Dernières publications de M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel. (@mtu_main_campus) sur Telegram

Publications du canal M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.
This is the Telegram channel of Mizan Tepi University Students Union
For any comment
@Sablaw
@MTU13bot
@SeudEmpire
for Discussion
@mizan_tepi_university
Ads: https://telega.io/c/MTU_Students_Union_Channel.
4,807 abonnés
2,571 photos
11 vidéos
Dernière mise à jour 06.03.2025 05:29

Le dernier contenu partagé par M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel. sur Telegram

M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

27 Feb, 19:08

1,410

በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት በ5ኛ እና 4ኛ አመት ተማሪዎች መካከል የምስለ ችሎት ውድድር  (Inter batch Moot Court Competition ) ዛሬ ተካሄደ ።
***
    ሚቴዩ ፣የካቲት 20/2017 ዓ.ም

ለተከታታይ ቀናት የማጣሪያ ውድድር ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ለፍጻሜ በቀረቡት ሁለት ቡድኖች መካከል በወቅታዊ የአገራችን የወደብ ጥያቄ  ዙሪያ በማተኮር አለም አቀፍ ድንጋጌዎችን መሠረት ያደረገ እጅግ ማራኪና አስተማሪ በአጠቃላይ ታዳሚውን ያስደመመ ውድድር (ክርክር) ተደርጓል።

ምስለ ችሎቱን የዩኒቨርሲቲው ህግ ትምህርት ቤት አንጋፋ መምህራን(ዳኞች) የሆኑት በመሐል ዳኛነት ዳኛ ጌታሁን ተሾመ ጨምሮ ዳኛ ምንዳ ግርማ ፣መዝገቡ አቢይ፣እውነቱ ተስፋዬ እና ዳኛ ተግባሩ ተረፈ ክርክሩን በስርዓት የመሩት ሲሆን ምስለችሎቱን የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳት ዶ/ር ተረፈ ጌታቸው ፣ የአካዳሚክ ዳይሬክተር የሆኑት ጥምቀቴ አለሜ (ረ/ፕ)፣ መምህራን እንዲሁም ተማሪዎች እስከፍጻሜው ተከታትለውታል።

እንደህግ ትምህርት ቤቱ ዲን መምህርት ሮዚና መኮንን ገለጻ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ጊዜያት በአገር አቀፍ ደረጃ በሚደረጉ ውድድሮች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ዝና ያለውና በተለያዩ ጊዜያት የዋንጫ ተሸላሚ ስለመሆኑ ጠቁመው ፤የዛሬው ውድድር  ዋና አላማ በቅርቡ በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ  አዘጋጅነት አገር አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር ላይ ዩኒቨርሲቲያቸውን የሚወክሉ ተማሪዎችን ለመምረጥ ስለመሆኑም ተናግረዋል።

በዛሬው ውድድር  አሸናፊ ለሆነው የአምስተኛ አመት ተማሪዎች እንዲሁም በተለያዩ የውድድሩ መስፈርቶች ለተመረጡ ተማሪዎች የእውቅና የምስክር ወረቀት ከዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት እጅ  የተቀበሉ ሲሆን በፍጻሜው ውድድር በbest ora list 1ኛ ተማሪ ፋሲል ዘለቀ እንዲሁም ከሴቶች female best ora list በመሆን ደግሞ ተማሪ ቅድስት ዘራአንበሳ አሸናፊ ሆነዋል።

በመጨረሻም ዶክተር ተረፈ ጌታቸው ባደረጉት የማጠቃለያ ንግግር የምስለ ችሎት (Moot court) ውድድር ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል ፤ ከዚህም በዋናነት ተማሪዎች ከአቻዎቻቸው ጥሩ ልምድ እንዲቀስሙ ከማስቻሉም በላይ የሚገኙበትን ተቋም በማስተውወቅ በኩል ትልቅ ጥቅም እንደሚሰጥ በንግግራቸው አስረድተው ይህ ፕሮግራም በዚህ መልኩ እንዲሳካ ለሰሩ የኮሌጁ መምህራን  የተሰማቸውን አድናቆት  በመግለጽ አመስግነዋል።

Mizan-Tepi University
Light of the green Valley!
facebook :https://www.facebook.com/p/Mizan-Tepi-University-MTU-100067612844902/
website: www.mtu.edu.et
telegram: https://t.me/mtueduet
Email: [email protected]

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/MTU_Main_Campus
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

21 Feb, 10:41

1,390

በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ የተገነባው የህጻናት ማቆያ ማዕከል ዛሬ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ማቴዩ ፣ የካቲት 13/2017

በ420 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው የመኝታ ፣ የመመገቢያ ፣ የመጫወቻና መጸዳጃ ክፍሎች ያሉት ይህ የህጻናት ማቆያ የምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ኤልሳ ከበደ ለፕሮግራሙ ታዳሚዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የግንባታውን ሂደት አሰመልክተውም አጭሪ ሪፓርት አቅርበዋል።

የማዕከሉ ግንባታ በተለያዩ ምክንያቶች መዘግየቱን የጠቆሙት ወ/ሮ ኤልሳ ከበደ እነሆ ዛሬ ለምረቃ በመብቃቱ እጅግ መደሰታቸውን ገልጸው ለስራው መሳካት በተለያየ መንገድ የድርሻቸውን ለተወጡ የዩኒቨርስቲው የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች ፤ የስራ ክፍሎችና ግለሰቦችን ያመሰገኑ ሲሆን በተለይ በቅርብ የመጣውም አመራር ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ለዚህ ደረጃ እንዲበቃ ማድረጉንም አድንቀዋል።

የማዕከሉ ስራ መጀመር ለሴት ሰራተኞቻችን ትልቅ እፎይታን እንደሚሰጥ ገልጸው ማዕከሉ ለጊዜው 30 ህጻናትን በእድሜ ደረጃ በመክፈል ተቀብሎ እንደሚያስተናግድ ተደርጎ ስለመሰራቱም ጠቁመው በዋናነት ማቆያው ሴት የመንግስት ሰራተኞች ልጆቻቸውን ለማሳደግ ሲሉ ስራ ለቀው የኢኮኖሚ ጥገኛ እንዳይሆኑና እንደሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ሴት መምህራን ከዚህ በፊት አገልግሎቱ በተቋሙ ባለመኖሩ የተሻለ አገልግሎት በመሻት ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ለቀው ይሄዱ እንደነበር ገልጸው በመጠኑም ቢሆን የማዕከሉ ስራ መጀመር በዚህ ረገድ የሚስተዋለውን የመምህራን ፍልሰት ይቀንሳልም ብለዋል ።

ዶክተር ግርማ ጥላሁን የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ተወካይ እና የዩኒቨርስቲው ጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ባስተላለፉት መልዕክት የዛሬው ህንጻ ለአገልግሎት ተመርቆ በመዘጋጀቱ እንኳን ደስ አላችሁ ብለው ፤ ተመሳሳይ የህጻናት ማቆያ ማዕከላትም በቀሪዎቹ ግቢዎቻችን በተቻለ ፍጥነት ተከፍተው አገልግሎት መስጠት እንደሚገባቸው ገልጸው ፤ የማዕከላት መኖር ፋይዳቸውን በተመለከተ ሰራተኞች በተሰማሩበት ልዩ ልዩ ሙያዎች ውጤታማ እንዲሆኑም የሚኖረውንም ሚና ከፍተኛ ስለመሆኑ በአጽንኦት ገልጸዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም ማህበረሰብን ባለን አቅም ማገልገልና መጥቀም ከዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ጀምሮ መሆን እንዳለበት ተናግረው የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የእቅዱ አካል በማድረግ በትኩረት መንቀሳቀስ እንደሚገባውም አሳስበዋል።

በማቆያ ማዕከሉ አገልግሎቱን የሚሰጡ 5 ሞግዚቶች ፤ አንድ ነርስ እንዲሁም የጽዳት ስራ የሚያከናውኑ ሰራተኞች ፤ በተጨማሪ የህጻናት መኝታና መጫወቻ አሻንጉሊቶች የተሟሉ ስለመሆኑም በምረቃው ስነስርዓት ተገልጿል።

በመጨረሻም የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ተወካይና የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ግርማ ጥላሁን ፤ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ብሩክ ገ/ጻዲቅና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ማዕከሉን መርቀው ከፍተዋል።
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

13 Feb, 17:41

1,548

#ExitExamResult

" የፈተናው ውጤት ተለቆ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል " - የትምህርት ሚኒስቴር አመራር

🔴" የፈተና ውጤት ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ጋር መጥቷል " -  የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት

የሀገር አቀፍ መውጫ ፈተና ውጤት ለዩኒቨርሲቲዎች መላኩን የትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት አጭር ቃል ፥ " ፈተናው ተለቆ ለዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል " ብለዋል።

" በነገራችን ላይ ለዩኒቨርሲቲዎች ነው የሚላከው ሊንኩም ይላክላቸዋል። ውጤት ሁሉም ዩኒቨርሲቲ ጋር ደርሷል " ሲሉ ገልጸዋል።

ምን ያክል ተማሪ አለፈ ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ " ውጤቱ አሁን ስለተለቀቀና ለተቋማት ስለተላከ አጠቃላይ ዳታውን የምናየው ነገ ነው " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት ቡኩሉ፣  " ውጤቱ ተለቋል። የሁሉም ዩኒቨርሲቲ መጥቷል " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ውጤት መመልከቻ ሊንኩ ደርሷችኋል ? ስንል ላቀረብንለት ጥያቄ በሰጠን ምላሽ ደግሞ፣ " ዝም ብሎ ውጤቱ ነው የመጣው " የሚል አጭር ምላሽ ሰጥቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የፈተናው ውጤት በኦንላይ የሚታይበት መንገድ ካላ ጠይቆ ያቀርባል።
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

13 Feb, 11:13

1,780

#Exit_Exam_Result

ሀገር አቀፍ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ተለቋል።

https//:result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ExitExam የሚለውን በመምረጥና የራስዎን User Name በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ይችላሉ።

በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም መሠጠቱ ይታወቃል።
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

13 Feb, 10:07

1,774

Exit exam result ዛሬ ይለቀቃል
መልካም ያሰማን።

የተማሪዎች ህብረት
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

13 Feb, 05:30

1,660

ተማሪዎች በአመቱ መጨረሻ በሚሰጠው የመውጫ ፈተና የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችሉ በዩኒቨርሲቲው በየደረጃው የተዋቀረው ግብረ ሀይል (Task force ) ሀላፊነቱን በአግባቡ መወጣት እንዳለበት ተገለጸ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሚቴዩ ፣የካቲት 5/2017
ዛሬ ተማሪዎች እንዳሁም ከትምህርት ክፍል ጀምሮ የተዋቀረው ግብረ ሀይል አባላት በተገኙበት በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም ስለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን የውይይቱ አላማ ተማሪዎች አስፈላጊውን የህሊና ዝግጅት እንዲያደርጉና ያላቸውን ጊዜ በቅርበት ከመምህራኖቻቸው ጋር በመስራት መጠቀም እንዲችሉ ለማሳሰብና በራስ የመተማመን ስሜት ከወዲሁ እንዲያዳብሩ ሲሆን በውይይቱ ላይ ከትምህርት ክፍል ጀምሮ የተደራጀው ግብረ ሀይ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት በጠራው ውይይት ተገኝቷል።

በውይይቱ መምህራን ተማሪዎቻቸው በፈተናው አመርቂ ውጤት እንዲያመጡ የሚያስችላቸውን ዝግጅትና ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ተማሪዎች ገልጸው ፤ አሁን ላይ የመመረቂያ ጊዜያቸው መቃረቡን ተከትሎ ለፈተናው ከሚያደርጉት ዝግጅት በተጨማሪ የመመረቂያ ጽሁፍ የሚያዘጋጁበት ወቅትም እንደመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የጊዜ መጣበብ ስለመኖሩም ጠቁመው ያላቸውን ጊዜ ከመምህራኖቻቸው ጋር በመቀራረብ መልካም የሆነ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ዶክተር ተረፈ ጌታቸው የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት በበኩላቸው ተማሪዎችን የማብቃት ጉዳይ ዋና ትኩረት የሚሰጠው ስለመሆኑ ተናግረው ብቁና ኩረጃን የሚጸየፍ ተማሪ ከማፍራት አኳያ ተማሪዎች በሚማሩት ትምህርት በየጊዜው ከመምህራኖቻቸው ጋር ስላደረጉት ውይይት የመከታተያ ፎርማት የተዘጋጀ መሆኑንና ግብረ ሀይሉም የተሰጠውን ሃላፊነት መወጣት እንዳለበት አሳስበው በሳምት 3 ጊዜ በትምህርት ክፍል 2 ጊዜ በኮሌጅ እንዲሁም በሳምንት አንድ ጊዜ ከፍተኛ አመራሩ ክትትልና ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመው ፤ ተማሪዎች በአመቱ መጨረሻ በሚሰጠው የመውጫ ፈተና የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችሉ በየደረጃው የተዋቀረው ግብረ ሀይል (Task force ) ይህን ሀላፊነቱን በአግባቡ መወጣት እንዳለበትም ገልጸዋል ።

በትምህርት ዘመኑ ማብቂያ ከሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀው የሚወጡ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች አገር አቀፉን የመውጫ ፈተና ከሰኔ 2-- 10/2017 ዓ.ም እንደሚፈተኑ ታውቋል።
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

12 Feb, 21:33

1,702

Congratulations!
Mizan-Tepi University students graduation Ceremony will take place colorfully on Saturday February15, 2025 in the main Campus .

እንኳን ደስ አላችሁ !
የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ በዓል ቅዳሜ የካቲት 8/2017 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል።
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

12 Feb, 12:55

1,855

For all 2017 Graduate Class Students.


The place for meeting was changed from central library to Graduation Hall, every GC Students must participate on the meeting.

Being on time.

Mizan Tepi University Students Union.
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

11 Feb, 19:41

2,002

ማስታወቂያ

ለተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ

ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የ2017 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች!!

"ምን ቢቃጠሩ ደረሰ ቀኑ"  እንዲሉ። አመታት አልፈው ጥቂት ወራት ቀርቶታል። ታድያ የExit Exam ዝግጅት ምን ይመስላል?

እንደ አጠቃላይ ስለ መውጫ ፈተና(Exit Exam) ዝግጅትን በተመለከተ የዩንቨርስቲያችን ከፍተኛ አመራሮች በሚገኙበት በነገው እለት ማለትም በቀን 05/06/2017 ከቀኑ 10፡00 ስዓት ጀምሮ በCentral Library ከሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች ጋር ወይይት ይኖራል። ስለሆነ ሁሉም የጊቢያችን ተመራቂ  ተማሪዎች  በሰአቱ ተገኝታችሁ የውይይቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ  እናሳስባለን።

  የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት።
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

11 Feb, 08:16

2,436

ማስታወቂያ

ለሪሚያል ተማሪዎች በሙሉ

የአንደኛ ተርም የትምህርት ጊዜ የተጠናቀቀ ስለሆነ ለእረፍት ወደ ቤተሰብ መሄድ የምትፈልጉ ተማሪዎች መሄድ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ሁለተኛው ተርም ትምህርት የሚጀምርበት ጊዜን በተመለከተ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

For further information
👉@sablaw

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት