እንዳንተ ያለ ሰው ፈጣሪ ቢሰጠኝ 🥰
ብቀበል ከሰማይ ሽልማትን ባገኝ 🫶
አምላክ ቢሸልመኝ መንገዴን አቅንቶ
ቢሰጠኝ የልቤን አንተን መሳይ አይቶ👫
ጠርቶ አመጣህና መውደቄንም ሰምቶ 🥀
እንድትሆን ከጎኔ ለኔ ተመኝቶ
ሊያነሳኝ ከጥልቁ አንተን መልዐክ አድርጎ 💫
ሸለመኝ ፍቅርህን ልብ ውበትን ጨምሮ 🌹
አቆመን በሕይወት ያለ አንዳች እሮሮ❣
አሳመረኝ ዛሬ ሕይወትን ሸልሞ
ሰራኝ እንደገና ፍቅርህን ቀምምሞ
ያንተን ፍቅር ለኔ የኔን ላንተ ሰርቶ 💕
ቢመሽም ላይጨልም ፍቅራችንን አፅንቶ ♾
ብወድቅ ሊያነሳኝ እንዳይተወኝ ከቶ
ደስ ሲለን ልንኖር መስመራችን ሰምሮ
አቆመን በአንድ ላይ ጌታ አሳምሮ
ሕይወትን ሰጥቶናል የማይጠፍ ደግሞ♥️