University of Gondar Community School Official @uogcommunityschool Channel on Telegram

University of Gondar Community School Official

@uogcommunityschool


This is means of communication for University of Gondar Community school Communities

University of Gondar Community School Official (English)

Welcome to the official Telegram channel of the University of Gondar Community School! This channel, @uogcommunityschool, serves as a means of communication for the vibrant and diverse community of the University of Gondar Community School. Who is it? The University of Gondar Community School is a prestigious educational institution located in the heart of Gondar. With a rich history and a commitment to academic excellence, the school is dedicated to providing a high-quality education to its students. What is it? The University of Gondar Community School Official Telegram channel is a platform where students, parents, teachers, and alumni can stay connected and informed about the latest news, events, and announcements from the school. Whether you're looking for information on upcoming events, important updates, or simply want to connect with other members of the school community, this channel is the place to be. Join us on @uogcommunityschool to be a part of our vibrant community and stay up to date with everything happening at the University of Gondar Community School. We look forward to connecting with you and sharing the exciting journey of learning and growth together!

University of Gondar Community School Official

13 Feb, 19:38


የኬጅ 2 ተማሪዎች ፈተና እርማት ተሣትፎ የሚያሣይ ፎቶ በከፊል

University of Gondar Community School Official

09 Feb, 12:03


ቀን 02/6/2017ዓ.ም
ለጎንደር ዩኒቨርሢቲ ማህበረሠብ ት/ቤት የተማሪ ወላጆች በሙሉ የ1ኛ ደረጃ ቁጥር 2 በ2017 ዓ ም በ2 ኛዉ ወሠነ ትምህርት በአዲሥ ሥራ የሚጀምር በመሆኑ
በቁጥር 1 ት/ቤት በ4ኛና በ5ኛ ክፍል በመማር ላይ ያሉ የአዘዞ እና አካባቢዉ ተማሪዎች ማለትም በአባሣሙኤል መሥመር ከአዘዞ መናፈሻ መለሥ እንዲሁም በፋሢል ከአይራ ጀምሮ ነዋሪ የሆኑት ወደ ጎንደር ዩኒቨርሢቲ ማህበረሰብ ት/ቤት 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ቁጥር 2 ከየካቲት 09/2017 ጀምሮ በአካባቢያቸዉ በአዲሡ ት/ቤት ትምህርታቸዉን የሚጀምሩ መሆኑን አዉቃችሁ ዝግጁ እንድትሆኑ፡ የካቲት ወር 2017 ዓ ም የሠርቪሥ ክፍያ መክፈል የማይጠበቅባችሁ መሆኑና የመኖሪያ አድራሻ ለዉጥ ያደረጋችሁ ወላጆች ከየካቲት 03_04/2017 ዓ ም ድረሥ ብቻ በአሥቸኳይ ዋናዉ ግቢ ካለዉ ት/ቤት በመምጣት ሪፖርት እንድታደርጉ በአክብርት እናሣዉቃለን።


ት/ቤቱ

University of Gondar Community School Official

09 Feb, 11:58


ቀን 02/6/2017ዓ.ም
ለጎንደር ዩኒቨርሢቲ ማህበረሠብ ት/ቤት ቁጥር 1 እና 2 ከኬጅ 1 እሥከ 2 ኛ ደረጃ ያሉ ተማሪዎች የ2ኛዉ ሠሚሥተር ትምህርት የሚጀምረዉ ሠኞ በ03/06/2017 ዓ ም ሥለሆነ ሙሉ ቀን ት/ቤት ሥለሚዉሉ ወላጆች ምሣቸዉን አሥይዛችሁ እንድትልኩ ከአክብሮት ጋር እናሣዉቃለን።

ት/ቤቱ

University of Gondar Community School Official

09 Feb, 11:28


ቀን 02/6/2017ዓ.ም
ለጎንደር ዩኒቨርሢቲ ሠራተኞች ልጆቻችሁን ወደ ት/ቤቱ ለማሥገባት የተመዘገባችሁ የፈተና ቀን ካሁን ቀደም ባወጣነዉ መርሀ ግብር መሠረት ሠኞ በ03/06/2017 ዓ ም የ4ኛና የ5ኛ ክፍል ተማሪዎ ፈተና መሆኑን አሥታዉሣችሁ ወላጆች የተመዘገበዉን ልጅ ይዛችሁ ጥዋት 2:00 ላይ ዋናዉ ግቢ እንድትገኙ በአክብሮት እናሥታዉሣለን።

ት/ቤቱ

University of Gondar Community School Official

09 Feb, 11:13


ቀን 02/6/2017ዓ.ም
ለጎንደር ዩኒቨርሢቲ ማህበረሠብ ት/ቤት የተማሪ ወላጆች በሙሉ የየካቲት ወር 2017 ዓ ም ልዩ ልዩ የት / ቤት ክፍያዎች ከየካቲት 03 እሥከ የካቲት 18/2017 ዓ ም ድረሥ በተለመደዉ የሒሣብ ቁጥር ባንክ ገቢ በማድረግ ኦርጅናል ደረሠኝ ይዞ በመምጣት የዉሥጥ ገቢ ደረሠኝ እንድታሥቆርጡ መልእክት እያሥተላለፍን የባንክ ኮፒ ደረሠኝ የማንቀበል መሆኑን
በአክብሮት እናሣዉቃለን።

ት/ቤቱ

University of Gondar Community School Official

03 Feb, 12:46


ቀን 24/5/2017ዓ.ም
ለጎንደር ዩኒቨርሢቲ ማህበረሠብ ት/ቤት ቁጥር 1 ለ6ኛ፡ ለ8ኛና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከጥር 26 እስከ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ ም ድረሥ ከጥዋቱ 2:00 እሥከ 6:30 ድረስ የማጠናከርያ ትምህርት እንደሚሠጥና ወደ ት/ቤት እንድትመጡ መልእክት ማሥተላለፋችን ይታወቃል።
ይሁን እንጅ በተለያዩ ፕሮግራም መደራረብ ምክንያት የሠርቪሥ እጥረት በማጋጠሙ የ6ኛ ፣እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች በቤታችሁ ሁናችሁ እረፍት እንድታደርጉ እያሣወቅን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ግን በግላችሁ እየመጣችሁ የማጠናከርያ ትምህርቱን እንድትከታተሉ እንላለን።

ት/ቤቱ

University of Gondar Community School Official

01 Feb, 17:12


ቀን 24/05/2017 ዓ.ም
ማስታወቂያ
👉የፈተና ፕሮግራም እና ተያያዥ ጉዳዮችን ስለማሳወቅ✍️
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ቁጥር 2 አዲስ ግንባታ መጠናቀቁን አስመልክቶ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን አወዳድሮ ለመቀበል የምዝገባ ማስታወቂያ ወጥቶ በየክፍል ደረጃው የተመዘገባችሁ ተማሪዎችና አመልካች ወላጆች በሙሉ
1ኛ/ የተወዳዳሪ ተማሪዎችን መፈተኛ ጊዜ ከየካቲት 03 አስከ 06/2017 ዓ.ም ባሉት ቀናት የሚሰጥ ሆኖ
👉በ03/06/2017 የ4ኛና 5ኛ ክፍል ተማሪዎች
👉በ04/06/2017 ዓ.ም የ2ኛና የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች
👉በ05/06/2017 ዓ.ም የ1ኛ ክፍል ተማሪዎች
👉በ06/06/2017 ዓ.ም የኬጅ 2 ተወዳዳሪ ተማሪዎች የፈተና መስጫ ጊዜ ሆኖ ስለተወሰነ በተቀመጠው የፈተና መስጫ ቀን ወላጆች (አባት ወይም እናት) ተፈታኝ ተማሪዎችን በመያዝ 👉ከጥዋቱ 2፡00 ሰዓት ላይ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ት/ቤት ዋናው ግቢ እንድትገኙ፤
2ኛ/ ለፈተና የሚዘጋጁ የትምህርት አይነቶችና የይዘት ሽፋን በተመለከተ፡-
ለኬጅ 2 ተወዳዳሪ ተማሪዎች ለኬጅ 2 ሊመዝኑ የሚችሉ አማርኛ፣ እንግሊዘኛና የሂሳብ የትምህርት አይነቶች ሆነው የጥያቄ ብዛት ከ3ቱ የትምህርት አይነቶች የተውጣጡ 20 ጥያቄዎች የሚዘጋጅ መሆኑ፤
ከ1ኛ እስከ 3ኛ ክፍል ላሉ ተወዳዳሪ ተማሪዎች አማርኛ፣ እንግሊዘኛና የሂሳብ የትምህርት አይነቶች ሆነው የጥያቄ ብዛት ከ3ቱ የትምህርት አይነቶች የተውጣጡ 30 ጥያቄዎች የሚዘጋጅ መሆኑ፤
ከ4ኛ እስከ 5ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች አማርኛ፣ እንግሊዘኛ፣ ሂሳብ እና አካባቢ ሳይንስ የትምህርት አይነቶች ሆነው የጥያቄ ብዛት ከ4ቱ የትምህርት አይነቶች የተውጣጡ 40 ጥያቄዎች የሚዘጋጅ መሆኑ፤
ከ1ኛ አስከ 5ኛ ክፍል የሚዘጋጁ ጥያቄዎች በ2017 የትምህርት ዘመን በአማካይ በሁሉም ት/ቤቶች ይሸፈናሉ ተብለው የሚታሰቡ የርዕስ ሽፋን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሪዎችን መማሪያ መጽህፍት መሰረት ተደርጎ የሚዘጋጅ ይሆናል፤
ተወዳድረው የሚያልፉ ሁሉም ተማሪዎች ቁጥር 2 ት/ቤት የሚመደቡ ይሆናል፤
ወላጆች ለተፈተና ልጆችን ይዘው ሲመጡ የወላጆችን ማንነት የሚገልጽ መታወቂያ፣ የተወዳዳሪ ተማሪዎችን ማንነት የሚገልጽ ፎቶ ያለው የልደት የምስክር ወረቀት ወይም ፎቶ ያለበት የትምህርት ውጤት መግለጫ ካርድ ኮፒ መያዝ የግድ ይሆናል፡፡
👉ማሳሰቢያ፡-
ማንነትን የሚገልጽ መታወቂያ ያልያዘ ወደ መፈተኛ ክፍል መግባት አይፈቀድም፤
ተፈታኝ ተማሪ ሞባይል መያዝ አይፈቀድም፤
ከአቅም በላይና በሚታወቅ ችግር ካልሆነ በስተቀር ልጅን ለማስፈተን ወላጅ መምጣት የግድ ይሆናል፤

ት/ቤቱ

University of Gondar Community School Official

01 Feb, 16:01


ቀን 24/5/2017ዓ.ም
ለጎንደር ዩኒቨርሢቲ ማህበረሠብ ት/ቤት ቁጥር 1 ለ6ኛ፡ ለ8ኛና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከጥር 26 እስከ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ ም ድረሥ ከጥዋቱ 2:00 እሥከ 6:30 ድረስ የማጠናከርያ ትምህርት ሥለሚሠጥ በተለመደዉ ሠዓት በየፊርማታችሁ በመገኘት ወደ ት/ቤት በመምጣት የማጠከርያ ትምህርት እንድትከታተሉ መልእክት እናሥተላልፋለን።
ማሣሠቢያ፡ ያለበቂ ምክንያት ት/ቤት መቅረት ወይም መዘግየት አይፈቀድም።

ት/ቤቱ

University of Gondar Community School Official

30 Jan, 17:02


ቀን 21/5/2017ዓ.ም
የጎንደር ዩኒቨርሢቲ ማህበረሠብ ት/ቤት ቁጥር 1 ከ1ኛ እሥከ 12 ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በ1ኛዉ ሠሚሥተር እየተሠጠ ያለዉን ፈተና ወረቀት ዓርብ በ23/05/2017 ለተማሪዎች ተመላሽ ሥለሚሆን ሙሉ ቀን ት/ቤት ሥለሚዉሉ መምህራን ጥዋት ሥትመጡ ለሹፊሮች በተለመደዉ ከሠዓት እንዲመጡ መልእክት እንድታሥተላልፉ ትብብራችሁን እንጠይቃለን።

ት/ቤቱ

University of Gondar Community School Official

30 Jan, 05:45


ቀን 21/5/2017ዓ.ም
የጎንደር ዩኒቨርሢቲ ማህበረሠብ ት/ቤት ቁጥር 1 እና 2 ከ1ኛ እሥከ 12 ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በ1ኛዉ ሠሚሥተር እየተሠጠ ያለዉን ፈተና ወረቀት ዓርብ በ23/05/2017 ለተማሪዎች ተመላሽ ሥለሚሆን ሙሉ ቀን ት/ቤት ሥለሚዉሉ ወላጆች ምሣቸዉን አሥይዛችሁ እንድትልኩ ከአክብሮት ጋር እናሣዉቃለን።

ት/ቤቱ

University of Gondar Community School Official

28 Jan, 11:36


ቀን 20/5/2017ዓ.ም
የጎንደር ዩኒቨርሢቲ ማህበረሠብ ት/ቤት ቁጥር 1 እና 2 ከ1ኛ እሥከ 12 ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በ1ኛዉ ሠሚሥተር እየተሠጠ ያለዉን ፈተና እረፍት እንዲያደርጉ ነገ በ21/05/2017 ዓ ም በቤታቸዉ ሆነዉ እንዲያጠኑ እና ት/ቤት የማይመጡ መሆኑን እያሣወቅን፡
ለሐሙሥ በ22/05/2017 ለሚሠጠዉ ፈተና ዝግጅት አድርገዉ እንዲመጡ ከአክብሮት ጋር እናሣዉቃለን።

ት/ቤቱ

University of Gondar Community School Official

24 Jan, 19:14


የጎንደር ዮዩኒቨርስቲ የአይን ህክምና እና ማስልጠኛ ማእክል የዩኒቨርሢቲያችን ሰባኛው እና መቶኛ ክበረ በዓል ምክኒያት በማደረግ ለጎንደር ዩኒቨርሢቲ ማህበረሠብ ት/ቤት ቁጥር ፩ ለመምህራንና ለአሥተዳደር ሠራተኞች
በአጠቃላይ የአይን ምርመራ፡ .የመነጽር ልኬታ እና መነጸር ለሚያስፈልቸው ነፃ የመነጸር እደላ በ15/05/2017 ዓ ም በተያዘዉ መርሐ ግብር መሠረት ሙሉ ቀን በት/ቤቱ ግቢ ተከናዉኗል። በመርሐ ግብሩ የዩኒቨርሢቲያችን ከፍተኛ አመራሮችና የዩኒቨርሲቲዉ የቦርድ አባላት እንግዶች በት/ቤቱ ግቢ በመገኘት በት/ቤቱ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ምልከታ ከማድረጋቸዉ በተጨማሪ ለት/ቤቱ ማህበረሠብ በማህበረሠብ አገልግሎት እየተሠጠ ያለዉን የአይን ምርመራ ሒደቱን አበረታትተዋል።
በመሆኑም ለት/ቤታችን በዩኒቨርሢቲያችን ከፍተኛ አመራሮች በኩል እየተረግልን ላለዉ ልዩ ልዩ ማበረታቻዎች፡ የአይን ሕክምናና ሥልጠና ማዕከል አሥተባሪ የሆኑትን አቶ ሠማልኝ፡ የሕክምና ቡድን አባላትንና የአይን ሕክምና ትምህርት ክፍልን ለት/ቤቱ ማህበረሠብ በልዩ ሑኔታ ለሠጡን ሙያዊ የጤና እንክብካቤና ክትትል ድጋፍና የመነፀር ሥጦታ በት/ቤቱ ሥም እጅግ ከፍ ያለ ምሥጋናችን እናቀርባለን።
በሚቀጥለዉ መርሐግብርም ለቁጥር 2 ት/ቤት መምህራንና የአሥተዳደር ሠራተኞች እንዲሁም ለተማሪዎች የአይን ምርመራ፡ የመነፀር ልኬታና በነፃ እደላ እንደሚደረግ የማእከሉ አሥተባባሪ አቶ ሠማልኝ ቃል ሥለገቡልን በድጋሜ ምሥጋናችን እናቀርባለን።
ት/ቤቱ።

University of Gondar Community School Official

22 Jan, 08:44


ቀን 14/5/2017ዓ.ም
የጎንደር ዩኒቨርሢቲ 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቁጥር 1 በ14/05/2017 ዓ ም ሊሠጥ የነበረዉ የሥነ ጥበብ ትምህርት ፈተና ጥር 22/2017 ዓ ም የሚሠጥ መሆኑን አዉቃችሁ ለሑሉም የትምህርት አይነቶች ፈተና ተገቢዉን ዝግጅት እንድታደርጉ ከአክብሮት ጋር እናሣዉቃለን።

ት/ቤቱ

University of Gondar Community School Official

19 Jan, 07:41


ሐሙሥ 16 የሚለዉ 15/05/2017 ለማለት ሥለሆነ ቀኑ በዚህ ተሥተክክሏል

University of Gondar Community School Official

18 Jan, 07:37


ለጎንደር ዩኒቭርስቲ ማህበረሠብ ት/ቤት ቁጥር 1 እና ቀጥር 2 መምህራን : የአስተዳደር ሰራተኞች እና ተማሪዎች በሙሉ በመጀመሪያ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በዓል በሠላም አደረሣችሁ እያልን፡ የጎንደር ዮዩኒቨርስቲ የአይን ህክምና እና ማስልጠኛ ማእክል የዩኒቨርሢቲያችን ሰባኛው እና መቶኛ ክበረ በዓል ምክኒያት በማደረግ ለት/ቤታችን ማህበረሠብ በሙሉ
1.አጠቃላይ የአይን ምርመራ
2.የመነጽር ልኬታ
3.መነጸር ለሚያስፈልቸው ነፃ የመነጸር እደላ በቅርቡ ስለሚደረግ እውቅና ኑሯቹህ እንድትዘጋቹ በአክብሮት እያሣወቅን ፡ በዚሁ አጋጣሚ የጎንደር ዩኒቨርሢቲ የዓይን ሕክምናና የሥልጠና ማእከልን በት/ቤታችን ማህበረሠብ ሥም ምሥጋናችን ከወዲሁ እናቀርባለን።
ት/ቤቱ።

University of Gondar Community School Official

18 Jan, 06:13


መልካም የከተራ እና የጥምቀት በዓል ይሁንላችሁ !!

University of Gondar Community School Official

17 Jan, 11:23


👆👆👆የ7ኛ_ክፍል_ተማሪዎች_የአማርኛ_ቋንቋ_ማስታወሻ_ኖት

University of Gondar Community School Official

17 Jan, 08:39


👉 Final exam schedule for G_9--12👆👆

University of Gondar Community School Official

17 Jan, 08:38


👉Final exam schedule for G_ 5--8 👆👆

University of Gondar Community School Official

17 Jan, 08:36


👉Grade 1--4 Final exam schedule👆👆

University of Gondar Community School Official

16 Jan, 18:51


ቀን 08/05/2017 ዓ.ም
ተጨማሪ መረጃ ለመስጠት የወጣ ማስታወቂያ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ት/ቤት በ2017 የት/ዘመን በ2ኛው ወሰነ ትምህርት ልጆቻችሁን ለማስተማር እያመለከታችሁ ለምትገኙ የዩኒቨርሲቲው ቋሚ ሰራተኞች በሙሉ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ቁጥር 2 አዲሱ ግንባታ መጠናቀቁን አስመልክቶ በ2017 ዓ.ም በሁለተኛው ወሰነ ትምህርት ከኬጅ 2 አስከ 5ኛ ክፍል አዲስ ገቢ ተማሪዎችን አወዳድሮ ለመቀበል ከጥር 06 እስከ ጥር 20/2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በምዝገባ ላይ መሆናችን ይታወቃል፡፡
ስለሆነም ወላጆች ለምዝገባ ሲመጡ ማሟላት የሚገባቸው መረጃዎ ችና መገንዘብ የሚገባ ጉዳዮች በተመለከተ፡
1. በኬጅ 2 ለሚወዳደሩት ተማሪዎች እስከ ጥር 30/2017 ዓ.ም ድረስ ዝቅተኛው የመመዝገቢያ እድሜ 5 አመት ከ9 ወር ሲሆን ከፍተኛው 7 አመት ከ 6 ወር ሆኖ ከኬጅ 2 አስከ 5ኛ ክፍል የሚመዘገቡት ከሚማሩበት ት/ቤት በ2017 ተማሪ ስለመሆናቸው የክፍል ደረጃ የሚገልጽ ማስረጃ ከሚማሩበት ት/ቤት ማምጣት የሚገባ ሆኖ ተማሪዎች በሚወዳደሩበት የክፍል ደረጃ ወደኋላ ያለውን በ2016 የተማሩበት የትምህርት ውጤት መግለጫ (ሪፖርት ካርድ) ዋናና ኮፒ ማቅረብ እንደሚገባ፤
2. ለቅድመ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ኬ 2 ለመወዳደር በ2017 የትምህርት ዘመን በኬጅ 2 ወይም በኬጅ 3 እየተማሩ ያሉና ማስረጃ ለሚያቀርቡት ለውድድር የሚመዘገቡ መሆኑ፤
3. ከ1ኛ አስከ 5ኛ ክፍል ተወዳድረው የሚያልፉ ተማሪዎች በሚኖሩበት አቅራቢያ ት/ቤት ምደባ የሚደረግ ሆኖ የክፍል ጥበት ካጋጠመ ት/ቤቱ በሚመድበው ት/ቤት (ግቢ) ይሆናል፡
4. ለቁጥር 2 ት/ቤት በዩኒቨርሲቲው በኩል የሚቀርብ የተማሪ ሰርቪስ የሚቀርብ አለመሆኑ፤
5. በኬጅ 2 አዲስ የሚገቡ ተማሪዎች ለ2017 የት/ዘመን በቁጥር 2 ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ሁሉም የሚመደቡ መሆኑን፤
6. የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ የነበሩ በአሁ ሰዓት በጥሮታ የተለዩት በግል ማህደራቸው ለትምህርት ደረጃው የሚመጥን ልጅ ካላቸው እንደማንኛውም ሰራተኛ ልጅ እኩል ተወዳዳሪ የሚሆኑ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ ኑረው በሞት የተለዩት ደግሞ የሟች የስጋ ልጅ ስለመሆኑ በሰው ሀብትልማት አስተዳደር በሚቀርብ ማስረጃ እየተረጋገጠ እንዲወዳደሩ ይደረጋል፤
7. በየክፍል ደረጃው የሚገቡ ተማሪዎችን ለመለየት ሲባል የሚዘጋጀው የፈተና ጥያቄ በ2017 የት/ዘመን በአንደኛው ወሰነ ትምህርት የተማሩትን በመንግስት ስርዓት ትምህርት የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች ሆኖ የተማሪዎችን መማሪያ መጽህፍት መሰረት ተደርጎ የሚዘጋጅ ይሆናል ፤
8. ሀሰተኛ ማስረጃ ማቅረብ በየትኛውም መንገድ የማጣራት ስራ ስለሚሰራ በአሰራር የሚያስጠይቅ ይሆናል፡
9. ለ2017 የት/ዘመን በኬጅ 1 ውድድር የቀረበ የልጅ እድሜ መረጃ ስለሚገናዘብ አመልካች ወላጆች ክፍል ቀንሶ ወይም ጨምሮ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ በተለያዩ የማጣሪያ ዘዴ ስለሚገናዘብ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቃል፡፡
10. ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውጭ በምንም አይነት ሁኔታ ት/ቤቱ ምዘገባ የሚያስተናግድ አይሆንም፤

በአጠቃላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የውድድርና የቅበላ ሂደት ሁሉንም የዩኒቨርሲቲያችን ሰራተኞች ባሳተፈ ሁኔታ በፈተና ወድድር ብች በጥራት እንዲፈፀም ለማድረግ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች አባል የሆኑበት እና የዩኒቨርሲቲው የመምህራን ማህበር ተወካይ ያካተተ ለት/ቤቱ አጋዥና አማካሪ ኮሚቴ በምርምርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት በኩል ተዋቅሮ በጋራ በምክክር እየተሰራ ይገኛል፡፡
ስለሆነም በዚህ ሰዓት ማንኛውም ወላጅ (ሰራተኛ) ልጄ ወደ ት/ቤት እንዲገባ በማመልከቻ በልዩ ሁኔታ ይታይልኝ በማለት የሚቀርብ ጥያቄ በት/ቤትም ሆነ በፕሬዚዳንት ጽ/ቤት የማይሰተናገድ መሆኑን በጋራ ስለተወሰነ በውድድሩ ብቻ የሚፈፀም መሆኑን እንድታውቁትና ያለአግባብ ጊዜ እንዳይባክን ትብብር እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ት/ቤቱ!

University of Gondar Community School Official

16 Jan, 18:38


ለት/ቤታችን የተማሪ ወላጆች በተለይም ከ5ኛ እሥከ 8ኛ ክፍል ለሆኑ ተማሪዎች ከዚህ በላይ የተጫነዉ የአማርኛ ትምህርት አጋዥ ፁሑፍ አዉሮዶ እንዲያነቡ ማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለዉና ተጠቀሙበት እንላለን።

University of Gondar Community School Official

14 Jan, 14:42


ቀን 06/5/2017ዓ.ም
በት/ቤቱ የተማሪ ሠርቪሥ ተጠቃሚዎች የተማሪ ወላጆች በሙሉ ነገ ጥዋት የተማሪ ሠርቪስ ሥላለ ተማሪዎች በተለመደዉ ሠዓት በመገኘት በሠዓቱ እንዲሣፈሩ እንድታደርጉ ከአክብሮት ጋር እናሣዉቃለን።

ት/ቤቱ

University of Gondar Community School Official

14 Jan, 11:43


ቀን 06/5/2017ዓ.ም
በት/ቤቱ የተማሪ ሠርቪሥ ተጠቃሚዎች የተማሪ ወላጆች በሙሉ ለአሁን ብቻ ከት/ቤት በመምጣት ልጆቻችሁን እንድትወሥዱ ከአክብሮት ጋር እናሣዉቃለን።

ት/ቤቱ

University of Gondar Community School Official

13 Jan, 16:58


በት/ቤቱ የተማሪ ሠርቪሥ ተጠቃሚዎች የተማሪ ወላጆች በሙሉ ለተሽከርካሪዎች ነዳጅ ለማግኘት እሥካሁኑ ሠዓት ጥረት እየተደረገ መሆኑን በሚመለከታቸዉ መልእክት የተላለፈልን ሥለሆነ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ ካልቀዱ ነገ ጥዋት በየፌርማታዉ የሠርቪሥ መኪና ካልመጣ ተማሪዎችን በሚቻለዉ መንገድ ሁሉ ወደ ት/ቤት እንድትልኩ ከወዲሁ ከአክብሮት ጋር እናሣዉቃለን።

ት/ቤቱ

University of Gondar Community School Official

13 Jan, 10:38


የማሥታወቂያ ማሥተካከያ
ቀን 05/5/2017ዓ.ም
👉2ኛ ማስታወቂያ✍️
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ት/ቤት በ2017 የት/ዘመን በ2ኛው ወሰነ ትምህርት ልጆቻችሁን ለማስተማር ማመልከት ለምትፈልጉ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች በሙሉ

የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ልጆቻቸውን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ት/ቤት አስገብቶ ለማስተማር በየአመቱ ያለውን ከፍተኛ ፍላጎትና ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ሲባል በዩኒቨርሲቲው በኩል ተጨማሪ የት/ቤቶች ማስፋፊያ ግንባታ ሥራ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ግንባተውን በፍጥነት አጠናቆ ስራ ለማስጀመር ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ቃል በተገባው መሰረት በከፍተኛ አመራሩ በኩል በልዩ ሁኔታ ውሳኔ እየተሰጠበትና በቅርበት ክትትል እየተደረገበት በአሁኑ ሰዓት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ቁጥር 2 ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ በመሆኑ በ2017 ዓ.ም በሁለተኛው ወሰነ ትምህርት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን አወዳድሮ በመቀበል በት/ቤቱ የመማር ማስተማር ስራውን ለማስጀመር በዝግጅት ላይ የሚገኝ መሆኑን በመግለጽ በ2017 ዓ.ም በ2ኛው ወሰነ ትምህርት ከ1ኛ አስከ 5ኛ ክፍል በተለያዩ ት/ቤቶች በ2017 ዓ.ም በመማር ላይ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው ቋሚ ሰራተኛ ልጅ የሆኑ ተማሪዎችን ብቻ አወዳድሮ በመለየት በአዲስ በተገነባው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ቁጥር 2 ተቀብሎ ለማስተማር ለውድድር ምዝገባ ለማካሄድ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወሳል፡፡
በተጨማሪም ከአሁን በፊት የዩኒቨርሲቲያችን ሰራተኞች በደረጃ 2 (ኬጅ 2) ተማሪዎችን ወደ ት/ቤቱ እንዲገቡላቸው የነበረውን የወላጆች ከፍተኛ ጥያቄ መሰረት በማድረግ የኬጅ 2 ተማሪዎችን በ2017 በ2ኛው ወሰነ ትምህርት በውድድር እንዲገቡ እንዲደረግ በከፍተኛ አመራሩ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡
ስለሆነም ያለውን ቦታ በማጣበብ በደረጃ 2 (ኬጅ 2) ተማሪዎችን በፈተና ውድድር ተቀብሎ ለማስተማር ልጆቻችሁን ለማስመዝገብ ፍላጎት ያላችሁ አመልካች ወላጆች የልጅ እድሜ እስከ ነሀሴ 30/2017 ዓ.ም ድረስ ዝቅተኛው 6 አመት ከፍተኛዉ አስከ 6 አመት 11 ወር ከ29 ቀናት) የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ልጆችን ብቻ ከጥር 06 እስከ ጥር 20/2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት አስፈላጊውን መረጃ አሟልታችሁ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ት/ቤት ቁጥር 1 ግቢ ድረስ በመምጣት ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች መዝጋቢ ኮሚቴ ልጆቻችሁን በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንድታስመዘግቡ እያሳወቅን፤ ለምዝገባ ከተቀመጠው ቀናት ውጭ ቀድሞ ወይም ዘግይቶ የሚመጣ አመልካች ት/ቤቱ የማያስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እያስገነዘብን፤ ለምዝገባ መሟላት የሚገባቸው መረጃዎች በተመለከተ፡-
1ኛ/ አመልካቾች በሚሰሩበት ግቢ ከሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ማስተባበሪያ በኩል የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ እና ልጅ መሆንን የሚገልጽ ከወሳኝ ኩነት የተሰጠ የልጅ የልደት የምስክር ወረቀት ከሰራተኛ የግል ማህደር ጋር ተያይዞ ስለመገኘቱ የሚገልጽ ደብዳቤ፤
2ኛ/ ተማሪው/ዋ ከሚማርበት /ከምትማርበት ት/ቤት በ2017 ዓ.ም በቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በደረጃ 3 (በኬጅ 3) በትምህርት ላይ መሆንን የሚገልጽ ከት/ቤት የተፃፈ ኦርጅናል ማስረጃ፤
3ኛ/ አመልካች ወላጅ የዩኒቨርሲቲው ቋሚ ሰራተኛ መሆኑን የሚገልጽ የግል መታወቂያ
4/ኛ ለውድድር ተመዝጋቢ ተማሪ ማንነትን የሚገልጽ ፎቶ ያለው የት/ቤት ሪፖርት ካርድ ወይም የደረጃ ማጠናቀቂያ ሠርቲፊኬት ዋናውና አንድ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ (የየትኛውም ዓ.ም)
5ኛ/ ለውድድር ተመዝጋቢ ተማሪ ከወሳኝ ኩነት የተሰጠ የልደት የምስክር ወረቀት ዋናውንና አንድ ፎቶ ኮፒ እና ከአንድ ክላሰር ጋር፤
ት/ቤቱ!
👉ማሳሰቢያ፡-
• ሀሰተኛ ማስረጃ ማቅረብ በአሰራር ያስጠይቃል፤
• ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውጭ በምንም አይነት ሁኔታ ት/ቤቱ አያስተናግድም
• ከኬጅ 2 እስከ 5ኛ ክፍል ውጭ ሌላ የክፍል ደረጃ አይመለከትም
• የተማሪ ቅበላ በውድድር ብቻ ስለሚፈፀም ማመልከቻ ይዞ ወደ ት/ቤት መምጣት የራስን ጊዜ ከማባከን በተጨማሪ በት/ቤቱ ላይ የስራ ጫና ስለሚፈጥር የተማሪ ይግባልኝ ማመልከቻ በፍጹም ት/ቤቱ አያስተናግድም፡
ተወዳድረው የሚያልፉ ተማሪዎች ለአንድ ሰሚስተር በቁጥር 2 ት/ቤት እንዲማሩ የሚመደቡ ይሆናል፤
• ት/ቤቱ የተማሪ ሰርቪስ አያቀርብም፡፡

University of Gondar Community School Official

10 Jan, 17:54


👉Attention!!👆👆👆👆

University of Gondar Community School Official

08 Jan, 07:21


ቀን 28/04/2017
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ት/ቤት ልጅ ለማስገባት በማመልከቻ ት/ቤቱ የማያስተናግድ መሆኑን ስለማሳወቅ

አዲስ በተገነባው በጎንደር ዪኒቨርሲቲ ማህበረሰብ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ቁጥር 2 በ2017 ዓ.ም በ2ኛው ወሰነ ትምህርት ከ1ኛ አስከ 5ኛ ክፍል በተለያዩ ት/ቤቶች በ2017 ዓ.ም በመማር ላይ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው ቋሚ ሰራተኛ ልጅ የሆኑ ተማሪዎችን ብቻ በፈተና በውድድር የሚቀበል ሲሆን ከዚህ ውጭ በየትኛውም የክፍል ደረጃ የሚገኝ ተማሪ እንዲሁም በማመልከቻ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ ይሁን የውጭ አመልካች ት/ቤቱ የማይቀበል መሆኑን በጥብቅ እያሳወቅን፡ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከተማሪ ቅበላ ጋር በተያያዘ ወደ ት/ቤት የሚመጣ ባለጉዳይ በምንም አይነት ሁኔታ የማናስተናግድ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃልን፡፡
ት/ቤቱ!

University of Gondar Community School Official

06 Jan, 17:36


ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቋሚ የአካዳሚክና የአስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ በመጀመሪያ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን፤ የሚመለከታችሁ የዩኒቨርሲቲያችን ሰራተኞች አዲስ በተገነባው ት/ቤት ልጆቻችሁን አወዳድሮ ለማስገባት በዚህ ማስታወቂያ በወጣው ፕሮግራም መሰረት አስፈላጊውን መረጃ በመያዝ ተማሪ ልጃችሁን ለወድድር እንድታስመዘግቡ በአክብሮዎት እንገልፃለን፡፡

University of Gondar Community School Official

06 Jan, 16:06


ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሠብ ት/ቤት መምህራን፡ የአሥተዳደር ሠራተኞችና ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሰን! መልካም የገና በዓል!!።

University of Gondar Community School Official

03 Jan, 17:09


ቀን :ታህሳስ 25/2017ዓ.ም
ለት/ቤታችን ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ
ከዚህ በታች  ያለዉን ዝርዝራችሁን  በማየት የስም እና የእድሜ ስህተት ካለ እስከ ታህሳስ 28  ከቀኑ 6 ሰአት  ብቻ ለዚህ  ተግባር በተወከለዉ መ/ር ወይም ለርዕሰ መ/ር አቶ ወንድራድ ጌጡ አማካኝነት   በአካል ት/ቤት በመምጣት ወይም  ስልክ በመደወል
👉 የ2ኛ ደረጃ ርዕሰ መ/ር ስልክ 0918076319 ወይም
👉 ለተወከለዉ መ/ር 0929272272 በመደወል ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን   እናሳዉቃለን  ::
         👉 ማሳሰቢያ ✍️
👉 በተቀመጠዉ ጊዜ ገደብ  የማያስተካክል ተማሪ ለሚፈጠረዉ  የፊደልና የእድሜ ስህተት  ሀላፊነቱን ተማሪዉ/ዋ የምትወስድ  ይሆናል !!
👇👇👇👇👇👇👇👇

University of Gondar Community School Official

27 Dec, 18:30


ተማሪዎች በተግባር ትምህርት ላይ ሢለማመዱ የሚያሣይ ፎቶ በከፊል።

University of Gondar Community School Official

27 Dec, 18:15


Second round gardening tips site work

University of Gondar Community School Official

27 Nov, 11:49


የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሠብ ት/ቤት ቁጥር 1 የ1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በመማር ማስተማሩ ዙርያ ከወላጅ ተወካዮች ጋር የተደረገ ዉይይት (ሕዳር 18/2017 ዓ ም) ፎቶ በከፊል።

University of Gondar Community School Official

26 Nov, 13:48


የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሠብ ት/ቤት ቁጥር 1 የ1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የ2017 ዓ ም የ1ኛዉ ሩብ ዓመት የመማር ማሥተማር እንቅሥቃሤ ያለበትን ጥንካሬና በክፍተት የሚታዩትን እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት ተሠጥቶ መሠራት ባለባቸዉ ተግባራት ዙርያ ከመምህራን ጋር የተካሄደ የምክክር መድረክ እና የአዳዲሥ መምህራን ትዉዉቅ ፕሮግራም (ሕዳር 17/2017 ዓ ም) ፎቶ በከፊል።

University of Gondar Community School Official

24 Nov, 14:24


በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ት/ቤት ቁጥር 2 በ2017 የት/ዘመን የመማር ማስተማር ስራዎች አስመልክቶ ከተማሪ ወላጆች ጋር በ15/03/2017 ዓ.ም በጋራ የምክክር መድረክ ሲካሄድ የተሣታፊ ወላጆች የሚያሳይ ፎቶ በከፊል

University of Gondar Community School Official

21 Nov, 19:55


በጎንደር ዩኒቨርሢቲ ማህበረሠብ ት/ቤት የአዲሥ መምህራን እንኳን ደህና መጣችሁና ከነባር መምህራን ጋር የትዉዉቅ መድረክ ፎቶ በከፊል።

University of Gondar Community School Official

19 Nov, 12:02


ለቅድመ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪ ወላጆች በሙሉ የተማሪዎች የሻሂ ዳቦ ወርሀዊ ክፍያ ከሌሎች ክፍያዎች ጋር በተማሪዎች ስም አብሮ በአንድ ደረሰኝ መክፈል የሚቻል ሲሆን በተጨማሪም የጥቅምት ወር 2017 የሻሂና ዳቦ ክፍያ ያላጠናቀቃችሁ ወላጆች ካላችሁ ከህዳር ወር 2017 ዓ.ም ጋር በአንድ ደረሰኝ አጠቃሎ መክፍል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

ት/ቤቱ!!

University of Gondar Community School Official

18 Nov, 16:50


ቀን 08/03/2017 ዓ.ም
ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት የተማሪ ወላጆች በሙሉ
ጉዳዩ የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባትን ይመለከታል
የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት በጎንደር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ በኩል እድሜያቸው ከ9 ዓመት እስከ 13 ዓመት ለሆኑ ሴት ህፃናት ይሰጣል፡፡ በመሆኑም የክትባቱን አስፈላጊነት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ክትባቱ በት/ቤቱ ስለሚሰጥ ልጆቻችሁ እንዲከተቡ ፈቃዳችሁን በልጆቻችሁ በኩል እንድትገልፁልን እናሳስባለን፡፡
ት/ቤቱ

University of Gondar Community School Official

18 Nov, 12:01


ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሠብ ት/ቤት ቁጥር 2 የተማሪ ወላጆች በሙሉ የሕዳር ወር 2017 ዓ ም ልዩ ልዩ ክፍያዎች የዉሥጥ ገቢ ደረሰኝ ለማሥቆረጥ ከ16 _ 17/03/2017 ዓ ም ለ2 ተከታታይ የሥራ ቀናት በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ደረሠኝ ለሙቁረጥ ባለሙያ ሥለሚመደብ በተጠቀሠዉ ቀናት ተገኝታችሁ ደረሠኝ ማሥቆረጥ የምትችሉ ሢሆን ከዚህ ወጭ ባሉት ቀናት ቁጥር 1 ት/ቤት እየመጣችሁ በተቀመጠዉ ፕሮግራም መሠረት ጊዜዉ ሣያልፍ ደረሠኝ ማሥቆረጥ የሚገባ መሆኑን በአክብሮት እናሣዉቃለን።
ት/ቤቱ!

University of Gondar Community School Official

16 Nov, 15:03


የተከበራችሁ የጎንደር ዩኒቨርሢቲ ማህበረሠብ ት/ቤት የተማሪ ወላጆች በሙሉ፡
የሕዳር ወር 2017 ዓ ም የመጀመሪያ ዙር ፈተና ከሠኞ 09/03/2017 እስከ 11/03/2017 ዓ ም ድረሥ በቁጥር 1 ት/ቤት በሑሉም የክፍል ደረጃዎች የፈተና ፕሮግራም ሥለሆነ ተማሪዎች ከጥዋቱ 5:00 ጀምሮ ወደ ቤት ሥለሚለቀቁ ወላጆች ሠዓቱን ጠብቃችሁ ልጆችን እንድትቀበሉ በአክብሮት እናሣሥባለን።
ት/ቤቱ!።

University of Gondar Community School Official

15 Nov, 17:15


👉Grade 9-12 First Monthly Exam One Schedule !!

University of Gondar Community School Official

15 Nov, 17:14


👉Grade 1-4 First Monthly Exam one Schedule !!

University of Gondar Community School Official

15 Nov, 13:05


የተከበራችሁ የጎንደር ዩኒቨርሢቲ ማህበረሠብ ት/ቤት የተማሪ ወላጆች በሙሉ፡
የሕዳር ወር 2017 ዓ ም ወርሐዊ የትምህርት ክፍያ፡ የትራንሥፖርት ክፍያና የቅድመ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የቁርሥ አገልግሎት 245 ብር እስከ ሕዳር 20/2017 ዓ ም ድረሥ በተለመደዉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሒሣብ ቀጥር 1000509668047 በአካል በመክፈል ሦሥት ቀን ባልበለጠ ጊዜ ደረሠኙን ት /ቤት በማምጣት የዉሥጥ ገቢ ደረሠኝ እንድታሥቆርጡ እያሣሠብን በአንድ ጊዜ ለመክፈል የፈለገ የአመቱን ወይም የ6ወር በአንድ ጊዜ መክፈል የሚቻል ሢሆን ሠርቪሥ እየተጠቀመ የሠርቪሥ አገልግሎት ሣይከፍል የተገኘ ተማሪ ከመሥከረም ወር ጀምሮ እንዲከፍል የሚደረግ ሆኖ በተጨማሪም የሚያሥቀጣ መሆኑን በጥብቅ እናሣሥባለን።

👉ማሳሰቢያ፡
ከተቀመጠዉ አሠራር ዉጭ ሥህተት በመፈፀም አላሥፈላጊ የሆነ የሥራ ጫና መፍጠር አያሥፈልግም።
ት/ቤቱ!!

University of Gondar Community School Official

10 Nov, 04:27


በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ት/ቤት በ2017 የት/ዘመን የመማር ማስተማር ስራዎች አስመልክቶ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ቁጥር 1 ከተማሪ ወላጆች ጋር በ30/02/2017 ዓ.ም በጋራ የምክክር መድረክ ሲካሄድ የሚያሳይ ፎቶ በከፊል

University of Gondar Community School Official

23 Oct, 10:16


ለጎንደር ዩኒቨርሢቲ ማህበረሠብ ት/ቤት ቁጥር 2 የተማሪ ወላጆች በሙሉ የትምህርት ክፍያ ደረሠኝ ለማሥቆረጥ ከት/ቤቱ ድረሥ የሒሣብ ባለሙያ የተላከ ሥለሆነ ከዋናዉ ግቢ ሣትመጡ በት/ቤታችሁ ግቢ ተገኝታችሁ ከዛሬ 13_18/02/2017 ዓ ም ድረሥ በሥራ ሠዓት አሥከ ቀኑ 8:00 ድረሥ ደረሰኝ እንድታሥቆርጡ በአክብሮት እናሣዉቃለን።
ከሠላምታ ጋር።

University of Gondar Community School Official

22 Oct, 12:07


Thank you very much for sharing our school environment and students pictures.

University of Gondar Community School Official

22 Oct, 12:03


የልጆቻችን ውሎ በፎቶ!

University of Gondar Community School Official

22 Oct, 08:46


የልዩ ልዩ ክፍያ ጊዜ ስለማሳወቅ

University of Gondar Community School Official

18 Oct, 10:14


ለት/ቤታችን የ6ኛ፡ የ8ኛ እና 12 ኛ ክፍል ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች በሙሉ የ2017 የት/ዘመን ከጥቅምት ወር ጀሞሮ የቅዳሜ ቀን ማጠናከሪያ ትምህርት ሥለተጀመረ የተማሪ ሠርቪሥ ሥለሚመጣ ተማሪዎች ከጥዋቱ 1:30 በሠአቱ አማካይ ፌርማታ ላይ ተገኝታችሁ እንድትሣፈሩ እያሣወቅን፡ በፒያሣ መሥመር ሹፌር አገኘሁ ቀናዉ ፌርማታ መነሻያ ብልኮ፡ ኤጅ ሆቴል፡ አራዳ ዋርካ፡ ቀይመሥቀል አጠገብ ዋርካ፡ አዉቶ ፓርኮ የኋንሥ ኮሌጅ፡ መሥመር
2ኛ/ በሆሥፒታል ሹፌር አቶ ፋሢል መነሻ ቀበሌ 15 ሥታዲየም፡ ሆሥፒታል፡ ዲፖ፡ ልደታ መሥመር
3ኛ/ በሸዋ ዳቦ መሥመር ሹፌር አቶ ጠጁ መነሽያ ጊወርጊሥ፡ ሸዋ ዳቦ፡ ህዳሤ፡ ገንፎ ቁጭ፡ አይራ፣ መገንጠያ፡ አዘዞ መምህራን መኖሪያና በአባሣሙኤል መሥመር ሁሉንም
4ኛ/ሬድፎክሥ መምህራን መኖሪያ ግቢ ሹፌር ፋሢል መነሽያ ሠዓት 2:00 ላይ
መሆኑን አዉቃችሁ የሠርቪሥ አገልግሎት እንድታገኙ እናሣዉቃለን።

University of Gondar Community School Official

16 Oct, 11:24


ከላይ የተመለከተው በተሳሳተ መረጃ ያስመዘገበ ላይ የተወሰደ እርምጃ ነው። አሁንም በተሳሳተ መረጃ የተወዳዳደረ ካለ ጥቆማችሁን እንድትሰጡና የሚወሰዱ እርምጃወችን ምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

University of Gondar Community School Official

16 Oct, 02:53


ለሁሉም የት/ቤታችን የተማሪ ወላጆች በሙሉ የ2017 የጥቅምት ወር የትምህርት ክፍያና የመሥከረም ወር የትራንሥፖርት ክፍያ ገና ያልተጀመረ ሥለሆነ የመክፈያ ጊዜ መልእክት እሥኪተላለፍ ድረሥ በትእግሥት እንድትጠብቁ እያሣወቅን ፡ የመክፈያ አይነቱ ሣይገለፅላችሁ መክፈል ለአሠራር እያሥቸገረ ሥለሆነ በት/ቤቱ በማሥታወቂያና በዚህ ኦፊሻል የቴሌግራም ገፅ University of Gondar Community school Official page መልእክት ሣይተላለፍ ያለቦታዉ እንዳትከፍሉ በጥብቅ እናሣሥባለን።

University of Gondar Community School Official

15 Oct, 14:47


ለሁሉም የት/ቤታችን የተማሪ ወላጆች በሙሉ ተማሪ ልጆቻችሁ የደረት ባጅ እያደረጉ ከት/ቤት በር እንዲገቡ እንድትሞክሩልንና የደረት ባጅ በተለይ የኬጅ ተማሪዎች መያዛቸዉን እያረጋገጣችሁ እንድልኩ አደራ እንላለን።

University of Gondar Community School Official

15 Oct, 09:01


አቶ ፀጋየ ከማህበረሰብ ትምህርት ቤት ሀላፊነቱ ጎን ለጎን በኤክስተሽን ፕሮግራም ተምሮ 4.0 ነጥብ ይዞ ማስትሬቱን በማጠናቀቁ አድናቆታችንና እንኳን ደስ አለህ ማለት እንወዳለን።

University of Gondar Community School Official

13 Oct, 10:05


ለቅድመ አንደኛ ደረጃ የኬጅ 1 ተማሪ ወላጆች በሙሉ
በ2017 የት/ዘመን በኬጅ 1 ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሠብ ት/ቤት ትምህርት የሚጀምሩ ህፃናት አሥፈላጊዉን መረጃ በማሟላት ሠኞ በ04\02/2017 ዓ ም ወደ ት/ቤት ይዛችሁ እንድትመጡ በድጋሜ እያሣወቅን፡ ት/ቤት የሚቆዩት እሥከ 9:00 ሠዓት መሆኑ፡ እሥኪላመዱ ድረሥ ወላጅ በሠዓቱ ተገኝቶ መረክብ እንዳለበት፡ ወላጆች ለት/ቤቱ የሚሞላዉን መረጃ በትክክለኛዉ በአካል ተገኝቶ መረጃ መሥጠት እንደሚገባ፡ ከኬጅ 1 ተማሪዎች ወላጅ ዉጭ ያለ መታወቂያና ያለበር ፈቃድ ግቢ መግባት የማይፈቀድ መሆኑን፡ አሥፈላጊዉን የባንክ ደረሠኝ ከት/ቤቱ በማምጣት ዉሥጥ ገቢ ደረሠኝ ማሥቆረጥ እንደሚገባና ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ሢመጡ የደረት ባጅ እንዲይዙ እንዲደረግ በአክብሮት እናሣዉቃለን።

ት/ቤቱ!

University of Gondar Community School Official

11 Oct, 07:43


(የት/ቤታችን የበላይ ጠባቂ ፕ/ር ቢንያም መልዕክት)

ሰላም ለሁላችሁም

የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ ት/ቤት የ2017 የት/ት ዘመን የተማሪዎችን ቅበላ አጠናቆ ከኬጂ᎐1 ውጭ በሁሉም ደረጃ ትምህርት ተጀምሯል፡፡ የኬጅ᎐1 ተማሪዎችም በመጭው ሰኞ ይጀመራል፡፡ በዚህ እያሳለፍን ባለነው ከባድ ሁኔታ ውስጥ ሌተ ከቀን በቅንነት እየሰሩ ላሉት ለእነ አቶ ፀጋየ፣ በሁሉም ደረጃ ለሚገኙ ርዕሳነ መምህራንና ለመላው የት/ቤቱ መምህራን ሁላችንም ልናግዛቸው እንደሚገባ እያሳሰብኩ በእኛ በኩል ለት/ቤቱ ለአፈፃፀም የተወሰኑትን ለማጋራት ያክል

1. በዚህ አመት በተለይ በኬጅ_1 ያለውን ከፍተኛ ጥያቄ ከግምት በማስገባት በአንድ ከፍል 35 ተማሪዎችን ለመቀበል ታስቦ የነበረውን ወደ 50 አሳድገነዋል፡፡ ይህም የሆነው ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ እስከ ጥር ድረስ የተጀመረውን ህንጻ አጠናቀን ሁለተኛው ወሰነ ት/ት የተማሪዎችን ቁጥር ወደ standard ለመመለስ ነው፡፡ በዚህም የተቋሙን ሰራተኛ ከፍተኛ ፍላጎት ለማሟላት ተጠባባቂዎችን ጭምር በመጥራት ከ300 በላይ ልጆች መቀበል ችለናል። ይህም በት/ቤቱ ታሪክ ትልቁ ቁጥር ቢሆንም ከተመዘገቡት ከፍተኛ ቁጥር አንፃር መቀበል የቻልነው 50% አካባቢ ብቻ መሆኑን፤

2. የኬጂ᎐1 ተማሪዎች የመቀበል አቅማችን ለማሳደግ ከተሰሩት ስራዎች ውስጥ አንዱ ከKG2-5ኛ ክፍል ያሉ ክላሶች ሴክሽኖችን ማጠፍ ነው፡፡ ለምሳሌ 2ኛ ክፍል 4 ሴክሽን ካለ ወደ 3 ሴክሽን በመቀነስ የተረፈው አንድ ክፍል ለተቀበልናቸው KG᎐1 ተማሪወች እንዲውል በማድረግ ነው፡፡ በዚህም በተለያየ ምክንያቶች ት/ቤቱን የለቀቁ ተማሪወችን ክፍት ቦታ ማሸጋሸግ የተቻለ ሲሆን በክፍል ሊኖር የሚገባው ቁጥርም ከስታንዳርዱ ከፍ ብሏል፡፡ ይህም የሆነው በKG ግማሽ ሰሚስተር የማንቀበል በመሆኑ ተጨማሪ ክላስ በመፍጠር ወደ ስታንዳርድ ቀጥር እንዲቀንስ የምናደርግ መሆኑን

3ኛ. በአዘዞ መምህራን መኖሪያ አካባቢ አዲስ እያሰራነው ያለነው ህንፃ እንዳለቀ ሁለተኛው ወሰነ ት/ት ላይ ከኬጅ 2-5ኛ ቀጥሩን በስታንዳርድ አድርገን ተማሪወችን በግልጽ የፈተና ውድድር ለመቀበል አቅደናል፡፡ ለዚህም የህንፃው ማለቅ እና የመምህራን ቅጥር ወሳኝ በመሆኑ የዪኒቨርሲቲያችን ሰራተኞች በሙሉ በምትችሉት ሁሉ ድጋፍ እንድታደርጉ፤

4ኛ. ከላይ ያለው እንደተጠበቀ ሆኖ በተፈጠሩ የተወሰኑ ክፍተቶች የአስተዳደር ካውንስሉ በተሰጠው ሀላፊነት መሰረት  የስፔሻሊስት ሀኪም ልጆችን፣ PhD ይዘው ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑ በቁጥርም ትንሽ በመሆናቸው እንዲሁም በአገልግሎት እና/ወይም በኋላፊነት የተሻለ አበርክቶ አድርገዋል ያላቸውን የተወሰኑ እድሎች ሰጥቷል። ከዚህ በተጨማሪ ከከተማው ማህበረሰብ ውስጥ የተለያዩ አበርክቶ ለዩኒቨርስቲው ያደረጉትን መመሪያው በሚያዘው መሰረት የተወሰኑ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎችን ተቀብለናል፡፡ እነዚህ ውሳኔዎች በሙሉ በጋራ የተወሰኑ እና በቃለ ጉባኤ የሰፈሩ መሆኑን እና ት/ቤቱ ፈትኖ እንዲቀበል በተወሰነው መሰረት ባለፈው ማክሰኞ ፈተና ተሰጥቷል።

5ኛ. እንደሚታወቀው ት/ቤቱ በአነስተኛ ክፍያ ስለሚያስተምር ከክፍያ የሚሰበሰበው የት/ቤቱን ወጭ ከ30% በላይ አይሸፍንም። ከዚህ ጋር ተያይዞ ባለፈው አመት ክፍያ ለመጨመር አቅደን የነበር ቢሆንም ካለው የኑሮ ውድነት አንፃር ችግሩን በከፊል ለመቅረፍም የወላጅ ኮሚቴው በቀሳቁስ (in-kind) አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ሰወችን በማፈላለግ አሁን አዘዞ ላይ ያለው ኬጅ የት/ት ግብዓቶችን እና ለአጠቃላይ ት/ቤቱ ትልቅ እገዛ ተደርጓል። በዚህ አመት ካለው አካባቢ ሁኔታ አንፃር ብዙ ከውጭ አስተዋፅዖ የሚያደርግ ስለማይኖር ከህንፃው ማለቅ ጎን ለጎን መማሪያ ክፍሎችን በቁሳቁስ ለማሟላት የሚያግዝ ኮሚቴ ስለምናዋቅር የምትችሉትን ድጋፍ እንድታደርጉ አድራ ማለት እንወዳለን።

በአጠቃላይ ት/ቤቱ ላይ ግልፅ እና የሁሉንም የሰራተኞቻችን ልጆች እንደ ልጆቻችን በማየት እድል እንደምንሰጥና ነገር ግን ካለው ከፍተኛ ፍላጎት አንፃር ሁሉንም ማስተናገድ ስለማይቻል በግልፅ አሰራር እንዲሰራ መመሪያ ማስተላለፋችንን መግለፅ እወዳለሁ።   መመሪያው ከሚፈቅደው እና አስተዳደር ካውንስሉ በቃለ ጉባኤ ወስኖ ከላከው ዝርዝር ውጭ የገባ እንዲሁም የተሳሳተ መረጃ ያስገባ የምታውቁት ካለ ጥቆማችሁን ለጸረ ሙስና ቢሮ (ወ/ሮ ንግስት) አልያም ለፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሀላፊ (አቶ ታምራት) በሰልክ፤ በአካል አልያም በጹሁፍ እንድታስገቡ ማስታወስ እወዳለሁ። እሰካሁን የደረሱን ጥቆማዎችን እያጣራን የምንገኝ ሲሆን እናንተ ከምትሰጡን ጥቆማዎች ጋር በአስቸኳይ በማየት የአሰራር ክፍተት ተፈጥሮ ከሆነ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን እና የተወሰደውን ርምጃም ለሰራተኛው የምናሳወቅ መሆኑን ማረጋገጥ እወዳለሁ።

በዚሁ የልጆቻችን ደህንነት ለመጠበቅ የት/ቤቶችን አጥር እንዲሁም ሰርቪሰች ግቢ ውስጥ ቢበዛ በር ላይ እንዲያሳፍሩ መንገዶችም እንዲስተካከሉ እያደረግን እንገኛለን። የልጆቻችን ደህንነት ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው በመሆኑ የምታያቸው ክፍተቶች ሲኖሩ ለት/ቤቱ ኋላፊዎች እንድታሳውቁ ማስታወስ እወዳለሁ።

መልካም ቀን!

ፕ/ር ቢንያም ጫቅሉ
የት/ቤቱ የቦርድ ሰብሳቢ