ፍኖተ አብን @namavoice Channel on Telegram

ፍኖተ አብን

@namavoice


ይህ ቻናል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ወቅታዊና ስትራቴጂካዊ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቋሞች ለአባላት፣ ደጋፊዎችና ምልዓተ ሕዝቡ የሚቀርቡበት የቴሌግራም አማራጭ ነው።

ፍኖተ አብን (Amharic)

ፍኖተ አብን በቴሌግራም አማራጭ እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ወቅታዊ, ስትራቴጂካዊ, ፖለቲካዊ, ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቋሞች ለአባላት፣ ደጋፊዎችና ምልዓተ ሕዝቡ አለ። ይህ አማራጭ ታናሎውን የሚሰጥ መረጃውን በቴሌግራም ቢሮ እና ፈተና እንዲሰጡበት እንደሚመለከት፣ ለቴሌግራም አማራጭ አብን እንዲያሰራጭ የሚለውን መረጃና ትክክለኛ መረጃ በማድረግ እና በመረጡ፣ አዝናኝ አማራጭ እንደሚመልከት መለራመድ እንደሚገኝ ይህን አማራጭ በጣም እንድናገር አስተያየት ይሆናል።

ፍኖተ አብን

09 Aug, 06:26


The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 20 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.

ፍኖተ አብን

17 Oct, 18:43


ለመላው የአማራ ሕዝብ ፣
ለንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊዎች ፣
ለመላው አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን፣

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) አስቸኳይ የኅልውና ማረጋገጫ ሕዝባዊ ጥሪ፣

የአማራና የኢትዮጵያ ደመኛ ጠላት የሆነው የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር(ትሕነግ) ከሐምሌ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የከፈተብንን መጠነ ሰፊ ወረራ ለመመከትና የአገራችንንና የሕዝባችንን ኅልውና ለመታደግ መላው የአማራ ሕዝብ ከአገር መከላከያ ሰራዊትና ከአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን እየተፋለመ ይገኛል፡፡

አሸባሪው የትሕነግ ሰራዊት በእብሪት በለኮሰው የተስፋፊነት ጦርነት በሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ በሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ በዋግኽምራና በአፋር በሕዝባችን ላይ በሕይወት፣ በአካልና በንብረት እጅግ አሰቃቂ የሆነ ግፍና ጉዳት አድርሷል፡፡

ዛሬም በኃይል በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ግልፅ የዘር ማጥፋት፣ የአስገድዶ መድፈር፣ የዝርፊያና የጅምላ ውድመት እያደረሰ ይገኛል፡፡

የአማራ ሕዝብ የክልሉ መንግስት ሐምሌ 18 ቀን 2013 ዓ.ም ያወጀውን የኅልውና ዘመቻ የክተት ጥሪ ተከትሎ ባደረገው ኹለገብ ፍልሚያ የጠላት ጦር እጅግ ከፍተኛ የሰራዊትና የቁስ ኪሳራ እንዲደርስበት በማድረግ ግስጋሴውን ለመግታት ችሏል፡፡ በዚህ ሕዝባዊ ተጋድሎው የትሕነግን ሕዝባችን በኃይል አንበርክኮ አገር ለማፍረስ የነበረውን ህልም እስከ ወዲያኛው አክሽፎበታል፡፡

ይሁን እንጂ የአገር መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ኃይሎች በጠላት ላይ ያገኙትን ወታደራዊ ብልጫ በማጠናከር አስተማማኝ ወደ ሆነ ድል ለመለወጥ በመንግሥት በኩል የታየው ከልክ ያለፈ ዳተኝነት እንዲሁም የአመራር ክፍተት በሕዝባችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለ ከመሆኑም በላይ የመከዳት ስሜት ፈጥሮበት ይገኛል፡፡

የጥቅምት 24-2013 ዓ.ም የትሕነግ የክህደት ጥቃትን ተከትሎ ለስምንት ወራት ከተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ዛሬም ወራሪው ኃይል ዳግም እንዲያንሰራራ እድል ማግኘቱን አስተውለናል። በዚህ ረገድ በወገን ኃይል በኩል ባለው አሰላለፍና ስልት ረገድ የተሻሻለ ነገር ባለመታየቱ፣ ተስፋ ቆርጦ የነበረው ወራሪ ጦር የልብ ልብ አግኝቷል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በተለይ በደቡብና በሰሜን ወሎ ግንባሮች የሚስተዋሉ የአመራር ክፍተቶችንና ደካማ ጎኖችን በመጠቀም ደሴና ከምቦልቻን ጨምሮ አካባቢውን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

የተከበርከው የአማራ ሕዝብ ሆይ!

ግንባር ቀደም የወረራው ገፈት ቀማሽ የሆንከው አንተ ነህ፤ ጦርነቱም በዋነኝነት የራስህ መሆኑን ለአፍታ እንኳ መዘንጋት የለብህም፡፡ እስካሁንም ጉዳዩ በአገራዊ ማእቀፍ ተይዟል በሚል ማናቸውንም እገዛ ስትጠብቅ ቆይተሀል፡፡ ከእንግዲህ ወገኖችህ በአረመኔው የትሕነግ ጦር ለጅምላ ሞትና ስቃይ ተዳርገው ፣ ሚሊዮኖች በስደት ለረሃብና እርዛት ተጋልጠው ባለበት ሁኔታ ተጨማሪ መዘናጋት ካሳየህ ውርደቱ ለልጅና ለልጅ ልጆችህ የሚተርፍ ይሆናል፡፡

ስለሆነም አማራ ነኝ የምትል ሁሉ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ ትሕነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ ቆርጠህ ተነሳ። መዋጋት የምትችል ሁሉ ወደ ጦር ግንባር ዘምተህ ወራሪውን የጠላት ኃይል በመተናነቅ ታላቅ የነፃነት ታሪክ አካል የመሆን አደራ ወድቆብሀል፡፡ በተለያዩ አሳማኝ ምክንያቶች ውጊያ መግባት የማትችል ደግሞ በደጀንነት ሐብትህን፣ ንብረትህን፣ ጉልበትህን፣ እውቀትህን ለወራሪው የጠላት ኃይል አሳልፈህ የዘረፋ ግብዓት ከማድረግህ በፊት ለወገንህ መድኅንነት ያለስስት አውለው፡፡

አብን በተለይ በአሁኑ ሰዓት በወሎ በኩል አጠቃላይ ለዘረፋ፣ ለውድመትና ለጭፍጨፋ ያሰፈሰፈውን የጠላት ኃይል ቅስም ለመስበር የሚያስችል ሙሉ የመከላከል ሥምሪት መወሰድ አለበት በሚል ሕዝባችን ማናቸውንም የአዘቦት ሥራና የትምህርት እንቅስቃሴዎች ከወድሁ በማቆም በሙሉ ኃይሉ ወረራውን ለመቀልበስ እንዲረባረብ ጥሪ ያደርጋል፡፡

አብን በሌሎቹም የአማራ አካባቢዎች ወራሪው ኃይል ጥቃት በከፈተባቸው ግንባሮች ሕዝባችን ለአፍታ ሳይዘናጋ ከአገር መከላከያ ሰራዊትና ከአማራ ኃይሎች ጋር በንቃት ተባብሮ በመቆም በወራሪው ላይ የማያዳግም ርምጃ እንዲወስድና አካባቢውን ከአሸባሪው ርዝራዦች ፍፁም እንዲያፀዳ ጥሪ ያደርጋል፡፡

መንግስት በፍላጎት፣ በውሳኔ ሰጭነት፣ በትጥቅና ስንቅ አቅርቦት እንዲሁም በማስተባበር ረገድ የታዩበትን ጉልህ ክፍተቶች በማረም፣ በማስተካከል፣ በብቃትና በቁርጠኝነት በመሰለፍ፣ ሕዝብንና አገርን ከጥፋት ለመታደግ የሚያስችሉ ጠንካራና ፈጣን ርምጃዎችን ወስዶ የተጣለበትን ኃላፊነት እንዲያረጋግጥ በአፅንኦት እናሳስባለን።

በዚህ ረገድ በአንድ በኩል ያለው ነባራዊ ሁኔታ፣ በተለይም እስካሁን በቀጠለው ወረራ ምክንያት የደረሱት በርካታ ቁሳዊና ሰብዓዊ ውድመቶች እንዲሁም የተፈጠረውን ሰፊ ማኅበራዊ ምስቅልቅል፣ በሌላ በኩል ወረራውን ለመከላከልና ለመቀልበስ የተደረጉ መንግስታዊ ጥረቶችን ሚዛን ላይ በማስቀመጥ የሚፈጥሩትን ማኅበራዊና ፖለቲካዊ አንድምታዎች ማስተባበል አዳጋች እንደሚሆን ለመጠቆም እንወዳለን።

በጦርነት ውስጥ ያሉ ታሳቢዎች፣ እቅዶችና የዘመቻ ሥምሪቶች በአብዛኛው በወታደራዊ ምስጢርነት በጥብቅ ተይዘው የሚተገበሩ ጉዳዬች መሆናቸው አይሳትም። ከዚህ አኳያ በዘመቻ አመራርና በግንባር አወሳሰን ረገድ የስትራቴጂ ቅደም ተከተል እንደሚኖር ግምት ይወሰዳል። ነገር ግን በሰፊ ቀጠናዎች የሚኖረውን ትልቅ ማኅበረሰብ ለተከታታይና ላልተቋረጠ ወረራ ተጋላጭ የሚያደርግ እቅድና አመራር ማኅበረሰብን ከስሌት ውጭ ያደረገ በመሆኑ ስሁት ከመሆን አያልፍም።

የአማራ ክልል መንግሥት የተጀመረውን የዘመቻ ኅልውና ሂደት ከመቼውም ጊዜ በላቀ መልኩ በማጠናከር ፣ አሸባሪውን የትሕነግ ሠራዊት በአጭር ጊዜ ከሕዝባችን ላይ ለማስወገድ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ይጠይቃል፡፡

የፌዴራል መንግሥቱም ከእንግዲህ የሕዝብ ሰቆቃ ሞልቶ እንደፈሰሰ በውል እንዲገነዘብ፣ ከእንግዲህ ሕዝብን ለጥቃት፣ አገርን ለውርደትና ለመበታተን የሚዳርግ ማናቸውንም አይነት አካሄድ በአስቸኳይ በማረም የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲፈፅም ንቅናቄያችን ይጠይቃል፡፡

አብን ትሕነግን ለማስወገድ የሚደረገውን ማናቸውም አገራዊና ክልላዊ ጥረት በሙሉ ልብ ያለማመንታት እንደሚደግፍ እየገለፀ፣ በዚህ የመጨረሻው ምሽግ ፍልሚያ ላይ መላው የድርጅቱ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ደጋፊዎች በግንባር ቀደምትነት እንዲሰለፉ ታሪካዊና ትውልዳዊ ጥሪ ያስተላልፋል፡፡ አፈፃፀሙን በተመለከተ ከወድሁ የእቅድና የተግባራዊ ስምሪት መመሪያዎችን የሚያስተላልፍ ይሆናል።


ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር!

ጥቅምት 7 ቀን 2014 ዓ.ም

አዲስ አበባ ፣ ሸዋ ፣ ኢትዮጵያ!

ፍኖተ አብን

02 Jun, 14:11


የዛሬ ምሽት የሚዲያ ጥቆማ!

ዛሬ ምሽት ከ1:30 ጀምሮ በዋልታ ቴቪ "ከተሜነት እና መሰረተ ልማት" በሚል ርዕሠጉዳይ የንቅናቄአችን ምክትል ሊቀመንበር አቶ የሱፍ ኢብራሂም የሚከራከሩ ሲሆን፣ ምሽት ከ3: 20 ጀምሮ በፋና ቴቪ "የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ" ላይ አቶ ጣሂር ሙሃመድ የንቅናቄአችን ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ይከራከራሉ። እንዳያመልጥዎ!

#ምልክታችን ሠአት ነው።
#ሠአትን ይምረጡ!

#ጊዜው አሁን ነው!

ፍኖተ አብን

29 May, 16:41


ለሁሉም የድርጅታችን ፌስቡክ ተከታዮች:-
ይህ ከዚህ በታች የተቀመጠው link የድርጅታችን አዲስ የፌስቡክ ገፅ መግቢያ መሆኑን እያሳወቅን እንዲከተሉት በአክብሮት እንጠይቃለን።
https://m.facebook.com/National-Movement-of-Amhara-107657784698238/

ለሶስት ዓመታት ስንጠቀመው የነበረው ዋናው ገፃችን (አሁን ያላችሁበት) ከእንግዲህ ለረጅም ግዜ መጠቀም የማንችልበት የደህንነት ሁኔታ ስለገጠመን በሙሉ እስክንወጣ ድረስ ተከታዮቻችን አዲሱን ገፅ እንዲከተሉ ስንል ከምስጋና ጋር እናሳውቃለን።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፦

1. ፋና ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር «በአካል ጉዳተኞች መብቶች» ዙሪያ ባዘጋጀው የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክ ላይ አብንን በመወከል የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጣሂር ሙሐመድ ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተከራክረዋል፡፡

ይኼ የክርክር ፕሮግራም ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡00 ጀምሮ በፋና ቴሌቪዥን ስለሚተላለፍ እንድትከታተሉት እንጋብዛለን።

#ጊዜው አሁን ነው!

የአብን የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ሰዓት ነው፤ #ሰዓትን_ይምረጡ!

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!

ፍኖተ አብን

29 May, 15:37


ለሁሉም የድርጅታችን ፌስቡክ ተከታዮች:-
ይህ ከዚህ በታች የተቀመጠው link የድርጅታችን አዲስ የፌስቡክ ገፅ መግቢያ መሆኑን እያሳወቅን እንዲከተሉት በአክብሮት እንጠይቃለን።
https://m.facebook.com/National-Movement-of-Amhara-107657784698238/

ለሶስት ዓመታት ስንጠቀመው የነበረው ዋናው ገፃችን (አሁን ያላችሁበት) ከእንግዲህ ለረጅም ግዜ መጠቀም የማንችልበት የደህንነት ሁኔታ ስለገጠመን በሙሉ እስክንወጣ ድረስ ተከታዮቻችን አዲሱን ገፅ እንዲከተሉ ስንል ከምስጋና ጋር እናሳውቃለን።

ይህ በእንዲህ እንዳለ:-

1) ድርጅታችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን ነገ
እሁድ ግንቦት 22 ቀን 2013 ዓ.ም በደብረ ብርሃን ከተማ አፄ ዘራዓ ያቆብ አደባባይ ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የንቅናቄው አመራሮች በተገኙበት የድጋፍ ሰልፍና የምረጡኝ ቅስቀሳ ያካሂዳል።

2) በተመሳሳይ አብን በቡሬ ከተማ ቡሬ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እና በጢስ አባይ ከተማ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ ሕዝባዊ ውይይት ያካሂዳል።

ሰለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ የንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊዎች በድጋፍ ሰልፉና በሕዝባዊ ውይይቱ ላይ እንድትሳተፉ አብን ጥሪውን ያቀርባል።

#ጊዜው አሁን ነው!
የአብን የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ሰዓት ነው፤ #ሰዓትን_ይምረጡ!

https://t.me/NaMAVoice

ፍኖተ አብን

24 May, 16:50


«የደሴና አካባቢው ሕዝብ ችግሩን የተረዱና ለችግሩ መፍትሔ የያዙ አብን በእጩነት ያቀረባቸውን ኃቀኛ ልጆቹን ሊመርጥ ይገባል!»
~በለጠ ሞላ

«አብን የደሴና አካባቢው ሕዝብ የሚሰጠውን አደራ በብቃት ለመወጣት ዝግጁ ነው!»
~የሱፍ ኢብራሒም
**
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ቀጣይ በሚደረገው የመጀመሪያው አማራዊ ምርጫ አሸናፊ ለመሆን «ጊዜው አሁን ነው!» በሚል መሪ ኃሳብ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚያካሂደውን የምረጡኝ ቅስቀሳ በመቀጠል ትላንት ግንቦት 15 ቀን 2013 ዓ.ም በደሴ ወሎ ባሕል አምባ አዳራሽ የአብን ሊቀመንበር በለጠ ሞላና የንቅናቄው ም/ሊቀመንበር እና የደሴ ምርጫ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የአብን እጩ ተወዳዳሪ የሱፍ ኢብራሒም በተገኙበት ከደሴና አካባቢው ሕዝብ ጋር ደማቅ ውይይት አድርጓል።

በሕዝባዊ ውይይቱ የደሴና አካባቢውን ሕዝብ የሚመለከቱ እና የአማራ ሕዝብ ትግል በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ የሚመራባቸውን ስትራቴጅክ ምልከታዎች እና የአብን አማራጭ የፖሊሲ ኃሳቦች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የደሴና አካባቢው ሕዝብ በመልማት ጸጋው ልክ ያለማ ታታሪና ሥራ ወዳድ ሕዝብ መሆኑን የገለጽት የአብን ሊቀመንበር በለጠ ሞላ በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ ይሄን መዋቅራዊ ችግር በማስወገድ ደሴን ታሪኳንና ስሟን በሚመጥን መልኩ ለማልማት አብን የያዛቸውን አማራጭ ኃሳቦች አብራርተዋል።

ሊቀመንበሩ አክለውም አብን በአማራ ሕዝብ ትግልና በኢትዬጵያ ፖለቲካ ውስጥ ግንባር ቀደም ከሆኑ የፖለቲካ ፖርቲዎች አንዱ መሆኑን በማስታወስ ለዚህ ስኬታማነት አሁን በደሴ በእጩነት የቀረቡት አቶ የሱፍ ኢብራሂም ከፍተኛ ሚና አንዳላቸው ገልፀዋል። ታሪካዊቷ የደሴ ከተማ ሕዝብ አቶ የሱፍ ኢብራሂምን እና የደሴና አካባቢውን ሕዝብ ችግር የተረዱና ለችግሩ መፍትሔ የያዙ አብን በእጩነት ያቀረባቸውን ኃቀኛ ልጆቹን በመምረጥ ለአማራ ብሎም ለኢትዬጵያ ሕዝብ የፍትኅ፣ የዴሞክራሲና የእኩልነት ትግል ጉልህ እገዛ እንዲያደርግ አቶ በለጠ ጠይቀዋል።

አብን የደሴ ከተማ አሁን ያለችበት አጠቃላይ ሁኔታ ታሪኳን የማይመጥን መሆኑን በማስታወስ የባለቤትነት ስሜት ያለው ወይም አቅም ያለው አመራር እንዴሌላት አመላካች የሆኑ ገፅታዎችን በማንሳት አብን ከተመረጠ የሚያከናውናቸውን ስራዎች ያብራሩት የአብን ምክትል ሊቀመንበርና የደሴ ምርጫ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የአብን እጩ ተወዳዳሪ አቶ የሱፍ ኢብራሒም ደሴ የምትለወጥበትና የልማት ማዕከል የምትሆንበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል።

ኃላፊዎቹ አክለውም የደሴ ከተማ ሕዝብ በሚመጥነውና በሚጠበቅበት ደረጃ የፖለቲካ ተሳትፎ ማድረግ እንዳይችል እና ለዘመናት በፍቅር አብሮ የኖረውን፣ የአንድ ቤተሰብ አካል የሆነውን ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን የሕብረተሰብ ክፍል በመከፋፈል ለመናኛ አጀንዳቸው ማዋል የሚፈልጉ፣ ኃላፊነት የጎደላቸው አካላትን በመረጃና በእውቀት ላይ የተመሰረተ አቋም በመውሰድ እንዲያከሽፋቸው የጠየቁት አቶ የሱፍ አብን የደሴና አካባቢው ሕዝብ የሚሰጠውን አደራ በብቃት ለመወጣት ዝግጁ ነው ብለዋል።

በሕዝባዊ በውይይቱ የተሳተፉ የኅብረተሰብ ክፍሎችም በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ በአማራ ሕዝብ ስም ስልጣን ይዘው አውቀቱ፣ ፍላጎቱና ቁርጠኝነቱ የሌላቸውን በድምጻቸው ለመቅጣትና በምትኩ የሕዝቡ ጥያቄዎች ለመመለስ ትክክለኛውን አመራር ለመስጠት ፍላጎትና ብቃት ያለው አብንን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

#በምርጫ ካርድዎ የመዋቅርና ሕግ ሰራሽ ችግሮችን ሰንኮፍ ነቅሎ ዲሞክራሲን ማስፈኛ ጊዜው አሁን ነው!

የአብን የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ሰዓት ነው፤ #ሰዓትን_ይምረጡ!