ወራዩ/ ህ/ አ/አ/ግ
ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እንደሚሰሩ ተገለፀ።
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ለአንደኛ አመት ሴት ተማሪዎች በህይወት ክህሎት ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።
የዩኒቨርሲቲው ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ስራ አስፈፃሚ ላለፉት ሁለት ቀናት በህይወት ክህሎት፣ በጤናና ስነ-ተዋልዶ እና በኤች አይ ቪ ኤድስ ዙሪያ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቋል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሽቱና ሳዲቅ ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችና ሌሎችም ድጋፎች እንደሚደረግላቸው ተናግረዋል።
ሰልጣኝ ሴት ተማሪዎች በበኩላቸው ከስልጠናው ያገኙት ግንዛቤ ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል።