TIKVAH-ETH @tekvahethio350600 Channel on Telegram

TIKVAH-ETH

@tekvahethio350600


TIKVAH-ETH (English)

Welcome to TIKVAH-ETH, a Telegram channel that focuses on promoting Ethiopian culture and heritage. Our channel, @tekvahethio350600, is dedicated to showcasing the rich history, traditions, and artistic expressions of Ethiopia. Whether you are a proud Ethiopian looking to connect with your roots or simply interested in learning more about this beautiful country, TIKVAH-ETH is the perfect place for you. From vibrant music and dance to delicious cuisine and stunning landscapes, we cover it all. Join our community of like-minded individuals who share a passion for Ethiopia and immerse yourself in the beauty of this East African nation. Discover the beauty of Ethiopia with TIKVAH-ETH today!

TIKVAH-ETH

19 Dec, 10:58


ሀሰተኛ የብር ኖት ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ ተያዘ።

አበርገሌ ወረዳ 16, 900 #ሃሰተኛ የብር ኖቶች ሲያዘዋውር ነበር የተባለ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የወረዳው ፖሊስ ለኢዜአ አስታወቀ።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር የዋለው ሃሰተኛ የብር ኖቶቹን ይዞ ትናንት በወረዳው ወርቃዲኑ ጥንስስ ከተማ ለመገበያየት ሲሞክር ተደርሶበት ነው።

በአሁኑ ወቅት ተጠርጣሪው ምርመራ እየተደረገበት መሆኑም ተገልጿል።

@tikvahethio

TIKVAH-ETH

19 Dec, 10:57


ዛሬ የብሔራዊ ስቴዲዬም ሁለተኛዉ እና የማጠቃለያ ምዕራፍ ግንባታ ፊርማ ተካሂዷል።

የሁለተኛ ምዕራፍ ስራዉ ዋና አካል የጣራ መሸከሚያ ምሶሶ ኮንክሪት ሙሊት ስራ መጀመሩን ስፖርት ኮሚሽን አሳውቋል።

@tikvahethio350600

TIKVAH-ETH

19 Dec, 10:57


#AddisAbaba

ትላንት "በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ" የወጣቶች እና በጎ ፍቃድ ቢሮ አስተባባሪነት በቢሮዉ ስር ባሉ 10 ወረዳና የኦሮሚያ ፣ አዲስ አበባ ፣ ደቡብ ፣ አማራ እና ትግራይ ወጣቶች አደረጃጀትን በማስተባበር በሰሚት የጋራ መኖርያ አከባቢ በመገኘት የጤፍ አጨዳ ፕሮግራም አድርገዋል።

ከፕሮግራሙ መልስ በጤፍ አጨዳዉ ላይ ለተሳተፉት በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የለሚ ኩራ ክ/ከ የወጣቶችና በጎ ፍቃድ ቢሮ ሀላፊ አቶ ባጫ ጂሬኛ ምስጋና በማቅረብ የወጣቱ ሀይል በቀጣይ በክፍለ ከተማዉ ለሚሰሩ ስራዎች ለይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅረበዋል።

Via Amanuel Eticha (TikvahFamily)

@tikvahethio350600

TIKVAH-ETH

19 Dec, 10:56


#AmharaBank (በምስረታ ላይ)

የባለአክሲዮኖች ውክልና እስከ ታህሳስ 15,2013 ዓ/ም ድረስ ይከናወናል።

ውክልና ሰጥተዋል ? እስካሁን ውክልና መስጠት ያልቻሉ ባለአክሲዮኖች የውክልና መስጫ ቀናት ስለተራዘመ በቀሩት ጠቂት ቀናት ውክልና እንድትሰጡ አደራጅ ኮሚቴው አስገንዝቧል።

ለተጨማሪ መረጃ : 7285 የአማራ ባንክ የጥሪ ማዕከልን ይጠቀሙ። @amharabsc

TIKVAH-ETH

19 Dec, 10:55


የደረግ ባለስልጣናቱ እንዴት ጣልያን ኤምባሲ ገቡ ?

(በ2017 በቲክቫህ ኢትዮጵያ ላይ የወጣ አጭር ፅሁፍ)

© #ViceNews #ጋዜጠኛ_ደረጄ_ኃይሌ

ነገሩ እንዲህ ነው ኢትዮጵያን ለ7 ቀናት ያስተዳደሩት ሌ/ጀነራል ተስፋዬ ገ/ኪዳን ወይም 'የተስፋዬዎች መንግስት' ሀገሪቷን መቆጣጠር ሲሳነው ይሸሻል።

ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ሀገሪቷን በተቆጣጠረበት እለት አንዳንዱ የደርግ ባለስልጣን ከሀገር ይወጣል ወደ 13 የሚጠጉ ባለስልጣናት ደግሞ የጣልያንን በር ያንኳኳሉ ጣልያንም አላሳፈረቻቸውም ኑ ግቡ ትላቸዋለች።

ከገቡት መካካል አንዳንዱ ወዲያው ወጣ ሌላውም ጥቂት ቀናትን ቆይቶ ወጣ። ካልወጡት መካከል ግን ድፍን 26 ዓመት (ይህ ፅሁፍ በወቅቱ ሲፃፍ 2017 ነበር) ሙሉ በኤምባሲው ውስጥ እየኖሩ የሚገኙት 2 ባለስልጣናት ይገኛሉ።

ሁለቱም ባለስልጣናት የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ሲሆኑ የጣልያን ህገ መንግስት የሞት ፍርድን ስለማያስፈፅም ሁለቱን የደርግ ባለስልጣናት ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፎ አልሰጠም።

የጣልያን ኤምባሲ ሰዎቹን ገፍቶ ማስወጣትም አይፈልግም።

የጣልያን መንግስትም ሰዎቹን እንደ በጎ ፍቃድ ታሳሪዎች ነው የሚቆጥራቸው።

የቀድሞ ባለስልጣናቱን 'ከሰብአዊ መብት አያያዝ' ጋር በተገናኘ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጠበቃዎች እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ይጎበኟቸዋል።

ጣልያን ኤምባሲ ከገቡት እንዲሁም ገብተው ከወጡት መካከል ሜጀር ጀነራል ስዩም መኮንን (በማረፊያ ቤት ህይወታቸው አልፏል) ፣ ወሌ ቸኮል ፣ ፍሲካ ሲደልል ፣ ሽመልስ ማዘንጊያ ፣ ዶ/ር አለሙ አበበ ፣ ሸዋንዳኝ በለጠ ይገኙበታል።

በአሁን ሰዓት ጣልያን ኤምባሲ ውስጥ የሚኖሩት ሁለቱ (2) ባለስልጣናት አንዱ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበሩት ብርሀኑ ባየህ እንዲሁም በደርግ ስርዓት ከፍተኛ ተሰሚነት የነበራቸው ሌተናል ጀነራል ሀዲስ ተድላ (የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም) ናቸው።

ሀይሉ ይመንህ ራሳቸውን አጥፍተዋል።

ሌፍተናንት ጀነራል ተስፋዬ ገብረኪዳን የኢትዮጵያ የአንድ ሳምንት ፕሬዘደንት በብርሀኑ ባየህ እንደተገደሉ ይነገራል።

@tikvahethio350600

TIKVAH-ETH

19 Dec, 10:50


በጣልያን ኤምባሲ የሚገኙት የደርግ ባለስልጣናት !

በጣሊያን ኤምባሲ በቁም እስር ላይ የሚገኙት የሞት ፍርደኞቹ ሁለት የደርግ ዘመነ መንግሥት ባለሥልጣናት በአመክሮ እንዲፈቱ የፌደራሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጠየቀላቸው፡፡

ባለሥልጣናቱ በዘር የማጥፋት ወንጀል የተከሰሱ መሆኑን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ያለው ሕጋዊ አካሄድ በአመክሮ እንዲፈቱ ቀድሞ ውሳኔውን ላሳለፈው ፍርድ ቤት ጥያቄ ማቅረብ ነው ብሏል፡፡

የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፕሬስ ሴክሪታሪያት ኃላፊ አወል ሱልጣን ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የፍርደኞቹ ውሳኔ ከሞት ወደ እድሜ ልክ እንዲቀየር አፅድቀዋል ብለዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ዐቃቤ ሕግ ሁለቱ ግለሰቦች ላለፉት ሰላሳ (30) ዓመታት በጣልያን ኤምባሲ በቁም እስር ላይ የቆዩ መሆናቸውን መነሻ በማድግ በአመክሮ ቢፈቱ ሲል ምክረ ሃሳቡን ለፍርድ ቤት አቅርቦ ውሳኔው እየተጠባበቀ ነውም ብለዋል፡፡

በኤምባሲው ተጠልለው የሚገኙት የቀድሞ ወታደራዊ መኮንኖች የ85 ዓመቱ ሌተናል ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እና የ77 ዓመቱ ሌተናል ጀነራል አዲስ ተድላ ናቸው።

ምንጭ፦ አሐዱ ቴሌቪዥን

@tikvahethio350600

TIKVAH-ETH

19 Dec, 10:48


#ASTU

የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) በተለያዩ መርሃግብሮች ሲያስተምራቸው የነበሩ ተማሪዎቹን በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ይገኛል።

ዛሬ 1 ሺህ 300 ተማሪዎችን እያስመረቀ የሚገኘው፡፡

ከዚህ ውስጥ 1 ሺህ 228 በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን 70 በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም 2 ተመራቂዎች በሶስተኛ ዲግሪ ናቸው።

@tikvahethio350600

TIKVAH-ETH

19 Dec, 10:47


#AtoLilayHailemariam

የትግራይ የጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር አቶ ሊላይ ኃይለማርያም መብራት በዓደዋ እና አክሱም ከተሞች በዚህ ሳምንት እንደሚገባ ለኢፕድ አሳውቀዋል።

በትግራይ ክልል በሚቀጥለው ሳምንት የባንክ አገልግሎት በሰፊው እንደሚጀምር አሳውቀዋል።

አቶ ሊላይ ፥ "መቐለ በጥሩ እንቅስቃሴ ውስጥ ነው ያለችው። ወደ ቀደመ መልኳ ተቀይራለች" ብለዋል።

የመንግስት ተቋማትም አገልግሎት እንዲሰጡ እንዲከፈቱ መደረጉን ተናግረዋል።

በሰለማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰው ሁሉም ሰው ወደ ሥራ ገበታው እንደተመለሰ አሳውቀዋል።

ጥሪውን ተቀብለው ወደሥራ ያልገቡ ሠራተኞች ላይ በአገሪቷ ህግ መሠረት ዕርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።

MORE : https://telegra.ph/AtoLilay-12-19

@tikvahethio350600

TIKVAH-ETH

17 Dec, 13:11


ፕሬዚዳንት ማክሮን በኮቪድ-19 ተያዙ።

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት #ኢማኑኤል_ማክሮን በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ዛሬ ጠዋት ይፋ አድርጓል፡፡

ማክሮን ምልክቶችን ካሳዩ በኋላ ባደረጉት ምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ነው ጽ/ቤቱ የገለጸው፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ለ ሰባት ቀናት ራሳቸውን እንደሚያገሉም ስካይ ኒውስን ዋቢ አድርጎ #አልዓይን ዘግቧል፡፡ ይሁንና ፕሬዜዳንቱ ስራቸውን እንደሚቀጥሉ ተገልጿል፡፡

@tikvahethio350600

TIKVAH-ETH

17 Dec, 13:10


በሐመር ወረዳ የአንበጣ መንጋ ተከስቷል !

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ ሁለት ቀበሌዎች የበረሃ አንበጣ መንጋ ተከስቷል።

የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

አርሶ አደሩ የደረሱ ሰብሎችን ከማሳ ላይ ፈጥኖ መሰብሰብ እንደሚገባም ተገልጿል። #SRTA

@tikvahethio350600

TIKVAH-ETH

17 Dec, 13:10


#DrAbrhamBelay

ዶክተር አብርሃም በላይ በዓዲግራት እና ውቅሮ ከተሞች የመብራት አገልግሎት በሁለት ቀናት ውስጥ እንደሚጀምር አሳወቁ።

ዶ/ር ኣብርሃም ይህን ያሳወቁት በዓዲግራት ከተማ ከአገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደሆና ኢዜአ ገልጿል።

በውይይቱ ላይ የአገር ሽማግሌዎች ተቋርጦ የቆየው በተለይ የመብራት ፣ ቴሌኮም እና የውሃ አቅርቦት #በአፋጣኝ ወደ አገልግሎት እንዲመለስ ጠይቀዋል።

ዶ/ር አብርሃም መብራት በሁለት ቀን ውስጥ እንደሚጀመር ገልፀው ሌሎች መሰረተ ልማቶችን መልሶ የመገንባት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን አብራርተዋል።

@tikvahethio

TIKVAH-ETH

17 Dec, 08:26


መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ !

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው ያስመረቃቸው 3290 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን ፤ 1 ደግሞ በሶስተኛ ዲግሪ መሆኑ ታውቋል።

ከጠቅላላው ተመራቂዎች መካከል 30% እንዲሁም በጤና መስክ ከተመረቁት መካከል ደግሞ 38% ሴቶች መሆናቸው ከኢፕድ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethio350600

TIKVAH-ETH

17 Dec, 08:25


የእሳት አደጋ ፦

#ሐረማያ_ዩኒቨርሲቲ

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ህንፃ 3 የሚባለው የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ከሚኖሩበት ህንፃ የኤሌክትሪክ መቆጣጠሪያ ላይ የተነሳ የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በእሳት አደጋው በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ቢሆንም በሰው ላይ ምንም ጉዳት አለማድረሱን የዩኒቨርሲቲው ሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አስታውቋል።

#መካነ_ሠላም_ከተማ

በደቡብ ወሎ ዞን መካነሠላም ከተማ ድንገት የተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

መንስኤው ያልታወቀው የእሳት አደጋ በግምት ከለሊቱ 8፡00 ሰዓት አካባቢ የተከሰተ ሲሆን በሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆች ላይ ፣ በሴቶች የውበት ሳሎን እና በልብስ ስፌት ቤቶች ላይ ነው ጉዳት ያደረሰው፡፡

ከአምስት (5) በላይ ሱቆች እና ሌሎች የገበያ ቤቶች በእሳት አደጋው የተጎዱ ሲሆን የሱቅ እቃዎች ፣ የተለያዩ ማሽኖች እና ከ1 መቶ ሺህ ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ተቃጥሏል፡፡

@tikvahethio350600

TIKVAH-ETH

17 Dec, 08:18


#COVID19

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ -19) ን መነሻ ለማጥናት 10 ዓለም አቀፍ ተመራማሪዎችን የያዘ ቡድን በሚቀጥለው ወር ወደ ቻይና ዉሃን እንደሚያቀና የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

ቻይና በጉዳዩ ላይ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ፈቃደኛ አልነበረችም።

የዓለም ጤና ድርጅትም ከተማዋ ውስጥ ገብቶ ምርመራ ለማካሄድ እንዲፈቀድለት ለማግባባት ወራቶችን ወስዶበታል።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በከተማዋ የእንስሳት መሸጫ ገበያ እንደተነሳ ይታመናል።

ይሁን እንጂ የበሽታውን ምንጭ ለመፈለግ የሚደረገው ጥረት በተለይ ከአሜሪካ ጋር እስጥ አገባን አስገብቷት እንደነበር አይዘነጋም።

ምንጭ ፦ BBC

@tikvahethio350600

TIKVAH-ETH

16 Dec, 16:59


#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,451
• በበሽታው የተያዙ - 464
• ህይወታቸው ያለፈ - 5
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,662

አጠቃላይ 118,006 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,818 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 97,969 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

305 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethio350600

TIKVAH-ETH

16 Dec, 16:59


#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ ፣ ደሴ (ኮምቦልቻ) እና ሰመራ ተቋርጦ የነበረውን የበረራ አገልግሎት መጀመሩን ዛሬ ገልጿል።

@tikvahethio350600

TIKVAH-ETH

16 Dec, 14:57


#Telegram

ከ10:20 ጀምሮ ቴሌግራም ተቋርጦ እንደነበረ ተጠቃሚዎች ገልፀዋል።

ችግሩ #ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት እና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ውስጥ ነው የተከሰተው።

ድርጅቱም ከተጠቀሰው ሰዓት አስቶ ችግሩ እስከተፈታበት ሰዓት ድረስ ተጠቃሚዎች አገልግሎት ማግኘት እንዳልቻሉ አረጋግጧል፤ ምክንያቱን ግን አላሳወቀም።

በአሁን ሰዓት የቴሌግራም አገልግሎት ተቋርጦ በነበረባቸው ሁሉም ቦታዎች ላይ መስራት ጀምሯል ፤ ድርጅቱን ይህንን አሳውቋል።

@tikvahethio350600

TIKVAH-ETH

16 Dec, 14:56


#AtoTewoldeGebremariam

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮቪድ-19 ዓለም ዓቀፍ ቀውስ ባስከተለበት ወቅት ለነበረው ንቁ አገልግሎት ከኤርባስ የተበረከተለትን የዕውቅና ሽልማት ተቀበለ።

ሽልማቱን የተቀበሉት የኢትዮጵያ አየር መንገዶች ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ናቸው።

አቶ ተወልደ ፥ “ዓለም በፈለገን ጊዜ ተገኝተናል” ብለዋል።

“ለዚህ ስኬት ላበቁን ከ17 ሺህ በላይ ለሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞቻችን እና የማኔጅመንት ቡድን ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አጋር የሆነው ኤርባስ 350 ለሰጠው ዕውቅናም ምስጋና አቅርበዋል።

የኤርባስ ምክትል ፕሬዚዳንት ሃዲ ሃኩም በበኩላቸው ኤርባስ ለአየር መንገዱ የተሰጠው የዕውቅና ሽልማት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ቀውስ ጊዜ ለፈጸመው የማይታመን አገልግሎትና ስኬት ያለውን አድናቆት ለመግለጽ እንደሆነ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ/ENA/

@tikvahethio350600

TIKVAH-ETH

16 Dec, 14:54


ከነገ ጀምሮ በግንባታ ምክንያት ለ1 ወር የሚዘጉ መንገዶች !

አንድነት ፓርክን መጎብኘት በሚያስችለው የውስጥ ለውስጥ ዋሻ ግንባታ ምክንያት ከሂልተን ሆቴል ተነስቶ ወደ ቀኝ ለሚታጠፉ ተሽከርካሪዎችና ከካዛንችስ ወደ አራት ኪሎ የሚያስወጣው መንገድ ከነገ ጀምሮ እንደሚዘጋ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

በዚህም አሽከርካሪዎች ከኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል በንግድ ሚኒስቴር፣ በሂልተን ሆቴል ወደ 4 ኪሎ እንዲሁም ከካዛንቺስ መለስ አካዳሚ በሴቶች አደባባይ አቧሬ አድርገው ወደ 4 ኪሎ በመውጣት አማራጭ እንዲጠቀሙ መጠየቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

@tikvahethio350600