Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو (@ustaz_yasin_nuru_chanal) Kanalının Son Gönderileri

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو Telegram Gönderileri

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو
Wel-come to the official channel of TG Ustaz Yasin Nuru.
🇵🇸 Free Palestine 🇵🇸
My FB channel is ✅ ☟︎︎︎ https://www.facebook.com/ustazYassinNuru?mibextid=ZbWKwL
5,920 Abone
858 Fotoğraf
813 Video
Son Güncelleme 28.02.2025 15:14

Ustaz Yasin Nuru_ኡስታዝ ያሲን ኑሩ _أستاذ ياسين نورو tarafından Telegram'da paylaşılan en son içerikler


ሙሐመድ ﷺ በፍቅሩ ዓለምን የገዛው ነብይ
اللَّهُمَّ صل عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ
.
إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡

ይህ የወራሪዋ ጦር መስጂዱን አፈራርሰው ቁርአኑን እየቀደዱ ሲያነዱት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ነው

የምናየው ልብን ያደማል የምንሰማው ይሰቀጥጣል። የጀግኖቹም ትዕይንት ያስደምማል የቀሳሞቹ ገድል ልብን በወኔ ይንጣል። የወራሪዋ ጭካኔ ልብን ያንዘፈዝፋል ቁርአኑን ቀደው ሲያነዱት ስታይ አይንህ ይቀላል።

በቀስተኞች ተራራ ላይ ካንተ በቀር ማንም ባይኖር እንኳ ቦታህን አትልቀቅ።
ሰዎች ስለ ጋዛ መፃፍ ቢያቆሙ ህመም ብሶታቸውን ጀግንነት ገድላቸውን መመዝገብ ያለብህ አንተ ብቻ እንደሆንክ እያሰብክ ስለ ጋዛ ጻፍ።

ሲስቁ አብረሀቸው ሳቅ ሲያለቅሱም እንዲሁ አብረህ አንባ። እርዳታውን የነፈጋቸው ሁሉ ፈተናውን ወድቋልና ሰበብ ማድረስህን ለአላህ አሳይ!

የጋዛ ሸሂዶች ስም ዝርዝር በአሜሪካ

ዕድለኛ ትውልድ ነን ።

📝 ሙስሊም ያልሆኑ ምሑራን
ስለ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ ዐ ወ) ስናገሩ፡

✓ ሞሃንዳስ ካራምቻንድ ጋንዲ (መሃተመ ጋንዲ ) ይባላል::

(ሕንድን ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነጻ ያወጣ የሠላማዊ ትግል መሪ)

ክፍል-0⃣1️⃣

‹... በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕዝቦችን ልብ በጭብጡ ውስጥ ስላስገባው ሰው ምርጥ
የሕይወት ቅጽበቶች ለማወቅ ፈለግኩ፡፡
… (አንብቤ ስጨርስ) በዚያ ወቅት በነበረው
የሕይወት ማእቀፍ ውስጥ ለእስልምና ቦታ ያስገኘለት የሰይፍ ኃይል እንዳልሆነ ከምንም
በላይ አመንኩ፡፡
ይልቁንም ቦታ ያስገኘለት የነቢዩ (ሙሐመድ) ቅልል ያለ እና በመተናነስ የተሞላ ሕይወት፣ እንከን የለሽ ቃል ኪዳን አከባሪነት፣ ለጓዶቹ ያሳየው
ፍጹም መሰጠት (አጋርነት)፣ የተስተዋለበት ታላቅ ወኔ እና ፍርሃት አልባነት፣ እንዲሁም
በአምላክ እና በተልእኮው ላይ የነበረው ጥልቅ መተማመን ነበር፡፡
(ትግሉን) ያስኬደለት እና በየመንገዱ ያገኘውን እንቅፋት ያስገበረለት ሰይፍ ሳይሆን እኒህ ባሕሪዎቹ ነበሩ፡:
(የነቢዩ /ሙሐመድ/ን የሕይወት ታሪh መጽሐፍ) ሁለተኛ ጥራዝ አንብቤ ጨርሼ
ስዘጋው ስለታላቅ ሕይወቱ ተጨማሪ የማነበው ነር ባለመኖሩ እያዘንኩ ነበር፡፡»
ያንግ ኢንዲያ – 1924

ክፍል ሁለት ይቀጥላል........................... ።

╭┈─────── ೄྀ࿐ 🇵🇸ˊˎ-
╰┈➤𝐉𝐎𝐈𝐍:☞ https://t.me/ustaz_yasin_nuru_chanal

🛑 የጁምዓ ሰላት አንደ ረከዓ እና ሁለት ረከዓ ያገኘ ሰው እንዴት እንደሚሰግድ ያውቃሉ?


📌 ሶላቱል ጁምዓን በዑዝር ምክንያት መሳተፍ ያልቻሉ ሙሳፊር ያልኾኑ ሙስሊሞች፤ ሶላቱ-ዙህርን እንደተለመደው አራት ረከዓህ መስገድ ግዳጃቸው ነው፡፡ እንዲሁም ወደ ጁምዓ መስጂድ አርፍደው የመጡና፤ ከዚያም ኢማሙ ላይ ከሁለተኛው ረክዓህ ሩኩዕ መነሳት በኋላ የደረሱበት ሰዎች፤ ምንም ረክዓህ ስላላገኙ፤ የቀረውን የሱጁድ እና የተሸሁድ ስርአት ከኢማሙ ኋላ በመከተል ይሰግዱና፤ ኢማሙ ሲያሰላምት፤ እነሱ በመነሳት ባለ አራት ረከዓህ ሶላት (ዙህር) ይሰግዳሉ፡፡ ግን ኢማሙ በሁለተኛው ረክዓህ ሩኩዕ ላይ እያለ ከደረሱበትና እነሱም ያንን ሩኩዕ ኢማሙ ሳይነሳ በፊት ከደረሱበትና ሩኩዕ ካደረጉ አንድ ሙሉ ረክዓህ አግኝተዋልና፣ ኢማሙ ባሰላመተ ጊዜ፤ እነሱ ይነሱና የቀረውን አንድ ረክዓህ በመስገድ ያሰላምታሉ ማለት ነው፡፡ አንድን ሙሉ ረክዓህ ለማግኘት የመጨረሻው ጊዜ ኢማሙን ሩኩዕ ላይ እያለ መድረስና፤ ከሩኩዕ ቀና ሳይል እኛም አላሁ አክበር ብለን በቆምንበት ቦታ ከሐረምን በኋላ ወዲያው ሩኩዕ ማድረጋችን ነውና፡፡


ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ አንሁ) ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፡- "ከጁምዓ ሶላት አንድን ረክዓህ ያገኘ ሰው፤ የቀረውን ሌላ ረክዓህ ወደሱ ይጨምር፡፡ ሁለቱም ረክዓዎች ያመለጡት ሰው አራትን ረክዓህ ይስገድ" (አል-በይሀቂይ፡ ሱነኑል-ኩብራ 5531፣ ጦበራኒይ፡ አል-ሙዕጀሙል ከቢር 9545)፡፡

📌 ግለሰቡ የጁምዓ ሶላት ሁለቱም ረክዓዎች አምልጠውት ኢማሙ ከማሰላመቱ በፊት ቢደርስና፤ ከኋላቸው ነይቶ ቢቀመጥ፤ ኢማሙ ያሰላመተ ጊዜ እሱ ተነስቶ አራት ረክዓህ የሚሰግድ ከኾነ፤ መጀመሪያውኑ ነይቶ የሚቀመጠው ዙህርን ሶላት ነው ወይስ ጁምዓን? ለሚለው ጥያቄ፡- ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ) የሰጡት ምላሽ፡- ግለሰቡ ሁለቱ ረክዓዎች አምልጠውት ኢማሙን በተሸሁድ ላይ ኾኖ ካገኘው፣ በዙህር ኒያ ከኢማሙ ጋር ተሸሁድ ይቀመጥና ኢማሙ ሲያሰላምት ተነስቶ አራት ይሰግዳል የሚል ነው፡፡ (አሽ-ሸርሑል ሙምቲዕ፡ 4/160)፡፡

📌 የጁምዓ ቀን ሶላት (ሶላቱል ጁምዓ) ከበፊቱ የሚሰገድ (ሱንነቱል-ቀብሊያ) የለውም፡፡ ነገር ግን ከቤቱ ለጁምዓ ሶላት ተዘጋጅቶ መስጂድ የመጣ ሰው ኢማሙ ወደ ሚንበር እስኪወጣ ድረስ፤ አላህ ያገራለትን ያህል ሶላት መስገድ ይችላል፡፡ ይህ ሙጥለቅ (በመጠን ያልተገደበ የኾነ) የሱንና ሶላት ተብሎ ይጥጠራል፡፡ ከአዛን በኋላ ግን የሚሰገድ የኾነ የሱንና ሶላት የለውም፡፡ ሰልማኑል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "አንድ ሙስሊም በጁምዓ ቀን ሰውነቱን የታጠበ ከኾነ፣ ጥሩ መዓዛ ባለው ቅባት የተቀባ ወይንም ሽቶን በልብሱ የነሰነሰ ኾኖ ወደ መስጂድ ኼዶ፤ በሁለት ሰዎች መሐል፤ በመሐላቸው በመለየት ሳይቀመጥ (ሳያስቸግር)፤ ከዚያም የተጻፈለትን (አላህ ያገራለትን ያህል) ከሰገደ፣ ኢማሙም መናገር ሲጀምር በዝምታ ካዳመጠ፤ ቀጣዩ ጁምዓ እስኪመጣ ድረስ በዚህ መሐል ያለው ኃጢአት ይማርለታል" (ቡኻሪይ 883)፡፡

📌 ጁምዓ ሶላት ከበኋላው የሚሰገድ የኾነ ሶላት (ሱነኑል በዕዲያ) አለው፡፡ ግለሰቡ እዛው መስጂዱ ውስጥ ከኾነ የሚሰግደው ባለ ሁለት ረክዓህ ሶላት ሁለት ጊዜ በመስገድ እስከ አራት ረክዓህ መስገድ ሲችል፤ በቤቱ መስገድ ከፈለገ ደግሞ ሁለት ረክዓህ ይሰግዳል ማለት ነው፡፡ ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ከናንተ ውስጥ ከጁምዓህ በኋላ መስገድን የሚፈልግ ሰው አራት (ረክዓህ) ይስገድ" (ሙስሊም 2075)፡፡
ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ሶላቱል ጁምዓን ከሰገደ በኋላ ወደቤቱ ሄደና ሁለት ረክዓህ ሶላትን ሰገደ፡፡ ከዚያም፡- ‹‹የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ያደርጉ ነበር›› በማለት ተናገረ፡፡ (ሙስሊም 2076)፡፡

📌 በጁምዓ ቀን ኢማሙ ኹጥባህ እያደረገ በዚህ መሐል መስጂድ የገባ የአላህ ባሪያ፤ መቀመጥን ከፈለገ ቅድሚያ ቀለል ያለ ሁለት ረክዓህ መስገድ ተገቢው ይኾናል፡፡ ሶላቱንም ቀለል እና ፈጠን በማድረግ፤ በቀሪው ጊዜ የኢማሙን ኹጥባህ ለመስማት መጓጓት አለበት፡፡ ምንም ሳይሰግድ መቀመጡ ሱንናን መቃረን ይኾንበታል፡፡ ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በጁምዓ ቀን ለሰዎች ኹጥባ እያደረጉ አንድ ሰው ገባና (ተቀመጠ)፡፡ እሳቸውም ‹‹እንትና! ሰግደሀልን?›› አሉት፡፡ ሰውየውም፡- አልሰገድኩም! አለ፡፡ እሳቸውም፡- ተነስና ሁለት ረክዓህ ስገድ! በማለት አዘዙት" (ቡኻሪይ 930፣ ሙስሊም 2055)፡፡

“ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለኔ ይቀርብልኛልና።”

ረሱል (ﷺ)

የካእባ ልብስ #ኪስዋ የአለማችን #ውዱ ልብስ 🕋

🕋 የልብሱ ክብደት 1000 ኪ .ግ የሚመዝን ሲሆን አጠቃላይ የካዕባን ልብስ ለማዘጋጀት #ከ20 ሚሊዮን ሪያል በላይ ይፈጃል።

🕋 ይህ የካዕባ ልብስ በንጉስ አብዱልአዚዝ ኮምፕሌክስ የሚዘጋጅ ሲሆን ኪስዋውን ለማዘጋጀትም 200ባለሞያዎች ይሳተፉበታል::

🕋 በአለም ረጅሙ እና ኮምፒውተራይዝ የሆነው የስፌት ማሽን ይህን የካዕባን ልብስ ለማዘጋጀት አገልግሎት ላይ የሚውል ሲሆን የስፌት ማሽኑም 16 ሜትር የሚረዝም ነው::

🕋 የካዕባ ልብስ ኪስዋ 670 ኪሎ የሚሆነው ጥቁር ሀር ሲሆን በሀሩ ላይ ለሚፃፈው የቁርኣን አንቀፆችም 120 ኪሎ 21ካራት #የወርቅ_ክር እና 100ኪሎ #የብር_ክር አገልግሎት ላይ ይውላል::

🕋 በልብሱ ላይ የሚፃፈው የቁርዓን አንቀፆችም በሰዎች እጅ በጥንቃቄ የሚጠለፍ ነው

🕋 የዘንድሮ አመት 1445 የካእባ ልብስ ኪስዋ የመቀየር ስነ ስርዓትም የፊታችን ቅዳሜ ሙሀረም 1 የሚከናወን ይሆናል ኘሮግራሙም በቀጥታ የቴሌቭዢን ስርጭት ይተላለፋል !!