Latest Posts from ማራናታ.....MARANATHA😍 (@maranathawoch) on Telegram

ማራናታ.....MARANATHA😍 Telegram Posts

ማራናታ.....MARANATHA😍
ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደምመስላቸው ጌታ ሰለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንድደርሱ እንጅ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ሰለ እናንተ ይታገሳል።2ኛ ጴጥ 3፥9 ገና በጣም ጥቅት ጊዜ ነው፤ ሊመጣ ያለውም ይመጣል አይዘገይምም። ዕብራ 10፥37
የመወያያ ግሩፕ👇
@Marantawoch

Inbox Comment @Taddyapostolic
12,253 Subscribers
1,643 Photos
73 Videos
Last Updated 06.03.2025 04:17

The latest content shared by ማራናታ.....MARANATHA😍 on Telegram

ማራናታ.....MARANATHA

28 Dec, 15:04

680

በአፍሪካ ውስጥ አንዳንድ አከባቢ እንድሁም በአውሮፓ የምትገኙ ውድ ክርስቲያን ቅዱሳን ወንድሞች እህቶች ሠላምታችን በያላችሁበት ይድረስ እያልኩኝ ለአሰፈላጊ ጉዳይ ስለፈለገናችሁ በያላችሁበት ሆናችሁ በዚህ ዩዘር ነሚ በውስጥ መሠመር ያናግሩኝ፦ @Uwillnverwalkalone

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH
ማራናታ.....MARANATHA

28 Dec, 12:53

824

Hadera eyesus😭
ማራናታ.....MARANATHA

28 Dec, 12:31

801

Ahun ዶዮገና እና ማሬ ንኡሰ መዝሙር እያቀረብ ነዉ
ማራናታ.....MARANATHA

28 Dec, 11:36

895

የ ጠዋቱ ፖሮግራም በዚህ ተጠናቋል የከሰአቱ የሚቀጥል ይሆናል
ማራናታ.....MARANATHA

28 Dec, 11:14

915

ሪዕስ: ማኖር እና መኖር
ማራናታ.....MARANATHA

28 Dec, 10:43

929

Be kes wesen
ማራናታ.....MARANATHA

28 Dec, 07:40

1,047

አሁን ሀደሮ ቃጨቢራ እና ዱራሜ ንዑሰ እየዘመሩ ነው
ማራናታ.....MARANATHA

28 Dec, 07:35

1,010

Ye kidame ken mejemerya amliko
ማራናታ.....MARANATHA

28 Dec, 07:28

1,157

#RIP #አትበሉ !!!
RIP meaning....[ Rest in peace ]
ሁላችን እንሞታለን ።
🖍ሰው ከሞት በኃላ ሰው ስለተማለደ እግዚአብሔር ምንም አያደርግም በህይወት እያለ የሠራው ሥራ እንጂ ነፍሱን በሰላም የምያሳረፈው።
🖍በእርግጥ ሥጋ ከሥጋ ስለይ ልያሳዝን ይችላል ነገር ግን እውነተኛ ክርሰቲያን ኢየሱስ ብቻው አምላክ (አብ) ነው ብሎ አምኖ ከሥጋ ድካም ማረፉ በመንፈሳዊ ዓይን ካየን የምያስደስት እንጂ አያሳዝንም ።
🖍ሰው በህይወት እያለ የሠራው ሥራ ጽድቅ ወይም ኃጥአት ብሆን ኢየሱስ ለእያንዳንዱ በመጨረሻ ዋጋ ይሰጣል በራዕይ 22:12 እንደተጻፈ ።
🖍እኛ ነፍስ በሰላም ትርፍ ስላለን አይደለም እኛ ማደረግ ያለበት ነገር ብኖር ለምያዝኑ ቤተሰብ የምያጽናና ቃል መናገር :- እግዚአብሔር መጽናናትን ይሰጣችሁ , አይዞአችሁ እኛ ልንሄድ ወዳለው ቦታ ከእኛ ቀድማ/ሞ ሄዷል አታዝኑ....ወዘተ ናቸው ።
🖍ሰው ከሞት በኃላ ሰው ስለማለደ እግዚአብሔር ምንም አያደርግም በህይወት እያለ የሠራው ሥራ እንጂ ነፍሱን በሰላም የምያሳረፈው።
🖍እውነተኛ ክርስቲያኖች ሰው ከሥጋ ድካም አርፎ ወደ አምላኩ ከሄደ RIP አትበሉ እኔን ብሆንም።
🖍ሁላችንም አንድ ቀን በበጉ ሠርግ እንገናኛለን ከቅዱሳን ጋር እስከዛ ድርስ እምነታችሁን አጥብቃችሁ ያዙ ካመነንበት ግዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ቀርቧልና አይዞአችሁ በርቱ...😭
አመሰግናለሁ
By ወንድማችሁ ነኝ
ማራናታ.....MARANATHA

28 Dec, 04:13

1,137

የማለዳ ትምህርት

ቀን 19/04/2017 ዓ/ም

ርዕስ፦ እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን እንመላለስ

ውድ ቅዱሳን! እንደምን አደራችሁ? ብለን ስላምታችንን እያቀረብን የማለዳ ትምህርታችንን እናቀርባለን። ለዛሬ ያለን ትምህርት " እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን እንመላለስ" የሚል ነው።

ብዙ ሰዎች ባለንጀራቸውን ፤ ጓደኛቸውን፤ ዘመዳቸውን..... ወዘተ ደስ ለማሰኘት ብለው እግዚአብሔር የማይገኝበት ቦታ ይውላሉ። በዛሬው ቀን እኔ፤ አንተ፤ አንች ዬት ልንውል ነው?

🚶‍♂ሰውን ደስ የሚናሰኝበት ቦታ ነው ወይስ እግዚአብሔርን ደስ የሚናሰኝበት ቦታ ነው?

አንዳንድ ሰዎች ስነጋገሩ " እኔ ከጓደኛዬ ከሚለይ ብዬ ዛሬ መጠጥ ቤት ገባሁ፤ እሱ አልኮል ነገር ስጠጣ ብቻዬ ለስላሳ ነገር ከሚጠጣ ብዬ እኔም ከእሱ ጋር ጠጣሁ፤ ጓደኛዬ አሳሰተኝ" ይላሉ። ይህ የማንን ሀሳብ ለማስደሰት ያደረገ ይመስላችኋል?

የጓደኛውን ሀሳብ ካላችሁ ልክ ናችሁ። የእግዚአብሔር ቃል ግን

🕎በ1ኛ ተሰሎ 4፥1 ላይ " እንግድህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ፦ ልትመላለሱ እግዚአብሔርንም ደስ ልታሰኙ እንዴት እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ እንደ ተቀበላችሁ ፤ እናንተ ደግሞ እንደሚትመላለሱ ከፍት ይልቅ ትበዙ ዘንድ በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፥ እንመክራችሁማለን" ይላል።

ይህ መልካም ምክር ነው። ለዛሬ ውሎአችንም ይሁን ለወደፊት ለሚንኖረው ኑሮአችን ይጠቅመናል። በዛሬ ቀን እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን እንዋል። በጓደኞቻችን ግፍት ተመርቸን ሀጢያት ውስጥ አንገኝ አደራ። ምክንያቱም፦ ሰውነታችን ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘትና በእርሱ ሀሳብ ብቻ ለመመላለስ የተፈጠረች ናት።

🕎 ሮሜ 12፥1 " እንግድህ ወንድሞች ሆይ፦ ሰውነታችሁ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መስዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው። የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታወቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጅ ይህን አለም አትምሰሉ" ይላል።

🗣 ይህን አለም አትምሰሉ ማለት ምን ማለት ነው? እኛ አለምን የሚንመስለው በፊታችን ሳይሆን በሀሳባችን፤ በአነጋገራችን፤ በአለባበሳችን፤ በአመጋገባችን ከአለማዊ ሰው ጋር ስንውል ነው አለሚን የሚንመስለው።

ስለዚህ ከዛሬ ጀምረን ውሎአችን እንቀይርና ከጓደኞቻችን ሀሳብ አንስተን ወደ እግዚአብሔር ሀሳብ እንመልስ።

🤷‍♂🤷‍♀ በእኛ ውሎ እግዚአብሔር ይደሰት እንጅ እንዳያዝነን አደራ፤ አደራ ውድ በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ ቅዱሳን ።

እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን እንመላለስ

🤷‍♂🤷‍♀ በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ 🤷‍♂🤷‍♀

የውሎአችን ስንቅ ከማራናታ

መልካም ቀን!!!!

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH

Inbox @Taddyapostolic