******
ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም
ክቡር የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በስብሰባው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው በሰጡት የሥራ መመሪያ በዚህ በሪፎርም ጊዜ ሕዝቡ የሚፈልገው ፖሊስ፤ በጣም ዲሲፕሊን የሆነ፣ የማይሰርቅ፣ አለባበሱ የሚያምር፣ ሥርዓት ያለው፣ ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም የሚችል እና የትም ቦታ ሄዶ ወንጀል መከላከል የሚችል ብቃት ያለው፣ በዘር የማያምን፣ ከፖለቲካና ከሀይማኖት ወገንተኝነት የፀዳ ፖሊስ ነው ብለዋል።
ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል የስትራቴጅክ እና ከፍተኛ አመራሮች የአመራር መርሆዎችን (leadership principles) በትክክል ተገንዝበው ሥራ ላይ እንዲያውሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናም ሰጥተዋል።
የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትም ቀርቦ በክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ከተሰጡ በኋላ ተጠናቋል።
ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል አያይዘውም ጠንካራና ከችግር ፈጥኖ የሚወጣ ፖሊስ ለመፍጠር የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የጀመረውን የአቅም ግንባታ አጠናክሮ እንዲቀጥል መመሪያ ሰጥተዋል።
በቀጣይ በተቋሙ የተፈጠሩ የድሮን እና የሌሎች የቴክኖሎጂ አቅሞች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
አመራር ሁሌም እየተማረና የቡድን ሥራ አጠናክሮ የሚሰራ ከሆነ የማንሻገረው ምንም አይነት ችግር የለም ያሉት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጌቱ ተ/ዮሐንስ ናቸው።
አመራሮቹ ውይይት ሲያካሄዱ የቆዩት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተዘጋጀው ''የፖሊስ የመነሳት ዘመን'' በሚል ሰነድ ላይ ነው።
አመራሮቹ ስብሰባውን ካጠናቀቁ በኋላ የፎረንሲክ ሳይንስ ኢንስቲትዩት የምርመራ ልህቀት ማዕከልን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።