Neueste Beiträge von ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ (@moaetewahedob) auf Telegram

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ Telegram-Beiträge

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ
"ነፍሳችን በስጋ ስንኖር ብዙ መከራ አለባት።
እንዲሁም ከስጋችን ከተለየች በኋላ እንደሰራነው ስራ ጥሩ ወይም መጥፎ እጣፈንታዎች ይገጥሟታል።
ታዲያ በህይወት ስንኖር ነፍሳችንን የምታሻግር አንድ መንገድ አለች ይህችም ቀጥተኛዋ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ናት። "
https://t.me/MoaeTewahedoB

አስተያየት ና ጥያቄ ያለው ብቻ‼️
@sosi5555
ይህ ፔጅ ታህሳስ 30/4/2014
11,268 Abonnenten
3,538 Fotos
199 Videos
Zuletzt aktualisiert 06.03.2025 12:42

Der neueste Inhalt, der von ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ auf Telegram geteilt wurde.

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

06 Mar, 11:58

158

🕰🔔

9:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰
    

     @MoaeTewahedoB
ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

06 Mar, 10:37

358

አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!

አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሰዋል፤ ያበሰብሰዋልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #ትምህርት_በእንተ_ሐውልታት መጽሐፍ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው
@MoaeTewahedoB
ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

06 Mar, 08:59

559

🕰🔔

6:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰
    

     @MoaeTewahedoB
ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

06 Mar, 07:14

520

እመቤታችን ለምን ሞተች? መልሱ በአጭሩ፦
1) የሞተችው ለመበስበስ ሳይኾን የትንሣኤን አካል ገንዘብ ለማድረግ ነው። ይኸውም ኢመዋቲ አካልን ገንዘብ ለማድረግ እንጂ ለመበስበስ አይደለም። ይህ ዮሐንስ ዘደማስቆ በመደነቅ የገለጸው ነው። ሰውነቷ እንዲበሰብስ ልጇ አለመፍቀዱን ሞታ መበስበስ ሳያገኛት ከልጇ ትንሣኤ በኋላ በልጇ ሥልጣን በሦስተኛው ቀን መነሣቷን ብዙዎቹ ቅዱሳን ሊቃውንት የገለጹት እና እኛም የምናምነው ነው።

2) የሞተችው ሰው ስለ ኾነች ነው። አምላክ በመውለዷ ምክንያት በሕሊናቸው ሰው አይደለችም የሚሉ ሰዎች እንዳይኖሩና በእርሷ ሰው የመኾን ጉዳይ ጥርጣሬ እንዳይፈጠር ሞትን ትቀምስ ዘንድ ልጇ ፈቅዷል። ይህ እነ አብሮኮሮስ በአጽንዖት ያስረዱት ነው። ይህ ምክንያት ቃል ሰው አልኾነም የሚለውን ክሕደትናና እርሷም ሰው አይደለችም የሚለው ስሕተት የሚያርም ነው።

3)  ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዳለው ያረፈችው የልጇን የሞት ጽዋ ለመቅመስ ነው። ይህም እንዲኾን የእርሱ ፈቃድ ነው።

4) ሞቷ የመሸነፍ ሳይኾን የክብር እና የድል እንደ ኾነ እንድናውቅ ነው። ይህን ለመረዳት የሞቷን ዜና ከልጇ ዘንድ የተላከው ቅዱስ ገብርኤል ሊያበሥራት ሲመጣ የድል ምልክት የኾነውን የዘንባባ ዝንጣፊ ይዞ መምጣቱን እነ ማክሲሞስ ተናዛዚው የቀደሙ ትውፊቶችን ማዕከል አድርገው "The Life of The Virgin" በሚለው መጽሐፍ ዘግበዋልና።

5) ሞቷ ተራ ሞት ሳይኾን በመደነቅና በመገረም የሚናገሩት ሞት ነው። ቅዱስ ያሬድ "ማትሰ ለመዋቲ ይደሉ  ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኲሉ" - ሞትማ ለሚሞት ይገባል የማርያም ሞት ግን ለኹሉ ያስደንቃል" የሚለው ለዚህ ነው። እንደ በሥጋና በደም ኾነን በድፍረት ከመናገር ልንቆጠብና ልናደንቅ ይገባል።
@MoaeTewahedoB
ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

06 Mar, 07:14

463

የጎሠቆለ ባሕርይ (Fallen Nature)

ይህን ጉዳይ ትንሽ ዘርዘር አድርጎ ለመረዳት አዲሱን "ዐይነ ልቡና" የሚለውን መጽሐፌን ይመልከቱ። አምስት ኪሎ "ሰርዲኖስ የመጻሕፍት መደብር" ዋና አከፋፋይ ኾኖ በሌሎችም የመጻሕፍት መደብር ታገኙታላችሁና። ዛሬ በአጭሪ ላቀርብ ወዳሰብኹት ጉዳይ ልግባ።

የጎሠቆለ ባሕርይ የሚባለው በዋነኛነት አዳም ከበደለ በኋላ የኾነው ነው። አዳም ከውድቀቱ በኋላ የሰውነት ባሕርዩ አልተለወጠም። ከውድቀት በፊት ኾነ ከውድቀት በኋላ በሰውነት ለውጥ የለምና። ነገር ግን ከውድቀት በፊት በንጹሕ ባሕርይ መልክአ እግዚአብሔሩ ሳይደክም፤ የጸጋ ልብስን ለብሶ በፍጥረት ላይ የገዥነትን ሥልጣን ተጎናጽፎ በክብር ይኖር ነበረ። ሕገ እግዚአብሔርን ተላልፎ በወደቀ ጊዜ ግን የባሕርይ ውድቀት (ሕማም) ወይም ንዴተ ህላዌ (የባሕርይ ድህነት) ገጠመው።

- Fallen Nature በዋነኛነት የመልክአ እግዚአብሔር መድከምን፦ አዳም የተፈጠረው በእግዚአብሔር መልክ ነው። ያን በተፈጥሮ የተሰጠውን መልክአ እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ ባያጣውም በሕግ መተላለፉ ምክንያት አደከመው። አንዱና ዋነኛው የጎሠቆለ ባሕርይ ምልክት ይህ ነው። ኹለተኛው የጎሠቆለ ባሕርይ የሚባለው ከጸጋ እግዚአብሔር የተራቆተ፦ ማለትም እግዚአብሔር አልብሶት የነበረውን የብርሃን ልብስ ያወለቀ፥ የእግዚአብሔር ልጅነትን ያጣ ባሕርይ ነው። ሦስተኛ ከባሕርዩ መጎሥቆል የተነሣ ለኃጢአት የሚያዘነብል መኾን ነው። አራተኛ ጉሥቁል ባሕርይ ያለው ሰውነት ርግማንን ተሸክሟል። ይኸውም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ነው። በሥጋው ወደ መቃብር ገብቶ መበስበስ (ሞተ ሥጋ)፤ በነፍሱ ወደ ሲኦል መግባት ነው (ሞተ ነፍስ) ዋናው ሞተ ነፍስ ከእግዚአብሔር መለየት ገጥሟቸዋል። ስለ ርግማን ሞት ስናነሣ በዋነኛነት የነፍስ ከሥጋ መለየትን ብቻ ሳይኾን የሥጋን ወደ መቃብር ገብቶ መበስበስ፣ የነፍስን ከእግዚአብሔር መለየት (ሞታ ለነፍስ ርሒቅ እም እግዚአብሔር እንዲል ሊቁ ቅዱስ ያሬድ) ይህን ይመለከታል። የሐዲስ ኪዳንን ሞት ለመረዳት "ዐይነ ልቡና" የምትለውን መጽሐፌን ይመልከቱ። እነዚህ በመሠረታዊነት ሰውነትን የጎዱና ያደከሙ ናቸው።

-በባሕርዩ መጎሥቆል ምክንያት የመጡ ጎጂ ያልኾኑ ኹኔታዎች ወይም ሕማማት ዘአልቦቱ ኃጢአት (blemeless Passions) ኃጢአት አልባ ሕማማትን መቀበል ግን በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስለኛ ተብሎ በፈቃዱ ለቤዛነት ብሎ የተቀበላቸው ናቸው፤ እመቤታችን ደግሞ ሰው እንደ መኾኗ ያን እንድትቀበል ልጇ ወዳጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቅዷል። ስለዚህም ተርባለች፣ አዝናለች፣ ተሠቃይታለች፣ ሞታለች። እነዚህ ኹኔታዎች በራሳቸው ኃጢአቶች አይደሉም። እንደ ነውርና ርኲሰትም አይቆጠሩም። ጌታችንም እነዚህን ስለኛ ብሎ የተቀበለው በዚህ ምክንያትና ስለኛ ቤዛ ሊኾነን ነው። ይሄን የተቀበለው ደግሞ ሥግው ቃል እንደ መኾኑ ነው። ስለኛ መራቡን፣ መጠማቱን፣ መገረፉን፣ የእሾህ አክሊል መቀዳጀቱን፣ መራራ ሆምጣጤ መጠጣቱን፣ በመስቀል ላይ ዕርቃኑን መሰቀሉን፣ መሞቱን በእውነት የተቀበላቸው ቤዛ ሊኾነን እንጂ ያን በመቀበሉ ምክንያት የጎሠቆለ ባሕርይን ለብሷል ለመሰኘት አይደለም። ቃል ከሥጋ ከተዋሐደ በኋላ ሥግው እንደ መኾኑ ለቤዛነት የተቀበላቸውን ነገሮች የማዳን ሥራ (Economy of Salvation) እንላለን እንጂ በሌላ መንፈስ እንዲታይ ፈጽሞ አናደርግም።

እነዚህን ነገሮች ሥግው ቃል በፈቃዱ ያደረጋቸው ናቸው። ብዙ ቅዱሳን ሊቃውንትም ቅዱስ ቄርሎስ፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ፣ ቅዱስ ያሬድ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ... "ኅሥሩ" -"ጉሥቁል" ሥጋን ነሣ ሲሉ በአንድ በኩል ከደካማው አዳም ሰውነት የተከፈለውን ሰውነት መንሣቱን ለማሳየት ሲኾን በሌላ በኩል በፈቃዱ ሕማም፣ መከራና ሞት የሚስማማውን ሰውነት ገንዘብ ማድረጉን ለማመልከት ነው። ከዚህ ውጭ ከላይ በዋነኛነት የወደቀ ባሕርይን የሚገልጡ ነገሮች ያሉበትን ሰውነት ለበሰ ለማለት አይደለም። ለዝርዝሩ "ዐይነ ልቡናን" ይመልከቱ። በነገራችን ላይ አኹን እንኳን እኛ ኦርቶዶክሳውያን አምነን፣ ተጠምቀን በቅብዐ ሜሮን ከብረን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን የክርስቶስ አካል ከኾን በኋላ blemeless passions የሚባሉት ያልቀሩልን በራሳቸው ክፉዎች ስላልኾኑ ነው። እነዚህ ነገሮች አዲስ ሰውነትን ገንዘብ አለማድረግን የሚያመለክቱ አይደሉም። ይኸውም ማለት በጥምቀት ከአሮጌ ማንነት ወጥተን ክርስቶስን ለብሰን አዲስ የምንኾን መኾናችንን የሚያስቀሩ አይደሉምና። ከአሮጌ ማንነት በጥምቀት ከተላቀቅን በኋላ መልሰን ባረጀ ሰውነት ውስጥ እንዳለን አድርገን አንናገርም። በትንሣኤ አኹን ከለበስነው የበለጠ የከበረ ኢመዋቲ ኢድኩም ወኢሕሙም የኾነ ሰውነትን መልሳችንን ፍጽሙ ድኅነት ከትንሣኤ በኋላ መኾኑን የሚያረጋግጥ እንጂ አኹን ብትጠመቁም አሮጌ ማንነት ውስጥ ነው ያላችሁ የሚያስብል አይደለም። ሌላው ቀርቶ ያን አዳም በገነት እያለ ያወለቀውን የብርሃን ልብስ ስንጠመቅ እንለብሰዋለን (በተለይ ቅዱስ ኤፍሬምና ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በትኩረት ይህን ያስተምራሉና) ነገር ግን ለኛ ለዐይነ መጭማጮች  ከተጠመቅንም በኋላ ያን የብርሃን ልብስ መልበሳችን አለመታየቱ ያለመልበሳችን ማረጋገጫ ሊኾን አይችልም። ነገር ግን በግልጽ አኹን ያን ልብስ መልበሳችንን ማየት ባንችልም ከትንሣኤ በኋላ ተገልጦ እናየዋለን። ያኔ የሚገለጠው ግን ላልተጠመቁ ሳይኾን በጥምቀት ለከበሩት ክርስቶስን ለለበሱ ነው።  ይህን ልብ ማለት ይገባል።

- አካላዊ ቃል የተዋሐደው ሥጋ ንጹሕ ሥጋ ነው። ምንም ዓይነት ነውርና ነቀፋ የለበትም። መንሣትና መዋሐድ ያለመቀዳደም የኾነ ስለ ኾነ ከእመቤታችን የነሣው ሰውነት ንጹሕና ነውር ነቀፋ የሌለበት ነው። የኃጢአት ጠባሳም አላገኘውም። ጸጋን የተመላ፣ መልክአ እግዚአብሔሩ ያልደከመ፣ ኃጢአት ያልገዛው፣ መርገም ያላረፈበት ንጹሕ ሰውነት ነው። ቅድስት ድንግል ማርያም የተጠበቀችው የጉሥቁልና ውጤት ከኾነው ከጸጋ መራቆት፣ ከመልክአ እግዚአብሔር መድከም፣ ለኃጢአት ከማዘንበል፣ ከመርገመ ሥጋ ወነፍስ፣ ከልማደ አንስት በወሊድ ጊዜ ከሚመጣ ምጥ ኹሉ ነው። ይህ ከእርሷ በቀር ከሰው ወገን ለማንም ቀድሞ የተደረገ አይደለም። ስለዚህም ምክንያት በዋነኛው የውድቀት ምልክት አንጻር አድርገን ስናይ እርሷ የወደቀ ሰውነትን ገንዘብ እንዳታደርግ ልጇ ጠብቋታል እንላለን። የእርሷን ሕይወት በልዩ ኹኔታዎች እንዲመላ ያደረገው እርሱ አምላኳ ነውና። የጎሠቆለ ሰውነትን አልለበሰችም ስንል ሕማም፣ ኀዘን፣ መከራ፣ ሞት የማይስማማውን ሰውነት ገንዘብ አድርጋለች ማለታችን አይደለም። ይህን የሚልም አይኖርም ይልቅስ ከላይ እንዳልኹት ከዋነኛው የጒሥቁልና ውጤት መጠበቋን ማዕከል በማድረግ የወደቀ ሰውነትን አልለበሰችም እንላለን። አበውም ያስተማሩት በዚህ አግባብ ነው። በዝርዝር የእርሷን ጉዳይ ለመረዳት "ዐይነ ልቡና" ይነበብ። ልጇ በፈቃዱ ስለኛ የሞተው በማስመሰል ሳይኾን በአማን ነው። ሞትንም በፈቃዱ የተቀበለው ያ ሥጋ የዕሩቅ ብእሲ ሥጋ ሳይኾን የሥግው ቃል ሥጋ ነውና። ሞትን ስለኛ የተቀበለው ሥጋ ራሱ ለኛ ሕይወትን የሚያድል ነው። የሞተውም ሊበሰብስ ሳይኾን ሞትን በሞቱ ገድሎ ሞት የወረሰውን ሰውነት ሕይወት ሊያለብሰው ነው። ይህ የቅዱስ አትናቴዎስና የቅዱስ ቄርሎስ የትምህርት ማዕከል ነው።
ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

05 Mar, 18:01

894

🕰🔔

3:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰
    

     @MoaeTewahedoB
ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

05 Mar, 15:52

798

“ተወዳጆች ሆይ! ስለ ቅዱሳን ሰማዕታት ብቻ የምትሰሙ አትሁኑ፡፡ እነርሱን ለመምሰልም ተጣጣሩ እንጂ፡፡ ለጊዜው ብቻ የምታደንቋቸው አትሁኑ፡፡ ወደ ቤታችሁ ብቻ ሳይሆን ወደ ልቡናችሁ ውሳጤም ዘልቀው እንዲገቡ አድርጉ፡፡ ዘወትር አስቧቸው፡፡ በልቡናችሁ ጓዳ እንዲገቡ አድርጓቸው፡፡ እናንተን ትተው ይሔዱ ዘንድ አትፍቀዱላቸው፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ዘወትር እያያችኋቸው ትበረታላችሁ፡፡ በእምነት ትጸናላችሁ፡፡ የለበሱትን የጽድቅ ጥሩር፣ የያዙትን ምግባረ ወንጌል፣ የእምነት ጋሻ፣ የመዳን ራስ ቁር፣ የመንፈስ ቅዱስንም ሰይፍ እየተመለከታችሁ ትበረታላችሁ፡፡”

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
@MoaeTewahedoB
ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

05 Mar, 14:07

835

🕰🔔

11:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰
    

     @MoaeTewahedoB
ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

05 Mar, 11:56

1,058

🕰🔔

9:00
ተንስኡ ለጸሎት

በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
እግዚኦ ተሰኃለነ❖
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥
አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥

አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰
    

     @MoaeTewahedoB
ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

05 Mar, 09:42

832

🥰