የካቲት 26/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰምድር ውሃ ፕሮጀክት አካል የሆነውንና በሲዳማ ክልል ደቡባዊ ዞን ዳራ ወረዳ አዳሜ ጤሶ ቀበሌ ላይ በ92 ሚሊየን ብር ወጭ ያስገነባውና ከ24ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
በምርቃት ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ በ55 ወረዳዎች ውስጥ እየተተገበሩ ከሚገኙ አንዱና ቀድሞ የተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል።
ክቡር ሚኒስቴሩ በማከል ፕሮጀክቱ አመት ሳይሞላው የተመረቀና ትልቅ ስኬት ያየንበትነው ብለዋል።
ፕሮጀክቱን አጠናቀን ለህብረተሰቡ ስናስረክብ መንከባከብ ብቻ ሳይሆን ወረዳው በሚዘረጋው የክፍያ ስርአት በመክፈል ውሀውን በቁጠባ መጠቀም አለበት በማለት አሳስበዋል።
በመጨረሻም ክቡር ሚኒስትሩ የፕሮጀክቱ አላማ ድርቅ በሚያጠቃቸው አካባቢዎች የከርሰ ምድር ውሀ ተጠቃሚ ማድረግ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ የከብት ማጠጫ ገንዳ ጭምር ያካተተ መሆኑን በመግለጽ በግንባታ ላይ የተሳተፈውን ገነነ አኩማ ኮንስትራክሽን አመሥግነዋል።
የሲዳማ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ክቡር አቶ በየነ በራሳ አካባቢው ለረጅም ጊዜ የቆየ የውሃ ችግር የነበረበት ቢሆንም አሁን ላይ ትላልቅ ሁለት ፕሮጀክቶች መገንባታቸው ችግሩን ሙሉ በሙሉ እንደሚፈታ ገልጸዋል።
ክቡር ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ፕሮጀክቱ ስናስመርቅ ውሃ ጥምን ከማርካት በላይ መሆኑን በመግለጽ በዚህ ፕሮጀክት የሴቶችን ጫና፣ ጤና፣ ትምህርት ላይ ያለውን ችግር እንደሚቀርፍ ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ፕሮጀክቱ በክልላችን እንዲገነባ እድሉን ለሠጡን ውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና ፕሮጀክቱን በቃሉ ገንብቶ ላስረከበን ገነነ ከኩማ ኮንስትራክሽን ምስጋና አቅርበዋል።
የሲዳማ ክልል ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ ኢ/ር ከበደ ጋኖሌ ፕሮጀክቱ በጊዜው ተገንብቶ መጠናቀቁ ከፍተኛ ማህበራዊ ና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፣ህብረተሰቡን ከውሀ ወለድ በሽታ ከረጂም ጉዞ ድካም ተላቀዉ ለዚህ በመብቃታቸው ጊዜና ገንዘባቸውን እንደሚቆጥቡ ገልጸዋል።
ኢ/ር ከበደ በመጨረሻ ኮንትራክተሩን ጨምሮ ለፕሮጀክቱ በወቅቱ መሳካት ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ ምስጋና አቅርበዋል።
ፕሮጀክቱ በአዳሜ ቴሶና እና ቁማጦ ቀበሌዎች ከ24ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግና 19 ቦኖዎችን እንዲሁም 3 የእንስሳት ውሃ መጠጫ ገንዳዎች አካቷል ።
በመጨረሻም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፕሮጀክቱን ገንብቶ በቃሉ መሠረት አጠናቆ ላስረከበው ገነነ አኩሜ ኮንስትራክሽ የምስክር ወረቀት አበርክቶለታል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto