ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ @nwdnews Канал в Telegram

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
የብፁዕ አቡነ ኤርምያስ እና የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ እንዲሁም የሌሎች መምህራን ትምህርቶች፣ ስብከቶችና ተግሳጾች በተጨማሪም በሀገረ ስብከቱ የሚከወኑ ዓበይት ክንውኖች የሚተላለፉበት የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የቴሌግራም ቻናል ነው። የቻናሉ ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በመጋበዝ የቤተክርስቲያንን አገልግሎት ያፋጥኑ።
5,866 подписчиков
2,793 фото
8 видео
Последнее обновление 01.03.2025 05:47

የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ እና የዘመናዊ መረጃ ምንጮች

የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ በሰሜን ወሎ ክልል ውስጥ በፖለቲካ ውሎ በሚኖሩ ምርጥ የሚዲያ መረጃ ምንጮችን ከአስፈላጊ ምርጥ የእውቀት መረጃ መረጃ ይደርሳል። ይህ ቻናል በመምህራን ታሪክ እና በዓለም ታሪክ የተመለከተ ምርጥ ምርጥ ይደርሳል። እንደዚህ የሚገኝ እውቀት መረጃ በዕድል አስፈላጊ ነው።

የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ዋነኛ ግንባር ምንድን ነው?

የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ በሰሜን ወሎ ክልል ውስጥ በደረጃዎች ተገድሺ ነው። በዚህ ቻናል የሚከናወኑ ስብከቶች ላይ በመዳረሻ እንዲሁም የቤተክርስቲያን አገልግሎት ይቀርባሉ።

ከሌላ የሚዲያ ተግባራት መሰረት በቤተ ክርስቲያን መንደር ይገኛሉ። ይህ ጉዳይ መረጃታዊ እንዲኖሩ ይህ ድረ-ገጽ የዚህ ቻናል ይወስነዋል።

የቻናሉ መለያ ምንድን ነው?

የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ በቴሌግራም ላይ ይገኛል። በቻናሉ ወይም በመዳረሻም የሚከወኑ የጋብዝ ይሆናሉ።

ይህም ለህዝቡ ማዕከል ወይን ይወስዳል። በአማርኛ እንዲሁም በሌላ ምርጥ የሚሰጠውን የሚዲያ ገጽታ እንዲመለከተው ይገኛል።

በሚዲያ የሚከናወኑ ስብከቶች ምን እንደሚያቀርባሉ?

በዚህ ቻናል የሚነሳ ወይም የሚቀርባው መረጃ ስብከቶች የአስተዳደር ወገኖች ቢያነሱ ይቀርባሉ።

የተቀባይነት መንገድ ወይም የትምህርቶች መግለጥ ይሆናል። ይህም በአማርኛ የተነቃቃ ሥራ ወይም የቴሌግራም ወረቀት ማሳያ ይቀርባል።

የሚዲያው ውስጥ ምን እንደሚያይቅ አይቁ?

ይህ ድረ-ገጽ ኢንተርኔት ገጽታን ይኖራል ወይም ያልተሳማ የተሳሳቢ ክንውና ይለዋወጣል።

አንዳንድ ግለሰቦች በቱርሱ እና ግዢት ዝርዝር ይቀየሩ የተለዋዋጮቹ ዝርዝር አገልግሎት ላይ ይኖራል።

Телеграм-канал ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

መርሐ ግብርድን የብፁዕ አቡነ ኤርምያስንና የብፁዕ አቡነ ቄርሎስን እና የሌሎች መምህራን ትምህርቶችን፣ ስብከቶችንና ተግሳጾችን በተጨማሪም ሀገረ ስብከቱ ዓበይት ክንውኖችን የሚተላለፉበት የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት አዝናኝ ቴሌግራም ቻናል ነው። የቴሌግራምን ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በመጋበዝ የቤተክርስቲያንን አገልግሎት ያፋጥኑ።

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ Последние сообщения

Post image

https://youtu.be/zWpAZcDHJ-c?si=QbWG2sFlpgW01zk2

28 Feb, 13:41
459
Post image

ፋሲካ የሌለው ጾም በየኔታ መ/ር ኤርምያስ አዳነ የሰሜን ወሎ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌልና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ዋና ክፍል ኀላፊ

28 Feb, 13:41
381
Post image

ታሪክ ጌታ ከቅድስት ሰኞ ጀምሮ እስከ ዓርብ ኒቆዲሞስ ከቆመ ሳያርፍ ከዘረጋ ሳያጥፍ ዓርባ ቀን በትህርምት ጾሟል ሐዋርያት እሑድ እሑድን አውጥተው ቢቄጥሩ ጎደለባቸው አስቀድመው አምስት ቀን ጹመው ለስብከተ ወንጌል ይፋጠኑ ነበርና …

የኋላውንም ሁለት መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ ታሪኮች ደግሞ እንዲህ ያብራራልናል።

① በኢየሩሳሌም ፎቃ በሮም ህርቃል ነገሠ ፎቃ በኢየሩሳሌም ባሉ ምእመናን መከራ አጸናባቸው ምንም አንድ አካል ሁለት ባሕርይ በማለት ብንለያይ ወረደ ተወለደ በማለት አንድ ነንና መጥተህ አጥፋልን እኛ ላንተ እንገዛለን ብለው ወደ ሕርቃል ላኩበት እሱም ከአይሁድ ጋራ ጨዋታ መሐላ ነበረውና ቸል ብሎ ተዋቸው ኋላ ግን "ግዙራን ይነሥእዋ ለመንግሥትከ" የሚል ራእይ አየ።

መንግሥቱን የሚወስድበት ኡመር ወልደ አድ እንደሆነ ባያውቅ "ግዙራን የተባሉ ሌላን እለ? አይሁድ አይደሉምን" ብሎ "ያን የላካችሁብኝ ነገር አልረሳሁትም ነገር ግን ሐዋርያት ነፍስ የገደለ መላ ዘመኑን ይጹም ብለዋል ጾሙን ብፈራ ነው እንጅ" አላቸው ያንድ ሰው ዕድሜ ቢኖር ሰባ ሰማንያ ዘመን ነው ይህንንስ እኛ እንጾምልሃለን አሉት መጥቶ አጥፍቶላቸዋል በኢየሩሳሌም ያሉ ምእመናን አምስት አምስት ቀን ተካፍለው ጹመውለታል ያላወቁት አንድ ጊዜ ጹመው ትተውታል ያወቁትን ግን ቀድሞም ሐዋርያት ጹመውታል ብለው ሥራት አድርገው በዓመት በዓመት የሚጾሙት ሁነዋል!

② የሮም ሊቃነ ጳጳሳት ቀሳውስት ዲያቆናት ምእመናን ጹመውታል የሮሙን ንጉሥ ከፋርሱ ንጉሥ ተጋብቶ ሲኖር ሚስቱን በድሎ ሰደዳት ሒዳ ለአባቷ አንተን ያህል አባት እያለኝ በድሎ ሰደደኝ አለችው። እሱም ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት ብሎ ሒዶ እኔ ከሀገሩ ጠብ የለኝም ጠቤ ካንድ ሰው ነው ጠላቴን ስጡኝ ባትሰጡኝ ግን ጠቤ ከናንተ ጋራ ነው አላቸው ቢትወደዱ «ፎቃ» ይባላል ባንድ ሰው ምክንያት ብዙ ሰው እናስጠፋለን። አውጥተን እንስጥ እንጂ አላቸው። ማን ይነግሣል አሉት እኔ እነግሣለሁ አላቸው አወጥተው ሰጡት ፎቃ ነገሠ።

የጥጦስን የአስባስያኖስን ዘመን ለመመለስ በሮም ባሉ ምእመናን አገዛዝ አጸናባቸው ኋላ ባሪያውን ለማይገባ ገረፈው ህርቃልን ቢትወደድነት ሹሞት ነበረና ሔዶ በማይገባ ገረፈኝ ብሎ ነገረው አትገድለውም አለው ማን ይነግሣል አለው እኔ እነሣለሁ አለው ጊዜ አይቶ ገደለው ህርቃል ነገሠ። ከዚህ በኋላ የሮም ምእመናን መጥተው እኛም ከወገኖቻችን ካነገሥክልን ብድራችንን እንድንመልስ አይሁድን አጥፋልን ብለው አማሉት እሱም ከአይሁድ ጋራ ጨዋታ መሐላ ነበረውና ቸል ብሎ ተዋቸው ኋላ ግን ግዙራን ይነሥእዋ ለመግሥትከ የሚል ራእይ አየ ግዙራን የተባሉ ሌላ እለን አይሁድ አይደሉምን ብሎ ያን ያላችሁኝን ነገር አልረሳሁትም ነገር ግን ሐዋርያት ነፍስ የገደለ መላ ዘመኑን ይጹም ብለዋል ጾሙን ብፈራ ነው እንጂ አላቸው ያንድ ሰው ዕድሜ ቢኖር ስባ ሰማንያ ዘመን ነው። ይህነንስ #እኛ_እንጾምልሃለን አሉት መጥቶ አጥፍቶላቸዋል በሮም ያሉ ምእመናን አምስት አምስት ቀን ተካፍለው ጹመውለታል ያላወቁት አንድ ጊዜ ጹመው ትተውታል ያወቅቱ ግን ቀድሞውም ሐዋርያት ጹመውታል ብለው ሥርዓት አድርገው ባመት ባመት የሚጾሙት ሁነዋል።

ወደ እኛ የደረሰው እንዴት እንደሆነ ለማሳየትም ለመሰናዶው ሳምንት የሕርቃልነቱን ስያሜ ተቀብለው ከዐቢይ ጾም ቀድሞ ባለው ሳምንት እንዲዘከር በድንጋጌ ያጸኑ በዘመነ ሕርቃል በእስክንድርያ የነበሩ ፴፯ኛው ፓትርያርክ አቡነ አንደራኒቆስ መሆናቸውን ዜና ጳጳሳቱ ይነግረናል።

"Pope Adronicus, the 37th Patriarch of Alexandria, acknowledged this request. From that time, “Heraclius Week” began to be observed."

በአጋዥ የታሪክ ማነጻጸሪያ ደግሞ በስንክሳራችን ዕረፍቱ ጥር ፰ የሚዘከረው በቅዱስ ማርቆስ መንበር ፴፯ኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ቅዱስ አንደራኒቆስ በዘመኑ የፋርስ ንጉሥ ክስራ [Kessra the king of Persia] ከሮሙ ንጉሥ ህርቃል ጋር ስላደረገው ጦርነትና እስክንድርያ ባሉ ምእመናንም ላይ ይደርስ ስለነበረው መከራ ተከታዩን ታሪክ ይነግረናል።

«በሹመቱም ወራት ፀሐይን የሚያመልክ የፋርስ ንጉሥ ክስራ ተነሣና የሶርያንና የፍልስጤምን ከተሞች ወርሮ ዘረፋቸው፡፡ ወደ ግብጽም መጥቶ እስክንድድርያ ከተማ ደረሰ፡፡ በዙሪዋ በመነኮሳት የተሞሉ ሰባት መቶ ገዳማት ነበሩ፡፡ እነርሱም ገንዘብ ያላቸው በተድላ የሚኖሩ ነበሩ፡፡ ስለዚህም በእነርሱ ላይ እግዚአብሔር ሥልጣንን ሰጥቶት ገዳማቱን አፈረሰ፡፡ እነርሱንም ሸሽተው ካመለጡት በቀር ሁሉንም ገደላቸው፡፡ ገንዘባቸውንም ሁሉ ማረከ፡፡

የእስክንድርያ ሰዎችም ንጉሥ ክስራ ያደረገውን ባዩ ጊዜ የከተማውን በር ከፈቱለት፡፡ እርሱም ‹ይህችን አገር በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ አታፍርሳት፣ በውስጧ ያሉትን ብርቱዎች ግደላቸው-ዐመፀኞች ናቸውና› እንደሚለው በሕልሙ አየ፡፡ በዚህም ጊዜ የሀገሩን ንጉሥ ይዞ ካሠረው በኋላ ለሀገሩ ሰዎች ‹‹በጦር ሠራዊት አደራጃቸዋለሁና ከ18 ዓመት ጀምሮ ያሉትን ብርታት ያላቸውንም ሁሉ ሰበስቡልኝ፣ ለእያንዳንዳቸው ደመወዛቸውን 20 የወርቅ ዲናር እከፍላለሁ›› አላቸው፡፡ ሕዝቡም ሁሉ እውነት ወርቅ የሚቀበሉ መስሏቸው 8 ሺህ ብርቱዎችን ቆጥረውና መዝግበው በሰጡት ጊዜ ንጉሡ ክስራ ሁሉንም በሰይፍ ገደላቸው፡፡ ወደላይኛው ግብጽ በመሄድም ኒቅዮስ ደርሶ ሰባት መቶ በሥራቸው ክፉ የሆኑ መነኮሳትን በሰይፍ ገደላቸው፡፡ የሮም ንጉሥ ሕርቃልም የፋርሱ ንጉሥ ክስራ ያደረገውን በሰማ ጊዜ ሠራዊቱን ሰብስቦ መጥቶ ንጉሥ ክስራን ከነሠራዊቱ ሀገሩንም ጭምር አጠፋቸው፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የአባ እንድራኒቆስ ገድሉ እጅግ ያማረ ነበር፡፡ … »

ሕርቃል ከአርመናውያን ቤተሰቦች በ575 ዓ.ም. በቀጰዶቅያ ተወልዶ በ641 ዓ.ም. በቁስጠንጥንያ ያረፈ በእምነቱም የመለካውያኑ (Chalcedonian Christianity) ተከታይ የነበረ የሮማውያን ንጉሥ ቢሆንም ካቶሊካውያኑ የእኛውን ንጉሥ አፄ ካሌብን [Saint Elesbaan] በቅድስና እንደሚዘክሩት «ምንም አንድ አካል ሁለት ባሕርይ በማለት ብንለያይ ወረደ ተወለደ በማለት አንድ ነንና መጥተህ አጥፋልን» ብለው ደጅ ለጠኑት በእስክንድርያ እና በኢየሩሳሌም ለነበሩ ምእመናን ባለውለታ በመሆኑ ኦርቶዶክሳውያኑ የልዩነት ድንበሩን ጠብቀው ሲያከብሩት ኖረዋል።

የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ሰላም ፣ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማርያም ፍቅርና የኢየሱስ ክርስቶስ የረድኤቱ ሀብት የቅዱስ መስቀሉም ሞገስ ሁል ጊዜ ለዘለዓለሙ ከሁላችን አይራቅ!

ከሰሙነ ሕርቃል በረከት ያሳትፈን!

26 Feb, 19:12
633
Post image

. ሰሙነ ሕርቃል “Heraclius Week”
⊙∗⊕━━✦༒༒✦━━⊕∗⊙
(መንደርደርያ ሐሳብ)

ሀገር ለቀው፣ ባህር ጠልቀው፣ ገደል ወድቀው የሚሰደዱትን መከራ ጸንቶባቸው የሚቸገሩትን በዓለም ሁሉ ያሉ ምእመናን ለስዱዳኑ ተስፋ፣ ለምንዱባኑ ረዳኤ፣ ለሕዙናን ናዛዜ፣ ለግዱፋን ዐቃቤ ፣ ለጽዑራን መጽንዔ የሆናቸው ክርስቶስ በቸርነት ይድረስላቸው🙏

እንኳን ለዐቢይ ጾም ቀዳሜ ሳምንት (ዘወረደ፣ ሙሴኒ፣ ሰሙነ ሕርቃል…) በሠላም አደረሳችሁ!

☞ «መገለጫውን ሲያይ ነው እንጂ የጾሙትስ ሐዋርያት ናቸው»

☞ «ምንም አንድ አካል ሁለት ባሕርይ በማለት ብንለያይ ወረደ ተወለደ በማለት አንድ ነንና መጥተህ አጥፋልን»

☞ «ሰሙነ ሕርቃል ዘትከውን እምቅድመ ጾም ዐቢይ …»

#ሰሙነ_ሕርቃል ለጾመ እግዚእ የመሰናዶ ሳምንት [Preparation Weekinitial week] ተብሎ ተገልጧል። ከስምንቱ የዐቢይ ጾም ሳምንታት ከቅድስት ቀድሞ ለሚጾመው የዘወረደ ሳምንት አንዱ ምክንያት ሕርቃል ንጉሠ ሮም እንደሆነ ይታወቃል።

፲፪ኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ቅዱስ ዲሜጥሮስ ድኅረ አስተርእዮ ያለውን ፵ ዕለት ዐቢይ ጾም (A 40 day fast post Theophany) በ250 ዓ.ም. አውጆ በሮም በኢየሩሳሌምና በአንጾክያ በነበረችው አሐቲ ቤተክርስቲያን ቅቡልነት አግኝቶ ጸንቷል። ይህ ህርቃል ግን የተጨመረ በ616 እንደሆነ ይነገራል። ነገር ግን መጠሪያው የመሰናዶ ሳምንት ቀድሞ የነበረ እንጂ ሕርቃል በሚል እንዳልነበር መረጃ በማቅረብ የሚሞግቱ ቅብጣውያን አሉ። ኋላ ከ13ኛው ምዕተ ዓመት ወዲህ በኢብን አል አሰል በኩል ጾመ ሕርቃል (ሰሙነ ሕርቃል) በሚል ተለይቶ እንደተጠራ አስረጂ ጠቅሰው ይገልጻሉ።

(We find mention, of this week being referred to as “Hercules Week” as late as AD 1245 by Al-Safawy Le Ibn Al-Assal as being a fast distinct from the Great Fast proper )

በእኛም ዘንድ የጾሙን ምክንያት ሊቃውንቱም መጻሕፍቱም በተለያየ መንገድ ገልጠውታል።

፩) ጥንቱን ሐዋርያት ዐቢይ ጾምን ከእሑድ በቀር ቆጥረው ቢጎድልባቸው ቀድሞ ያለውን አምስት ቀን ከቁጥር ጨምረውታል።

፪) በኢየሩሳሌም የበራንጥያው ንጉሥ ፎቃ [Flavius Phocas Byzantine emperor ] ያደረሰባቸውን መከራ እና ጥፋት ያራቀላቸው ንጉሠ ሮም ሕርቃልን ምክንያት አድርገው ምዕመናነ ኢየሩሳሌም ስለጦሙት።

፫) የፋርስ ንጉሥ ቅስራ [Kessra the king of Persia] በግብፃውያን ላይ ያደረሰውን መከራ ለማቅለል ንጉሥ ሕርቃል ዘምቶ ድል ቢነሳላቸው ሊቀ ጳጳሳቱ አባ እንድራኒቆስ በአዋጅ ከአጽዋማቱ ገብቶ እንዲቆጠር አድርገውታል።

፬) ንጉሥ ሕርቃል ግዙራን መንግሥቴን ይወስዳሉ ብሎ ቢሰጋ አይሁድን ዘምቶ ለመውጋት መሐላውን ቢያፈርስ የሮም ሊቃነ ጳጳሳት ቀሳውስት ዲያቆናት ምእመናን አንድነት ጹመውለታል። …

የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ምዕላድ የሆነው መጽሐፈ ስንክሳር በመጋቢት ፲ ምንባብ ሥር ነገረ መስቀሉ የሚከብርባቸውን ሁለት ምክንያቶች እንዳሉ ይነግረናል። አንደኛ ዕፀ መስቀሉ በኢየሩሳሌም ተቆፍሮ የተገኘበት ሲኾን ኹለተኛው ደግሞ ዕፀ መስቀሉ በፋርስ ንጉሥ በምርኮ ከወረደበት በሮሙ ንጉሥ ሕርቃል አማካኝነት ወደ ቆስጠንጥንያ የተመለሰበት ነው ይለናል። በአርኬውም የመጨረሻ አንጓ ላይ
"… መስቀል ተረክበ እምዘተኀብዐ ወገብረ መድምመ
በኢየሩሳሌም ቅድመ ወበፋርስ ዳግመ።" ይላል።

ከምርኮ የተመለሰበትን መንገድ በሚተርከው ክፍል ጥንተ ነገሩ እንዲህ ተቀምጧል።

✧ በሮሜ ንጉሥ በሕርቃል ዘመን የፋርስ ሰዎች በግብጽ አገር በበላይነት ኖረው ወደ አገራቸው ሊመለሱ ወደዱ። ከሹማምንቶቻቸው አንዱ የጦር መኰንን ተነጥሎ ወደ ኢየሩሳሌም አልፎ ደረሰ ወደ ከበረ መስቀል ቤተ ክርስቲያንም ገባ። መስቀሉም በላዩ በተተከለበት ግንድ ፊት ታላቅ ብርሃን ሲበራ አይቶ ሊያነሣው እጁን ዘረጋ። እሳትም ወጥታ እጁን አቃጠለችው። ከክርስቲያን በቀር ማንም ሊነካው እንማይችል የመስቀልን የክብሩን ነገር ሰዎች ነገሩት። ሁለት ዲያቆናትንም ይዞ የከበረ መስቀልን እንዲሸከሙ አዘዛቸው። ከኢየሩሳሌምም ብዙ ሰዎችን ማርኮ ወደ አገሩ ተመለሰ። የፋርስ ሰዎች ኢየሩሳሌምን እንዳጠፏት ብዙዎች ሰዎችንም እንደማረኩና የከበረ የክርስቶስንም መስቀሉን እንደ ወሰዱ የሮም ንጉሥ ሕርቃል በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ። ስለርሱም #እንዲጾሙ_ምእመናንን_አዝዞ ወደ ፋርስ ዘምቶ ወጋቸው ብዙዎችንም ገደላቸው የከበረ ዕፀ መስቀልንም እየፈለገ በአገራቸው ሁሉ ዞረ ግን አላገኘውም። ያ ዲያቆናቱንና መስቀሉን የወሰደ መኰንን ከቦታዎች በቤቱ አንጻር ባለ በአንድ ቦታ ላይ ወስዷቸው ጥልቅ ጉድጓድ እንዲቆፍሩ አዝዞ በዚያ የከበረ መስቀልን አስቀበረ እነዚያንም ዲያቆናት ገደላቸው። ነገር ግን ያ መኰንን የማረካት የካህናት ወገን የሆነች በእርሱ ቤት የምትኖር አንዲት ብላቴና ነበረች። እርሷ የከበረ መስቀልን ሲያስቀብርና ሁለቱን ዲያቆናት ሲገድላቸው በቤቱ ውስጥ ሁና በመስኮት ትመለከት ነበር ወደ ንጉሥ ሕርቃልም ሒዳ መኰንኑ ያደረገውን ሁሉ ነገረችው። ይህንም ንጉሥ ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ያቺ ብላቴናም መራችው ከእርሱም ጋር ብዙ ሠራዊት ሁኖ ኤጲስቆጶሳትና ካህናትም ነበሩ። ወደ ቦታውም እስከምታደርሳቸው ያቺን ልጅ ተከተሏት ቆፍረውም የከበረ ዕፀ መስቀልን አገኙ ከዐዘቅቱም አወጡት ንጉሡና ሠራዊቱም ሰገዱለት። በልብስ መንግሥቱም አጐናጸፈው ታላቅ ክብርንም አከበረው ከሠራዊቱ ጋር እጅግም ደስ አለው ።

ይህንኑ በሚደግፍ ተወዳጁ ሊቅ የእስሙናዩ ቅዱስ ሳዊሮስ (Severus of El Ashmunein ﺳﺎﻭﻳﺮﺱ ﺍﻷﺷﻤﻮﻧﻴﻦ ‏) በድርሳኑ "ንሕነሰ ንጸውማ ንሥሓ በእንተ ሕርቃል ንጉሥ ሶበ ቀተሎሙ ለአይሁድ ወበልዐ ኪዳነ ዘተካየዶሙ ወዝንቱ ዕውቅ በዜና ሕርቃል ንጉሥ " ሲል ከነምክንያቱ አስረድቷል።

(እኛስ የምንጾመው ስለ ንጉሡ ሕርቃል ንስሐ ነው፤ አይሁድን በገደለ ጊዜ መኃላውን አፍርሷልና (ቃሉን በልቷልና) ይኽም በንጉሥ ሕርቃል ዜና የተነገረ ነው)

የመጽሐፈ ሕግ ወሥርዓት [ፍትሐ ነገሥት] ሐተታ ደግሞ መነሻው ከጥንት ሐዋርያት እንደሆነ በማውሳት ሌሎች እንደ ምክንያት የሚጠቀሱ ሁለት አጋዥ ታሪኮች አክሎ ያስቀምጥልናል።

በማከልም ከዐቢይ ጾምና ከረቡዕ ዓርብ (ጾመ ድኅነት) ውጪ የተጨመሩት አጽዋማት መነሻቸው የግብፃውያን ቀኖና እንደሆነም ፍትሐ ነገሥቱ ይጠቁማል።

«ወአጽዋምሰ አካልዓን እለ ተወስኩ ላዕለ ዝንቱ ወተሠርዑ በቤተ ክርስቲያን ቅብጣዊት። ወእምኔሆሙ ዘይከውን በአምሳለ ጾም ዐባይ በተጠናቅቆ። ወይእቲ ስሙነ ሕርቃል ዘትከውን እምቅድመ ፆም ዐቢይ»

(በዚህ ላይ የተጨመሩ ሌሎች ጾሞች ግን በግብፃውያኑ ቤተክርስቲያን የተሠሩ ናቸው፤ ከእነርሱም እንደ ዐቢይ ጾም በመጠንቀቅ የሚሆን አለ። ይህችውም ከዐቢይ ጾም ቀድማ የምትሆን የሕርቃል ጾም ናት)

በተለየ የሕርቃልን ጾም ሲያብራራ ደግሞ
⇨ ይህችውም ከዓቢይ ጾም አስቀድማ የምትሆን ስሙን ህርቃል ናት መገለጫውን ሲያይ ነው እንጂ የጾሙትስ ሐዋርያት ናቸው ሕልሙን ያየ ናቡደነፆር ሲሆን “ራእየ ዳንኤል” እንዲል

26 Feb, 19:12
480