Ethio Book Review

@etbookreview


The largest Ethiopian Digital Book Platform. Visit https://ethiobookreview.com

Ethio Book Review

01 Oct, 04:15


ኤክሴ ናት ከተለያየን ነፍፍፍፍፍ....ፍፍፍ ግዜ ሆኖናል። ከነፍፍ ጊዜ በኋላ ተደዋውለን ሻይ እየጠጣን ነው። በዝብዘባችን መሃል ለምን ያኔ ተውሺኝ አልኳት

"honestly speaking  ያኔ መተው ነበረብኝ" ብላ ፀዴ ፈገግታ ፈገግ አለች ።

"ይብራራ"- አልኮት
ጥቂት ፈገግታ እና ብዙ  ጭፍግግታ በተላበሰ ፊቴ ።

"ጭንቅሌህ ሃሳብ አልባ ነበር። የማይጥምህን ሃሳብ ነፍስህ ተረጋግታ አትሰማም ።አንተ ያልፈለከው ካልሆነ ነፍስህ ትቅበዘበዛለች😢ሁሌ ከአንተ የፈለቀ ሃሳብ ትክክለኛ እና አዳኝ ይመስልሃል። soft dictator ነህ። አምባገነንነትህ እንደእኔ አራዳ ያልሆነ ካልሆነ አይባንነውም።ነፍስህ ሊብራል አይደለችም።

ፍቅርህ እጅ መንሻህ ነበር ።
መከራከርያ፤መደራደርያህ፤ማፅናኛህ ፤መፅናኛህ  ፍቅር ነበር ። ፍቅር ከእውነት የሚበልጥ ይመስልካል። ቅናትክ ፈጣጣ ነበር ። ስሜትህን አሁንም አሁንም ታንፀባርቃለህ።

emotional intelligence ይጎልሃል ።
የሆነው ሆኖ አሁን ቢሆን ኖሮ አልተውክም ነበር። ያኔ ሙሉ ሰው ፍለጋ ላይ ነበርኩ።
ሙሉ የሚባል  concept አለመኖሩን ለመረዳት ብዙ ነፍስ ጋር ተዋሃድኩ ይሁን እንጂ ጉድለት መልክ እና ይዘቱን እየቀያየረ ሁሉም ጋር እንዳለ ተከሰተልኝ።

ጉድለት ይዞ ምሉዕ ፍለጋ መባተል ያለመብሰል ምልክት ነበር።
አለመብሰል ነበር ያዳከረኝ 🚶‍♀🚶‍♀🚶‍♀
ትላንት  ካንተ ጋር ለመሆን ፍላጎት  አልነበረኝም ፤ ዛሬ ደሞ እድሉ የለኝም ።
ጭንቅላቷ ሰላብኝ። ከነፍስ ነፍስ መባተሏ እንዳበሰላት ገባኝ ። 

ማሳሰብያ፦
የመለያየት ምክንያት ፍፁም ነፍስ ፍለጋ መባተል ነው፦
አለመብሰል በረከታችንን ያሳጣናል


Source: noahbookdelivery

Ethio Book Review

18 Sep, 04:06


“እሺ” እና “እምቢ”

ሕይወት ተፈጥሯዊ ሂደቷን እንድትቀጥልና ሁኔታዎች በራሳቸው መስመር እየያዙ እንዲሄዱ መለማመድ የምንችላቸው ሁለት ልምምዶች አሉ፡፡ እነዚህ ልምምዶች ከለመድናቸው እጅግ ቀላል የሆኑ፣ ካላወቅንበት ግን የሚከብዱ ልምምዶች ናቸው፡፡

1. ለተገቢው ነገር “እሺ” ማለት፡- በሕይወታችን መልካም ነገሮች እንዲገቡ በሩን የሚከፍተው ቁልፍ!

በሚገባና በተረጋጋ መንፈስ አስባችሁበት ትክክለኛ እንደሆነ ላመናችሁበት ነገር “እሺ” ማለት ሌሎች መልካም ነገሮች እየተወለዱ የሚሄዱበትን መስመር ይከፍትላችኋል፡፡

2. ተገቢ ላልሆነ ነገር “እምቢ” ማለት፡- በሕይወታችን ጤና-ቢስ ነገሮች እንዳይገቡ በሩን የሚዘጋው ቁልፍ!

በሚገባና በተረጋጋ መንፈስ አስባችሁበት ትክክለኛ እንዳልሆነ ላመናችሁት ነገር “እምቢ” ማለት ደግሞ በሕይወታችሁ መልካም ያልሆኑ ነገሮች እየተበራከቱ እንዳይሄዱ መንገዱን ይዘጋዋል፡፡

እነዚህ ሁለት ልምምዶች ፍርሃትን አልፎ መሄድን ይጠይቃሉ፡፡

በአንድ ጎኑ፣ “እሺ” ለምንለው ነገር ብቁ ባንሆንስ፣ ባይሳካስ፣ በኋላ ብጸጸትስ . . . እና የመሳሰሉትን ፍርሃቶች ማስወገድን ይጠይቃል፡፡

በሌላ ጎኑ ደግሞ “እምቢ” በማለታችን ምክንያት ችግር ቢደርስብንስ፣ እድል ቢያመልጠንስ፣ ሰዎች ቢቀየሙንስ . . . እና የመሳሰሉትን ፍርሃቶች ማስወገድን ይጠይቃል፡፡

Source: Dr Eyob Mamo

Ethio Book Review

17 Sep, 06:42


ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በኢትዮዽያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት ነበሩ። ረዘም ላለ ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስሰማ ከልብ አዝኛለሁ። ያቆዩት ውርስ እና ቅርስ ፀንቶ እንዲቀጥል ነፍሳቸውም በሰላም እንድታርፍ እመኛለሁ።

Professor Beyene Petros embodied the spirit of peaceful political struggle, playing a pivotal role in fostering a culture of non-violence and constructive political dialogue in Ethiopia. I am deeply saddened to hear of his passing after a prolonged period of medical care. May his legacy endure, and may he rest in eternal peace.

Ethio Book Review

15 Sep, 11:31


እንዴት አገኛችሁት?

Ethio Book Review

15 Sep, 10:03


በዚህ ዓመት . . .

ራሳችሁን ያላዘጋጃችሁለትን ነገር ለምናችሁ ለጊዜው እጃችሁ ከምታስገቡ ይልቅ፣ ራሳችሁን በማሳደጋችሁና በማሻሻላችሁ ምክንያት ነገሩ ወደ እናንተ ቢመጣና እስከወዲያኛው ቢቆይ ይሻላችኋል፡፡

Ethio Book Review

13 Sep, 13:08


Cowards experience death multiple times before their final demise.
'
ለተጨማሪ ጠቃሚ አባባሎችና ምክሮች፡ https://www.ethiobookreview.com/amharic-quotes

Ethio Book Review

11 Sep, 04:57


Happy Ethiopian New Year 2017

እንኳን ለ2017 አዲሱ አመት አደረሳችሁ

Baga bara haaraan isin gahe

Ethio Book Review

10 Sep, 09:50


እንኳን ለ 2017 ዓ.ም አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ!

ዘመኑ የሰለም፣ የፍቅር፣ የስኬት እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!

መልካም በዓል!

www.ethiobookreview.com

Ethio Book Review

06 Sep, 13:34


በቃ ተወው!

Ethio Book Review

06 Sep, 09:21


For you

Ethio Book Review

04 Sep, 07:28


አንዳንዴ ህይወት በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ትሞላለች፣ ግን ደግሞ አንዳንዴ ቀለል ያሉ ጥቅሶችና ንግግሮች አስተሳሰባችንን ለውጠው ቀናችንን ብሩህ ልያደርግልን ይችልላሉ።
እርስዎስ ምን ሀሳብ አለዎት?

https://www.ethiobookreview.com/amharic-quotes

Ethio Book Review

04 Sep, 04:00


ይሞክሩት

Ethio Book Review

03 Sep, 17:13


ይህንን አባባል እንዴት ያዪታል?

Ethio Book Review

02 Sep, 12:55


የንባብ ጥቅም

1. ከቀደሙት ዘመናት ጋር ያገናኛል፡፡የቀደሙት የተጻፉጽሑፎች በዚያ ዘመን ስለነበሩ ታሪክና ሥራ በግልጽ እንድናውቅ ያደርጉናል፡፡

2. ጥሩ እውቀት እንዲኖረን ያደርጉናል፡፡
3. አንድ ወጥ ቋንቋና ዕውቀትን ያስጨብጣል፡፡የቀደሙጸሐፊዎችን አባባል እንድንጠቀምበት ይረዳናል፡፡
4. ሰው የሦስት ዘመን ውክልና ያለው በመሆኑ ያለፉትንና የወደፊቱን እንዲኖር ያደርጉታል፡፡

አንብቡ ለማለት ያክል ነው!
www.ethiobookreview.com