Dernières publications de Ministry of water and Energy የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር (@mowieethiopia) sur Telegram

Publications du canal Ministry of water and Energy የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

Ministry of water and Energy የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
ይህ ስለ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተለያዩ ወቅታዊ መረጃዎችን የምታገኙበት የሚኒስቴሩ የቴሌግራም ቻናል ነው፡፡
5,724 abonnés
4,511 photos
23 vidéos
Dernière mise à jour 06.03.2025 15:04

Canaux similaires

Addis Fortune
13,927 abonnés
Borkena
7,270 abonnés

Le dernier contenu partagé par Ministry of water and Energy የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር sur Telegram

Ministry of water and Energy የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

05 Mar, 21:21

400

ከ24ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለአገልግሎት መስጠት ጀመረ።

የካቲት 26/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰምድር ውሃ ፕሮጀክት አካል የሆነውንና በሲዳማ ክልል ደቡባዊ ዞን ዳራ ወረዳ አዳሜ ጤሶ ቀበሌ ላይ በ92 ሚሊየን ብር ወጭ ያስገነባውና ከ24ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

በምርቃት ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ በ55 ወረዳዎች ውስጥ እየተተገበሩ ከሚገኙ አንዱና ቀድሞ የተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል።

ክቡር ሚኒስቴሩ በማከል ፕሮጀክቱ አመት ሳይሞላው የተመረቀና ትልቅ ስኬት ያየንበትነው ብለዋል።

ፕሮጀክቱን አጠናቀን ለህብረተሰቡ ስናስረክብ መንከባከብ ብቻ ሳይሆን ወረዳው በሚዘረጋው የክፍያ ስርአት በመክፈል ውሀውን በቁጠባ መጠቀም አለበት በማለት አሳስበዋል።

በመጨረሻም ክቡር ሚኒስትሩ የፕሮጀክቱ አላማ ድርቅ በሚያጠቃቸው አካባቢዎች የከርሰ ምድር ውሀ ተጠቃሚ ማድረግ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ የከብት ማጠጫ ገንዳ ጭምር ያካተተ መሆኑን በመግለጽ በግንባታ ላይ የተሳተፈውን ገነነ አኩማ ኮንስትራክሽን አመሥግነዋል።

የሲዳማ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ክቡር አቶ በየነ በራሳ አካባቢው ለረጅም ጊዜ የቆየ የውሃ ችግር የነበረበት ቢሆንም አሁን ላይ ትላልቅ ሁለት ፕሮጀክቶች መገንባታቸው ችግሩን ሙሉ በሙሉ እንደሚፈታ ገልጸዋል።

ክቡር ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ፕሮጀክቱ ስናስመርቅ ውሃ ጥምን ከማርካት በላይ መሆኑን በመግለጽ በዚህ ፕሮጀክት የሴቶችን ጫና፣ ጤና፣ ትምህርት ላይ ያለውን ችግር እንደሚቀርፍ ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፕሮጀክቱ በክልላችን እንዲገነባ እድሉን ለሠጡን ውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና ፕሮጀክቱን በቃሉ ገንብቶ ላስረከበን ገነነ ከኩማ ኮንስትራክሽን ምስጋና አቅርበዋል።

የሲዳማ ክልል ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ ኢ/ር ከበደ ጋኖሌ ፕሮጀክቱ በጊዜው ተገንብቶ መጠናቀቁ ከፍተኛ ማህበራዊ ና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፣ህብረተሰቡን ከውሀ ወለድ በሽታ ከረጂም ጉዞ ድካም ተላቀዉ ለዚህ በመብቃታቸው ጊዜና ገንዘባቸውን እንደሚቆጥቡ ገልጸዋል።

ኢ/ር ከበደ በመጨረሻ ኮንትራክተሩን ጨምሮ ለፕሮጀክቱ በወቅቱ መሳካት ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ ምስጋና አቅርበዋል።

ፕሮጀክቱ በአዳሜ ቴሶና እና ቁማጦ ቀበሌዎች ከ24ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግና 19 ቦኖዎችን እንዲሁም 3 የእንስሳት ውሃ መጠጫ ገንዳዎች አካቷል ።

በመጨረሻም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፕሮጀክቱን ገንብቶ በቃሉ መሠረት አጠናቆ ላስረከበው ገነነ አኩሜ ኮንስትራክሽ የምስክር ወረቀት አበርክቶለታል።

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto
Ministry of water and Energy የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

05 Mar, 21:16

299

በ134 ሚሊየን ብር ወጭ የተገነባው የገደብ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

የካቲት 25/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በባስኬት ፈንድ ፕሮጀክት በውሀ ልማት ፈንድ በጌዲኦ ዞን ገደብ ከተማ በ134 ሚሊየን ብር ወጭ ያስገነባው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

በመርሃግሩ ላይ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ ውሃ ላይ እያሉ ዉሃ ለተጠሙ ህዝቦች ውሃ እንዲጠጡ መደረጉ ለከተማው አስደሳች መሆኑን ተናግረዋል ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማከል በክልላችን በርካታ ትላልቅ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመው ገደብም የዚሁ አካል ነው ብለዋል።

የገደብ መጠጥ ውሀ ፕሮጀክት ከ51ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያስጠቅም ቢሆንም ከከተማው ነዋሪ ፍላጎት በላይ ስለሆነ የህብረተሰቡን ችግር ፈቶ ለሌሎች ተግባራት ማዋል እንደሚቻል ጠቁመዋል።

በስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የመጠጥ ውሃን ተደራሽ ከማድረግ ጎን ለጎን በሀገራችን የነበረውን ውሃን በፍትሀዊነት ያለማዳረስ ችግር ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑን አንስተው፤ በሁሉም ክልል ፍትሀዊ የውሃ ተጠቃሚነት እንዳልነበርና አሁን ላይ ችግሩን ለመፍታት እንደ ሀገር ከፍተኛ ገንዘብ ተበጅቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ።

ክቡር ሚኒስትሩ በማከል የገደብ ከተማ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ስናስመርቅ ውሃውን ለህብረተሰቡ በፍትሀዊነት ክፍፍል የማድረግ ታች ያለው አካል ሀላፊነት ሲሆን ከህብረተሰቡ የሚጠበቀዉ ለማያገኘው አገልግሎት ተገቢውን ክፍያ በመክፈል ሌሎች ፕሮጀክቶች እንዲገነቡ አስተዋጾ ማድረግ እንዳለበት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም ክቡር ሚኒስትሩ ሁሉም ህብረተሰብ በመክፈል ፣ በመንከባከብ ፣ ብክነትን በመቀነስ መጠቀም ከቻለ ተጨማሪ ፕሮጀክት መስራት ይቻላል በማለት አሳስበዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የውሀና ኢነርጂ ሚኒስትርን ጨምሮ የበላይ አመራሮች የሀገር ሽማግሌዎች ኮንትራክተሮችና የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል።

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto
Ministry of water and Energy የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

05 Mar, 21:02

333

የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ መሆናቸው ማህበራዊ ችግራቸውን እንደሚፈታላቸው ገለጹ።

የካቲት 24/2017 (ው.ኢ.ሚ)የውሀና ኢነርጅ ሚኒስቴር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዲላ ከተማ በዋን ዋሽ ፕሮግራም ያስገነባው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የማህበራዊ ችግሮቻቸውን እንደፈታላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የዲላ ከተማ መሳ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት ጫካ እንደገለጹት ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የውሀ ችግር እንደነበርና አሁን ላይ የዚህ ፕሮጀክት መተግበር የመጠጥ ውሃ ፍላጎትን ብቻ ሳይሆ ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ እና ከጤና ጋር ተያያዠ የሆኑ ችግሮችን እንደሚፈታላቸው ገልጸዋል።

ወ/ሮ ትእግስት በማከል ፕሮጀክቱ በተለይ ለሴቶች ውሃ ለመቅዳት የሚያባክኑትን ጊዜና የሚደርስባቸውን ድካም ሙሉ በሙሉ በማስቀረትና በከተማ ግብርና በመሰማራት ኢኮኖሚያቸውን ለመደገፍ እንደሚጠቀሙበት በመግለጽ ቨፖሮጀክቱ ትግበራ የተሳተፉትን አካላትን አመስግነዋል።

አቶ ታምራት ዶኦዮ ከተማዋ የንጹህ መጠጥ ውሀ ተጠቃሚ በመሆኗ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ከተማዋ እስከዛሬ በውሃ ተከባ የውሃ ችግር ያለባት እንደነበረችና አሁን ላይ ይህ ችግር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ እንደተፈታ ገልጸዋል።

አቶ ታምራት በማከል ፕሮጀክቱ ከመጠጥ ውሃ ባለፈ በከተማዋ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚሰጥና በተለይ ለትምህር ቤቶች ፣ ለጤና ተቋማት፣ ድርጅቶችና ሌሎችም በውሃ እጥረት ምክንያት ይደርስባቸው የነበረውን ችግር በመቅረፍ የተሳለጠ አገልግሎት እንዲሰጡና ልማቱ እንዲፋጠን አስተዋጾ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በአግባቡ ለሁሉም ህብረተሰብ መዳረስ እንዲችልና የውሃ ብክነት እንዳይፈጠር ያረጁ የውሃ ማስተላለፊያ መስመሮች ቢቀየሩ የሚል ምክር አዘል አስተያየትም ሰጥተዋል።

ፕሮጀክቱ 3500 እና 3000 ሜትር ኪዩብ የሆኑ ሁለት ሪዘርቬየር ያሉት 116 ሊትር ውሃ በደቂቃ የሚያመነጭ ሲሆን192 ሺ የህብረተሰብ ክፍልን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto
Ministry of water and Energy የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

04 Mar, 19:54

440

ከ348 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ የተገነባው የዲላ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡

የካቲት 25/2017ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በዋን ዋሽ ብሔራዊ ፕሮግራም ከ348 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ የተገነባው የዲላ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡

የምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ ርእሰ መስተዳደር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ ፕሮጀክቱ ከተማችንን አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርግና ከተማችን የብልጽግና ተምሳሌት፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለኢንቨስትመንት ሳቢ፣ የሚያደርግ ፕሮጀክት እንድናስመርቅ ከጎናችን ለነበሩ ፈተናዎችን ላሻገሩን ክቡርዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋን አመሠግናለሁ ብለዋል።

ክቡር ርእሰ መስተዳድሩ በማከል ህብረተሰቡ ውሃን በመጠቀም ሁሉን አቀፍ ስራ በመስራት፣ ከጽዳት ጋር በማቀናጀት፣ የተበላሹ መስመሮችን በማስተካከል በቀጣይ ሌሎችም ፕሮጀክቶችን በመስራት ገቢ ማግኘት እንዲያስችል ጥገና ፣ ጥበቃ እና እንክብካቤ በማድረግ ህይወት ያለው ለማድረግ የዲላ ከተማ ውሀና ፍሳሽ አገልግሎት ሀላፊነቱን እንዲወጣ አደራ በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።

ፕሮጀክቱን በቦታው ተገኝተው ያስመረቁት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 1.6 ሚሊየን የህብረተሰብ ክፍሎችን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራን ነው ስንል በአንድ ዞን ሁለት ከተሞች ማስመረቃችን የስኬታችን ማሳያ ነው ብለዋል። ክቡር ሚኒስትሩ በማከል የዲላ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ከተማዋ የነበረባትን ችግር ሙሉ በሙሉ ከመቅረፍ ባሻገር መሠረታዊ ለውጥ ያመጣል ለዚህም ውሃ ላይ ብቻ ሳይሆን ሳንቴሽን ላይ ህብረተሰቡ እና አመራሩ በመተባበር መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አክሊሉ አዳኝ ውሃ የህብረተሰቡ መሠረታዊ ችግር ላይ የሚሰራው ስራ ሌሎች ልማቶችን በማሳለጥ በጤና ፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚና በአጠቃላይ በልማቱ ዘርፍ የሚያሳድረው ተጽእኖ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ይህን ታሳቢ በማድረግ እንደ ክልል በ14 ከተሞች በተለያዩ ፕሮግራሞች 1.2 ሚሊየን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ መሆኑን ገልጸው ዛሬ የሚመረቁት ፕሮጀክቶች የዚሁ አካል ናቸው ብለዋል።

ኢ/ር አክሊሉ በማያያዝ የዲላ ከተማ መጠጥ ውሀ ፕሮጀክት ነባር የሆነውን ስምና ችግሮች ር ስለሚፈታ በአግባቡ ከብክነት በጸዳ በመጠቀም ገቢ እንዲያስገኝ ልናደርግ ይገባል ብለዋል።

በዋን ዋሽ ብሔራዊ ፕሮግራም የገንዘብ ድጋፍና በውሀ ልማት ፈንድ አስተባባሪነት የተተገበረው የዲላ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት 192ሺ የህብረተሰብ ክፍሎች የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ በማድረግ የከተማውን የመጠጥ ውሃ ችግር እንደሚፈታ ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ ዘላቂነት ያለው አገልግሎት እንዲሰጥም ህብረተሰቡም አስፈላጊውን ጥበቃና እንክብካቤ ማድረግ እንዳለበትም በምርቃቱ ላይ ተገልጿል ፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ፣የክልሉ ባለስልጣናት እና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto
Ministry of water and Energy የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

04 Mar, 19:48

373

ለውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ለተጠሪ ተቋማት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

የካቲት 24/2017 ዓ/ም በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተዘጋጀ በተቋሟዊ ተግባቦት /organizational communication/ ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለተቋሙና ለተጠሪ ተቋማት አመራሮች እየተሰጠ ነው።

የስልጠናውን መርሃ ግብር ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚንስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ሡልጣን ወሊ ውድ ጊዜና ገንዘብ ተመድቦ የአቅም ግንባታ ስልጠና የተዘጋጀው በተቋማችን ውጤታማ ስራ ለመስራት፣ ትክክለኛ ተግባቦትና ጤናማ ግንኙነት ወሳኝ በመሆኑ ነው ብለዋል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ያሉት ሚንስትር ድኤታው በቀጣይ በየስራ ክፍላችን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የስራ ክህሎታችንን ከፍ ለማድረግ፣ ጤናማ ግንኙነትና ትክክለኛ ተግባቦት መሰረታዊ ጉዳይ ነው ብለዋል።

እንደ አመራር መረጃ ልውውጣችንና የተግባቦት ደረጃችን የት፣ መቼ፣ ከማን ጋርና እንዴት የሚሉ ጥያቄዎችን በአግባቡ የሚመልስና ስራችንን ውጤታማ በሚያደርግ መልኩ መሆኑንም በጥንቃቄ ማየት አለብንም ብለዋል።

ክቡር ሚንስትር ድኤታው አክለው የተቋማችንና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ከፍ በማድረግ ዘመኑን የዋጀ ስራ ለመስራት፣ ጥራት ያለው አገልግሎት ለማቅረብና በቡድን የመስራትን መንፈስ ለማጠናከር የአቅም ግንባታ ስልጠናው ከፍተኛ ጠቀሜታ ስላለው ትኩረት ሰጥተን መከታተል አለብን ብለዋል።

ከአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የመጡ የዘርፉ ምሁራን በተቋማዊ ተግባቦት፣ የተግባቦት ዋና ዋና ጉዳዮችና ሀይድሮፖለቲክስና ዲፕሎማሲ በሚሉ ርዕሶች ላይ ሰፊ ማብራሪያ በመስጠትና የቡድን ስራ በማሰራት ጠለቅ ያለ ግንዛቤ አስጨብጠዋል።

ሰልጣኞችም በቡድን ስራ በመሳተፍና በመወያየት፣ ጥያቄዎችን በመጠየቅ የነቃ ተሳትፎ አድረገዋል ፣ ስልጠናው ለስራቸው ውጤታማነት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለውም ገልፀዋል።

ስልጠናው ለሁለት ቀናት እንደሚቀጥልም ተገልጿል።

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto
Ministry of water and Energy የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

04 Mar, 19:43

353

“የዓባይ ግድብ እና ዓድዋ የአንድነታችን ማሰሪያ የቁጭታችንም ማሳያ ስኬቶቻችን ናቸው” –

ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር

ዓባይ ግድብ እና ዓድዋ ድል የአንድነታችን ማሰሪያ፤ የቁጭታችንም ማሳያ ስኬቶቻችን ናቸው ሲሉ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ:: ሁለቱም ስኬቶች በሕዝቡ እና በመሪዎች ቅብብሎሽ የተገኙ ድሎች መሆናቸውን አስታወቁ::

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ (ዶ/ር) ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳስታወቁት፤ የዓባይ ግድብም ሆነ ዓድዋ የኢትዮጵያውያን አንድነት የተረጋገጠባቸው ስኬቶች ናቸው:: ኢትዮጵያውያውን በሁለቱም ላይ አንድነታቸውን አሳይተዋል፤ በቁጭት በሠሩት ሥራ የማይደፈር ማንነት እንዳላቸው አረጋግጠዋል::

ሁለቱም ታላላቅ ስኬቶች ኢትዮጵያውያን በብቃት የተጫወትንባቸው ሜዳዎች ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ጠላትን በዝረራ ከጨዋታ ወጪ ያደረግንበትን ድልም አስመዝግበንበታል ብለዋል:: ዓባይ ግድብ ሆነ ዓድዋ ድል ኢትዮጵያ ይደርስባት የነበረውን የውጭውን ጫና በብቃት የመከተችበት ሲሆን፤ ያንን የተሳሳተ አስተሳሰብ ያኮላሸችበት ስኬቷ እንደሆኑም ገልጸዋል::

እንደ ኢንጂነር ሀብታሙ (ዶ/ር) ገለጻ፤ ዓድዋ ድል እና ዓባይ ግድብ የኢትዮጵያውያን አንድነት የተረጋገጠባቸው ናቸው:: ዓድዋ ላይ እንደ አሁኑ ጊዜ ቴክኖሎጂ አልነበረም::

ተንቀሳቃሽ ስልኩ፣ ኢንተርኔቱ እና ሌላ ሌላው አልነበረም::

እንዲያም ሆኖ ለኢትዮጵያ አንድነት ሲባል ከጥግ ጥግ ድረስ በአራቱም ማዕዘን ንቅናቄ በመፍጠር ኢትዮጵያ የእኔ ናት ብሎ ስለሚያምን ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ሕዝቡ መንቀሳቀስ ችሏል:: በወቅቱ የራሱ የሆነና እንዲፈታለት የሚፈለገው ችግር ሊኖርበት ይችል ይሆናል:: ነገር ግን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ድርድር አያውቁም:: የዓባይ ግድብም በተመሳሳይ የሚጠቀስ ነው::

የዓባይ ግድብ በየትኛውም ክልል ሆኖ የትኛውም ቀበሌ ውስጥ ያለ ሰው ዓባይ ሲባል አንዳች የአንድነት እና የመተባበር መንፈስ ውስጡ እንዳለ ይታወቀዋል:: የእኔነት ስሜቱ የጎላ ነው:: ምክንያቱም ከሌለው ነገር ላይ ለዓባይ ግድብ አቋድሷል::

በዓድዋ በኩል ወይ ራሱ አሊያም ልጆቹን ወደ ግንባር እንዳላከ ሁሉ ለዓባይ ግድብም እንዲሁ በጉልበቱ፣ በገንዘቡና በሀብቱ ተሳትፏል:: ከዚህ መነሻነትም ዓድዋ ድልና ዓባይ ግድብ የአንድነት ማሳያ ናቸው:: ሁለቱም የኢትዮጵያውያን ምልክት ናቸው::

ሚኒስትሩ፣ ሁለቱም የውጭ ጫና የፈተናቸው ታላላቅ ስኬቶች ናቸው:: ኢትዮጵያ በዓድዋ ጦርነት ጊዜ የተዋጋችው አንድን ሀገር ብቻ አይደለም:: በወቅቱ ከጣሊያን ጋር ኅብረት ከፈጠሩትና የቅኝ ግዛትን ማስፋፋት ከሚፈልጉት ሀገራት ጋር ሁሉ ነበር ማለት ይቻላል:: ኢትዮጵያ በወቅቱ ያሸነፈችው የተነሱባትን ኃይሎች ሁሉ ነው:: ይህ ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል::

የዓባይ ግድብን በተመለከተ ደግሞ እኛን ስትገዳደረን የነበረችው ግብጽ ብቻ አይደለችም ያሉት ኢንጂነር ሀብታሙ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ ማሸነፍ የቻለችው በድህነቷ እንድትዘልቅ የሚፈልጉ ኃይሎችን ጭምር እንደሆነ አስረድተዋል::

ኢትዮጵያ በዓባይ ግድብ ምክንያት በጸጥታው ምክር ቤት ስትወሰድ ዓላማው ኢትዮጵያን በዚያ ደረጃ ማብጠልጠል ነው:: በመሆኑም በኢትዮጵያ ጥንካሬ እሱን ወደ አፍሪካ ኅብረት መመለስ መቻል ትልቅ ስኬት ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን አመልክተዋል::

በዓድዋ ጊዜ በውጊያ የነበረው የቅኝ መግዛት ሕልም ኢትዮጵያ እንዳጨናገፈች ሁሉ አሁን ደግሞ በኢኮኖሚው በኩል በቅኝ ለመግዛት የተቋመጠውን አካሔድ ኢትዮጵያ ያሸመደመደችው መሆኑ ሁለቱን የሚያመሳስላቸው ጉዳይ ነው ብለዋል::

እርሳቸው እንዳሉት፤ በጣም ወሳኙ ጉዳይ በኢትዮጵያ የውሃ ልማት ታሪክ ዛሬ ያመጣነው ስኬት በአንድ ጀምበር የመጣ ሳይሆን በትውልድ ቅብብሎሽ የተገኘ ስኬት ነው:: በዚህ ስኬት ውስጥ የመሪዎች ቅብብሎሽ አለ:: ንጉሱ አጼ ኃይለስላሴ የአሜሪካ ኩባንያ ቀጥረው ኢትዮጵያ ውስጥ ለግድብ የሚሆን ብዙ ቦታ ካስጠኑ በኋላ ብድር ጠይቀው ተከልክለዋል:: ይሁንና አንድ ቀን ኢትዮጵያውያኑ እንደሚገነቡት ተስፋ አድርገው አልፈዋል::

ሙሉውን ለማንበብ
https://press.et/?p=146503

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikt
Ministry of water and Energy የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

28 Feb, 17:29

945

ሁለተኛው አድዋችን የሆነው ህዳሴያችን የጋራ ማንነታችን መገለጫ ነው።

ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ

የካቲት 21/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “አድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል!” በሚል መሪ ቃል በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ተከበረ።

በአሉን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ሁለተኛው አድዋችን የሆነው ህዳሴያችን የጋራ ማንነታችን መገለጫ ነው፤ አድዋ የትም ቦታ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሚዘክረው በመሆኑ ማንነታችንን ያበሰርንበት ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከ ዳር በዘመቱበት ወቅት ሁሉም ዜጋ በተሰማራበት ዘርፍ የድርሻቸውን በመወጣት አሻራቸውን ያኖሩበትና ትልቅ ስኬት የተመዘገበበት በመሆኑ ልንዘክረው ይገባል ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ ጀግኖች አባቶቻችን በሀገር ጉዳይ በጋራ ሲቆሙ ብሔር ሳይለዩ የጀግንነት ድርሻቸውን ተወጥተዋል ብለዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም ሁለተኛው አድዋችን የምንኮራበትና የአንድነታችን የጋራ መገለጫችን በመሆኑ በወቅቱ የነበሩ መሪዎች ዋጋ ከፍለው እዚ አድርሰውልናልና ልናስቀጥለው ይገባል፤ በተጨማሪም የይቻላል መንፈስ ያዳበርንበት በመሆኑ የጋራ ሀገር ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የምትሆን ኢትዮጵያን እንገምባ ብለዋል።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ጌጡ በዓሉን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የመወያያ ሰነድ አቅርበው እንደተቋም ሁለተኛውን አድዋችንን ለማስቀጠል ሁሉም በተሰማራበት ዘርፍ ኃላፊነታችንን በመወጣት የራሳችንን አሻራ ማስቀመጥ እንዳለብን ጠቁመዋል።

መድረኩ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን በቀረበው የመወያያ ሰነድ ዙሪያ ከሰራተኞች በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ክቡር ሚኒስትሩ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
Ministry of water and Energy የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

28 Feb, 17:26

322

The implementation of the One WASH Program (Phase II) has shown promising results.

The Ministry of Water and Energy is currently evaluating the One WASH Program (Phase II) in collaboration with stakeholders starting from February 25, 2025, in Adama City.

In his opening speech, H.E. Ambassador Dr. Asfaw Dingamo, State Minister of Water and Sanitation, emphasized that the primary goal of this platform is to review the achievements of the One WASH Program (Phase II), identify existing gaps, and address issues crucial for the program’s upcoming third phase.

The National One WASH Program in Ethiopia aims to meet the WASH milestones set forth in the Sustainable Development Goals by integrating various projects into a cohesive initiative.

This approach seeks to enhance service delivery across rural, urban, and pastoral communities, as well as in schools and health institutions, while optimizing resource utilization.

Over the past decade, significant strides have been made in providing clean water, sanitation, and hygiene through the collaborative efforts of the Ethiopian government, development partners, civil society organizations, and other stakeholders. Notably, access to clean water has reached 79.12% in urban areas and 70% in rural regions, with basic sanitation coverage at 42%, reflecting substantial progress.

However, many citizens still lack access to these essential services. H.E.Ambassador Dr. Asfaw highlighted several challenges, including planning and implementation constraints, the need for new partnerships, and ensuring the sustainability of the program.

He also pointed out the impacts of climate change, capacity building needs, and monitoring gaps as significant obstacles that require due attention.

To overcome these challenges and achieve even better outcomes, continued commitment from all stakeholders is essential. The Ambassador noted that the discussions would align the sector's development with the country’s strategic priorities, paving the way for the implementation of the third phase of the One WASH Program.

Participants actively engaged in the discussions, raising questions, sharing experiences, and identifying areas needing improvement. The session was moderated by HE Mr. Motuma Mekassa, the Minister's Advisor, who provided valuable insights and responses.

The workshop brought together representatives from federal ministries, stakeholders, non-governmental organizations, civil society, and regional bureaus, all dedicated to advancing the WASH agenda in Ethiopia.

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto
Ministry of water and Energy የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

28 Feb, 17:25

233

ለማንኛውም እድገት መሰረት እና ወሳኝ በሆነው የሀይል ዘርፍ ላይ መምከር ውጤታማ ስራ በመስራት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ተባለ፡፡

የካቲት 20/2017ዓ.ም አዲስ አበባ (ው.ኢ.ሚ) በሶላር ኢነርጂ ቴክኖሎጅ ላይ የሚመክረው የባለድርሻ አካላት ውይይት እና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ተካሄደ፡፡

መድረኩን በይፋ የከፈቱት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ለማንኛውም እድገት መሰረት እና ወሳኝ በሆነው የሀይል ዘርፍ ላይ መምከርና ውጤታማ ስራ መስራት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ እምቅ የታዳሽ ሀይል ባለቤት ብትሆንም 46 በመቶ በታች የሚገመተው የህብረተሰብ ክፍል የሀይል ዘርፉ ተጠቃሚ መሆን አልቻለም ብለዋል፡፡

86በመቶ የሚሆነው በአብዛኛው የገጠሩ የማህብረተሰብ ክፍል ደግሞ በባዮ ማስ ላይ ጥገኛ ሲሆን ከ10 በመቶ የሚሆነው ብቻ ንጹህ የማብሰል ዘዴን ይጠቀማል ብለዋል፡፡

ይህ ንጹህ ያልሆነ የማብሰል ዘዴ የማህበረሰቡን ጤና በተለይም የህጻናት እናቶችን እንዲሁም አቅመደ ካሞችን በቤት ውስጥ ጭስ ምክንያት ለሚከሰቱ ትራኮማ፣ የመተንፈሻ አካላት ችግርና ተያያዥ ለሆኑ በሽታዎች ከማጋለጡ ባለፈ ከደን መመንጠር ጋር ተያይዞ የአፈር ለምነትን በመቀነስ፣ የመሬት መሸርሸርን በማስከተል ለአየር ንብረት ለውጥ እና የግብርና ምርታማነትን በመቀነስ ረገድ አስዋጽኦው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

ይህንንና ተያያዥ ችግሮችን ለመቅረፍ በተለይም እስካሁን የኤሌክትሪክ ተደራሽ ያልሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በግሪድና በኦፍ ግሪድ ቴክኖሎጅ ተደራሽ ለማድረግ መንግስት ብሔራዊ የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ቀርጾ ከልማት አጋሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በርካታ ጥረቶችን በማድረግ አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል፡፡

የሶላር ቴክኖሎጅ ተግባራዊ ሲደረግም ለመብራትና ለማብሰያነት ከማዋል ባለፈ የግብርና ምርታማነትን በመጨመር የህብረተሰቡን የንሮ ደረጃ ለማሻሻል ታላሚ ያደረገ ሲሆን ለዚህ ደግሞ እንደ አዴሌ ያሉ ፕሮጀክቶቻችን ማሳያ ናቸው ብለዋል፡፡

በዘርፉ ለሚሰራው ስራ የግሉ ዘርፍ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስተር ዴኤታው ዘርፉን የበለጠ በማጠናከር ውጤታማ ስራ ለመስራት ሀይል በማልማትና በማሰራጨት ረገድ የግሉ ዘርፍ ተሳታፊ የሚሆንበት በፖሊሊ የተደገፈ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯልም ብለዋል፡፡

መድረኩ መንግስት ከግሉ ዘርፍ ጋር በሀይል ማምረትና ማሰራጨት ላይ የሚሰራውን ስራ የሚያጠናክር ውይይት የሚደረግበት ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሶላር ልማት አሶሴሽን ኃላፊ ወ/ሮ ሀዊ ተስፋየ በበኩላቸው መድረኩ በዘርፉ ከመንግስትና ባለድርሻ አካላት በሶላር ኢነርጂ ላይ ለሚሰራው ስራ ጠቃሚ ነገሮች የሚገኙበትና ትብብሩን የበለጠ የምናጠናክርበት ነው ፡፡ በሶላር ኢነርጂ ገበያ ላይም የራሱ የሆነ ድርሻ አለው ብለዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ በሶላር ኢነርጂ ላይ የተሰማሩ መንግስታዊ ተቋማት፣ የልማት አጋሮች፣ የውጭ እና የሀገር ውስጥ የግሉ ዘርፍ ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡

በእለቱ የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሶላር ኢነርጂ ቴክኖሎጅ ምርቶችን ለእይታ አቅርበዋል፡፡

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto
Ministry of water and Energy የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

19 Feb, 07:04

264

The count Down.

Four Days to go for the 19th Regional Nile Day.