Últimas publicaciones de ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . . (@samuel_dereje) en Telegram

Publicaciones de Telegram de ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .
ሽ ራ ፊ : ቃ ላ ት

ስ ባ ሪ ፡ ተ ረ ኮ ች

😊 - @Samvocado




https://linktr.ee/samueldereje
2,329 Suscriptores
386 Fotos
23 Videos
Última Actualización 09.03.2025 05:54

Canales Similares

Memers Texts
1,884 Suscriptores
your favorite punching bag
1,119 Suscriptores

El contenido más reciente compartido por ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . . en Telegram

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

07 Sep, 13:49

3,562

.

የሆነ እለት ሳቃቸዉ ለእናንተ ብቻ እንዳልሆነ ይገባችኋል። ለሌላ ስቀዉ  ወይ በሌላ ታቅፈዉ አይታችሁ ሳይሆን የሆነ ቅጽበት እንደመገለጥ የምትረዱት ሃቅ ነዉ። በምክንያት ሳይሆን "አሃ" ብለዉ ልቤ ነገረኝ የሚሉት።

የሚሰጧችሁ ሙቀት ዉስጥ የሆነ አይነት አዘቦትነት አለ። መሳማቸዉ ክት አይደለም። እቅፋቸዉ መቁነጥነጥ አለዉ። ይሄ ነዉ የማይሉት ግን ልብ አዉቆ "ቅር" የሚለዉ።  ዉሸት ስለሆነ ሳይሆን ጥልቅ ስላልሆነ።  

እንዲህ ናቸዉ። ቀስበቀስ ይቀርቡና እናንተን እያረጉ ፣ እያሰመጡ እነሱ ግን አይጠልቁም።  ሲሄዱም እንደዛ ነዉ ።
ድንገት — እንደተንሳፈፉ . . .


.

@samuel_dereje
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

06 Sep, 08:24

3,347

.

እንዲ ጷግሜ ሲሆን . . .
ዝናብ ያጨቀየዉ የጸበል መንገድ ትዝ ይለኛል። ጷግሜ በገባ ቁጥር የምንመላለስበት እያንዳንዱ ሁነት — ዛሬ ይመስል።

ሁሉን አስታዉሳለሁ ... ሳቅሽን ፣ ጸጉርሽን ፣ በጸበል የራሰ ነጠላሽን ፥ ፊትሽ ላይ የቀሩትን ነጠብጣብ የጸበል ዘለላዎች በጠዋት ጸሃይ ለመድረቅ ሳይረቱ
ሊተዉሽ ያመነቱትን። በብርድ የሚርበተበቱ ጥርሶችሽን ፣ ጥዬሽ እንዳልሮጥ ልመናሽን!

እንዲ ጷግሜ ሲሆን . . . አንቺን ፣ ጷግሜያችንን አስታዉሳለሁ። የወራት ሃጥ በቅንጣቢ ቀናት ልናጥብ የኖራንቸዉን ስፍር ቀናት ።

ዛሬ እንደትናንት አብረን ዘመን አንቋጭም። እንዲህ በልብ እንናፍቃለን እንጂ ልንኖረዉ አልታደልንም።


.

@samuel_dereje
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

01 Sep, 16:53

3,242

.



@samuel_dereje
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

30 Aug, 16:29

2,764

.

በፍሎረንስ ትርታ መሃል በሚያስገርም ውበቱ ፣ ቴክኒካል ብቃቱ እና በጥልቅ ተምሳሌታዊነቱ  ወደር የሌለዉ ግዙፍ የእምነበረድ ሃዉልት ቆሟል - የማይክልአንጀሎ ዳዊት። ይህ የእምነበረድ ጥበብ ብቻ አይደለም። ሰዉ የመሆን የምናብ ጥግ ፤ በጥበብና በጥበበኛ ፥ በአካልና በአለት ፥ በማመንና በፍርሃት መሃል የነበረ ንግግር እንጂ።

ማይክልአንጀሎ ከዛ ቀደም ዳዊትን የሳሉ ወይ የቀረጹ ጥበበኖች እንዳደረጉት ጎልያድን ድል ካደረገ በኋላ በጀግንነቱ ሊስል አልመረጠም። ይልቅ ዳዊትን ጎሊያድን ከመግጠሙ በፊት ከነሰዋዊ መሸበሩ መቅረጽን መረጠ እንጂ። ድልን ብቻ ሳይሆን ከድል በፊት ያለን ፍርሃት ሊያሳየን።

የ26 አመቱ ማይክልአንጀሎ 4 አመት የፈጀ ዳዊት እዉን ለመሆን ተዓምራዊ ማመን የሚጠይቅ ነበር። በሌሎች ቀራጺዎች ተደጋግሞ ተሞክሮ ተስፋ የተቆረጠበትን ግዙፍ እብነበረድ ብሎክ የፍሎሬንቲን ሪፐብሊክን ጥንካሬ እና ነፃነትን ወደ ሚያመለክት የጥበብ ስራ መቀየር መቻል።  

ቅርጹ የዳዊት ጡንቻዎች ፈርጥመዉ ፣ ደምስሮቹ ተወጥረዉ ፣ ዓይኖቹ ወደ ጠላቱ አተኩሮ ያሳያል። በሚያስደንቅ 5.17 ሜትር ቁመት ላይ የቆመው ዳዊት የአናቶሚካል ፍጹምነት ታይቶበታል።  የሃዉልቱ ምጣኔ ፥ የጡንቻዎቹ ዉጥረት ፥ ያተኮረ እይታዉ የእያንዳንዱ ጥርብ ዝርዝር የሰዉን ልጅ ጥበባዊ ጣሪያ ማሳያ ፥ ሰዉ የመሆን ምልክት ነዉ። የማይክለንጀሎ ዳዊት የሰዉ ልጅ መንፈስ ልዕልና ምስክር ነዉ። 


It stands not just as a masterpiece of Renaissance sculpture, but as one of the greatest artistic achievements in human history.
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

29 Aug, 09:19

2,454

.



@samuel_dereje
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

25 Aug, 07:21

2,971

.



@samuel_dereje
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

23 Aug, 08:17

2,700

.


የስንቶቻችን ህሊና ከበቀል ፍትህ ተጠማ? የምን ያህላችን ልብ ከቂም ምህረት ናፈቀ? እዉነት ሁላችን ሰላም ናፈቅን ወይስ "የእኛ" ያልናቸዉ የማይሞቱበት ጦርነት?

እያየን ምልክቶቻችን በጥላቻ ጭቃ ላቆጡ። አርያዎቻችን ከአትሮኖስ መርዝ ወረወሩ ። የደንባራ እረኞቻችን ሰይፍ የእልፍ መንጋ አንገት ቀላ።

ስለነጻዉጪዎቻችን ስንጮህ ስለራሳችን ማንባት ዘነጋን። ለሁላችን የመጣን ሞት መላክ "እንደእኛነት" ከመጋፈጥ ምሮ እንዲያልፈን የቤታችንን በር ዘር መቀባት ወደድን።

በልባችን ካለዉ እባብ የምንፈራዉ ጠላት ማን ነበር? ኩሸት ከሚተፋ ምላሳችን በላይ መጥፊያችን ከየት መጣ?

. . . እኛ የእኛዉ ጠላት ፥ እኛ የእኛዉ ባዳ።


@samuel_dereje
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

21 Aug, 11:18

2,681

.

Speak a little softer. Maybe much softer. Turn more pages, highlight more lines. Quit doubting (if I start). Start writing (if I stop). Savor moments (if I forget). Compliment that stranger on her smile and turn her into more than a stranger. Write stories for her, so she can share them with my daughter. Face my fears, take them out for coffee, and have tales to share my son. Plant dreams in the quiet corners of my mind. Leave my mark on the world, evidence that I lived, here, and here, and here.

Inhale. Exhale. Carry on. Carry on.


Inspiration and Form - @Spokensincerly - Five year plan



@Samuel_dereje
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

18 Aug, 09:15

2,895

በክኒኑ ፈንታ ቀለም እና ቃላት ፥ ሐኪሞች ሲያድሉ
ሕመሙን ማስጌጥ ነው ፣ የሰው ልጅ ዕድሉ::
- በዕዉቀቱ ሥዩም


ቋጠሮዎች ነን - የሰዉ ልጆች። ብዙ ድርብርብ ፍላጎት ፥ ስሜት ፥ ማንነት አሉን። ደሞም ወጥ አይደለንም። በኖርን ቁጥር እንደቅርፊት የሆነ የምንተወዉ ማንነት አለ። ለዉጥ አይቀር እንዲሉ። እንደዛዉ በብዙ ተለወጥን ፣ ኖርን እንበል እንጂ ከጉያችን የማይጠፋ እንኛነትም አለ። ልጅ ሆነን የነበረ።

የዚህ ተከታታይ የሃሳብ ቅኝት ግብ ያ ነዉ። ሕመሙን ማስጌጥ ብቻ ሳይሆን ዉስብስቡን የማንነት ድሪቶ በቀለም እና ቃላት ለመፍታት መሞከር።

በዚህ ቅኝት አንዳንዴ ጥሬ መሳይ ደረቅ ሃሳቦች ይገጥመን ይሆናል። ለምን ከዓመታት በፊት ስለሞቱ ፈላስፎች ይገደናል? ልትሉ ትችላላቹ። የኔ መልስ የምንቆምባቸዉ ትከሻዎች ስለሆኑ ነዉ።

መቼም በሰብአዊ መብት ታምናለህ? ሰዉ ልጅ ክብር ይገባዋል ብለህ? ምን ሃይማኖተኛ እንኳን ባትሆን? አትርሳ የካንት እዳ አለብህ። የሃይማኖተኛ ሃገር ሆኖ መገዳደሉ ገርሞህ ያዉቃል? የሚያደርጉት ግራ ገብቶህ እዉነት እነዚህ በአምላክ ያምናሉ ብለህ? ኒቼ ሊያወራህ ይፈልጋል። ሰዎች የማይረዱህ ይመስልሃል? ወይ ለሆንካቸዉ ነገሮች ወላጆችህን ፣ አስተዳደግህን ኮንነህ? ፍሮይድ ህመምህ ይገባዋል። ድንገት ከዉስጥህ የሚወጡ ማንነቶች አይተህ ታዉቃለህ? ስትናደድ ወይ ሲከፋህ? ማን ነዉ ደሞ ይሄ ሰዉ ብለህ? ዮንግ ለምን የሚለዉን ያስረዳሃል። ያለህ ምንም ሳይመስልህ ሌሎች የያዙት አጓግቶህ ያዉቃል? ለምን በእኩዮችህስ እንደምትቀና? ሬኒ ዤራርድ መልስ አለዉ።

በዚህ ቅኝት የትናንት ሃሳቦችን ከህይወታችን ፥ ከልማዳችን ጋር እያስተያየን አሃ እንላለን። Join me, The Journey is worth it!



ቅኝት የምናደርግበትን አዲሱን ቻናሉን ለመቀልላቀል @samvocado1 ላይ መቀላቀል እፈልጋለሁ ብላቹ ላኩልኝ።
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

14 Aug, 15:39

2,398

.


ሰለሞን “የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ እግዛብሄርን መፍራት ነዉ’’ እንዲል ሶቅራጥስ ደግሞ “የጥበብ ሁሉ መጨረሻ ራስን ማወቅ ነዉ” ያላል!


ሳድግ ፣ ትንሽ ሳዉቅ የገባኝ አንድ እዉነት ሁሉም ሰዉ ልቡ መሃል ባዶነት ይዞ መዞሩን ነዉ። ያን ባዶነት አንዳንዱ በትዳር ፣ አንዳንዱ በስራ ፣ አንዱ በሃብት ፣ አንዱ በጥበብ ፣ አንዱ በልጅ . . . ሊሞላዉ ያሳዳል።

 ያን ባዶነት ከቀልቡ ሆኖ ላዳመጠዉ እልፍ ጥያቄዎች ይወልዳል። ሰዎች ጥያቄ የሞላን ፍጥረቶች ነን። ብዙ ያልጠየቅናቸዉ ፣ ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉን።

እኛ ማን ነን? ስንት አይነት ማንነት አለን? ለምን ያጣነዉ እንሻለን? ለምንስ እንጓጓለን? ለምንስ ምኞታችን አይሞላም? እንዴት ብዙዎቻችን ባዶነት ልባችን መሃል ተሸክመን? ለምን ፍቅር እንሻለን? ምን ይሆን እንዲ መወደድ መድነቅ የሚያስርበን?. . እልፍ ቀላል መሳይ ዉስብስብ ጥያቄዎች።

ትልቁ ጸጋዉ ሰዉ ያወቀዉን ማቆየቱ ነዉ። መጻፍ መቻሉ። ጽፎ ለልጁ ያቆያል። ልጁ ከአዲስ አይጀምርም አባቱ ካቆመበት እንጂ — ሃሳብ ቅብብሎሽ ነዉ። እኔም እነዚህ ጥያቄዎች መልስ አገኝ ዘንድ ፍልስፍናን ፣ ስነልቦናን ፣ ስነ-ጽሁፍን ማገር አድርጌ ለመቃኘት እሞክራለሁ።

በዚህም ቅኝት ኢማኑኤል ካንት ፥ ኒቼ ፥ ካርል ዮንግ ፥ ዥክ ላኮን ፥ ሬኒ ዤራርድን ብሎም ከተለያዩ ልቦለዶች ገጸባህሪያትና ሃሳቦች እየተዋስን መልስ እናስሳለን።

የካንት ተሻጋሪ ማንነት ( Transcendental Self ) ሃሳብና የሞራል ፍልስፍናዉን ተጠቅመን። ስለ ሰዉነት ፥ ስለነጻነት ፥ ራስን ስለመግዛትና ስለ ህሊና ህግ እንቃኛለን። በሌላ ጽንፍ ደግሞ በኔቼን Übermensch ወይም ልዕለሰብ ሃሳብ ታግዘን  ስለፈጠራ (creativity) ፣ ስለሃያልነት ፣ ስለፈጣሪና ምግባር ብሎም ጀርመናዊዉ ፈልስፋ ለማህበርሰብ ህግ መገዛት ራስን በፍቃድ ማሰር ነዉ ሲለን ምን ሊነገርን ነዉ የሚለዉን እናያለን።

ስንት አይነት ማንነት አለን? ራስን መሆን ምን ማለት ነዉ? እንዴትስ መሆን እንችላለን? የሚሉትን ጥይቄዎች በካርል ዮንግና ሌሎች ሳይኮአናሊስቶች ታግዘን ለመመልስ እንሞክራለን።

ለምን እንጓጓለን? ለምን ያጣነዉን እንሻለን? ከእኩዮቻችን ምን ያፎካክረናል? ሰዉ ያገኘዉን ለምን ይንቃል? ያጣዉንስ በምን ምክንያት ነዉ የሚያከብረዉ? ወዘተ የሚሉትን ደግሞ በሬኒ ዤራርድና ላኮን ሃሳቦች እንፈትሻለን።

ነገር ግን ህይወት ፍልስፍናዊ ብቻ አይደለም። ስሜትም የሚመራን ነን። ሰዉ አይደለን። ለዛ ይመስለኛል በእዉቀቱ “በሞቷ ፊትለፊት" የሚለዉ ግጥሙ ላይ . . .

በሞቷ ፊትለፊት፥ ሀሳብ ሁሉ መና
ምከር ሁሉ ኦና
አንባን አይገድብም፥ የስው ፍልስፍና
” ያለዉ።

እዉነት አለዉ። ለዚህም ረዘም ያሉ ተረኮችን እንጽፋለን። ስሜቶችን እንካፈላለን። ከዛም አልፎ በዉብ ቃላትና ጥልቅ ገጸባህሪያት የተጻፉ የተላያዩ ደራሲያን መጽሃፍትን እንቃኛለን። በመጽሃፍቱ ታሪክ ፣ በገጸባህሪያቱ ህይወት ሃዘንን ፣ እንባን ፣ ፍቅርን ፣ ማጣትን ፣ ማመንን ሁሉ እንቃኛለን።

ሃሳብ እንባን አያቆምም። ነገር ግን የዛፍ ስር አፈሩን ከጎርፍ እንደሚያስጥል በሃዘን ፥ በመከዳት በብቸኝነት የሚመጣ ትርጉም ማጣት ይዞን እንዳይጠፋ አጥብቆ ይይዘናል። ምክንያቱም ጽንሰ-ሃሳባዊ መሰረት ፥ የራሳችን እሴትና የህሊና ህግ እንዲኖረን ይረዳናል። ግለሰባዊ ሰላም ራስን ከማወቅ የሚገኝ ነዉና።

ኒቼ ራስን አለመሆን, “የመንጋ አሳቢ” መሆን ነዉ ይላል። Herd mentality የሚለዉ።  ማወቅ ሂደት ነዉ። ብዙ ስራና ብዙ ጉዞ የሚጠይቅ ነዉ። የማንኛዉም ጉዞ መጀመሪያ የሚሄዱበትን ማወቅ ነዉ። ያን ነዉ በዚህ ቻናል የምንቃኘዉ። ሃሳብ ፣ ስነጽሁፍን እንደሰረገላ ተጠቅመን ራስን መሆን ላይ ለመድረስ።


አብራቹኝ ለመጓዝ ፍላጎታችሁ ከሆነ ወራዊ Subscription ያለዉ የቴሌግራም ቻናል ጀምሪያለሁ። ያዉ በእኛ ሃገር Substack , Patreon የመሳሰሉ Creativity monetization መንገዶች ስለሌሉ Improvised Substack በሉት። ቻናሉን ለመቀላልቀል Subscription'ኑ በወር 100 ብር ነዉ። ቻናሉና ፍላጎቴ እኔ ከማጋራቸዉ ጹፍና ሃስቦች ዉጪ Live audio ዉይይቶች ፥ ክርክሮች የምናደርግበት ጥሩ ተዋስዖ ያለዉ one vibrant community መገንባት ነዉ። እንደምትቀላቀሉ ተስፋ አለኝ።

እንዴት የሚለዉን ለማወቅ ከታች ያለዉን መንገድ ተከተሉ!