TenaSeb - ጤና ሠብ (@tenaseb) के नवीनतम पोस्ट टेलीग्राम पर

TenaSeb - ጤና ሠብ टेलीग्राम पोस्ट

TenaSeb - ጤና ሠብ
ሠላም- 👋
ይህ በጤና ዙርያ መረጃ የምታገኙበት ቻናል ነው::
ለበለጠ መረጃ 👉🏽 https://youtube.com/@tenaseb-?si=TAxp4fhX-YijtoJn
4,868 सदस्य
309 तस्वीरें
55 वीडियो
अंतिम अपडेट 09.03.2025 10:55

TenaSeb - ጤና ሠብ द्वारा टेलीग्राम पर साझा की गई नवीनतम सामग्री

TenaSeb - ጤና ሠብ

11 Feb, 11:56

1,810

⚡️ጨቅላ ህፃናት ላይ የሚታዩ ህክምና የሚፈልጉ አደገኛ ምልክቶች

⚫️የጨቅላ ህፃናት መታመም ለቤተሰብ ከባድ ነገር ነው። ጨቅላ ህፃናት ሲታመሙ እንደ ሌላ እድሜ ላይ እንዳለ ሰው ያመማቸውን ስለማይናገሩ ሁኔታውን የበለጠ ከባድ ያደርገዋል።

⚫️ስለዚህ የህፃኑን መታመም ቀድሞ ለይቶ ማወቅ የ የወላጅ ሃላፊነት ይሆናል።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ምልክቶችን ልጅሽ ላይ ካስተዋልሽ ቶሎ ወደህክምና ተቋም መውሰድ ይኖርብሻል።

⚪️ጡት በደንብ የማይጠባ ከሆነ፣ በሆነ ባልሆነው የሚነጫነጭ ከሆነ እንዲሁም እያባበልሽውም ካለማቋረጥ የሚያለቅስ ከሆነ

⚪️በተደጋጋሚ የሚያስመልሰው ከሆነ እንዲሁም ምንም ነገር ባፉ አልወስድ ካለ።

⚪️ቆዳው እንዲሁም ነጭ የአይኑ ክፍል ቢጫ እንደሆነ ካስተዋልሽ።

⚪️ ከተወለደ በ 2 ቀናት ውስጥ ምንም ካካ ነገር ከሌለው፣ ሆዱ እየተነፋ የሚሄድ ከሆነ

⚪️እትብቱ የተቆረጠበት ቦታ የሚደማ ከሆነ እንዲሁም ሌላ ፈሳሽ የሚወጣው ከሆነ

⚪️ጡት ሲጠባ የሚያቆራርጥ ከሆነ፣ ከንፈሩ እንዲሁም እጆቹ የሚጠቁሩ ከሆነ
እነዚህን ምልክቶች ካስተዋልሽ ቶሎ ልጅሽን ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ ይኖርብሻል።


ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
TenaSeb - ጤና ሠብ

09 Feb, 13:26

2,050

ጤናማ የሆነ የወር አበባ ኡደት

የአንድ ለአቅመ ሄዋን የደረሰች ሴት ሰውነቷ ላይ በሚፈጠሩ ሆርሞኖች ምክንያት በየወሩ የወር አበባ ታያለች።

ይህም ሂደት ተፈጥሯዊ የሆነ እና ለእርግዝና ብቁ መሆኗን ማሳያ ነው።

መደበኛ የወር አበባ

* በአማካኝ 5 ቀን ይቆያል።

* ከ21-35 ቀናትን በአማካኝ ደግሞ በየ28 ቀኑ ይመጣል።

* መጠኑ ከ 10-80 ሚ.ሊ ወይም በአማካኝ 50 ሚ.ሊ ደም ነው።

* የሚፈሰዉም ደም ጠቆር ያለ እና የማይረጋ ነዉ።

* የወር አበባ ዑደት ተዛባ የምንለው አንዲት ሴት ወትሮ ከምታየው የተለየ ጠባይ ሲገጥማት ነው፡፡

* በመሆኑም የሚመጣበትን ጊዜው የሚያዛባ ከሆነ፣ ከወትሮው የተለየ ብዙ ደም ፍሰት፣ መጓጎል ካለ ወይም በጣም አነስተኛ ከሆነ፣ እርግዝና ሳይፈጠር ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሳትጠቀሚ የወር አበባሽ በጊዜው ካልመጣ በተለያዩ የማህፀን ፣እንቁልጢ(Ovary)ችግሮች ምክንያት የሚከሰት የወርአበባ መዛባት ሊሆን ስለሚችል ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነው።
TenaSeb - ጤና ሠብ

06 Feb, 09:47

2,212

የማህፀን መውጣትን(Uterine Propapse) እንዴት መከላከል ይቻላል?

1) ለዚህ ችግር ከሚያጋልጡ ነገሮች መቆጠብ።

እነዚህ አጋላጭ ነገሮች ምንድን ናቸው?

√ የሆድ ውስጥ ግፊት የሚጨምሩ ሁኔታወች(የሆድ ድርቀት፣ለረጅም ጊዜ የቆየ ሳል፣ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሆድ ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት)
√ ብዙ ልጅ በምጥ መውለድ
√  ከመጠን ያለፈ ውፍረት
√ ሲጋራ ማጨስ
√ ማረጥ
√ የማህፀን ቀዶጥገና
√ የምጥ መርዘም
√ የጅማት በሽታወች
√ የስኳር በሽታ

📌ስለዚህ ጫና የሚፈጥሩ ስራወችን(ለምሳሌ ከባድ እቃ መሸከም፣ ለረጅም ሰዓት መቆምን) መቀነስ
📌ክብደት መቀነስ እና ሲጋራ አለማጨስ አስፈላጊ ነው።

2) የመቀመጫ አካባቢ እንቅስቃሴ (Kegel's exercise)

ይህን እንቅስቃሴ የሚሰራው በቀን ለ3 ጊዜ ሲሆን
📌ይህም ለ 3 ሴኮንድ ያህል ሽንትና ፈስ ሊያመልጠን ስንል እንደምንይዘው አፍነን መቆየት እንደገና ለ3 ሴኮንድ እረፍት መውሰድ ለ10 ጊዜ ያክል ደግሞ መስራት። ይህንን በቀን ለ3 ጊዜ ቢያንስ ለ3 ወር ያክል መስራት ይኖርብናል።
📌ይህንን እንቅስቃሴ የወለዱ ሴቶች ቢሰሩት ከወሊድ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የማህፀን መውጣት ይከላከላል።

ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
TenaSeb - ጤና ሠብ

02 Feb, 06:49

2,228

የቅድመ ወሊድ ክትትል አስፈላጊነት

አንድ እናት በወሊድ ወቅት ሊያጋጥሟት ከሚችሉ ችግሮች ለመከላከል እንዲሁም ጤነኛ ህፃን ለመውልድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው።

መቼ ነው የቅድመ ወሊድ ክትትል ማድረግ የሚያስፈልገው?

📌ለማርገዝ ስታስቢ ጀምሮ ሃኪም ብታማክሪ እና ምርመራ ብታደርጊ ይመከራል። ምክንያቱም በዚህ ወቅት ለተለያዩ የጤና ችግሮች ለምሳሌ እንደ ስኳር፣ ደምግፊት፣ ለሚጥል በሽታ የምትወስጃቸው መድሃኒቶች ካሉ አንዳንዶቹ ፅንሱ አፈጣጠር ላይ ችግር ሊፈጥሩ ስለሚችሉ ከማርገዝሽ በፊት ወደ ሌላ አይነት መድሃኒቶች እንዲቀየሩ ይደረጋል። እንዲሁም እርግዝና አስቸጋሪ የሚሆንባቸው የጤና ችግሮች ካሉም ቀድሞ ምርመራ በማድረግ እና ህክምና በማግኘት በእርግዝና ወቅት ከሚደርሱ ውስብስብ ችግሮች መከላከል ይቻላል።

ከዚህም በተጨማሪ ከማርገዝሽ ወራት በፊት ጀምሮ ፎሊክ አሲድ እንድትወስጁ በማድረግ ፅንሱ ላይ ከሚፈጠሩ የስርዓተ ነርቭ ችግሮች መከላከል ይቻላል።

* ማንኛውም ነፍሰጡር የሆነች ሴት ነፍሰጡር እንደሆነች ካወቀችበት ጊዜ ጀምሮ በጤና ተቋማት የቅድመ ወሊድ ክትትል ማድረግ አለባት።

የቅድመ ወሊድ ክትትል ምን ምን ያካትታል?

* ስለ እርግዝናው እና ህክምና ታሪክሽ ሙሉ መረጃ ይወሰዳል

* ሙሉ አካላዊ ምርመራ

* የደም ምርመራ(የኤችአይቪ፣ ሄፓታይትስ፣ የደም አይነት፣ የሲፊሊስ ምርመራ)

* የሽንት ምርመራ

* የስኳር በሽታ ምርመራ

* እንዳስፈላጊነቱ የሾተላይ መከላከያ መርፌ ሊሰጥሽ ይችላል።

* እንዳስፈላጊነቱ የአልትራሳውንድ ምርመራ

* ከዚህም በተጨማሪ የወሊድ እቅድሽን ከሃኪምሽ ጋር ትወያያለሽ።
TenaSeb - ጤና ሠብ

28 Jan, 05:30

2,250

ጥያቄ: እርጉዝ ነኝ ቡና መጠጣት እችላለሁ?

መልስ: ቡና በውስጡ ካፊን የተባለ ንጥረነገር የሚይዝ ሲሆን ይህም ንጥረ ነገር የመነቃቃት ስሜትን ይፈጥራል። ነገርግን ከመጠን በላይ ከተወሰደ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።
✍️በእርግዝና ወቅት ከመጠን በላይ ቡና መጠጣት ፅንሱ ላይ መቀንጨር እና የእድገት ችግር፣ ውርጃ እንዲሁም ካለጊዜው መወለድ አይነት ችግሮችን ያስከትላል።

ከመጠን በላይ የምንለው መቼ ነው?
✍️እንደቡናው አይነት እና እንደምንጠቀመው መጠጫ ይዘቱ ቢለያይም፣ በእርግዝና ወቅት ከ 200 ሚሊግራም(ወደ 2 ሲኒ) በላይ ቡና በቀን ውስጥ መጠቀም አይመከርም። 
***
ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
TenaSeb - ጤና ሠብ

25 Jan, 13:22

2,475

እድሜ እየገፋ ሲሄድ ሰውነትም ከእርጅና ጋር ተያይዞ ዝቅተኛ መጠን ያለው ኮለጅን ያመርታል ይህ ደግሞ ቆዳን እንዲደርቅና እንዲሸበሸብ ያደርገዋል፤ ነገር ግን እድሜ ሳይገፋም ሊከሰት ይችላል።

የቆዳ ማለስለሻዎችን መጠቀም፦ ሃኪም በማማከርና የጎንዮሽ ጉዳት የማያስከትሉ የቆዳ ማለስለሻዎችን መጠቀም ለዚህ ይረዳል።

የፀሃይ ብርሃን ተጋላጭነትን መቀነስ፦ በአብዛኛው ከቤት ሲወጡ አልያም ወደ አንድ ቦታ ሲንቀሳቀሱ በተቻለ መጠን በበዛ መልኩ ለፀሃይ ብርሃን አይጋለጡ፣ ሁሌም ግን መከላከያውን ይጠቀሙ።

በቂ እንቅልፍ፦ እንቅልፍ በአግባቡ አለማግኘት ሰውነት ኮርቲሶል የተሰኘውን ሆርሞን በብዛት እንዲያመነጭ ያደርገዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በሀኪም ያልታዘዙ የፊት ቀለም ማንጫ ክሬም አለመጠቀም እና በቂ ውሀ መጠጣት ይመከራል።
TenaSeb - ጤና ሠብ

23 Jan, 14:49

2,359

ጥያቄ: የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

መልስ: የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምልክቶች እንደ በሽታው የደረሰበት ደረጃ ይለያያሉ። አንዳንድ ሴቶች ላይ ምንም  ምልክት ሳያሳይ መጥፎ ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል።

ዋና ዋና ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው :
📌ከወር አበባ ጊዜ ውጭ የሚኖር ወይም ከእርጣት በኋላ የማህፀን ደም መፋሰስ ወይም የወር አበባ ከተለመደው በተለየ መብዛት፣ ለረጅም ጊዜ መፍሰስ ወይም መዛበት
📌የተለየ ጠረን ያለው የማህጸን ፈሳሽ
📌ከግንኙነት በኋላ የሚኖር የደም መፍሰስ
📌በታችኛው የሆድ ክፍል የሚሰማ ህመም ፣ የወገብ ህመም
📌ሽንት ለመሽናት መቸገር ፣ የሽንት መጠን መቀነስ
📌የድካም ስሜት ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ እና ክብደት መቀነስ ወዘተ።
***
ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
TenaSeb - ጤና ሠብ

20 Jan, 15:34

2,331

በእርግዝና ወቅት እንድታስወግጃቸው የሚመከሩ ምግቦች

📌 በበቂ ሁኔታ ያልበሰለ ስጋ እና ጥሬ የአሳ ስጋ የተለያዩ በሽታ አምጭ ፓራሳይቶች በደንብ ባልበሰለ ወይም በጥሬ ስጋ ላይ መኖር ስለሚችሉ እነዚህን ምግቦች አብስለሽ መመገብ ይኖርብሻል።

📌በበቂ ሁኔታ ያልበሰለ እንቁላል       ያልበሰለ እንቁላል መመገብ ሳልሞኔላ(salmonella) ለተባለ ባክቴሪያ የማጋለጥ እድል አለው ስለዚህ እንቁላልን ሳታበስዪ በጥሬው መጠቀም የለብሽም።

📌የአልኮል መጠጥ በእርግዝናሽ ወቅት አልኮል መጠጣት Fetal Alcohol syndrome ለተባለ ችግር እንዲሁም የፅንሱ እድገት ላይ ችግር ይፈጥራል። ስለዚህ ማንኛውንም አይነት የአልኮል መጠጥ(ባህላዊ ወይንም ዘመናዊ) በእርግዝና ወቅት መጠቀም የለብሽም።

📌ሲጋራ ማጨስ የፅንሱ እድገት እና ጤንነት ላይ ችግር ስለሚፈጥር ሲጋራ ከማጨስ እንዲሁም ከሚጨስበት አካባቢ መራቅ ይኖርብሻል።

📌ቫይታሚን ኤ የበዛባቸው ምግቦች እንደ ጉበት ይህ ንጥረ ነገር በብዛት ከተወሰደ የፅንሱ አፈጣጠር ላይ እክል ስለሚፈጥር ጉበት በእርግዝና ወቅት አዘውትረሽ መመገብ የለብሽም።

📌ያልተፈላ ወተት
ወተት ለፅንሱ አካላዊ እድገት እንዲሁም የአጥንት እና ጥርስ ጥንካሬ አስፈላጊ ነው ስለዚህ ወተት ስትጠጪ አፍልተሽ ወይም ፓስቸራይዝድ መሆን አለበት።

📌በፅዳት ያልተሰራ ሰላጣ
ጥሬ አትክልት መብላት ሲያስፈልግሽ በጥንቃቄ፣በፅዳት የተሰራ እና ያልቆየ መሆን አለበት።
***
ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
TenaSeb - ጤና ሠብ

19 Jan, 14:50

2,028

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለከተራና ለጥምቀት በዓል በሠላም አደረሳችሁ!

@tenaseb
TenaSeb - ጤና ሠብ

18 Jan, 08:32

2,200

የደም ግፊት ከሚገባው በላይ ሲጨምር የደም ቧምቧዎችን እና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን ሊጎዳ ይችላል። ይህም የደም ብዛት ወይም ከፍተኛ የደም ግፊት ይባላል። የራስ ምታት፣ የአይን ብዥታ፣ ራስ ማዞር፣ እና ሌሎች ምልክቶች በ ግፊት ምክንያት ሊታዮ ቢችሉም በአብዛኛው ጊዜ ግን ምንም ምልክት የማያሳይ ሲሆን ዝምተኛው ገዳይ (silent killer) የሚለው ስም ይሰጠዋል። ዶ/ር ዝማሬ የ ደም ግፊት ምርመራ ጠቀሜታን ትገልጽልናለች፤ ይከታተሉን።