የሆነ እለት ሳቃቸዉ ለእናንተ ብቻ እንዳልሆነ ይገባችኋል። ለሌላ ስቀዉ ወይ በሌላ ታቅፈዉ አይታችሁ ሳይሆን የሆነ ቅጽበት እንደመገለጥ የምትረዱት ሃቅ ነዉ። በምክንያት ሳይሆን "አሃ" ብለዉ ልቤ ነገረኝ የሚሉት።
የሚሰጧችሁ ሙቀት ዉስጥ የሆነ አይነት አዘቦትነት አለ። መሳማቸዉ ክት አይደለም። እቅፋቸዉ መቁነጥነጥ አለዉ። ይሄ ነዉ የማይሉት ግን ልብ አዉቆ "ቅር" የሚለዉ። ዉሸት ስለሆነ ሳይሆን ጥልቅ ስላልሆነ።
እንዲህ ናቸዉ። ቀስበቀስ ይቀርቡና እናንተን እያረጉ ፣ እያሰመጡ እነሱ ግን አይጠልቁም። ሲሄዱም እንደዛ ነዉ ።
ድንገት — እንደተንሳፈፉ . . .
.
@samuel_dereje