A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

@aahdabofficial


A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

22 Oct, 06:18


በፅ/ቤት ዘርፍ  ስር ያሉ ዳይሬክቶሬቶች  የሩብ አመት የዝግጅት ምእራፍ  አፈፃፀም ተገመገመ

የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የፅ/ቤት ዘርፍ ስር የሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች የ2017 የሩብ አመት  የዝግጅት ምእራፍ አፈፃፀም ተገመገመ።

በሩብ አመቱ የዝግጅት ምእራፍ እቅድን ለቡድን እና ለሰራተኛ ከማውረድ እና ስራን በእቅድ ከመምራት ጀምሮ ከለውጥ ስራ ጋር  በተያያዘ የመልካም አስተዳደር እና የኪራይ ሰብሳቢነትን ለመከላከል የተሰሩ ስራዎች ተገምግመዋል።

አቶ አብዲሳ አራርሶ የቢሮው የፅ/ቤት ኃላፊ ስብሰባውን በመሩበት ወቅት እንደተናገሩት በዘርፉ በዝግጅት ምዕራፍ የተሰሩ ስራዎች አዳጊ እና መሻሻሎች የታዩባቸው መሆኑን አሳውቀዋል።

ኃላፊው አክለውም በሩብ አመቱ የታዪ ክፍተቶችን በመድፈን ዘርፉ አላማ ፈፃሚዎችን ደግፎ መስራት ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት የተግባር ምእራፉን በውጤት ማጠናቀቅ ይገባል ብለዋል።

በስብሰባው የፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዲሳ አራርሶን ጨምሮ የዘርፉ ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል።

A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

21 Oct, 12:47


ማስታወቂያ

የማህበር ቤት ተመዝጋቢ የሆናችሁ እና ቀደም ሲል ስም ዝርዝራችሁ ተገልፆ ቅጽ 01 አስሞልታችሁ የመመለሻ ቀን የተራዘመባችሁ ተመዝጋቢዎች በሙሉ።

ቅፁን እና አስፈላጊውን  መረጃዎች ይዛችሁ ከጥቅምት 13/2017ዓ.ም ጀምሮ እስከ ተቅምት 19/2017 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ብቻ ባምቢስ ግሪክ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ ህንፃ 6ኛ ፎቅ የቤት ማህበራት ዳይሬክቶሬት በመገኘት መረጃችሁን እንድታስገቡ እናሳወቃለን፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ

A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

18 Oct, 08:58


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡

1. ዶ/ር ጌዲዮን ጥሞቲዮስ፦ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር
2. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፦ የቱርዝም ሚንስቴር ሚንስትር
3. ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ፦ የፍትህ ሚንስቴር ሚንስትር

ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት

A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

16 Oct, 08:51


በሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ተነሺዎች ለአረጋዊያን እና ለአካል ጉዳቶኞች ቅድሚያ በመስጠት አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል

የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
ለሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ተነሺዎች እና ተለዋጭ ቤት የሚሰጣቸው  አረጋዊያን እና ለአካል ጉዳቶኞች ቅድሚያ በመስጠት አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ ክብርት ቅድስት ወልደ ጊዮርጊስ ዛሬ ተገልጋዮችን እያስተናገዱ ባሉበት ወቅት ተናግረዋል።

በተለይም የጤና እክል ያለባቸውን ፣ አካል ጉዳተኞችን እና አረጋዊያንን ቅድሚያ በመስጠት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የቢሮ ኃላፊዋ  አሳውቀዋል።

ከተማ አስተዳደሩ የጀመረው እና ከተማዋን እያዘመነ ባለው የኮሊደር ልማት ስራ ለልማቱ ተነሺዎች ተለዋጭ ቤት በመስጠት ቢሮው የበኩሉን  አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።