Dernières publications de M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel. (@mtu_main_campus) sur Telegram

Publications du canal M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.
This is the Telegram channel of Mizan Tepi University Students Union
For any comment
@Sablaw
@MTU13bot
@SeudEmpire
for Discussion
@mizan_tepi_university
Ads: https://telega.io/c/MTU_Students_Union_Channel.
4,807 abonnés
2,571 photos
11 vidéos
Dernière mise à jour 06.03.2025 05:29

Canaux similaires

Ethio jops
2,168 abonnés
Ethiojobs ️️
1,698 abonnés

Le dernier contenu partagé par M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel. sur Telegram

M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

05 Mar, 23:45

270

የኢትዮጵያ ጦር የሶማሊያን ጦር በማሸነፍ ካራማራ ተራራ ላይ ደማቅ ታሪክ የፃፈበት 47ኛ ዓመት!

እንኳን ለድሉ መታሰቢያ በዓል አደረሰን🇪🇹


ልክ የዛሬ 47 ዓመት ሀገር ጠርታው ተኝቶ የማያድረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳር ዳር ተሰማማ። የተከበረች ሀገሩን የደፈረውን ጠላቱን ለመደምሰስ ተንቀሳሰ። ንቡ ተነሳ። አንበሳው አገሳ። ኢትዮጵያውያን ወደ ጦር ማሰልጠኛ ተመሙ። የእናት ሀገር ፍቅር ሰንቀው ሰለጠኑ።
ካራማራ ተራራ በኢትዮጵያውያን ጀግኖች ተመላች። በደስታ ዘለለች። ምስጢራዊት አረንጓዴ ቢጫ ቀይዋ ሠንደቅ በድል ተውለበለበች። የማይቀረው ድል ለእርሷ ብቻ የተሰጠ የሚመስለው አሸናፊነት ለኢትዮጵያ ኾነ። የኢትዮጵያ ሕዝብ በየካቲት 23 የዓድዋ ድልን አክብሮ በየካቲት 26 አዲስ ድል ተቀዳጀ። ሌላ የድል በዓል ለትውልድ አስቀመጠ።

የሚዛን  ቴፒ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት

ለአብሮነቶ ከልብ እናመሰግናለን🙏
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

05 Mar, 23:45

282

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ.ም 2ኛ ሩብ ዓመት የውስጥ ኦዲት ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሄደ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሚቴዩ ፣የካቲት 26/2017

የውስጥ ኦዲት ሪፖርቱ በዩኒቨርሲቲው ኦዲት ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ድንበሯ አድማሱ የቀረበ ሲሆን ሪፖርቱን የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዋቆ ገዳን ጨምሮ ምክትል ፕሬዝዳንቶች ፣ የካምፖስ ስራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም መካከለኛ አመራሩ አዳምጦ ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኋላ አስቸኳይ እርምት ማድረግ የሚገባቸው ዘርፎች ማስተካከያዎችን በአስቸኳይ እንዲያደርጉ የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ እንዲስተካከሉ ፕሬዚደንቱ አቅጣጫ አስቀምጠዋልአስቀምጠዋል።
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

04 Mar, 21:36

1,129

በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ለዋናው ግቢ ቤተመጽሐፍትና ዶክመንቴሽን ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሚቴዩ ፣ የካቲት 25/2017

በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ በአዲሱ የስራ ምደባ የስራ መደብ ቀይረው ወደ ክፍሉ ለመጡ ሰራተኞች በመሰረታዊ የቤተመጽሐፍት አገልግሎት አሰጣጥና ዲሲፒሊኖች እንዲሁም አገልሎቱን የሚሰጡ ሰራተኞች እና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ተማሪዎች መብትና ግዴታዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና ስለመሰጠቱ ታውቋል።

አቶ አበጀ መንበሩ የዩኒቨርስቲው ዋና ካምፓስ ቤተመጽሐፍትና ዶክመንቴሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአብዛኛው የትምህርት ተቋማት በዘርፉ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን በሚፈለገው መጠን አለመኖራቸው ለአገልግሎቱ ትልቅ ተግዳሮት ስለመሆኑ ጠቁመው ዩኒቨርስቲው ባለው የሰው ሀይል በተለያዩ አጫጭር ስልጠናዎች ግንዛቤ ያላቸውን ሰራተኞች በመጋበዝ በትንሹ ሰራተኛው ለተማሪው ቀልጣፋና ፈጣን የሆነ አገልግሎት እንዲሰጥ እንዲያስችለው እንዲሁም ሰራተኛው ስለዘርፉ መጠነኛ ግንዛቤ እንዲኖረው መሰል ስልጠና ያስፈልጋል ብለተብለዋል።
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

02 Mar, 06:30

1,779

እንኳን ለ129ኛው የአድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ቀን በሰላም አደረሰን! አደረሳችሁ! 

አድዋ ለእኛ ለኢትዮጵያዊያን የሕብረት፣ የሕብረ-ብሔራዊ አንድነትና የአሸናፊነት ምልክት ነው፡፡ ከኢትዮጵያ አልፎ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራትና የነፃነት ተጋድሎ የሆነው ይህ ድል የአልሸነፍ ባይነት መንፈስን አጎናፅፎ የመብትና የሉዓላዊነት ትግልን ያቀጣጠለ የመላው ጥቁር ህዝቦች የጋራ ታሪክ ነው፡፡ 

ጀግኖች አያት ቅደመ-አያቶቻችን በፈተናዎች ፀንተው ባደረጉት የአልሸነፍ ባይነት ተጋድሎ ያጎናፀፉንን በዘመን የማይደበዝዝ አንፀባራቂ ድል ነው።

በአድዋ ድል ለሰው ልጅ ሉላዊ ዕሴቶች የተሰጠውን ዋጋ አይተንበታል። እንደዚሁም እነሱ ስለ ሀገር ክብርና ሉዓላዊነት በላቀ የሀገር ፍቅር፣ በቃላት በማይገለጽ ወኔ እና ጀግንነት ከጫፍ ጫፍ በመትመም ድንበር ተሻግሮ፣ ዘመናዊ ትጥቅ ታጥቆና በጉልበቱ ተማምኖ የመጣውን ወራሪ ኃይል በአንድነት ድል ያደረጉበት የጋራ አኩሪ ታሪካችን፣ የብሔራዊ ክብራችን ዓርማ ሆኗል።

መላው  የጊቢያችን ተማሪዎች እንድሁም ማህበረሰብ በሙሉ በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ! አደረሰን!

ሳቢት ሳሊ
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት
#አድዋ💚💛❤️

ለየትኛውም ሀሳብ አስተያየት
https://t.me/MTUINSIDER
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

02 Mar, 05:57

1,661

ዛሬ የሚደረጉ የGC cup ጨዋታዎች
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

01 Mar, 20:45

1,607

ትምህርት ሚንስቴር ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ ብሔራዊ መታወቂያ ካርድ (ፋይዳ) በያዝነው የትምህርት ዘመን ሰኔ ወር ላይ ብሔራዊ የዩንቨርስቲ(Exit exam) ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች ቅድመ ሁኔታ መሆኑን ገልፃል። ኢትዮ ቴሌኮም እና ኢትዮ ፓስት ለዚሁ ስራ በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለምዝገባ ይገባሉም ብሏል።

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

01 Mar, 17:54

1,077

የዛሬው የGC cup ጨዋታ ውጤት
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

01 Mar, 06:18

1,308

በጉጉት ስትጠብቁት የነበረው የ2017 GC cup ዛሬ ይጀምራል።

ዛሬ 2 ጨዋታዎች የሚካሄዱ ይሆናል ።

ዛሬ ጠዋት 3:00 ላይ School of Law vs Othe Social Science B በሚያደርጉት ጨዋታ ይከፈታል ።

ከሰዓት 9:00
Othe Social Science 'A' vs FB 'B'
የምቀጥል ይሆናል።

For any Comment
https://t.me/MTUINSIDER
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

28 Feb, 15:47

1,473

ሰበር
======
የረመዿን ጨረቃ በሃገረ ሳዑዲ ዓረቢያ ስለታየች ነገ ቅዳሜ የካቲት 22, 2017 E.C.  የረመዿን የመጀመሪያ ቀን ይሆናል።

BREAKING NEWS: The Crescent of Ramadan 1446/2025 has been sighted in Saudi Arabia!

Subsequently, Ramadan 1446/2025 begins tomorrow.

ለዩኒቨርስቲያችን የእስልምና እምነት ተከታይ ተማሪዎቻችን በሙሉ
እንኳን ለረመዳን ጾም በሰላም  አደረሳችሁ!!

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት
M͍I͍Z͍A͍N͍ T͍E͍P͍I͍ U͍n͍i͍v͍e͍r͍s͍i͍t͍y͍ Students Union Channel.

28 Feb, 03:20

1,502

Best orators of the competition of 2025 Inter batch moot court competition at Mizan tepi University school of Law😘
FASIL ZELEKE and Kidist Zeranbesa