!
ሰኞ ጥቁር አይደለም ብሩህ ነው!
ይሄ ቻነል ሳምንታችንን እና ቀናችን በአዲስ ኃይል እንድንጀምር ያበረታታል!
ሁሉም ቀን ሰኞ ነው!
አዲስ እድል ነው
ሰኞ ደስ ይላል !

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

04 Nov, 05:28

ከይቅርታ ጋር ባህርዳር ስለሆንኩ ለ 3 ቀናት እዚህ አልኖርም ወዳጆች 🙏

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

01 Nov, 20:38

" ፈተናዎቼ ለተሻለ ነገር የተሰጡኝ መልካም አጋጣሚዎች ናቸው። አንዱ በር ሲዘጋ ሌላ ብር ሁል ጊዜ ይከፈታል። "

የ180 ቀን 60ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 120  😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 22
መጽናትን ተለማመድ

በፍጹም በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ። የታሪክ መዝገብ የሚያሳየው በፍጹም በፍጹም ተስፋ ባለመቁረጥ ያሳኩ ሰዎችን ታሪክ ነው። ማቋረጥ ማንም ሰነፍ ሰው ሊያደርገው የሚችለው ቀላሉ ነገር ነው። ለመሆኑ ተስፋ ቆርጠህ ከዚያ በኋላ ምን ትቆርጣለህ (ለጨዋታ ነው)። የነገ ማንነትህ እንዲያመሰግንህ ከፈለግክ ትንሽ ጽና ፣ ማድረግ ያለብህን ሁሉ አድርግ። የሚዘጉ በሮች ሲኖሩ የሚከፈቱ በሮችም ሁልጊዜ እንዳሉ አስታውስ።

ቃል ህይወት ነው ሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ያነቃቃል ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)

" ፈተናዎቼ ለተሻለ ነገር የተሰጡኝ መልካም አጋጣሚዎች ናቸው። አንዱ በር ሲዘጋ ሌላ ብር ሁል ጊዜ ይከፈታል። "

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

31 Oct, 20:08

" ለእያንዳንዱ እንቅፋት እና መንገድ መዘጋት አማራጭ የተግባር መንገድ እንዳለ አሁን አውቃለሁ። ከመንገድ ትንሽ ዞር በማለት ወደ ግቤ የሚወስደኝን አዲስ መንገድ አገኛለሁ።"

የ180 ቀን 59ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 121  😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 22
መጽናትን ተለማመድ

ጽናት ግትርነት ማለት አይደለም። ጽናት እንደወንዝ መፍሰስ ነው። ወንዝ በመንገዱ ላይ ደንቃራ ድንጋይ ሲያጋጥመው አማራጭ ፈልጎ ይፈሳል።

እንቅፋት እና መንገድ መዘጋት ሲያጋጥም ቢያንስ ሶስት አማራጮችን ማዘጋጀት ይገባል። ቆም ብለን በማሰብ እንቅፋቱን ዞረን ፣ በእንቅፋቱ ላይ ወይም በእንቅፋቱ ውስጥ ልናልፍ የምንችልባቸውን አማራጭ መንገዶች መፈለግ ይገባል።

ቃል ህይወት ነው ሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ያነቃቃል ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)

" ለእያንዳንዱ እንቅፋት እና መንገድ መዘጋት አማራጭ የተግባር መንገድ እንዳለ አሁን አውቃለሁ። ከመንገድ ትንሽ ዞር በማለት ወደ ግቤ የሚወስደኝን አዲስ መንገድ  አገኛለሁ።"

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

30 Oct, 20:52

" 'እምቢ' የሚል ቃልን ስሰማ ወደ 'እሺ' ስሄድ እንደሚያጋጥመኝ መወጣጫ ደረጃ አድርጌ እቆጥረዋለሁ። እስካሳካ ድረስ ጥቂት እገፋለሁ! " 

የ180 ቀን 58ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 122  😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 22
መጽናትን ተለማመድ

"እምቢ" ወደ "እሺ" ስትሄድ የምትሰማው ቃል ነው። ፈጥነህ እጅ አትስጥ። ለአንተ መልካሙን የሚሹት ወላጆችህ፣ ዘመዶችህ፣ ጓደኞችህ እና የስራ ባልደረቦችህ "ትክክለኛ ስራ " እንድትጀምር ቢነግሩህ እንኳን ተስፋ አትቁረጥ። ለአንተ ትክክለኛ ስራ ህልሞችህ ናቸው።

ከ13 ሶስት አመት የስደት ቆይታ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ አሁን የምሰራውን የስልጠና እና የሽያጭ ስራ ብዙ ወዳጆቼ እንደ ዋና ስራ አልቆጠሩትም። እንደው በማክበር ፊት ለፊት የሆነ ጠንካራ ተቃውሞ ይዘው ባይቀርቡም ለረጅም ጊዜ የቆየሁበትን የባንክ ሙያ ተቀጥሬ እንድሰራ እና ይሄን ነገር በትርፍ ሰአት እንድሞክረው ነበር የሚያበረቱኝ። ስለሚወዱኝ ። እንዳልጎዳባቸው። ያው የምትወደውን ካልወደዱልህ ግን ለምድ ለባሽ ተቃውሞ ነው።

አሁን በሙያዬ ወደደረስኩበት የማንነት ከፍታ ለመድረስ በውስጤ ያለውን ግጭት፣ እና ከሩቅም ከቅርብም የሚደርሱ "እምቢታዎችን" ማለፍ ግድ ብሎ ነበር። አሁን ላይ ለህልሜ ስለመታመኔ እና ስላለፍኳቸው ፈተናዎች እጅግ አመስጋኝ ነኝ።

ፈተኛዎቻችን የመሞረጃ በጎ እድሎቻችን ናቸው።

ቃል ህይወት ነው ሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ያነቃቃል ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)

" 'እምቢ' የሚል ቃልን ስሰማ ወደ 'እሺ' ስሄድ እንደሚያጋጥመኝ መወጣጫ ደረጃ  አድርጌ  እቆጥረዋለሁ። እስካሳካ ድረስ ጥቂት እገፋለሁ! " 

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

29 Oct, 19:41

" 'እጅ አለመስጠት' ከፍተኛ ውጤት ያላቸው ሰዎች አንድ የሚያደርጋቸው ብቸኛ ያጋራ መገለጫ መሆኑን ስላማምንበት መጽናትን እለማመዳለሁ ! " 

የ180 ቀን 57ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 123 😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 22
መጽናትን ተለማመድ

"ብዙ ሰዎች ልክ ሊሳካላቸው ሲል ተስፋ ይቆርጣሉ። አንድ ሜትር ሲቀራቸው ያቋርጣሉ። በጨዋታው የመጨረሻው ደቂቃ ተስፋ ይቆርጣሉ። ጥቂት ነጥብ ሲቀራቸው ይዝላሉ። " ሮዝ ፔርት

ትልቅ ውጤት የሚያመጡ ሰዎቹ ምናልባት ብቸኛው አንድ የጋራ መገለጫ ቢኖር መጽናት ነው። በአጭር ቋንቋ ተስፋ መቁረጥን አይቀበሉም። በቦታው በቆየህ ቁጥር ፣ ለአንተ የሚስማማ የሆነ ነገር የመሆን እድሉ የሰፋ ነው። ምንም ያህል ከባድ ቢመስልም በጽናት ይበልጥ በቆየህ ቁጥር የማሳካት እድልህ የሰፋ ይሆናል።

መጽናት የሚጠበቅብህ በፈተናዎቹ ውስጥ - ፈጽሞ አስቀድመህ (ምንም አይነት እቅድ ብታወጣ ወይም ቀድመህ ብታስብ) ልታያቸው የማትችላቸው ፈተናዎች ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንዴ ፈጣሪ ለግብህ ምን ያህል ታማኝ እንደሆንክም ይፈትናል።

መንገዱ ከባድ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን አዲስ ክህሎትን እያዳብርክ ሳለ፣ የራስህ ማንነት እያሳድግክ ሳለ፣ እና ፈታኝ ውሳኔዎችን እየወስንክ ሳለ ፤ እጅ ለመስጠት እምቢ ልትል ይገባል።

ቃል ህይወት ነው ሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ያነቃቃል ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)

" 'እጅ አለመስጠት'  ከፍተኛ ውጤት ያላቸው ሰዎች አንድ የሚያደርጋቸው  ብቸኛ ያጋራ መገለጫ መሆኑን ስላማምንበት መጽናትን እለማመዳለሁ  ! "

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

27 Oct, 04:05

" በቀላሉ እንዳያቸው እና በመንገዴ ላይ ተነቃቅቼ እንድቆይ፣ ለውጤን የሚያሳዩኝ ነጥቦች የሚታይ ቦታ ላይ በቀጣይነት እጽፋለሁ ! " 

የ180 ቀን 56ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 124  😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 21
ለስኬት ነጥብ መዝግበህ መያዝህን ቀጥል

ነጥብ መያዝ ያለብህ ማድረግ ፈልገህ ያላደረግካቸውን ( ያልሆንካቸውን) ሳይሆን ማድረግ ኖሮብህ ያደርግካቸውን እና የምትፈልጋቸውን ጥቂት ነገሮች ነው። የሰራኸውን የ 5 ደቂቃ ስፖርት መመዝገብ ፣ የ 10 ደቂቃ ንባብ እውቅና መስጠት፣ በስኬት ያጠናቀቅከውን አንድ የሽያጭ ስልክ ጥሪ ትርጉም ሰጥቶ መመዝገብ .......ወደ ምትፈልገው ሰው ማንነት የመሄድህን ጉዞ ያጠናክራል (It is Reinforcement of positive behaviours)።

አሉታዊ ነገሮች ላይ አተኩረህ ከመዘገብካቸው እነዛ ነገሮች ይጠናከራሉ። አዎንታዊ ነገሮችን በጥቂቱም ቢሆን እያደረግክ ነጥብ መያዝ እነዛን ነገሮች ያጠነክራል። አስታውስ ያተኮርክበት ይበዛል።

ነጥብ በመያዝ ውስጥ አንዱ ቁልፍ ነገር የምትመዘግበውን ነጥብ በጉልህ የሚታይ ቦታ ማስቀመጥ ነው። እድገትን የሚያሳዩ ነጥቦች ፍሪጅ ላይ፣ ግድግዳ ላይ፣ ቦርድ. .....ላይ በሚታይ መልኩ ማስቀመጥ ትኩረትን እና ኃይልን ይጨምራል።

ቃል ህይወት ነው ሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ያነቃቃል ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)

" በቀላሉ እንዳያቸው እና በመንገዴ ላይ ተነቃቅቼ  እንድቆይ፣  ለውጤን የሚያሳዩኝ ነጥቦች የሚታይ ቦታ ላይ በቀጣይነት እጽፋለሁ ! "

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

26 Oct, 03:58

" ሁሉም አስደሳች ለውጦቼን፣ አዎንታዊ ባህሪዎቼን፣ የገቢ እድገቴን እና ማንኛውም እንዲበዛልኝ የምፈልገውን ነገር ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ ነጥብ መዝግቤ በመያዜ የማደግ ጉጉት ላይ ነኝ ! " 

የ180 ቀን 55ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 125  😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 21
ለስኬት ነጥብ መዝግበህ መያዝህን ቀጥል

ወላጆች ልጆቻቸውን ለማበረታት ከሚያደርጉት ነገር አንዱ የልጆቻቸውን ቁመት የሆኑ ወራትን እያሳለፉ መለካት ነው። ይሄንን ማድረጋቸው ልጆች ከትናንትናቸው እና ከወደፊት ግባቸው (ብዙ ጊዜ የወላጆቻቸው ቁመት ላይ መድረስ 😁 ) አንጻር የት እንዳሉ ያሳያል። መለካታቸው እድገት ላይ መሆናቸውን ያሳያል። በዚህ ምክንያት ልጆች ይበልጥ በመብላት እና ወተት በመጠጣት እድገታቸውን ለመቀጠል ይበረታታሉ።

ስኬታማ ሰዎችም እንደዚሁ ተመሳሳይ መለኪያዎችን ነጥብ ይይዛሉ። ሁሉም አጓጊ ለውጦችን፣ አዎንታዊ ባህሪዎችን፣ የገቢ እድገትን እና ማንኛውም እንዲበዛላቸው የሚፈልጉትን ነገር  ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ ነጥብ ይይዛሉ።

ነጥበ መያዝ ፣ መዝግበን ለውጣቸውን እየተከታተልን ያለናቸውን ነገሮች ይበልጥ አዎንታዊ ውጤት እንድናመጣ ያነቃቃናል። እነዚያን ውጤቶች ያመጣውን ባህሪም ይበልጥ ያጠናክራል።

ተፈጥራዊ ዝንባሌያችን ሁልጊዜ ነጥባችንን ማሻሻል ነው።

ቃል ህይወት ነው ሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ያነቃቃል ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)

" ሁሉም አስደሳች ለውጦቼን፣ አዎንታዊ ባህሪዎቼን፣ የገቢ እድገቴን እና ማንኛውም እንዲበዛልኝ የምፈልገውን ነገር  ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ ነጥብ መዝግቤ በመያዜ የማደግ ጉጉት ላይ ነኝ  ! " 

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

24 Oct, 20:20

" በየቀኑ የሆነ አዲስ ነገር ለመማር ቁርጠኛ ነኝ  ! " 

የ180 ቀን 54ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 126 😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 20
ቀጣይነት ላለው እና ለዘላቂ መሻሻል ቁርጠኛ  ሁን

አንዱ የህይወት እውነት ትልልቅ መሻሻሎች ጊዜ መውሰዳቸው ነው፣ በአንድ ጀምበር አይሆኑም። ሆኖም በዚህ ዘመን የሚሸጡ ምርቶች እና አገልግሎቶች በአንድ ጀምበር ለውጥ ማምጣትን ቃል ይገባሉ። ከዚህም የተነሳ ብዙዎቻችን (እነዚህን ምርቶች እና አገልግሎቶች በመጠቀም) አቋራጭ እንጠብቃለን ፣ ያ ሳይሆን ሲቀር ደግሞ ተስፋ እንቆርጣለን።

በአንጻሩ በየቀኑ አንድ አዲስ ነገር ለመማር እና በየቀኑ በጥቂቱ ለመሻሻል ከቆረጥክ፣ በሂደት በእርግጠኝነት የምትፈልገው ግብ ትደርሳለህ።

በአንድ ነገር ላይ ተክኖ ለመገኘት ጊዜ ይፈጃል። ደጋግመህ መለማመድ፣ መለማመድ፣ መለማመድ ይጠበቅብሃል። ክህሎትህን ደጋግመህ ስራ ላይ በማዋል እና በማጥራት መሳል ይገባል። ኤክስፐርትነት፣ ብሰለት እና ጥበብ ለማጎልበት የሚያስፈልገውን ጥልቀት እና ዘርፈ ብዙ ልምድ ለማጎልበት አመታት ይፈጃል። በስራህ እና በህይወትህ ለማደግ እያንዳንዱ ያነበብከው መጽሐፍ፣ እያንዳንዱ የተማርክባቸው ክፍሎች እና እያንዳንዱ ተሞክሮህ የግንባታ ጡብህ ናቸው።

በየቀኑ በሁሉም ዘርፍ እየተሻሻልክ፣ እየተሻሻልክ ለመሄድ ቁርጠኛ ሁን። ያንን ማድረግ ከቻልክ በየቀኑ እራስህን በማሻሻልህ እና እሱን ተከትሎ በማይቀረው ስኬት ምክንያት የሚገኘውን በራስ መተማመን እና ለራስ የሚኖር ጤነኛ ግምት ማጣጣም ትችላለህ።

ቃል ህይወት ነው ሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ያነቃቃል ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)

" በየቀኑ የሆነ አዲስ ነገር ለመማር ቁርጠኛ ነኝ  ! " 

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

23 Oct, 20:14

" ክህሎቴን እና ባህሪዬን ለማሻሻል በጀመርኩት ጉዞ ውስጥ፣ ዘለቄታ ያለው ስኬት የማግኘት እድሌን አሰፋ ዘንድ ጉዞዬን የጀመርኩት ቀላል እና ልቆጣጠራቸው የምችላቸውን እርምጃዎች በመውሰድ ነው ! " 

የ180 ቀን 53ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 127 😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 20
ቀጣይነት ላለው እና ለዘላቂ መሻሻል ቁርጠኛ  ሁን

ክህሎትህን፣ ባህሪህን፣ የቤተሰብ ህይወትህን ወይም ቢዝነስህ ለማሻሻል በምትነሳበት ወቅት ትንሽ እና ልትቆጣጠራቸው የምትችላቸውን እርምጃዎች በመውሰድ ጀምር። ይሄንን ማድረግህ ዘለቄታ ያለው ስኬት የማግኘት እድልህን ያሰፋል።

በአንድ ጊዜ በፍጥነት ብዙ ነገሮችን ለማድረግ መሞከር አንተንም ይሁን አብሮህ በለውጥ ጉዞ ላይ ያለን ሰው ያጨናንቃል። ምናልባት ጥረትህ ካልተሳካ ደግሞ ለማሳካት ይከብዳል ወይም አይቻልም የሚለውን እምነትህን ያጠናክራል።

ነገር ግን የሚቻሉ እና አነስተኛ ልትወስዳቸው የምትችላቸው እርምጃዎች ስትወስድ ነገሩን በቀላሉ እንድትካነው እና በቀላላሉ እሻሻላለሁ የሚለውን እምነት እንድታጠናክር ይረዳሃል።

እራስህን ቀጣይነት ባለው እና ማለቂያ በሌለው መሻሻል ውስጥ ለማድረግ እራስህን በየቀኑ ልትጠይቃቸው የሚገቡት ጥያቄዎች:-

√ ዛሬ እንዴት መሻሻል እችላለሁ/እንችላለን?
√ ከዚህ በፊት ከሰራሁት/የሰራነው ምን የተሻለ መስራት እችላለሁ/እንችላለን?
√ አዲስ ችሎታ ወይም ብቃት ከየት መማር እችላለሁ?

ይሄንን ማድረግ ከቻልክ፣ እራስህን ስኬትህን የሚያረጋግጥ የእድሜ ዘመን እራስን - የማሻሻል ጉዞ ውስጥ ታገኘዋለህ።

ቃል ህይወት ነው ሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ያነቃቃል ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)

" ክህሎቴን እና ባህሪዬን ለማሻሻል  በጀመርኩት ጉዞ ውስጥ፣ ዘለቄታ ያለው ስኬት የማግኘት እድሌን አሰፋ ዘንድ ጉዞዬን የጀመርኩት ቀላል እና  ልቆጣጠራቸው የምችላቸውን እርምጃዎች በመውሰድ ነው  ! "

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

22 Oct, 20:30

" እኔ ቀጣይነት ላለው እና ለዘላቂ መሻሻል ቁርጠኛ ነኝ ! " 

የ180 ቀን 52ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 128  😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 20
ቀጣይነት ላለው እና ለዘላቂ መሻሻል ቁርጠኛ ሁን

ጃፓኖች ቀጣይነት ላለው እና ለዘላቂ መሻሻል የሚሰጡት ስም ካይዘን ይባላል። ካይዘን ለብዙ ስኬታማ የጃፓን የቢዝነስ ድርጅቶች አፕሬሽናል ፍልስፍና ብቻ ሳይሆን ለጦረኞቹ እድሜ ጠገብ ፍልስፍና ነው።
ቀጣይነት ላለው መሻሻል ቁርጠኛ ከሆናክ እና የተሻለ ስኬታማ መሆን የምትፈልግ ከሆነ፦
✔️ይሄን እንዴት የተሻለ ላድርገው
✔️ ወጪን ቆጣቢ በሆነ መልኩ እንዴት ልስራው?
✔️ በተሻለ ፍቅር እንዴት ልስራው?

የሚሉትን ተገቢ ጥያቄዎች ደጋግመህ
ብትጠይቅ ለመሻሻል ይረዳሃል።

ቃል ህይወት ነው ሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ያነቃቃል ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)

" እኔ ቀጣይነት ላለው እና ለዘላቂ መሻሻል ቁርጠኛ ነኝ ! " 

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

21 Oct, 20:18

" የሰዎችን ግብረ መልስ ልቤን ከፍቼ ብሰማም ፤ ሰውነቴ፣ ልቤ እና ስሜቴ የሚነግረኝንም ወደ ውስጥ አደምጣለሁ ። " 

የ180 ቀን 51ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 129  😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 19
ግብረመልስን ለጥቅምህ አውለው!

ግብረ መልስ ለማግኘት የምንጠይቀው አንድ ቆንጆ ጥያቄ
"አሁን ያለንን ግንኙነት/የምንሰጠውን የምርት አገልግሎት ወይም ሌላ ነገር ከ10 ስንት ትሰጠዋለህ?

እንበልና ምላሹ ከ 10 በታች ከሆነ የሚቀጥለው ጥያቄ መሆን ያለበት

"10 ከ 10 እንድትሰጠው ምን እንዳደርግ ትፈልጋለህ? ምን እናድርግ? "

እነዚህ ተከታታይ ጥያቄዎች ክፍተታችንን እና መፍትሄውን እንድናገኝ ይረዳናል።

ቃል ህይወት ነው ሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ጫ ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)

" የሰዎችን ግብረ መልስ ልቤን ከፍቼ ብሰማም ፤  ሰውነቴ፣ ልቤ እና ስሜቴ  የሚነግረኝንም ወደ ውስጥ አደምጣለሁ ። "!

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

20 Oct, 20:57

" የማገኛቸው መረጃዎች፣ ምክር፣ እና አስተያየቶች ባህሪዬን እንዳቀና እየረዱኝና  እና ስኬታማ የመሆን እድሌን እያሰፉልኝ ነው ። " 

የ180 ቀን 50ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 130  😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 19
ግብረመልስን ለጥቅምህ አውለው!

ለግብረ መልስ ምላሽ የምንሰጥበት የተለያየ መንገድ አለ። ለዛሬ ጥቅም የሌላቸውን ምላሾች እናያለን።

1. በጉዳይ መሰበር እና ማቋረጥ። አስታውስ ሁልጊዜ ግብረመልስ መረጃ ነው። እንደወቀሳ ከምትቆጥረው ይልቅ እንደ የማስተካከያ መመሪያ ቁጠረው። መሰበር እና ማቋረጥ ለጊዜው የስሜት ጫናህን ታቃልልበታለህ ። ነገር ግን የምትፈልገውን ውጤት አይሰጥህም።

2. ግብረመልስ የሰጠህ ሰው ላይ መናደድ። ግብረ መልስ የሰጠህ ሰው ላይ በመናደድ እጅግ ከልብ ጠቃሚ የሆኑ ግብረ መልሶችን ከምንጩ ታደርቃለህ። ሰዎች ላይ ስትናደድ ወይ መልሰው ይናደዳሉ ወይም ለአንተ ግብርመልስ መስጠት ያቆማሉ።

3. የተሰጠህን ግብረ መልስ ችላ ማለት።

አስታውስ ግብረ መልስ መረጃ ነው። የግል ጉዳይ አድርገህ አትቁጠረው። የምትቀበለውን ተቀብለህ ተጠቀምበት። ውጤታማው ምላሽ መሆን ያለበት "ለሰጠኸኝ ግብረ መልስ አመሰግናለሁ። ጊዜህን ወስደህ ያየኸውን እና የተሰማህን ለማካፈል ግድ ስላለህ አመሰግናለሁ። ከልብ አደንቅሃለሁ። "

ቃል ህይወት ነው ሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ጫ ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)

" የማገኛቸው መረጃዎች፣ ምክር፣ እና አስተያየቶች ባህሪዬን እንዳቀና እየረዱኝና እና ስኬታማ የመሆን እድሌን እያሰፉልኝ ነው !" 

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

19 Oct, 20:40

" እኔ እለታዊ ተግባር በመጀመሬ፣ ስለያዝኩት ፕሮጀክት ጠቃሚ ግብረመልሶችን ማግኘት ጀምሬያለሁ " 

የ180 ቀን 49ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 131  😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 19
ግብረመልስን ለጥቅምህ አውለው!

አንዴ ተግባራዊ እርምጃ መውሰድ ከጀመርክ በኋላ ትክክለኛውን ነገር እያደረግክ እንደሆነ እና እንዳልሆነ ግብረ መልስ ታገኛለህ። እውቀትህን፣ ችሎታህን፣ አመለካከትህን እና ጓደኝነትህን እያጎለበትክ እያለ በቀጣይነት እራስህን እንድታቀነ እና ወደፊት እንድትሄድ የሚያግዙህ ዳታ፣ ምክር፣ እርዳታ፣ አስተያየት እና ምናልባትም ወቀሳም ልታገኝ ትችላለህ።
አንዴ በሆነ ጉዳይ ላይ ግብረመልስን ካገኘህ በኋላ በአግባቡ ምላሽ ልትሰጥ ፈቃደኛ መሆን ይገባል።

በመንገድህ ላይ ሁለት አይነት ግብረ መልሶች ሊያጋጥሙህ ይችላሉ። አዎንታዊ እና አሉታዊ። እውነት ነው ምርጫችን አዎንታዊ ግብረ መልስ ነው - ያም ውጤት፣ ገንዘብ፣ ጭማሪ፣ እድገት፣ የተደሰተ ደንበኛ፣ ሽልማት፣ ደስታ፣ ውስጣዊ ሰላም፣ ቅርበት፣ ሊሆን ይችላል።
አዎንታዊ ግብረ መልስ በትክክለኛው መንገድ ላይ እንዳለህ አና ትክክለኛውን ነገር እያደረግክ እንደሆንክ ይነግርሃል።

አሉታዊ ግብረ መልስ ያለ መውደድ ዝንባሌ አለን - ያ ማለት ውጤት አለማግኘት፣ ትንሽ ወይም ምንም ገንዘብ አለማግኘት፣ ወቀሳ፣ አጥጋቢ ያልሆነ ግምገማ፣ በደሞዝ ጫማሪ ወይም እድገት መዘለል፣ ወቀሳ፣ ደስታ ማጣት፣ ውስጣዊ ግጭት፣ ብቸኝነት፣ ህመም ወዘተ። በአዎንታዊ ግብረመልሶች እንደምናገኘው ሁሉ በአሉታዊ ግብረ መልስ የምናገኛው ጠቃሚ መረጃዎች አሉን። ከመንገድ ስንወጣ፣ ትክክለኛው ባልሆነ ጎዳና ላይ እንደሆንን፣ የተሳሳተ ነገር እያደረግን እንደሆነ ይነግረናል። ይሄ እጅ ጠቃሚ መረጃ ነው።
አሉታዊ ግብረ መልሶችን "የመሻሻያ በጎ እድሎች" የሚል ስም ልትሰጣቸው ይገባል።
የምትፈልገው ግብ ላይ በፍጥነት ለመድረስ ወደ አንተ የሚመጡ ግብረ መልሶችን ልታስተናግድ፣ በጸጋ ልትቀበል፣ እና ልታቅፍ ይገባል።

ቃል ህይወት ነው ሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ጫ ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)

" እኔ እለታዊ  ተግባር በመጀመሬ፣ ስለያዝኩት ፕሮጀክት ጠቃሚ ግብረመልሶችን ማግኘት ጀምሬያለሁ " 

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

18 Oct, 20:46

" የምፈልገው ነገር እኔንም ይፈልገኛል። ስለዚህም በሂደት የምፈልገውን እስካገኝ ድረስ መጽናትን ተምሬያለሁ " 

የ180 ቀን 48ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 132  😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 18
ተቃውሞን ተቃወመው

ዝም ብለህ "ቀጣይ ተረኛ!" በል !

ወደ ምትፈልገው ወርቃማ ስፍራ ስትሄድ ብዙ ተቃውሞ እንደሚገጥመህ በደንብ ልትረዳ ይገባል። የመጀመሪያው የስኬት ሚስጥር ተስፋ አለመቁረጥ ነው። የሆነ ሰው "አልቀበልም" ሲልህ ማድረግ ያለብህ "ቀጣይ ተረኛ ! " በማለት መጠየቅ ነው።

ከዚህ ከጽናት ጋር ተያይዞ ደጋግሞ ከሚነሱት ታሪኮች ውስጥ አንዱ የሆነው የKFC ምግብ ቤት ባለቤት የኮለኔል ሃርላን ሳንደርስ ታሪክ አስተማሪ ነው። ኮለኔል ሳርደርስ በልዩ ሁኔታ የተጠበሰውን የዶሮ አሰራር ለማሳየት ከምግብ ማብሰያው ጋር መኖሪያ ስፍራው ትቶን ከወጣ በኋላ፣ በህልሙ የሚያምን አንድ ሰው እስኪያገኝ ድረስ 300 ተቃውሞዎችን አስተናግዶ ነበር። ሆኖም እነዚህን 300 አለመቀበሎች መልሶ ስላልተቀበላቸው በአሁን ሰአት በአለም አቀፍ ደረጃ በ80 ሃገራት ከ 11,000 በላይ የKFC ሬስቶራንቶች ሊኖሩ ችለዋል።

አንድ ሰው አይሆንም ካለህ፣ ሌላ ሰውን ጠይቅ። በአለም ላይ ከ7 ቢሊዮን በላይ ሰዎች እንዳሉ አስታውስ። የሆነ ሰው፣ የሆነ ቦታ ፣ የሆነ ጊዜ እሺ ይላል። በራስህ ፍራቻ ወይም መጠየፍ ውስጥ አትቀርቀር። ወደ ሚቀጥለው ሰው ሂድ። ጉዳዩ የቁጥር ጨዋታ ነው። የሆነ ሰው እሺ ሊልህ እየጠበቀህ ነው።

በድጋሜ አስታውስ የምትፈልገውን ለማግኘት መጠየቅ፣ መጠየቅ፤ መጠየቅ እና የምትፈልገውን እሺታ እስክታገኝ "የሚቀጥለው ተረኛ !"፣ "የሚቀጥለው ተረኛ !"፣ "የሚቀጥለው ተረኛ !" እያልክ መቀጠል አለብህ። መጠየቅ ሁልጊዜ የቁጥር ጨዋታ ነው፣ ነበር እና ሁልጊዜም ሆኖ የሚቀጥል ነው።

ተቃውሞን በፍጹም የግል ጉዳይህ አታድርገው፣ ምክንያቱም የግል ጉዳይ ስላልሆነ።

ቃል ህይወት ነው ሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ይፈጥራል ፣ ከዛም ተግባርን ያስጀምራል

ስለዚህም ሃሳቡን ከገዛን ይሄን አዎንታዊ ማረጋገጫ ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)

" የምፈልገው ነገር እኔንም ይፈልገኛል። ስለዚህም በሂደት የምፈልገውን እስካገኝ ድረስ መጽናትን ተምሬያለሁ " 

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

17 Oct, 21:07

" የሆነ ሰው አልቀበልም ሲለኝ ፣ በእርጋታ ከእርሱ ተለይቼ  የሚቀጥለውን ሰው እጠይቃለሁ፣ ምክንያቱም የሆነ ሰው፣  የሆነ ቦታ እሺ ሊለኝ እየጠበቀኝ እንደሆነ ስለማውቅ" 

የ180 ቀን 47ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 133  😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 18
ተቃውሞን ተቃወመው

የ SW ህግን አስታውስ
Some Will፡ Some Will not,  So What,  Somebody Else is Waiting for you.

ማንኛውም ሃሳብህን፣ እድል፣ ጥያቄህን፣ አስተያየህን ፣ የቢዝነስ ፕሮፖዛል.... አንዳንድ ሰዎች እሺ ይላሉ፣ አንዳንዶች ደግሞ አይሆንም ይላሉ። ስለዚህ ምን ይሁን? አንተን እና ሃሳብህን እየጠበቀ ያለ የሆነ ሰው፣ የሆነ ቦታ አለ።  ጉዳዩ ምን ያህል ሰው ጋር ደርሰሃል የሚል የቁጥር ጥያቄ እንደሆነ ተረዳ። አዎ የሚለውን መልስ እስክታገኝ ድረስ መጠየቅህን ቀጥል። አንተ እስከጸናህ ድረስ እሺ የሚለው መልስ ደጅ ላይ እየጠበቀህ ነው። አስታውስ አንተ የምትፈልገው እየፈለገህ ነው።

አንድ ሴሚናሮችን ማስተዋወቅ የፈለገች ሴት በቀን 3 ሰዎችን ምሽት ላይ ትደውል ነበር።በወር ውስጥ 90 ጥሪዎችን አደረገች።  ብዙዎቹ ደውሎች ብዙ ማብራሪያ የሚጠይቁ እና የማይወስኑ ሰዎች ነበሩ። የመጀመሪያዎቹ 81 ምንም ሴሚናር ላለመውሰድ የወሰኑ ሲሆን የመጨረሻዎቹ 9 ግን እያንዳንዳቸው ሴሚናሩን ለመውሰድ ተስማሙ። ስኬቷ 10% ነበር። ለሽያጭ በጣም ጥሩ የስኬት % ነው። 
እንበልና 50 ሰው እንቢ ሲላት "ይሄ ነገር አይሰራም" ፣ "እዚህ ነገር ላይ መድከም የለብኝም"፣ "ማንም እሺ አይልም" ብላ ተስፋ ብትቆርጥስ ኖሮ?

ነገር ግን እሷ ህይወቷን የቀየረውን ተሞክሮ የማካፍል ታላቅ ህልም ስላላት ነገሩ የቁጥር ጨዋታ እንደሆነ ተረድታ በተቃውሞ ፊት ጸንታለች። ለውጤት ያላት ጽናት አትርፏል። በእሷ ምክንያት 9 ሰዎች ህይወታቸው ተቀይሯል።

ውስጣዊ ፓሽን እና ምክንያትህን ለሚቀሰቅስ ምክንያት ቁርጠኝነት ካለህ ፣ ከልምድህ ትማራለህ፣ በመንገድህ ትጸናለህ እና በመጨረሻም የምትፈልገውብ ውጤት ትፈጥራለህ።

ቃል ህይወት ነው ሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ይፈጥራል ፣ ከዛም ተግባርን ያስጀምራል

ስለዚህም ሃሳቡን ከገዛን ይሄን አዎንታዊ ማረጋገጫ ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)

" የሆነ ሰው አልቀበልም ሲለኝ ፣ በእርጋታ ከእርሱ ተለይቼ  የሚቀጥለውን ሰው እጠይቃለሁ፣ ምክንያቱም የሆነ ሰው፣  የሆነ ቦታ እሺ ሊለኝ እየጠበቀኝ እንደሆነ ስለማውቅ" 

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

16 Oct, 20:54

"እኔ ተቃውሞ ወይም አለመቀበል መሰረተ ቢስ እምነት /myth/ እንደሆነ እና በአእምሮዬ ውስጥ ካልሆነ በቀር ህልውና እንደሌለው ተረድቻለሁ"

የ180 ቀን 46ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 134  😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 18
ተቃውሞን ተቃወመው

"ተቃውሞ ዝቅ እንዲያረገን ስለማንፈቅድ መልሰን መላልሰን ደክመን ሳይሆን ጠንክረን እንሄዳለን። ተቃውሞ ውሳኔያችንን ያጠናክርልናል። ስኬታማ ለመሆን ሌላ አማራጭ የለም"
እርል ግሬቭስ

ስኬታማ መሆን ካለብህ ተቃውሞን/አለመቀበልን እንዴት እንደምትይዝ ማወቅ አለብህ። ተቃውሞ የህይወት አካል ነው። ለቡድን ሳይመርጡህ ሲቀር፣ የመረጥከው ትምህርት ቤት ሳትገባ ስትቀር፣ የፈለግከውን ስራ ወይም እድገት ሳታገኝ ፣ የምትፈልገውን የደሞዝ ጭማሪ ሳታገኝ ስትቀር፣ ፍቃድ ሳታገኝ ስትቀር፣ ፕሮፖዛልህ ሰሚ ሲያጣ፣ ያቀረብከው የምርት ሃሳብ ሲዘለል፣ የቀጠረኽ ደንበኛ ሲቀር ሁሉም የተቃውሞ እና አለመቀበል ማሳያ ናቸው።

ተቃውሞ መሰረተ ቢስ እምነት /myth/ ነው

ተቃውሞን እና አለመቀበል ለማለፍ አስቀድመህ መረዳት ያለብህ ነገር ተቃውሞ/አለመቀበል መሰረተ ቢስ እምነት መሆኑን ነው።

አንበልና ለሃርቫርድ ዩንቨርስቲ አመለክትክ ባይቀበሉህ ። ምንም የተፈጠረ ነገር የለም። ከማመልከትህ በፊትም የሃርቫርድ ተማሪ አልነበርክም ካመለከትክም በኋላ የሃርቫርድ ዩንቨርስቲ ተማሪ አይደለህም። ህይወትህ የከፋ አልሆነም ባለበት ነው የቀረው። ምንም ያጣኸው ነገር የለም። ሰው የሌለውን ነገር አያጣም። እድሜ ልክህን ሃርቫርድ አልገባህም ያለ ሃርቫርድ እንዴት እንደሚኖር ታውቃለህ። እዚህ ጋር የከፋ የሚሆነው ለውስጥህ "እኔ ድሮም ትምህርት አይሆንልኝም ሃርቫርድ መግባት አልችልም ብለህ ለራስህ ከነገርከው ብቻ ነው" ።

ሌላው እንበልና ለሆነ ሰው እቃ መሸጥ ፈልገህ አልተቀበለህም እንበል። በዚህ ሁኔታም ህይወትህ ምንም የከፋ ነገር አይሆንም። ለሰውዬው እቃ ለመሸጥ ከመሞክረህ በፊትም አልሸጥክለትም ከሞከርክም በኋላ አልሸጥክለትም። ሁኔታዎች በነበሩበት ነው የሆኑት። ምንም የተቀየረ ነገር የለም።
ለውስጥህ ከእንግዲህ በኋላ ሽያጭ አይሆንልኝም ብለህ ካልነገርከው በስተቀር ነገሮች ባሉት ነው ያሉት ፣ ምንም የጎደለብህ ነገር የለም።

ስለዚህ መሰረት ቢስ እምነቱን ሳትቀበል ቀደም ብሎ ባየነው ምእራፍ ሃሳብ መሰረት መጠየቅህን ቀጥል።

ቃል ህይወት ነው ሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ይፈጥራል ፣ ከዛም ተግባርን ያስጀምራል

ስለዚህም ሃሳቡን ከገዛን ይሄን አዎንታዊ ማረጋገጫ ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)

"እኔ ተቃውሞ መሰረተ ቢስ እምነት (myth) እንደሆነና እና በአእምሮዬ ውስጥ ካልሆነ በቀር ህልውና እንደሌለው አሁን አረጋግጫለሁ"

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

15 Oct, 20:29

"እኔ ብቃቱ እና ጽናቱ ስላለኝ፣ እስካሳካ ድረስ መጠየቄን እቀጥላለሁ"

የ180 ቀን 45ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 135  😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 17
ጠይቅ ጠይቅ ጠይቅ

✔️ ፈልጉ ታገኙማላችሁ፣ አንኳኩ ይከፈትላችኋል
✔️ በመጠየቅ ብዙ የምትጋኛቸው ነገሮች አሉ፣ የምታጣው ግን የለም።

የኖተር ዳም ዩንቨርስቲ ጥናት እንደሚያሳየው

√ 44% የሚሆኑ የሽያጭ ሰራተኞች ከመጀመሪያ ሙከራቸው በኋላ መደወል ያቆምሉ
√ 24% የሚሆኑት ደግሞ ከ2ኛ ሙከራ በኋላ ያቆማሉ
√ 14% የሚሆኑት ከ 3ኛ ሙከራ በኋላ ተስፋ ይቆርጣሉ
√ 12% የሚሆኑት ደግሞ ከ 4 ሙከራ በኋላ ያቆማሉ

ይሄ ማለት ምን ማለት ነው 94% የሚሆኑት የሽያጭ ሰራተኞች ከ4 ሙከራ በኋላ ያቆማሉ ማለት ነው። ነገር ግን 60% የሚሆነው ግዢ የሚፈጸመው ከ 4 አለመቀበል በኋላ ነው። ይሄ ማለት 94% የሚሆኑት ሽያጭ ሰራተኞች ለራሳቸው ለ60% ለሚሆኑት ሰዎች የመሸጥን እድል አልሰጡም።

ስለዚህ አንኳንኳ አንኳንኳ

ቃል ህይወት ነው ሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ይፈጥራል ፣ ከዛም ተግባርን ያስጀምራል

ስለዚህም ሃሳቡን ከገዛን ይሄን አዎንታዊ ማረጋገጫ ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)

"እኔ ብቃቱ እና ጽናቱ ስላለኝ፣ እስካሳካ ድረስ መጠየቄን እቀጥላለሁ"

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

14 Oct, 20:52

"በጠየቅኩ ቁጥር እሺ የመባል እድሌን ስለማሰፋ፣ ስጠይቅ በጽናት ነው ምጠይቀው"

የ180 ቀን 44ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 136  😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 17
ጠይቅ ጠይቅ ጠይቅ

የምትፈልገውን እንዴት ትጠይቃለህ?

1. ማግኘትን እንደሚጠብቅ ሰው ሆነህ ጠይቅ
አዎንታዊ መልስን በመጠበቅ ውስጥ ሆነህ ጠይቅ። እንደተሰጠህ እየተሰማህ ጠይቅ። እሺን እየጠበቅ ጠይቅ።

2. እንደምትችል አስብ
ማሰብ ካለብህ እድገት ልታገኝ እንደምትችል፣ የፈለግከውን ደሞዝ ጭማሪ ልታገኝ እንደምትችል፣ ስኮላርሺፕ ልታገኝ እንደምትችል፣ ረፍዶም ቢሆን ቲኬት ልታገኝ እንደምትችል።

3. ሊሰጥህ የሚችል ሰው ጠይቅ።
ሰዎችን መርጠህ ጠይቅ። እራስህን ".....ለማግኘት ከማን ጋር ማውራት አለብኝ?" ፣ "ስለ..... የመወሰን መብት ያለው ማነው? ፣ "....ለማግኘት ምን ሊሆንልኝ ይገባል?" በማለት በመጠየቅ ትክክለኛውን ሰው ለይ። ሁሉም ሰው አይጠየቅም።

4. ግልጽ እና የተወሰነ አድርገው
ብዥታ ያለው ጥያቄ ብዥታ ያለው መልስ ያስገኛል። ከዚህ አንጻር:-

ማለት የሌለብህ: ጭማሪ እፈልጋለሁ
ማለት ያለብህ: የ5000 ብር ጭማሪ እፈልጋለሁ

ማለት የሌለብህ:  በዚህ ሳምንት ካንቺ ጋር የተወሰነ ጊዜ ማሳለፍ እፈልጋለሁ
ማለት ያለብህ:  በዚህ ሳምንት ቅዳሜ ከአንቺ ጋር እራት ልበላ እና ፊልም ላይ እፈልጋለሁ። ይመችሻል?

ማለት የሌለብህ:  ቤት ውስጥ እንድታግዘኝ እፈልጋለሁ
ማለት ያለብህ:  ከሰኞ እስከ አርብ ማታ ማታ እቃውን እንድታጥብልኝ እፈልጋለሁ

5. ደጋግመህ ጠይቅ
በመጠየቅ ውስጥ አንዱ ትልቅ መርህ፣ ስትጠይቅ እጅ አለመስጠት እና መጽናት ነው። ግብህ እንዲሳካ ሰዎችን ተሳትፏቸውን ስትጠይቅ አንዳንዴ አይቻልም ትባላለህ። ላለመሳተፋቸው ደግሞ ሌሎች ቅድሚያ የሚሰጧቸው ነገሮች፣ ኃላፊነት እና ምክንያት ሊኖራቸው ይችላል።

የሆነ ሰው አይሆንም ሲል በፍጹም እጅ ሳትሰጥ ደጋግመህ ጠይቅ ። ምናልባትም ያንኑ ሰው እራሱን ሊሆን ይችላል ደጋግመህ ጠይቅ።

እሺ የምትባልበት እድል አለ
√ በተለየ ቀን ስትመጣ
√ ሰውዬው የተሻለ ስሜት ላይ ሲሆን
√ አዲስ የምታሳየው መረጃ ሲኖርህ
√ ለእነሱ ያለህን ቁርጠኝነት ካሳየህ በኋላ
√ ነገሮች ሲቀየሩ
√ የተሻለ የማስወሰን ችሎታ ሲኖርህ
√ የበለጠ ከሰውየው ጋር ስትተዋወቁ
√ ሰውዬው የበለጠ ሲያምንህ
√ ኢኮኖሚው ሲሻሻል

ደጋግሞ መጠየቅን እና መቀበልን ከልጆች በላይ የሚያውቅ የለም።

ኮርጃቸው !!!

ቃል ህይወት ነው ሃሳብን ያቀናል፣ ስሜትን ይፈጥራል ፣ ከዛም ተግባርን ያስጀምራል

ስለዚህም ሃሳቡን ከገዛን ይሄን አዎንታዊ ማረጋገጫ ከልብ አብረን እንበል።

(ምናልባት አረፍተ ነገሩን ስንል ውስጣችን ይሄ ውሸት ነው ወይም አይቻልም የሚል ስሜት ከፈጠረብን ግን ሃሳቡን ሳንቀይር አረፍተ ነገሩን መቀየር እንችላለን።)

"በጠየቅኩ ቁጥር እሺ የመባል እድሌን ስለማሰፋ፣ ስጠይቅ በጽናት ነው ምጠይቀው"

ሰኞ ደስ ሲል 🤩😁🙏❤️

13 Oct, 20:37

"እኔ ሁልጊዜ የምጠይቀው በእርግጠኝነት እና እሺ የሚል መልስ አገኛለሁ በሚል አዎንታዊ መጠበቅ ነው"

የ180 ቀን 43ኛው ቀን #አዎንታዊማረጋገጫ

ቀሪ 137  😁😁 ቀን ብቻ

መርህ ቁጥር 17
ጠይቅ ጠይቅ ጠይቅ

በታሪክ ውስጥ ብዙ የጠየቁ እና የተቀበሉ ሰዎችን እናያለን። መጠየቅ አንዱ የስኬት መርህ ነው። ነገር ግን ብዙዎችን የሚቸግራቸው እና ወደኋላ የሚያስቀራቸው ነው። ምናልባት አንተ ማንኛውንም ነገር ከማንኛውም ሰው የምትጠይቅ ከሆነ ይሄ ችግር ብዙም ላይመለከትህ ይችላል። ብዙዎች ግን የህይወት አላማቸውን እና ህልማቸውን ለማሳካት የሚያስፈልጋቸውን መረጃ፣ እርዳታ፣ ገንዘብ፣ ጊዜ፣ እውቀት እና ሌሎች ጥሬ ሃብቶች ከመጠየቅ ይቆጠባሉ።

ብዙዎች ይሄን ከማድረግ የሚቆጠቡት የቸገራቸው፣ ሞኝ ፣ እና ጅል ላለመምሰል ነው። ከሁሉም በላይ የሚፈሩት ነገር ቢኖር ተቃውሞን ነው። አይሆንም የሚለውን ቃል መስማት አይፈልጉም።

የሚያሳዝነው ነገር ግን ማንም ሰው አይሆንም ከማለቱ በፊት በውስጣቸው ባለው ድምጽ ምክንያት አስቀድምው እራሳቸውን መቃወማቸው እና አይሆንም ማለታቸው ነው።

ጠይቅ - ምንም አትሆንም።

ካለመጠየቅ ደጃዝማችነት ይቀራል