来自 ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ (@wku_gg_media) 的最新 Telegram 贴文

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ Telegram 帖子

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
ይህ በወልቂጤ ማዕከል ግቢ ጉባኤ ማሰተባበሪያ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግ.ጉ አባላት መረጃ መለዋወጫ 'የቴሌግራም' ገፅ ነው።


👇👇👇ተከታዮቹን ገጾች ይቀላቀሉ 👇👇👇

Telegram፦
https://t.me/wku_gg_media

YouTube፦ https://www.youtube.com/@Wku_gg

የፎቶ ማኅደራችን
@wku_gg_gallerystore

ለሃሳብና አስትያይቶ @wkugg_bot
3,510 订阅者
3,117 张照片
74 个视频
最后更新于 01.03.2025 07:20

相似频道

Kenya MedLab Hub
1,786 订阅者

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ 在 Telegram 上分享的最新内容


እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም  አመታዊ የቃል ኪዳን መታሰቢያ (ለኪዳነ ምህረት) በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን !!!
" ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ።"
                  መዝ. ፹፱፥፫

እመቤታችን ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የማይጠፋ የዘላለም ኪዳን የተቀበለችበት ዕለት መታሰቢያ ነው
እግዚአብሔር ዓለሙን ከፈጠረ ጊዜ ጀምሮ ፍጥረታቱን ሁሉ በቸርነቱ ይጠብቃል፣ ይመግባል።
ሕግን ተላልፈው ኃጢአት ሰርተው፣ በመንፈሳዊ ህይወታቸው ዝለው ባሳዘኑት ጊዜ ከጥበቃውና ከበረከቱ እንዳይርቁ ስለቧለሟለቹ  ቅዱሳን ብሎ በቃል ኪዳኑ ይጠብቃቸዋል።
... "እመቤቴ ኪዳነምህረት ሆይ. . .
በአካል ሦስት ሲሆን በመለኮታዊ ባሕርዩ በአንድነቱ ጸንቶ የሚኖር የብርሃን መገኛ እሱ እግዚአብሔር አብ ለቃል ኪዳንሽ የተሰጠውን ልዩ ክብር ብሩህ አድርጎ ያሳየኝ_ዘንድ የቸርነቱ ጸዳለ ብርሃን
ዓይነ ልቡናዬን ይብራልኝ።
የቃል ኪዳኗ እመቤቴ ሆይ ከእግዚአብሔር በታች በሰማይም በምድርም አንቺ  የሁሉ እመቤት ነሽ.. "

🖍✥መልክአ ኪዳነምህረት✥

"እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የምሕረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበት አመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!"

        
   ◈◈◈ወ▮ዩ▮ግ▮ጉ◈◈◈

ኪዳነ ምሕረት

በድንቅ ጥበቡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ያደነው እጅጉን መሐሪ ስለሆነ ነው፡፡ የቀደሙት የብሉይ ኪዳን ኪዳናት ሕዝቡን ከሲኦል መታደግ አልቻሉም ነበር፡፡ ፍጹም የሆነው ኪዳን የተደረገው በሰባተኛው ኪዳን ይህም ለሰው ዘር ምሕረትን ባስገኝች በንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ነው፡፡  
 
የምሕረት ቃል ኪዳን የተሰጠችውን እናታችንንም ‹‹ኪዳነ ምሕረት›› እያልን የምንማጸናት ለዚህ ነው፡፡ ለአዳም የተገባለት የምሕረት ቃል በእርሷ ተፈጽሟልና፡፡ እመቤታችን አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ወልዳዋለችና፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራን ተቀብሎ እንዲሁም በመስቀል ተሰቅሎ ዓለምን ያዳነው ከእርሷ በነሣው ሥጋና ነፍስ ነውና፡፡  
 
በነገረ ማርያም ተጽፎ እንደምናገኘው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት በኋላ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ልጇ መቃብር ቦታ ጎልጎታ እየሄደች ትጸልይ ስለ ነበር  በየካቲት ፲፮ ቀን በጸለየችው ጸሎት ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ ጸሎቷም እንዲህ የሚል ነበር፤ ‹‹ልጄ ወዳጄ ሆይ፥ ከሥጋዬ ሥጋ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በቻለችህ ማኅፀኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡››
 
ጌታችንም ምን ሊያደርግላት እንደምትሻ ሲጠይቃት በስሟ ለሚማጸኑ፣ መታሰቢያዋን ለሚያደርጉ፣ ለችግረኛ ለሚራሩ፣ በስሟ ቤተ ክርስቲያን ለሚያንጹ፣ ዕጣን፣ ዘይትና መብአ ለቤተ ክርስቲያን ለሚሰጡ ምሕረትን እንዲያደርግላቸው ጨምራ ጠየቀችው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በየካቲት ፲፮ ዕለት የገባላትን ቃል ኪዳን እንዲህ በማለት በመሐላ አጽንቶታል፡፡  ‹‹መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበአቡየ ወበመንፈስ ቅዱስ ሕያው፤ በራሴ፣ በአባቴ እና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ፡፡›› 
የምሕረት ቃል ኪዳን የተሰጠበት ይህ ዕለት ታላቅ ነውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቅት ታከብረዋለች፡፡ ቀድሞ ለነበሩ ኪዳናት ማለትም ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ኖህ፣ ኪዳነ መልከ ጸዴቅ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ሙሴና ኪዳነ ዳዊት መደምደሚያ ነውና፡፡ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነው የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳን እየታሰበም በመዝሙር፣ በማኅሌትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡
 
በክርስቶስ ክርስቲያን ለምንባል ለእኛ የሐዲስ ኪዳን የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ይህ አዲስ ውል የተደረገልን ለነፍሳችን ድኅነት በመሆኑ በስሟ እየተማጸንን እንዲሁም መታሰቢያዋን እያደረግን ለተራቡት ማብላት፣ ለተጠሙት ማጠጣትና ችግረኛ መርዳት ይገባናል፡፡  

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎት፣ አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን! 

🎲 Quiz 'ወ/ዩ/ግ/ጉ የሳምንቱ ጥያቄ ፲፪'
ይህ በየሳምንቱ በሚድያ ክፍል እየተዘጋጀ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት ከምሽቱ 2:00 የሚቀርብላችሁ የሳምንቱ ጥያቄ የተሰኘ መርሐ ግብራችን ነው ይሳተፉ ሌሎችንም በመጋበዝ ያሳትፉ
🖊 5 questions · 45 sec

👉👉👉የእለቱ መልእክቶች 👈👈👈

👉 ከትላንት አንስቶ እስከ ዛሬ እለት ( አርብ እና ቅዳሜ ) በነበረው የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሀግብር ብዙ ቁም ነገር እንዳገኛችሁ ትልቅ እምነት አለን


👉መርሀግብሮችንም ዛሬ ማለትም ቅዳሜ ጨረሰናል እሁድ የተባለው መረሀግብ በመርሀግብራት መደራረብ ምክንያት ተሰርዞዋል 👈

በሃይማኖት ከማይመስሉን ጋር እንዴት እንኑር?

የመጨረሻ ክፍል


      " ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።" ወደ ሮሜ ሰዎች 12:18
በሃይማኖት አንድ አለመሆን ምክንያት ሰውን መጥላትና አብሮ መሥራት የሚገባውን ነገር አለመሥራት ተገቢ እንዳልሆነ መረዳት ይገባል:: ሆኖም ግን ሐዋርያው:- ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ ሲል ያለገደብ አልተናገረም ''ቢቻላችሁስ'' የሚል ገደብን ተናገረ እንጂ። ይህም ማለት ከሰዎች ጋር፣ ከገዢዎች ጋር የማንስማማባቸው ሁኔታዎች ይኖራሉ ይህም በሃይማኖት ጉዳይ፣ ስለ ተበደሉ ሰዎች ጉዳይና ሌሎች አግባብ ባላቸው ጉዳዮች ላይ መነጋገርና ለእነዚህም በቆራጥነት ዘብ መቆም አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ''በሰላም አብራችሁ ኑሩ'' ተብሏል ብለን ወደኋላ እንዳንል ''ቢቻላችሁስ'' አለ ሆኖም ግን እንዲህ ያለ ጉዳይ ሲገጥምም ቢሆን ትዕግሥትን እስከ ማጣትና በኅሊና አስክመታወክ በመድረስ ሳይሆን በአግባቡ፤ በትዕግሥት ሆኖ ተገቢ ያልሆነውን ነገር ብቻ በጽናት መታገል ይገባል:: እውነቱን ሳይለቁ ወደኋላም ሳይሉ ሌላው ወገን ጥላቻ ቢኖረው እንኳ እንደዚያ ሳይሆኑ በኀሊና ፍቅርን አጽንቶ መያዝ ይገባል።

   እንዲሁም ለዚህ ሁሉ የራስን አቅምና ማንነት መመዘንና ማወቅ ያስፈልጋል እኛነታችንና ጽናታችን የሚሸረሽር ከሆነ ከመጀመርያው አካሄዳችንን አርቆ ማጠርን መርሕ ማድረጉ ይጠ ቅማል። እንድ ሰው ወንዝን በዋና ለመሻገር የግድ ዋና መቻል ይኖርበታል፡ ዋና ሳይችል ወንዝ ውስጥ ቢገባ ውጤቱ ሕይወትን ለአደጋ ማጋለጥ ነው:: ስለሆነም በቀላሉ ከሌሎች ጋር በሚኖረን የሕይወት ቅርርብ ሳናውቀው የሌሎችን ባሕልና ልማድ የራሳችን አድርገን እንዳንቸገር ጥንቃቄ ያስፈልጋል ልማድ ጽኑ ነገር ነውና። ግብፃውያን መና እየተመገቡ በግብፅ የለመዱት ዱባና ነጭ ሽንኩርት ይናፍቃቸው ነበር። ነጻ ወጥተው በነጻነት እየኖሩ እያሉ የግብፅ ባርነት ትዝ ይላቸው ነበር። ብዙ ጊዜ ወደ ግብፅ መመለስን ይናፍቁ ነበር፥ ይህ ሁሉ የሆነው በግብፅ የነበረውን ነገር ለምደውት ስለነበረ ነው። ልምድ ከሥነ ህይወታዊ ተፈጥሮ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የሰውን ሕይወት የመቆጣጠር አቅም አለውና አንዳንዶች ልምድን ሁለተኛ  ተፈጥሮ /the second nature/ እስከ ማለት የደረሱት ከዚህ የተነሣ ነው። ስለሆነም ከመጀመሪያ ጀምሮ እንዳየነው ከማይመስሏቸው ጋር በማይገባ አካሄድ ሄደው እንደ ተጎዱት እንዳንሆን ያስፈልጋል:: በሌላም አንጻር እንደ ዜግነታችን-እንደ እኛነታችን ማበርከትና መሥራት ያለብንን ሳናደርግ እንዳንቀር ሁሉንም በአገባቡና በጊዜው እንደሚገባ ለማድረግ የእግዚአብሔር ጸጋና ጥበብ ያስፈልጋል፡፡ "ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ" 2ቆሮ.6:14 አለ እንጂ በምንም  ሁኔታ አትደባለቁ አላለም ችግር የሚፈጥረው አካሄዱ የማይታወቅ ሲሆን ነው:: ስለዚህ ነገሮችን ወደ ማይታወቅ አቅጣጫ እንዳይሄዱ አስቀድሞ መቆጣጠር በኋላም ፈጣንና ቆራጥ መንፈሳዊ ውሳኔ መወሰንና መፈጸም ይገባል፡፡ ተገቢውን ነገር በተገቢው ጊዜ ለማድረግ- ራሳችንን ለመጠበቅና ለመጥቀም ለሌሎችም ለመትረፍ አንድንችል የእግዚአብሔር ቸርነት  የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን ሁሉ ጸሎትና በረከት ይርዳን አሜን።
                   
    ስብሐት ለእግዚአብሔር

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ማድረግ አይርሱ

https://www.youtube.com/@Wku_gg

በሃይማኖት ከማይመስሉን ጋር እንዴት እንኑር?

ክፍል ፬

ቅ.ጴጥሮስ እና ሌሎች ሐዋርያትም ለአይሁድ ሲመልሱ ፍጹም ትህትናን በተሞላ ሁኔታ እንዲህ አሉ፡ ''ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል'' የሐዋ 5:29
ተገቢ ቢሆን የራሳቸውን ሕይወት ክደው ለተሰለፉበት ዓላማ ኃይልና ተግሣጽ ሌላም ነገር መናገር የሚገባ ቢሆን ኖሮ ይህንን ከማድረግ ወደኋላ ባላለ ነበር። ''ለእያዳንዱ መመለስ እንደሚገባ እንደ ተቀመመ በጸጋ ይሁን'' ያለው ለዚህ ነው በትዕግሥት ምክኒያት ግዴለሽነትና ፍርሃት፥ በመንፈሳዊ ቆራጥነት ሰበብ ደግሞ ነገሩ ከመስመር ወጥቶ አገባብ ወደ ሌለው ዘለፋ፥ ጠብና ክርክር እንዳይሄድ ሚዛኑን ለመጠበቅ ጥበብ ያስፈልጋል፡፡ ከሃይማኖት ውጭ ቢሆኑም አመስግኖ መናገር ካስፈለገ ይህ ማቆላመጥ ተገቢ ያልሆነ አይደለም: ሃይማኖትና ሃይማኖት ነክ ነገር እስካልተጐዳ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ማድረግ ተገቢ የሚሆንበት ጊዜ ይኖራል፡፡ ለምሳሌ ዳንኤል ለዚያ ከሐዲ ንጉሥ እንዴት በትሕትና እንደመለሰ ወደ ቤተ መንግስት ሲጠራም እንደሄደ እናያለን

«ለእያንዳንዱ እንዴት መመለስ እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ»... እንዳለ የምንናገረው ነገር እንደ የሰዉ ሁኔታ ይለያያል፡፡  ስለሆነም ከማንኛውም ሰው ጋር በሚኖር ግንኙነት ልዩነትን ወደሚያጐላና ሰው የጠላትነት ስሜት እንዲቀረጽበትና እንዲያድግበት የሚያደርግ አካሔድን ማስወገድ ያስፈልጋል:: ለምሳሌ ቅዱስ ጳውሎስ በአቴና ከተማ በአርዮስ ፋጎስ ተገኝቶ ሲናገር ምንም እንኳ በዚያ ጣዖት አምልኮ ስለ ተንሰራፋ መንፈሱ ያዘነና ጣፆታትን አማልክት እያለ በማምለካቸው ቢያሳስባቸውም ሲናገራቸው ግን «እናንተ የረከሳችሁ፣ እናንተ ጣዖ ታውያን » አላለም፤ ነገር ግን «እናንተ የአቴና ሰዎች ሆይ! እናንተ በሁሉ ነገር አማልክትን አጅግ እንደምትፈሩ እመለከታለሁ» አለ። የሐዋ.17:22።

ኃይለ ቃል መናገር አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ደግሞ ወደ ኋላ አላለም፥ በፍጹም ቆራጥነት ሰርግዮስ ጳውሎስ የተባለውን አገረገዢ እንዳያምን ሲ ያጣምም የነበረውን ኤልማስ የተባለውን ጠንቋይ ''አንተ ክፋት ሁሉ  የሞላብህ፥ የዲያብሎስ ልጅ፥ የጽድቅም ሁሉ ጠላት የቀናውን የጌታ መንገድ ከማጣመም አታርፍምን? አለው::'' የሐዋ.13:10
እንድ ክርስቲያን በማኅበራዊ ሕይወትም ሆነ በሥራና በአጠ ቃላይ በሀገራዊ ጉዳዮች እንደ አስ ፈላጊነቱ ከማንም ጋር መተባበርና አብሮ መሥራት ባለበት ጉዳይ ላይ አብሮ ይሠራል፡፡ እንደ ዜግነቱ የሚጠበቅበትን ሁሉ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ይልቁንም በማንኛውም መስከ የተሻለ ሆኖ በመገኘት ክርስትና ለመልካም ነገር እንቅፋት ሳይሆን ራስን የሚያስገዛና አእምሮን ብሩህ የሚያደርግ፥ ዓለም የምታሸንፈው ሳትሆን  አሸንፏት የሚገኝ መሆኑን በተግባር ማሳየት ይጠበቅበታል:: ''ለአይሁድም ለግሪክ ሰዎችም ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንም ማሰናከያ አትሁኑ።'' ያለውን ሊያስብ ይገባል 1ቆሮ.10 32

ይቀጥላል...

በሃይማኖት ከማይመስሉን ጋር እንዴት እንኑር?
ክፍል ፫
ታላቁ ቅዱስ መቃርዮስ ይህ ቅዱስ በአንድ ወቅት በመንገድ ቢሔድ ከእርሱ በፊት ቀደም ብሎ ይሔድ የነበረው ሌላ መነኩሴ አንድን የአህዛብ ካህን አግኝቶት የማይገባ ነገር  ስለተናገረው ደብድቦ መንገድ ላይ ጥሎት ሳለ ቅዱስ መቃርዮስ ደረሰና ለምን እንዲያ እንደሆነ ቢጠይቀው የማይገባ ነገር ስለ ተናገረው አንደደበደበው ነገረው:: አርሱ ግን በሚያጸና ፍቅርና ትሕትና ተናገረው:: በዚህ ጊዜ የአሕዛብ ካህነ ጣዖት የነበረው ሰው በቅዱስ መቃርዮስ ሁኔታ ተማርኮ እኔም እንደ አንተ መሆን እፈልጋለሁ ብሎ ክርስቲያን ሆኖ መንኩሶ በዚያ ገዳም የሚኖር ሆነ።

በግብፅ ውስጥ በበረሃ የሚኖርእንድ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰው ነበር። ከእርሱ ርቆ የሚኖር እንድ የማኒ ተከታይ የሆነ ካህን ጓደኞቹን ሊጠይቅ ሲሄድ ኦርቶዶክሳዊው ቅዱስ ካለበት ቦታ ሲደርስ መሸበት:: እርሱ መነናዊ (የማኒ ተከታይ) እንደ ሆነ ስለሚታወቅ ያልተቀበለኝ እንደ ሆነ ብሎ ወደዚህ የእግዚአብሔር ሰው ሄዶ ለማደር ፈራ ግን አማራጭ ስላጣ ሔዶ አንኳኳ ያ አረጋዊም ከፈተለት:: ማንነቱንም ዐወቀ ሆኖም በደስታ ተቀበለው የሚያስፈልገውን ካደረገለት በኋላ አስተኛው:: ሌሊት ይህንን ሁሉ አሰበና ያ መነናዊ ''እንዴት ስለ እኔ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ አልገባውም? በእውነት ይህ ሰው የእግዚአብሔር ሰው ነው'' አለና ከእግሩ ላይ ወድቆ ''ከአሁን በኋላ እኔ ኦርቶዶክሳዊ ነኝ'' ብሎ ከርሱ ጋር ኖረ(The wisdom of the desert fathers)
      በሃይማኖት ከማይመስሉን ሰዎች ጋር የሚደረግ ግንኙነት ከምንናገረው ጀምሮ እስከ ምናደርገው ነገር ድረስ ከፍ ያለ መንፈሳዊ ጥበብና ጥንቃቄን ይፈልጋል ጌታችን ''እነሆ እኔ በተኩላዎች መካከል እልካችኋለው: ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብ የዋሆች ሁኑ'' ሲል ተገቢውን ኣካሄድ ነግሮናል:: ማቴ10:16
ቅዱስ ጳውሎስም ''ዘመኑን እየዋጃችሁ በውጭ ባሉት ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ። ለእያንዳንዱ  እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ በጨው  እንደተቀመመ በጸጋ ይሁን።''ያለው ለዚህ ነው:: ቈላ.4÷5-6::
''በውጭ ባሉት ዘንድ'' ማለትም በእምነት ከእኛ ውጭ ላሉት ከተስፋ መንግሥተ ሰማያትና ከእግዚአብሔር ልጅነት ውጭ ባሉት ዘንድ ለእነርሱ እኛነታችንንና አምላካችንን የሚያስነቅፍ ምክንያትና መግቢያ የሚሆን ነገርን እንዳንሰጥ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልግ መሆኑን ነው::  ቅዱስ ጳውሎስ የገለጸው ለሃይማኖት ወንድሞቻችን ጥንቃቄ ቢያስፈልግም በውጭ ላሉት የሚያስፈልገው ጥንቃቄ ግን ለእምነት ወንድሞቻችን ከሚያስፈልገው በጣም የተለየ ነው:: ምክንያቱም በወንድሞች መካከል ብዙ መቻቻልና መግባባት እንዲሁም ፍቅር አለ በውጭ ባሉት ግን ይህ ሁሉ ስለማይኖር ለወንድሞች ከሚደረገው ጥንቃቄ የበለጠ ጥበብ ያስፈልጋል
    በሃይማኖት ጉዳይ በማይጎዳ ነገር ምክንያት አለመስጠት እንደሚገባ በሮሜ ለነበሩ ክርስቲያኖች እንዲህ አለ:- ''ለሁሉም የሚገባውን ስጡ፡ ግብር ለሚገባው ግብርን ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ፡፡ '' ሮሜ 13÷7:: ስለ ሃይማኖት ጉዳይ ብቻ ነው ልንደራደር የማንችለው:: ከዚያ ውጭ ባለ ነገር ምክንያት ሰጥተን ቢጣሉን እኛም መንፈሳዊ ዋጋ አይኖረንም፥ እነርሱም በዚህ ሰበብ በእኛ ላይ ጥላቻቸውን የሚያንጸባርቁበት ምክንያት ያገኛሉ:: ግብር መክፈል ሲገባን ባንከፍል ማክበር የሚገባንን ባናከብር ይህ ተገቢ አይደለም በዚህም ሰበብ ምክንያት የሚመጣው ነገር ቢኖር ለሃይማኖት ሲባል የመጣ አይሆንም። ለምሳሌ፦ ቅዱስ ጳውሎስ ሃይማኖቱንና ዓላማውን የማይነካና የማይጎዳ ነገር ያደርግ ነበር በአይሁድ ተከሶ ለፍርድ በቀረበ ጊዜ ለንጉሥ አግሪጳ እንዲህ አለ፦ ''ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፥ የአይሁድን ሥርዓት ክርክርንም ሁሉ አጥብቀህ አውቀሃልና በአይሁድ በተከሰስሁበት ነገር ሁሉ ዛሬ በፊትህ ስለምመልስ ራሴን እጅግ እንደተመረቀ አድርጌ እቆጥረዋለሁ'' የሐዋ.26 : 2-3። ነገር ግን በዚህ ጊዜ ንጉሡን ቢገሥጽና ቢዘልፍ ኖሮ ሁሉንም ነገር ባበላሸ ነበር::
ይቀጥላል ...

በሃይማኖት ከማይመስሉን ጋር እንዴት እንኑር ?
ክፍል ፪

ዳንኤልና ሠለስቱ ደቂቅ

ዳንኤልና ሠለስቱ ደቂቅ ወደ ባቢሎን ከሕዝበ እስራኤል ጋር ተማርከው የሄዱ ናቸው:: ከሀገራቸው ተማርከው ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅ ደስ: ከመስዋዕቱ ከመዝሙሩ ሁሉ ተለይተው ሄዱ:: በዚያም ላይ በባቢሎን ሀገር አስተማሪ፣ መምህርና መሥዋዕት አቅራቢ ካህን አልነበረም፦ ''አልቦ በዝ መዋዕል መልእክ ኢነቢይ ወኢገጉሥ ኢ ቁርባን ወኢመሥዋዕት ወኢጎበ እለ ያጸነሑ ዕጣነ'' ብለው እንደ ገለጹት ከዚያም አልፎ ነገራቸው ሁሉ በጥብቅ ቁጥጥርና በቅርብ ክትትል ይሆን ዘንድ ወደ ቤተ መንግስት ተወሰዱ በዚያም በተኩላዎች መካከል እንደተጣሉ በጎች ሆኑ። ሆኖም ግን ከአመጋገባቸው ጀምሮ ኑሮአቸውን በጥበብ አደረጉ፡፡
ናቡክደነፆር ያየውን ሕልምና ፍቺውን የባቢሎን አስማተኞችና መተተኞች መንገር ባልቻሉና የባቢሎንን ጠቢባን ሁሉ እንዲያጠፉ ባዘዘ ጊዜ ነቢዩ ዳንኤል በፈሊጥና በማስተዋል ተናገረው:: ወደ ንጉሡም ገብቶ ሕልሙንና ፍቺውን ለንጉሡ የሚያስታውቅበት ጊዜ እንዲሰጠው ጠየቀ:: ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ስለገለጠለት ወደ ንጉሡ ገብቶ፡- ''ምስጢር የሚገልጥ አምላክ በሰማይ ውስጥ አለ'' በማለት በአነጋገሩ እግዚአብሔ ርን ገለጠለት፡፡ ሕልሙን ከነፍቺው በመናገሩ ንጉሡ አከበረው:: ዳንኤል ይህ ሕልምና ፍቺ ለእርሱ ብቻ ስለ ተገለጠለት እነዚያ አስማተኞችና መተተኞች እንዲሞቱ አልፈለገም- አላደረገምም፡፡ እነርሱ እንዳይገደሉ አደረገ እንጂ። በዚህም ናቡከደ ነፆር ዳንኤልን ይህን ምሥጢር ትገልጥ ዘንድ ተችሎሃልና በእውነት አምላካችሁ የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ ሚስጥርን ገላጭ ነው በማለት ተናገረ፥ እግዚአብሔርን አከበረ። ት.ዳን 2:47።
ዳንኤልም በባቢሎን አውራጃ ሁሉ ላይ ዋና አለቃ ሆኖ በተሾመ ጊዜ ምንም እንኳ ሕዝቡ ጣዖት የሚያመልክና እግዚአብሔርን የማያውቅ የነበረ ቢሆንም እርሱ ግን እንደሚገባ በቅንነት ያገለግል ነበር። ሦስቱን ወጣቶችም በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ ሾማቸው:: እነርሱ ይህን ሹመት የተቀበሉት ለክብርና ለምድራዊ ተድላ ደስታ አልነበረም። በቤተ መንግሥት እያሉ ከጥሬ በቀር ሌላ ነገር የማይበሉ ይኽን ሹመት ለምን ይፈልጉታል? ነገር ግን በተሰጣቸው ጸጋ ሲሠሩ ሕዝቡ እንዲጠቀም ያውቃልና ዳንኤል አስሾማቸው እነርሱም ሕዝቡን በቅንነት አገለገሉ፡፡ ሆኖም ግን ንጉሡ የወርቅ ምስል አሠርቶ እንዲሰግዱ ባላቸው ጊዜ አልተስማሙም። ናቡከደነፆር ሆይ፥ በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም:: የምናመልከው አምላክ ከሚነደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህ ያድነናል፡ ንጉሥ ሆይ፡ ነገር ግን እርሱ ባያድነን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምከውም ለወርቅ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ ት.ዳን 3:16-18:: ስለሆነም ሕዝቡንና ንጉሱን ማገልገልና ከእነርሱ ጋር መተባበር በሚገባቸው ጉዳይ ላይ እንደሚገባ ይታዘዙና ያገለግሉ ነበር። ነገር ግን ሊደራደሩበት በማይችሉበት በሃይማኖታቸው ጉዳይ ሲመጡ ግን ቀኝም ግራም አላሉም።ዳንኤል እግዚአብሔርን በማምለኩ ምክንያት ሰዎች በተንኮል ይሞት ዘንድ ነገር በሠሩበት ጊዜ ይህንን ፈርቶ ከእነርሱም ጋር አልተባበረም:: በዚህ ወደ አንበሳ አፍ ቢጣልም የሚያመልከው አምላክ ከአናብስት አፍ አድኖታል። ሠለስቱ ደቂቅም ሆኑ ዳንኤል ሁሉንም ነገር እንደሚገባ በማድረግ በጥበብ በመኖራቸው ሁሉንም ነገር እንደሚገባ በማድረግ በአህዛብ ሀገር እግዚአብሔር እንዲታወቅ አደረጉ፡፡ ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት በማውጣት ወደዚያ ያስጣላቸው ንጉሥም ሳይቀር። ባሪያዎቹን ያዳነ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጐም አምላክ ይባረክ በማለት ተመልሷል ት.ዳን 3:29

እነዚህ በጨለማው ሀገር እንደ ከዋክብት አበሩ:: ኃጢአት አልጫ ባደረገው ሕዝብ መካከል ጨው ሆነው ተገኙ በክሕደትና በኃጢአት ዱቄት የሆነውን የባቢሎን መንግሥትና ሕዝብ በወንጌል እንደ ተገለጸው ለሦስቱ መስፈሪያ ዱቄት እርሾ ሆነው እንዲ ቦካ አደረጉ:: ማቴ.13፥33:: ከአሕዛብ ጋር በመኖራቸው የነርሱ ክብር የበለጠ ተገለጠ ለሌሎቼም እግዚአብሔርን የሚያስተዋወቁ ሆኑ:: የእነርሱ ብርሃን የአሕዛብን ጨለማ እሸነፈ፥ የእግዚአብሔር ብርሃንነት በእነርሱ መቅረዝነት ተገለጠ፡፡

ይቀጥላል ...

እግዚአብሔር ይመስገን #3_ሺህ_ሰብስክራይበር ደርሰናል

ይህ ቻናል በግቢ ጉባኤያችን የሚተላለፉ መልዕክቶችን እንዲሁም ልዩ ልዩ ትምህርታዊ ጽሑፎች ማጋርያ የመረጃ አውታራችን ነውና አገልግሎቱ ለብዙሃን ይዳረስ ዘንድ ለአዲስ ገቢ እህት ወንድሞች እንዲሁም ለሌሎች ከታች ያለውን ማስፈንጠርያ በማጋራት የድርሻዎን ይወጡ

ቴሌግራም https://t.me/wku_gg_media

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/@Wku_gg

ሀሳብ አስተያየትዎን በ @wkugg_bot ያጋሩን