The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

@beakal_chelsea


ይህ የቴሌግራም ቻነል የእግር ኳስ ዜናዎችን፣ ታሪኮችን እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተለይ ለእንግሊዙ የለንደን የእግር ኳስ ክለብ ቼልሲ ትልቅ ትኩረት በመስጠት ያቀርባል!

አላማችን ኢትዮጵያዊያን የቼልሲ ደጋፊዎች ጥራት ያለው እና ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ እንዲሁም ስለሚደግፉት ክለብ አኩሪ ታሪክ፣ ጠንካራ ማንነት፣ የድል አድራጊነት ባህል ጥሩ ግንዛቤ እንዲኖራቸው መስራት ነው።

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

25 Aug, 15:12


ዋው !!

ቼልሲዎች በማዱዌኬ (3)፣ ጃክሰን፣ ፓልመርና ፊሊክስ ጎሎች በጥሩ ብቃት ዎልቭስን 6 ለ 2 አሸንፈው የውድድር አመቱን የመጀመሪያ ሙሉ 3 ነጥብ ይዘው ወተዋል።

ጨዋታውን እንዴት አገኛችሁት?

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

25 Aug, 09:23


ከቪክቶር ኦሲሚዬን ወደ ካልቨርት ሊዊ?

የናፖሊው የፊት አጥቂ ናይጄሪያዊው ቪክቶር ኦሲሚየን የተጋነነ ደሞዝ እንዲከፈለው መጠየቁን ተከትሎ ቼልሲዎች ከእሱ ጋር ሲያደርጉት የቆዩትን ድርድር አቋርጠው ፊታቸውን ወደ እንግሊዛዊው የኤቨርተን አጥቂ ካልቨርት ሊዊ መመለሳቸው ዘ ሰን እና ስካይ ስፖርት ዘግበዋል።

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

19 Aug, 19:33


ፌሊክስ ተመልሷል!

ጆአዎ ፌሊክስ የልቡ መሻት ተፈፅሞለት ከአትሌቲኮ ማድሪድ በቋሚ ውል ወደ ቼልሲ ተመልሷል። ፌሊክስ እስከ ሰኔ 2030 ድረስ የሚያቆየውን የስድስት አመት ውል ከመፈራረሙ በፊት በለንደን የህክምና ምርመራ ያደርጋል። ኮንትራቱ እስከ 2031 ድረስ ያለውን አማራጭ ያካትታል።

እንኳን ተመለስክ!

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

17 Aug, 18:42


ምንድን ነው?

ቻሎባህ፣ ኮኖር፣ አሁን ደግሞ ቺሊ ከቼልሲ የተገፉበት መንገድ የተጨዋቾቹን ብቻ ሳይሆን የክለቡንም ክብር አይመጥንም። ተጨዋቾች ይመጣሉ ይሄዳሉ፣ አዲስ ነገር አይደለም። ለክለቡ እድገት አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ ተጨዋቾችን በተለያየ ምክንያት ማሰናበት የማያከራክር ጠቃሚ ውሳኔ ሊሆን ይችላል። ጥያቄው ለምን ይሰናበታሉ አይደለም፣ የሚሰናበቱበት መንገድ ግን ያሳቅቃል፣ ለቀድሞ ተጨዋቾቹ ሳይቀር የማይቋረጥ ቤተሰባዊ ፍቅር በመስጠት ለሚታወቀው የቼልሲ እግር ኳስ ክለብ ይህ አካሄድ ያልተለመደ እና ቅር የሚያሰኝ ነው። ማሰናበት የመጨረሻ አማራጭ ከሆነ የተጨዋቾችን ክብር እና የደጋፊውን ስሜት በማይነካ መልኩ መፍትሄ መስጠት አይቻልም ነበር?

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

12 Aug, 09:58


ፊሊክስ ሊመለስ ነው!

ፌሊክስ ወደ ቼልሲ ለመመለስ ፍቃደኛ ነው። የሳሙ ኦሞሮዲዮን ስምምነት ከከሸፈ በኋላ ቼልሲዎች በፌሊክስ ስምምነት ላይ እየሰሩ ነው። በሁለቱ ክለቦች መካከል ንግግሮች በመካሄድ ላይ ናቸው፣ ቼልሲዎች እንዴት እንደሚቀጥሉ ቶሎ ይወስናሉ ተብሎ ይጠበቃል። ፊሊክስ ቀድሞውንም በቼልሲ ደስተኛ እንደነበር እና በፕሪምየር ሊጉም መጫወት እንደሚመርጥ ተገልጿል። ከአንድ አመት በፊት ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ነበር ፊሊክስን በእቅዱ ውስጥ እንደሌለ ገልፆ የውሰት ውሉ እንዲቋረጥ የተደረገው።

ፊሊክስ እንዲመለስ ትፈልጋላችሁ?

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

11 Aug, 16:14


እንኳን ደህና መጣህ!!

አዲሱ ሰማያዊ ፔድሮ ኔቶ - የ2024/25 የውድድር አመት በጉጉት እንድንጠብቅ ከሚያደርጉን ጥቂት ምክንያቶች አንዱ ነው።

ከጉዳት ይጠብቅህ!!

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

31 Jul, 05:34


ፊሊፕ ዮርገንሰን አዲሱ ሰማያዊ፣ እንኳን ደህና መጣህ!

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

27 Jul, 16:04


ፊሊፕ ዮርገንሰንን ለሰማያዊዎቹ ሊፈርም ነው!

ቼልሲዎች የቪላሪያሉን ዴንማርካዊ ግብ ጠባቂ ፊሊፕ ዮርገንሰንን በ24.5 ሚሊዮን ዩሮ ለማስፈረም ተስማምተዋል።

ዮርገንሰን በቀጣዩ ሳምንት በለንደን የሜዲካል ምርመራውን እንደሚያከናውን እና ኮንትራቱን እንደሚፈርም ታውቋል።

ዮርገንሰን እና ሳንቼዝ የሰማያዊዎቹ ቁጥር አንድ ተመራጭ በረኛ ለመሆን ይፎካከራሉ።

የሳንቼዝን መጎዳት ተከትሎ የባለፈውን አመት በጥሩ ብቃት የጨረሰው ወጣቱ የቼልሲ ግብ ጠባቂ ፔትሮቪች እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል እስካሁን በግልፅ የተወሰነ ነገር የለም።

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

25 Jul, 17:05


የውድድር አመቱ እስኪጀመር ጓጉቻለሁ!

"እንደ ቡድን ረዘም ካለ እረፍት በኋላ የመጀመሪያው ጨዋታችን ነበር፣ ለእኔ ደግሞ በግሌ ከረዥም ጊዜ በኋላ ያደረኩት የመጀመሪያ ጨዋታዬ ነበር። በዚህ የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ላይ ወደ አቋሜ እንደምመለስ እና ወደ ሊጉ ውድድር ስንገነባ በጥሩ ብቃት እንደምጀምር አምናለሁ። በአዲሱ አሰልጣኛችን ኤንዞ ማሬስካ ስር የነበሩት የመጀመሪያዎቹ ቀናት በጣም አስደሳች ነበሩ። እስከዛሬ ከለመድኩት አሰለጣጠን ዘይቤ የተለየ ነው፣ ነገር ግን አሰልጣኙ የሚከተለው ታክቲክ እና ለመተግበር የሚፈልገው የጨዋታ ስልት ለእኔ በጣም የሚስማ ነው። ነገር ግን አሁንም የእኔ ሚና የበለጠ ለማጎልበት እና ምን እንደሚያስፈልግ የበለጠ ለማወቅ ብዙ መማር አለብኝ። አሁን ያለንበት ሁኔታ በጣም የሚያስደስት ነው፣ እናም የውድድር አመቱ እስኪጀመር ጓጉቻለሁ"

ሪስ ጀምስ ትላንት ቼልሲዎች በዝግጅት ወቅት የመጀመሪያውን የወዳጅነት ጨዋታቸውን በአሜሪካ ከደረጉ በኋላ የተናገረው።

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

08 Jul, 19:16


አዲሱ የሰማያዊዎቹ አለቃ ጣሊያናዊው ኤንዞ ማሬስካ በሚፋጀው የስታምፎርድ ብሪጅ መቀመጫ ላይ ተቀምጦ ቼልሲዎችን ወደ ስኬት ሊመራ ዝግጁ መሆኑን ዛሬ ከክለቡ የሚዲያ ክፍል ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል።

እንዲሳካለት ከልብ እንመኛለን።

በሹመቱ ምን ተሰማችሁ? ጣሊያናዊው በቼልሲ ቤት የምንመኘውን አይነት ቡድን ሰርቶ ደጋፊውን ማስደሰት ይችልይሆን? እስኪ ሀሳባችሁን አካፍሉን።

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

02 Jul, 19:21


መቶ ፐርሰንት የምችለውን ሁሉ ለማደርግ ቁርጠኛ ነኝ!!

"እኔ ከሳጥን እስከ ሳጥን ያለው ቦታ ላይ መጫወት የሚያስደስተኝ የአማካይ ቦታ ተጨዋች ነኝ። ቡድኔ ሲጠቃ ለተካላካይ መስመሩ ሽፋን ለመስጠት የምጥር፣ ስናጠቃም ወደፊት ሄጄ በተጋጣሚያች ላይ ጫና ለመፍጠር የበኩሌን ለማድረግ መቶ ፐርሰንት የምችለውን ሁሉ ለማደርግ ቁርጠኛ ነኝ። ዋንጫዎችን ማሸነፍ እፈልጋለሁ፣ ለዚህም የቼልሲ ተጨዋች በመሆኔ ደስተኛ ነኝ"

አዲሱ ሰማያዊ ኬርናን ዲውበሪይ ሃል (ኬዲኤች)

እንኳን ደህና መጣህ ብለናል!!

የሰሞኑን የቼልሲ አዳዲስ ፈራሚዎች እንዴት አገኛችኋቸው?

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

01 Jul, 16:17


ቻምፒየንስ ሊግ እና ፕሪምየር ሊግን ማሸነፍ እፈልጋለሁ!!

“በጥሩ ሁኔታ ለመጀመር በጣም አስፈላጊው ነገር ከአካባቢዬ ጋር መላመድ ነው ብዬ አስባለሁ፣ ይህም ቀላል እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ፣ እና በእርግጥ ለቼልሲ ቻምፒየንስ ሊግ እና ፕሪምየር ሊግ ማሸነፍ እፈልጋለሁ። በግሌ ብዙ ግቦችን በማስቆጠር ቡድኑን በተቻለኝ መጠን መርዳት እፈልጋለሁ። እናም የአለም ምርጥ አጥቂ መሆን እፈልጋለሁ"

ማርክ ጉዩ !

እንኳን ደህና መጣህ!

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

07 Jun, 12:23


የክረምቱ የመጀመሪያው ፈራሚ ቶሲን አድራቢዮ በነፃ ዝውውር ከፉልሃም ወደ ቼልሲ መምጣቱ ይፋ ሆኗል።

እንኳን ደህና መጣህ!

ይህን ዝውውር እንዴት አገኛችሁት?

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

03 Jun, 21:07


አዲሱ ሰማያዊ ኤንዞ ማሬስካ!

“በአለም ላይ ካሉ ታላላቅ ክለቦች አንዱ የሆነውን ቼልሲን መቀላቀል ለማንኛውም አሰልጣኝ ህልም ነው። በዚህ አጋጣሚ በጣም የተደሰትኩት ለዚህ ነው። የክለቡን የስኬት ባህል የሚያስቀጥል እና ደጋፊዎቻችንን የሚያኮራ ቡድን ለመስራት ጥሩ ብቃት ካላቸው ተጫዋቾች እና ሰራተኞች ጋር በጋራ ለመስራት ጓጉቻለሁ"

ኤንዞ ማሬስካ

ቼልሲዎች ጣሊያናዊውን ወጣት የእግር ኳስ ባለሟል ዋና አሰልጣኛቸው አድርገው መቅጠራቸውን ዛሬ ይፋ አድርገዋል።

እንኳን ደህና መጣህ!! መልካም የስራ ዘመን ይሁንልህ!!

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

27 May, 15:08


ማሬስካ ወደ ቼልሲ?

ቼልሲዎች ጣሊያናዊውን የሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካን በዋና አሰልጣኝነት ሊቀጥሩት ከጫፍ መድረሳቸውን ፋብሪዚዮ ሮማኖ ዘግቦታል።

ማሬስካ በቼልሲ የሚሳካለት ይመስላችኋል?

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

26 May, 14:59


ከብራይተን እንደገና?

ግርሃም ፖተር ብራይተንን ጥሩ ኳስ የሚጫወት ቡድን አድርጎት ስለነበር በቼልሲ ባለቤቶች ቼልሲን እንዲያሰለጥን እድል ተሰጥቶት ነበር፣ አልተሳካለትም እንጂ። ምክንያቱም ብራይተን እና ቼልሲ ሁለት በጣም የተለያየ ደረጃ ላይ ያሉ ክለቦች በመሆናቸው ነው። የፖቼቲኖም ቅጥር ተመሳሳይ ነው። አሁን ደግሞ ዲ ዘርቢም በብራይተን የሰራውን ግንዛቤ ውስጥ አስገብተው የቼልሲ ባለቤቶች በቼልሲ እድሉን እንዲሞክር እድል ሊሰጡት እንደሆነ በስፋት እየተዘገበ ነው። አዲሶቹ የቼልሲ ባለቤቶች አሰልጣኝ የሚቀጥሩት በጥናት ላይ ተመስርተው ሳይሆን በእድልና በግምት (በ "ደስ አለኝ - መሰለኝ" እንደሚባለው) ይመስላል። ለዚህም ማሳያው በሁለት አመቱ ውስጥ ቀጥረው ያሰናበቷቸውን እና አሁን ለመቅጠር የመጨረሻ እጩ ሆነው የቀረቡትን አሰልጣኞች መመልከት ይቻላል። ጥሩ ባለሙያዎች ሊሆኑ ይችላሉ፣ ናቸውም። ይሁን እንጂ አንዳቸውም በቼልሲ የልዕቀት ደረጃ ላይ የሚገኙ እንዳልሆኑ ግልፅ ነው። በቼልሲ ያለውን ጫና (ዋንጫ አላልኩም) ለመቋቋማቸው ምንም ማረጋገጫ የለም። ሊቋቋሙትም ላይቋቋሙትም ይችላሉ፣ እድላቸውን ይሞክራሉ። ከሆነላቸው ጥሩ ነው፣ ካልሆነላቸው ይሰናበታሉ። አሁን የሚቀጠሩት አልሆን ብሏቸው ሲሰናበቱ ደግሞ ሌሎች ወጣት "ታለንት" ያላቸው አሰልጣኞች ታላቁን ቼልሲ የማሰልጠን እድሉን እንደሚያገኙ ይጠበቃል።

ዲ ዘርቢ እድሉን ቢያገኝ በቼልሲ የሚሳካለት ይመስላችኋል?

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

22 May, 12:48


ፖቼቲኖ ለምን ተሰናበተ?

ፖል ሜርሰን የፖቼቲኖን የስንብት ውሳኔ በተመለከተ እንዲህ ብሏል

"ይሄ እብደት ነው፣ ስለ ፖቼቲኖ መሰናበት የምሰማውን ነገር ማመን አልቻልኩም። ቡድኑን እያሻሻለው ነበር፣ የአውሮፓ ውድድር ላይ ተሳታፊ እንዲሆን አስችሎታል፣ ማንችስተር ዩናይትድን በልጦ 6ኛ ደረጃ እንዲይዝ አድርጎታል"

……………………… …………………………

ሁኔታዎች እንደሚጠቁሙት ፖቼቲኖ የተሰናበተው ባስመዘገበው ውጤት የተነሳ አይደለም። የሊጉን ዋንጫ ቢወስድም እነ ቶድ ቦሊ የማይታዘዛቸውን አሰልጣኝ በቼልሲ እንዲቆይ አይፈቅዱም። በሚታዘዛቸው ወቅትማ ክለቡ ቢወርድም እንደግፈዋለን እያሉ፣ በፕሮጀክታቸው እንድናምን ሲጎተጉቱን ነበር። አሁን ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ? … ፖቼ መታዘዝ አቆመ ወይም አጉረምርሟል። በዋናነት ጋላጋር እና ቻሎባህ እንዲሸጡ አይፈልግም፣ ባለቤቶቹ ደግም በሁለቱ የአካዳሚ ተጨዋቾች ሽያጭ የሚያገኙት ገንዘብ ንፁህ ትርፍ በመሆኑ እንዲሸጡ ይፈልጋሉ። የፍላጎት ግጭቱን (conflict of interest) እነሱ አለቃ ስለሆኑ አሰልጣኙን በማሰናበት ለመፍታት ሞክረዋል። ቶማስ ቱኩልንም ያሰናበቱት የእኛን ፍላጎት አያከብርም ብለው ነው፣ የእነሱ ፍላጎት በቼልሲ ከፍተኛ ትርፍ ማጋበስ ነው። ተጨዋቾች የሚገዙት ከክለቡ ውጤት አንፃር ብቻ ሳይሆን ወደፊት ከሚያገኙት የሽያጭ ትርፍ አንፃር ነው። ፖቼቲኖ የተሰናበተው ከቼልሲ ውጤት አንፃር ቢሆን ኖሮ መሰናበት የነበረበት አሁን ሳይሆን ከ6 ወር በፊት ነበር። ያኔ የማንም መጫወቻ ሆኖ በየሳምንቱ ሲሸነፍና ደጋፊው ሲያዝን "በፖቼቲኖ እንተማመናለን፣ ከአሰልጣኙ ጋር የረጅም ግዜ ፕሮጀክት ነው ያለን፣ ደጋፊው ትዕግስት ሊኖረው ይገባል" እያሉ ያላግጡ ነበር። አሁን ደጋፊው በቡድኑ እንቅስቃሴ ተስፋ ማድረግ ሲጀምር የእነሱ ጥቅም ስለተነካ ብቻ በድንገት ያለምንም ማቅማማት በ30 ደቂቃ ንግግር ቶማስ ቱኩል ላይ የመዘዙትን የስንብት ሰይፋቸውን አወጡ። ጥቅማቸውን ለማስከበር የሚሄዱበት ርቀት እና ቡድኑ ውጤት ሲያጣ የሚያሳዩት ገደብ አልባ ትዕስት የሰማይ እና የምድር ያህል ይራራቃል።

አሁንም እየፈለጉ ያሉት የሚታዘዛቸውን ወጣት እና ልምድ የሌለው አሰልጣኝ መሆኑን ይፋ ማድረጋቸው ደግሞ የበለጠ ልብ ይሰብራል። ይህ ምን የሚሉት መስፈርት ነው? ትልልቅ ፕሮፋይል ያላቸው አሰልጣኞችን የማይፈልጉት ስለማይታዘዟቸው ከመሆኑ በስተቀር ሌላ ምን ምክንያት ሊኖራቸው ይችላል? … በዚህ አካሄዳቸው የምንወደው ክለባችን ባለቤቶች ቡድኑን ወደ ቀድሞ ክብሩ ይመልሱታል ማለት ዘበት ነው። ተጨዋቾች ውጤታማ ካልሆኑ ይሸጣሉ ወይ በውሰት ይሰጣሉ፣ አሰልጣኝም ቢሆን ካልሆነለት ይሰናበታል፣ የክለብ ባለቤት ክለቡን ሲያምስ ግን ምን ይደረጋል? … የቸገረ ነገር ነው የገጠመን፣ ቢሆንም ግን ይህም ይታለፋል!!