እንኳን ለድሉ መታሰቢያ በዓል አደረሰን🇪🇹❤
ልክ የዛሬ 47 ዓመት ሀገር ጠርታው ተኝቶ የማያድረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳር ዳር ተሰማማ። የተከበረች ሀገሩን የደፈረውን ጠላቱን ለመደምሰስ ተንቀሳሰ። ንቡ ተነሳ። አንበሳው አገሳ። ኢትዮጵያውያን ወደ ጦር ማሰልጠኛ ተመሙ። የእናት ሀገር ፍቅር ሰንቀው ሰለጠኑ።
ካራማራ ተራራ በኢትዮጵያውያን ጀግኖች ተመላች። በደስታ ዘለለች። ምስጢራዊት አረንጓዴ ቢጫ ቀይዋ ሠንደቅ በድል ተውለበለበች። የማይቀረው ድል ለእርሷ ብቻ የተሰጠ የሚመስለው አሸናፊነት ለኢትዮጵያ ኾነ። የኢትዮጵያ ሕዝብ በየካቲት 23 የዓድዋ ድልን አክብሮ በየካቲት 26 አዲስ ድል ተቀዳጀ። ሌላ የድል በዓል ለትውልድ አስቀመጠ።
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት
ለአብሮነቶ ከልብ እናመሰግናለን🙏