Latest Posts from ማራናታ.....MARANATHA😍 (@maranathawoch) on Telegram

ማራናታ.....MARANATHA😍 Telegram Posts

ማራናታ.....MARANATHA😍
ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደምመስላቸው ጌታ ሰለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንድደርሱ እንጅ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ሰለ እናንተ ይታገሳል።2ኛ ጴጥ 3፥9 ገና በጣም ጥቅት ጊዜ ነው፤ ሊመጣ ያለውም ይመጣል አይዘገይምም። ዕብራ 10፥37
የመወያያ ግሩፕ👇
@Marantawoch

Inbox Comment @Taddyapostolic
12,253 Subscribers
1,643 Photos
73 Videos
Last Updated 06.03.2025 04:17

The latest content shared by ማራናታ.....MARANATHA😍 on Telegram

ማራናታ.....MARANATHA

05 Dec, 12:20

1,002

𝑺𝒊𝒏𝒈𝒆𝒓 𝑺𝒂𝒎𝒖𝒆𝒍 𝑨𝒔𝒆𝒇𝒂🎙️
🎵𝑵𝒆𝒘 𝑺𝒊𝒅𝒂𝒎𝒊𝒄 𝑨𝒑𝒐𝒔𝒕𝒐𝒍𝒊𝒄 𝒔𝒐𝒏𝒈🎵

𝐁𝐮𝐥𝐮𝐥𝐮 𝐤𝐚𝐲𝐞𝐞𝐬𝐬𝐞 𝐦𝐚𝐧𝐧𝐚 𝐚𝐬𝐬𝐞 𝐰𝐨𝐫𝐢𝐞𝐡𝐮
𝐃𝐢𝐤𝐚'𝐚𝐡𝐨 𝐢𝐬𝐢 𝐲𝐢𝐧𝐨𝐲𝐢𝐡𝐚 𝐤𝐚𝐲𝐞𝐞𝐬𝐢𝐞𝐡𝐮
𝐓𝐢𝐧𝐢 𝐥𝐞𝐞𝐥𝐭𝐚𝐧𝐚 𝐢𝐬𝐢𝐫𝐞 𝐪𝐚𝐚𝐠𝐚𝐲𝐢 𝐬𝐚𝐦𝐦𝐢 𝐝𝐢𝐲𝐞𝐞𝐦𝐦𝐨. (2)
𝐌𝐢𝐬𝐡𝐢𝐡𝐮 𝐦𝐢𝐬𝐡𝐚𝐧𝐚 𝐛𝐚𝐱𝐢𝐫𝐞 𝐲𝐚𝐚𝐧𝐚 𝐤𝐚𝐞 𝐤𝐮𝐛𝐛𝐞𝐦𝐦𝐨

𝐇𝐚𝐰𝐚𝐦𝐨𝐨𝐦𝐦𝐨𝐡𝐚 𝐡𝐚𝐚𝐫𝐞 𝐦𝐚𝐧𝐧𝐚 𝐚𝐬𝐬𝐢𝐧𝐨𝐞 𝐦𝐚𝐧𝐧𝐚 𝐚𝐬𝐬𝐢𝐧𝐨𝐞 𝐚𝐧𝐞 𝐢𝐬𝐢
𝐌𝐢𝐬𝐡𝐚𝐦𝐨𝐦𝐨𝐡𝐚 𝐡𝐚𝐚𝐫𝐞 𝐦𝐚𝐧𝐧𝐚 𝐚𝐬𝐬𝐢𝐧𝐨𝐞 𝐦𝐚𝐧𝐧𝐮 𝐭𝐚𝐚𝐬𝐡𝐢𝐧𝐨𝐞 𝐚𝐧𝐞 𝐢𝐬𝐢
𝐆𝐢𝐦𝐛𝐨𝐲𝐢𝐡𝐮𝐰𝐚 𝐰𝐚𝐚𝐫𝐞 𝐦𝐚𝐧𝐧𝐚 𝐚𝐬𝐬𝐢𝐧𝐨𝐞 𝐦𝐚𝐧𝐧𝐮 𝐭𝐚𝐚𝐬𝐡𝐢𝐧𝐨𝐞 𝐚𝐧𝐞 𝐢𝐬𝐢
𝐌𝐢𝐬𝐡𝐚𝐦𝐞 𝐠𝐚𝐭𝐞𝐰𝐨𝐞𝐧𝐚 𝐠𝐚𝐥𝐚𝐭𝐚 𝐞𝐞𝐦𝐨𝐬𝐢 𝐠𝐚𝐥𝐚𝐭 𝐞𝐞𝐦𝐨𝐬𝐢 𝐦𝐨𝐡𝐨𝐧𝐚 𝐲𝐞𝐬𝐮𝐬

𝐌𝐚𝐧𝐧𝐮 𝐤𝐮𝐥𝐚𝐚𝐭𝐚 𝐚𝐧𝐞𝐭𝐚 𝐱𝐞'𝐧𝐞 𝐝𝐢𝐰𝐢𝐞𝐡𝐮
𝐌𝐢𝐧𝐬𝐡𝐞 𝐡𝐮𝐧𝐨𝐲𝐢𝐡𝐚 𝐬𝐡𝐚𝐥𝐭𝐚𝐤𝐢 𝐢𝐥𝐥𝐞 𝐥𝐚𝐢𝐞𝐡𝐮
𝐈𝐬𝐢𝐥𝐥𝐚 𝐧𝐚𝐚𝐝𝐞 𝐠𝐚𝐥𝐚𝐭𝐚 𝐚𝐝𝐡𝐢𝐫𝐨 𝐬𝐚𝐦𝐦𝐢 𝐝𝐢𝐲𝐞𝐞𝐦𝐦𝐨. (2)
𝐒𝐨𝐧𝐠𝐨𝐭𝐞 𝐚𝐥𝐛𝐚 𝐢𝐬𝐢𝐫𝐞 𝐤𝐮𝐥𝐚𝐲𝐢 𝐦𝐚𝐠𝐚𝐧𝐬𝐢𝐫𝐞𝐞𝐦𝐦𝐨

𝐌𝐚𝐧𝐧𝐮 𝐦𝐚𝐬𝐚𝐚𝐥𝐞 𝐝𝐢𝐭𝐢𝐝𝐡𝐞𝐡𝐨 𝐲𝐞 𝐡𝐮𝐧𝐞 𝐡𝐚𝐫𝐞𝐞𝐧𝐚
𝐑𝐚𝐫𝐞𝐞𝐦𝐦𝐨 𝐫𝐚𝐚𝐫𝐞 𝐡𝐢𝐝𝐡𝐚𝐚𝐡𝐚 𝐡𝐨𝐨𝐠𝐞 𝐣𝐚𝐧𝐣𝐮𝐫𝐚𝐲𝐢 𝐡𝐞𝐫𝐞𝐞𝐧𝐚
𝐊𝐚𝐰𝐚 𝐤𝐚'𝐚 𝐡𝐨𝐨𝐠𝐞 𝐢𝐬𝐢𝐰𝐚 𝐫𝐚𝐚𝐫𝐞 𝐟𝐨𝐥𝐢𝐬𝐡𝐢𝐫𝐨𝐦𝐦𝐨. (2)
𝐅𝐨𝐣𝐨 𝐝𝐢𝐰𝐞𝐞𝐧𝐚 𝐦𝐚𝐧𝐧𝐮𝐧𝐧𝐢 𝐭𝐚𝐚𝐥𝐞 𝐠𝐚𝐥𝐚𝐭𝐮𝐲𝐢 𝐝𝐚𝐚𝐦𝐦𝐨

𝐇𝐚𝐬𝐡𝐬𝐡𝐚 𝐛𝐚𝐫𝐫𝐚 𝐢𝐤𝐤𝐨 𝐢𝐬𝐢𝐫𝐞 𝐲𝐞𝐞𝐧𝐚 𝐡𝐨𝐫𝐨 𝐝𝐢 𝐢𝐤𝐤𝐚𝐞
𝐃𝐚𝐰𝐢𝐭 𝐠𝐞𝐝𝐞 𝐤𝐚𝐞 𝐤𝐮𝐛𝐛𝐞𝐧𝐚 𝐦𝐚𝐧𝐧𝐮 𝐦𝐚𝐲𝐚𝐚𝐞
𝐇𝐚𝐭𝐭𝐨 𝐝𝐢𝐲𝐞𝐞𝐦𝐦𝐨 𝐚𝐧𝐞𝐫𝐚 𝐚𝐬𝐞𝐰𝐨𝐨𝐭𝐚 𝐚𝐧𝐢𝐥𝐥𝐚 𝐚𝐟𝐨𝐨𝐦𝐦𝐨 (2)
𝐃𝐢𝐛𝐞𝐧𝐨 𝐠𝐚𝐧𝐚𝐲𝐢 𝐱𝐮𝐫𝐮𝐦𝐛𝐚 𝐮𝐟𝐮𝐮𝐟𝐚𝐲𝐢 𝐠𝐚𝐥𝐚𝐭𝐚 𝐞𝐞𝐦𝐦𝐨
𝑴𝒐𝒐𝒉𝒐𝒏𝒂 𝒚𝒆𝒔𝒖𝒖𝒔𝒊 (4)

@MARANATHAWOCH
ማራናታ.....MARANATHA

05 Dec, 12:18

962

አመታዊ #የአገልጋዮችና_መስካረዎች_ስልጤናና_ኮንፈረስ በታላቅ በረከት በዛሬው ዕለተ በታላቅ በእግዚአብሔር ጉብኝት
በደመና ነው የመራኝ እንዳልወርቅ ብኢሳት አመድ ነው የመራኝ አሜን
አሁንም የቀሪ ዘመናችሁ እግዚአብሔርን አብርሃም እንደባረከ እንዲሁም ደሞ ሙሴና ህዝቡን በደመና እንደመራ እንደመራ በኖራችሁ በዘመን ሁሉ ሃይልና ሞገስ ከእናንተ አይለይ አባቶቼ እወዳችኋለሁ

@MARANATHAWOCH
ማራናታ.....MARANATHA

05 Dec, 12:16

810

#WARA2017

የአገልጋዮች ሴሚናር በዋራ!
ሕዳር 2017 ዓ.ም

በደስታ አንድ ቀን በሰማይ ላይ
የተሰዋልንን ጌታን ስናይ



@MARANATHAWOCH
ማራናታ.....MARANATHA

05 Dec, 12:12

793

#Update

የኢትዮጵያና የአለማቀፍ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን 56ኛው የአገልጋዮች ሴሚናር በዋራ ሜዳ ላይ ዛሬ ይጀምራል። ጉባኤውም ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ይሆናል። ጌታ ኢየሱስ አገልጋዮቻችንን ይባርክልን።

@MARANATHAWOCH
ማራናታ.....MARANATHA

05 Dec, 12:11

849

Eve of 56th Apostolic church international Ministerial seminary !

በቤተክርስቲያናችን ለወንጌልና ለዶክትሪን የምንተጋውን ያህል ለመንፈስ አንድነት እንተጋለን። ቢሾፕ ደጉ ከበደ (በ55ኛ ዓ.ም በአገልጋዮች ሴሚናር ላይ የተናገሩት)

የእውነተኛዋ ቤተክርስቲያን የጅማረዋ እሳት የተለኮሰው ከኢየሩሳሌም ነው የፍጻሜዋ ለንጥቀት የሚያዘጋጅ እሳት የሚወጣው ግን ከኢትዮጵያ ነው ይህም ዓለምን ያጥለቀልቃል። (ቢሾፕ አማዶር)

“ወደዚያም ኮረብታ በደረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ የነቢያት ጉባኤ አገኙት፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ወረደበት፥ በመካከላቸውም ትንቢት ተናገረ።” (1ኛ ሳሙ 10፥10)

ዓመታዊ የአገልጋዮች ሴሚናር በዋራ ሜዳ ሳስብ ከግብፅ የወጣውን የእስራኤልን ልጆች ከነዓንን አንግበው እየተጓዙ ሳሉ ድፍን አንድ ዓመት በሲና ተራራ እግዚአብሔር አስተምሯቸዋል፤ ለቀጣዩ የአሕዛብን አገራት የሚወርሱበትን መንፈሳዊ ትጥቅና አደራረግ መክሯቸዋል ሕግና ስርዓት ጽፎ ሰጥቷቸዋል፤ ደግሞ ደጋግሞ አሳስቧቸዋል፤ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእግዚአብሔር ሥራ ብቻ የሚለዩ አገልጋይ ካህናት እንዲሆን አንድን ነገድ ለራሱ ሥራ ብቻ ለይቷል ይህም የሌዊ ልጆች ሆኗል።

እግዚአብሔር እስራኤልን ሲያስተምርም በየምድባቸው አድርጓል ይህንንም ያደረገው በሦስት ተራ ነበር።

1ኛ. ሙሴን ለብቻው (ዘጸ 19፥3 )
2ኛ. ሰባ ሽማግሌዎችን (አገልጋዮችን) (ዘኅ 11፥16) ሌዋውያኑም እንዲሁ
3ኛ. ጠቅላላውን የእስራኤል ሕዝብን (ዘኅ 8፥9)

የእስራኤል ልጆች በእነዚያ በአንድ ዓመት የሲና ተራራ ዙሪያ በቆየባቸው ጊዜአት ከአሥር ጊዜ ያላነሰ ሙሴ ወደሲና ተራራ እንደወጣና ከእግዚአብሔር ጋር ምክክር እንዳደረገ መጽሐፍ ቅዱሳችን ይናገራል። ውጤቱም “በእስራኤል ውስጥ መሪዎች ስለ መሩ፥ ሕዝቡም ነፍሳቸውን በፈቃዳቸው ስለ ሰጡ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ።” መሳ 5፥2 ይላልና።

ኢየሱስም በሥጋ በምድር በተመላለሰበት ዘመን ወደተራራ ይዟቸው እየወጣ ወደእርሱ አቅርቦ በጠንካራ ቃል የመከራቸው እና ዋኖች (ማቴ 17፥1) የተባሉ እንዳሉ እናነባለን። ይህ አድሎ አይባልም ይህ ጌታ ሰውን ከሰው ለይቶ ይመለከታል የሚያስብል የእግዚአብሔር ፍሕታዊነትን የሚጋፋ አይደለም ለአካሉና ለጋራ ዓላማ ጥቅቶችን አስታጥቆ መንፈሱን አፍስሶ ኃይሉን ሞልቶ ከድካሙ አበርትቶ ለብዙኃኑ እንዲተርፉ ያደርጋል።

“.....ሌዋውያኑም ደግሞ በፊታችሁ አለቆች ይሆናሉ፤ በርትታችሁም አድርጉ፥ እግዚአብሔርም መልካም ከሚያደርግ ጋር ይሁን።” 2 ዜና 19፥11 ተብሎ እንደተጻፈው ሌዋውያን በፊታቸው አለቆች እንዲሆኑ ይመርጣል።

የዓለም ኃይማኖት ጓዳው በሙሉ ግራ በተጋባበት በዚህ ዘመን አንድ ንግግር መናገር ቀርቶ አንድ የጋራ ስም ይዞ መቀጠል ባልቻሉበት የባቢሎንን የግንብ ሠራተኞችን ቋንቋቸው ያደባለቀ አምላክ እጁ ዛሬም አለችበት እላለሁ። ሰንሰለታማ የአመራር አሠራርን ተዋረድ የማይቀበሉ ሰማይ ተኮር ሳይሆን ገንዘብ ተኮር በሆነበት ዘመን ይህችን ቤተክርስቲያን ከአሜሪካ እስከ አውስትራሊያ ከደቡብ አፍርቃ እስከኢስያ በዓለም በአራቱም ማዕዘናት ተበታትነው የሐዋርያትን እውነት በመስዋዕትነት ተሸክመው እየሮጡ ያሉ ከእሳት የተነጠቁ ትንታግ (ዘካ 3፥2) አገልጋዮች የእርስበርስ መታያ ቀኑ እነሆ ደረሰ ይሄውም በዋራ ሜዳ ላይ ቁጥራቸው አይገመትም አዲስ ለመስዋዕት የሚቀቡ ብዙ ኢያሱዎች አሉ። “የሰማይን ሠራዊት መቍጠር የባሕርንም አሸዋ መስፈር እንደማይቻል፥ እንዲሁ የባሪያዬን የዳዊትን ዘርና የሚያገለግሉኝን ሌዋውያንን አበዛለሁ።” (ኤር 33፥22) የሚል ቃል ኪዳን ስላለው ገና ብዙ ለእግዚአብሔር ሥራ ማቃቸውን ጨርቃቸውን ጥለው የሚለዩ አሉ።

ምን እንደሚል ባላውቅም እድገቷ አስፈሪ ነው፤ የዓለምን ፊት ለመሙላት አሕዛብን ለመውረስ ከማኮብኮብ አልፋ ሩጫ ውስጥ ገብታለች። ኢየሱስ የቤቷ ብቸኛ ራስ አድርጋ ኢየሱስን ለዓለም አስተዋውቃ ኢየሱስን በጥምቀት ሰዎች እንዲለብሱ አድርጋ ኢየሱስ ብቻ (Only Jesus ) የሚል ስም ሰዎች የለጠፉባት ኢየሱስን ና የማለት የማራናታ ጥሪ ስልጣን የተሰጣት የአንዱ ሙሽራ አንዲት ብቸኛ ሙሽራይቱ የሆነች የክርስቶስ አካል ቤተክርስቲያን ይህች ናት። ኢየሱስ ብላ ጀምራ ቋንቋው ሳይደባልቅባት ኢየሱስን ትቀበለዋለች።

ዋናውን ለብቻው አገልጋዮችን ለብቻቸው ጠቅላላውን ሕዝብን እንዲሁ ለብቻቸው ለምንድነው በዚህ መልኩ በየምድቡ እንዲሆን እግዚአብሔር ለምንድነው የወደደው?(የዛሬይቱም ቤተክርስቲያን የተከተለችው ፈለግ ያው ራሱ ስለሆነ)

1ኛ. ቤተክርስቲያን የመንፈስ አንድነት እንዲጠበቅ አንድ ቋንቋ አንድ መንፈስ እና አንድ ንግግር መስማት “ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ አሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ.....” (1ኛ ቆሮ 1፥10)

2ኛ. የቤተክርስቲያን የወደፊቷ ራዕይ እና አሁናዊ ዕድገቷ በግልጽ ለሁሉም በጋራ መነጽር እንዲታይ ማድረግ ቤተክርስቲያን በሙላት እያንዳንዱ አገልጋይ ማየት እንዲችል (በሰፈሩ ባለችው በአንዲት አጥቢያ ትልቁን አካል እንዳይገምት)

3ኛ. የቤተክርስቲያን የዕድገቷን ልክ የሚመጥንና ዘመኑን ለመዋጀት የሚያስችል ቁመና ለአገልጋዮች እንዲኖራቸው ማስቻል አጋዥ ጥቆማ በዋኖች መቀበል። (ዓመቱን ሙሉ ሲያስተምር የቆየ አገልጋይ አሁን በተራው እሱም ቁጭ ብሎ የትምህርት አጥንትን እንድግጥ)

4ኛ. አገልጋዩ በራሱ ሚዛን አልያም በሰፈሩ ሚዛን ትክክል መስሎት እየተገበረ ያላቸው መልካም የመሰሉ ነገር ግን በቤተክርስቲያንና በመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን ዕይታ እንዲቃኙ ማድረግ እና ሌሎችም የዋኖችን የሸክም መጋራቶች ይኖሩታል።

የሌዋዊው  ዕጣፈንታ !

የአገልጋዮች የምድር በረከት

“አቤቱ፥ ሀብቱን ባርክ፥ የእጁንም ሥራ ተቀበል፤ የሚነሣበትን ወገብ ውጋው፥ የሚጠሉትም አይነሡ።” (ዘዳግም 33፥11)

የአገልጋዮች የሰማይ ዕድል

“የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፥ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይሆናል፤ የሚያገለግለኝም ቢኖር አብ ያከብረዋል።” (ዮሐ 12፥26)

ክብር ለኢየሱስ ይሁን!

በወንድም ሕዝቅኤል ጴጥሮስ የተሰናዳ!

@MARANATHAWOCH
ማራናታ.....MARANATHA

05 Dec, 08:24

1,161

ሰዎች በአሁኑ ሰዓት ማኀበራዊ ሚዲያን ለጉድ ይጠቀማሉ ነገር ግን በውጤት ደረጃ ግን ያን ያህል ነው። ለምን ቢባል በማኀበራዊ ሚዲያ ላይ የሚያየው ይሁን የሚሰማውን መረጃ ይስማል ወይም ያያል እንጂ ወደ ውጤት ለመቀየር አይሠራም።ይህ ሀሳብ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽኖ ብቻ ሳይሆን በቤተክርስቲያን እንቅስቃሴ ላይ ያለ ሁኔታን ልያካትት ይችላል።

ታዲያ መሠማት ጥሩ ሆኖ መከታተል ጥሩ ሆኖ ግን ወደ ተግባር አለመቀየር በኖኀ ዘመን እንደሆነ ለሰዎች ጥፍት የሚያመጣ እንዳይሆን እሰጋለሁ። ሰው ልጅ አለመሠማት ይሻላል ግን ስምተው ነው የሚያሰማርሩት።

በኖኀ ዘመን የነበሩ የሰው ልጅ ብዛት እንደ ሃስቶርካል ወደ 20ሚልዮን ይደረሳል ይላል....ነገር ግን ይህ ሁሉ ሰው በኖኀ የጥፋት ወኃ እንደሚመጣ በመቶ ዓመት ጉዞ ውስጥ ሰምተውታል የሚገርመው። ግን ከእነዚህ ሰዎች ከጥፋት ውኃ የዳኑት 8ነፍሳት ብቻ ነው። በእኔ ውስጥ አንድ ስጋት አለኝ እሱም በዚህ ዘመን አዎንታዊ የሆነ ሀሳብን በየቤተክርስቲያኑ ይሁን ከቤተክርስቲያን ውጭ ባለው አካሄድ ላይ ሰምቱዋል ግን በተግባር ደረጃ ላይ ስታይ ግን ዜሮ ነው።

ይህ ስጋት ያላችሁ ካላችሁ እስቲ መፍተሄው ምን ይሁን ትላላችሁ? ይህ አሁን ሌላ ሰውን ለመገምገም ሳይሆን ራስህን ብቻ ነው!!
ማራናታ.....MARANATHA

04 Dec, 03:46

1,854

የማለዳ ትምህርት እለት (እሮብ)
25/03/2017

አርዕስት፦ ምስጉን ነህ!

ወድ የማራናታ ቻናል ተከታዮች እንድምን አላችሁ እያንዳንዱ ቀናት ውስጥ የሚወረወሩብን የሰይጣን ፍለጻን ከእኛ ዘንድ በማራቅ ለዛሬው ቀን በምህረቱ አድረሶናል ምስጋናው ይግባው ወደ ማደሪያው እያልኩኝ ወደ ዛሬ ትምህርት ክፍል አልፋለሁ የትምህርቱ ርዕስ፦#ምስጉን_ነህ! በሚል አርዕስት እንማራለን።

ይህን ቃል ስምተን የማናውቀው አይደለም ሁል ጊዜ እንሰማለን እናነባለን ግን ላናሰተውለው ይችል ይሆናል። አብዛኛው ጊዜ ሰምዮች ከሆነን ወይም አንብበን ወደ ውጤትም የማንቀየር ከሆነ የቃሉ ዋጋ አቅምን/ውጤቱን ያጣል እና አንብባችሁ ወደ ተግባር የሚትቀየሩ ሁኑ እያልኩኝ የእግዚአብሔር መንፈስ እንዳሳሰበኝ ለእናንተ ላካፍላችሁ።

ብዙ ጊዜ ሰዎች ለምስጉን ሰው ምን አይነት ምንነት ይሰጡ ይሁን? ለባሕሪያው ብዬ እያሰብኩ ይህ መልእክቴ ወደ ልበ ከመጣ ጊዜ ጀምር አሰላስል ነበረና.... በሰዎች ዘንድ ምስጉን የሚባል ሰው ሰውን የሚያከበር፣ ደግ ሰው፣ በሰው ዘንድ የሚጠላ ተግባር የማያደርግ/የማይፈጽም በእያንዳንዱ ሕይወት እንቅስቃሴ ላይ ጥንቃቄን የሚያዛውተር፣ ከራሱ በላይ ለወንድሙ የሚኖር ወይም የሚያዝን ሰውን ሰዎች ምስጉን ነው በማለት ይገልጹታል/ ይጠሩታል በትንሹ። ሰውም ይህንን ማዕረግ ወይም ስም ለማግኘት በብዙ መንገድ ይጥራል ከሚያወራው ከአንድበት ንግግር አንስቶ የተለያዩ ድርጊቶችን በማሰተዋል ለማከናወን ይለፋል ይሁንና ይህ ሁሉ ጥረት በሰው ዘንድ ላለው መልካም ስም የሚከፈል መሥዋዕትነት ነው። 👇

እግዚአብሔርስ በራሱ አጠራር ምስጉን የሚል ሰውን በምን መሥፈርት እንደሚጠራ ያሰቀመጣቸውን መሥፈርቶችን እንመልከት እስቲ፦

መዝሙር 1፥1፦ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ። 2፦ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል።
3፦እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
4፦ክፉዎች እንዲህ አይደሉም፥ ነገር ግን ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ ናቸው።
5፦ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ፥ ኃጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር አይቆሙም።
6፦እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥ የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች።

ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ...ይህ ቃል ትልቅ የእግዚአብሔር ቃል ነው። እስቲ በክፉዎች ምክር ያልሄደ የሚለውን ቃል ስናይ በእኛ አረዳደር የክፉ ተግባሮችን እንዴት ብለን የሚንገለጸው በጣም ከተማረነው ትምህርትም እንድሁም ከተቀበላናቸው ጋር ስናይ... ክፉ ተግባሮች ብለን የሚንጠራው በጥቅቱ መሥፈርት ስጥተን እነዚህ ብቻ ናቸው ብለን ሰይመናል አመንዝራ የሚያደርግ ከሰው ጉቦ የሚቀበል ወዘተረፈ መሠፈረቶችን እንሰጥ ይሆናል እሱም ትክክል የሆነ ሀሳብ ነው። ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ከላይ በኩል ከጠቀስኩቸውም ጅምሮ ሌላ ደግሞ የተለቀና እግዚአብሔር ምስጉን የሆነ ሰው በክፉዎችም ምክር የማይሄድ ሰው የማያደርግ ሥርዓት ብሎ በዋናነቱ ያሰቀመጠው ብቻውን ገዥ የሆነ አንዱን አምላክ የማይለወጥ በብዙ ቁጥር ባለው ቃል የማይጠቀመውን ሰው እግዚአብሔር ምስጉን ሰው ነው ይላል።

ለስሙና ለብቻኝነቱ እግዚአብሔር በጣም ይቀናል።
በሚል 2፥10፦ ❝ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? በብሉይ ኪዳንም ይሁን በአዲስ ኪዳን እግዚአብሔር የራሱን ማንነት አስረግጦ የተናገረው በቃሉ እያለ የሚያጣምም ሰውን ክፉ ሰው ብሎ ነው የሚጠራው።

እሥራኤላዊያን በብዙ መንገድ ከእግዚአብሔር ዘንድ የደረሰው ቅጣት በክፉዎች ምክር ተታልሎ እግዚአብሔርን በሌላ ጣኦት ስቀየሩ ወይም ስሰግዱ ነው። በአሁኑ ዘመንም እግዚአብሔር ያ አምላክ ስለሆነ በተለያዬ መቅሠፍት አለምን የሚቀጣው የእግዚአብሔርን አንድነትን በአስተማሪዎች በኩል ወይም በክፉዎች አማካኝነት ስያጠፉ ነው። መንጋው ምንም የሚያውቀው ነገር ባይኖርም ግን ከአሰተማሪዎች ለተቀበሉት ትምህርት ተገዥ ሆነው ስለሚጓዙ መንጋውን ይቀጣል። ይህ ከድሮ ዘመንም ጀምሮ ያለ ነው።

የክፉ ትምህርትን የማያስተውል በሕይወቱ ላይ የመጣውን የማይረዳ የክፉ ትምህርትን ተቀብሎ በኃጢአት መንገድ የሚጓዝ ሰውን መጽሐፍ ቅዱስ ስናገር እንድህ ይላል በመዝ (92)፥6፦ሰነፍ ሰው አያውቅም፥ ልብ የሌለውም ይህን አያስተውለውም። ክፉ ሰው ክፉቱን በክፉ ተግባር ላይ ነው እንጅ የሚያውቀው አንዳች የለም ክፉን መፈጹሙን የለመደው አዕምሮ ውሰጠ ሕሊናው ነገሩ ክፉ እንደሆነ ቢነገረውም እንኳን ከመተገበሩ አይመልስም ለዚህ ነው ዳዊት ስነፍ ሰው አያውቅም ያለው መቺም ቢሆን ክፉ የሚያስትበት መንገዱ ነው እንጂ የምታየው የእግዚአብሔር አንድነት/ መልካምነት አይደለም ማለትም ጠማማነትና የእግዚአብሔር እውነታን ለመቀየር ነው ሥራው ለዚህ ነው ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ ያለው። በተለይ ልብ ማለት ያለባችሁ በተለያዬ ሁኔታ ክፉዎች ከእግዚአብሔር ከፀጋው ዙፋን ልያረቁ የተለያዬ አሳች የሆነ መንገድን መልካም በሚመስለው መንገድ ያሳዩታል ግን በኮንሸንስል የማንረዳ ከሆነን ዋጋ ልያሰከፈለን ይችላል።

ስለዚህ ከየትኛውም ከክፉ ሰዎች አካሄደ ባለመጓዝ መጠንቀቅ ለመደናችን ትልቅ ነገር ነው። የእግዚአብሔርን ስምና አንድነትን ለመቀየር እንደ ባላቅ አሳች መንገድ የሚጠቀሙ አስመሳይ የሆኑ ጓደኞች አይጠፉምና ለመደናችን ስንል በትኩርት መጠንቀቅ ያሻል እግዚአብሔር በሁሉ ከክፉ መንገድ ይጠብቀን ከክፉ ሀሳቢዎችም ይሰውረን።

መልካም ቀን ይሁንላችሁ!!

Group @marantawoch

🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂🤷‍♀

🌻የማለዳ ትምህርት በየማለዳ🌻
🌸የውሎአችን ስንቅ ከማራናታ🌸

🌼መልካም ቀን!!!🌼

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH
ማራናታ.....MARANATHA

03 Dec, 07:34

2,536

አስቸኮይ የእርዳታ ጥሪ!
ውድ በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጪ ያላችሁ በሙሉ፦
በኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተ/ያን የወላይታ ሶዶ ብሩ ተስፋ አጥብያ አገልጋይ በጣም የምንወደው ፤እጅግ ትሁትና ቅን የእግዚአብሔር አገልጋይ ቄስ ቶማስ ቶራጎ በደረሰበት የጤና እክል ምክንያት ህንድ ሀገር ህክምና እየተከታተለ መሆኑ ይታወቃል።ነገር ግን ለህክምናው የተጠየቀው  አጠቀላይ ገንዘብ (56,000 USD ) ወይንም 7,092,050 የኢትዮጵያ ብር ነው።
👉አስከአሁን ድረስ የተከፈለው የገንዘብ መጠን= 2100 Dollar (2,660,000) ብር
👉አሁን የተጠየቀው ቀሪ= 35,000 Dollar (4,432000) ብር
ስለሆነ አሁን ባለው ሁኔታ ህክምናውን በጥሩ እየተከታተለ ቢሆንም ቀሪው የተጠየቀው ገንዘብ እጅግ ከባድና ከአቅም በላይ ስለሆነ የእኛ የሁላችንም እርዳታ አስፈልጓል። ስለሆነም በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞችና እህቶች:-
👉"ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው"።
እሄንን ፅሁፍ የምታነቡ ሁላችሁም ዘር፤ሀይማኖት እና ብሄር ሳትሉ እሄንን አገልጋይ ለመርዳት የበኩላችንን እንድንወጣ በታላቅ አክብሮት እና በኢየሱስ ፍቅር እንለምናችኋለን ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት
(1000658186632)
Tomas Torago and Terzu Daya

ወንድማችሁ
ወ/ም መስፍን ሊራንሶ (ዶ/ር)
(Shenzhen,China)

👉👉ለሁሉም share በማድረግ እንድትተባበሩ👈👈
ማራናታ.....MARANATHA

03 Dec, 03:11

2,281

የማለዳ ትምህርት ዕለት (ማክሰኞ)
ቀን 24/03/2017 ዓ/ም

ርዕስ፦አጋጣሚ አይደለህም!!

ውድ ቅዱሳን ዛሬም እንደተለመደ የማለዳ ትምህርት ቢሆንም ግን የሚቀረበው የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነው በሁለት በኩል የተሳለ ነው። ከእግዚአብሔር እና ከቃሉ ጋር መላመድ አይቻልም። እግዚአብሔርም ቢሆን የእርሱ ቃሉ በጣም አሰፈሪና ነው። እሱ ስወርድ ሲና ተራራ የጨሱለት አምላክ ነው። ምድር በዳን ያናወጣል ሰማይና ምድርን ያንቀጠቅጣል እሱ ስመጣም ይሁን ቃሉን ስልክ በሚገርም ሁኔታ ታምር ይሠራል ለዚህም ነው ዳዊት ቃሉን ላከ ፈወሳቸው ያለው።... አሁን ለለመደነው ሕይወት ቃሉን ቢልክ እሱ ምን ሊያደረግ እንደሚችል ያውቃል በእኛ ሕይወት ውስጥ ቃሉን ቢልክ ኖሮ እኛን አሁን እያሰቸገረን ያለው ነገር ሁሉ ይቀየራል።

አልንለማመድ በሚል ርዕስ በሌላ ጊዜ አቀርባለሁ ነገር ግን የምንማረው የትምህርቱ ርዕስ በሰጋጣሚ አይደለህም ወደዚህ ምድር የመጣው በሚል እንማራለን።


በአጋጣሚ ወይም በደንገት አልተወለድክም/ሽም ሕይወትም ቢሆን ላንተ/ቺ ተፈጥሮን ያደለችህ አይደለም።ወላጆችህ በተለይ አንተን/ቺን ለመውለድ አላቀዱ ይሆናሉ እግዚአበሔር ግን ወንድሜ አቅደዋል። የአንተ መወለድ እግዚአብሔር እውነት ነው የምልህ አላሰደነቀም ይልቁን ይጠበቀው ነበር ጉዳይ ነው። ገና ያነ ድሮ በወላጆች ከመፀነስ በፊት በእግዚአብሔር ሀሳብ ውስጥ ተፀንሰህ ነበር። ስለአንተ እና ስለ እኔ በመጀመሪያም ያስብ ነበር። በዚህች ቅጽበታዊ ሕይወት ውስጥ የምትኖረው እግዚአብሔር በፍላጎቱ ስለፈጠረ ነው። እስከዚህ ያቆየ ያለ አላማ አይደለም።

መዝ 139፥15፦እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፥ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ፥ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም። እያንዳንዱን የአካል ክፍሎችን ይሁን ብሎ ይገጣጥማቸው እግዚአበሔር ነው።ዘርህን፣የቆዳህን ቀለም፣ ፀጉርህንና ሌላውን መልክህን የመረጠው ሆነ ብሎ ነው። ያንተ አካል ረጅም ይሁን አጭር ምንም....እርሱ በፈለገው ሁኔታ ወስኖ ነው የሠራው።

እኔ የእግዚአብሔር ጥበብና እውቀት በጣም ይገርመኛል አንተን የፈጠረህ እኔንም እንደዛው የፈጠረው በምክንያት ስለሆነ የምትወለድበት ጊዜና ቦታ ምን ያህል ዘመን እንደምትኖር በሕይወት ያለው ታለንትን ሁሉ ወስኖ ነው የፈጠረው። የመውለዳውን የመሞቻውን ቀን ሰዓትና ጊዜን በመምረጥ አስቀድሞ የሕይወትህ ቀናት አቅዷቸዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል በመዝሙር 139፥16፦ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ።ይላል።

አሁን ያለህበት አከባቢም ቢሆን ላንተ የማይመቺ የማትወደው ልሆን ይችላል ነገር ግን በአጋጣሚ አይደለም። አሁንም መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ይገልጻል...ሐዋር 17፥26-27፦.....የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፥ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም። ይላልና። እንግሊዝኛው እንዲህ ይላል ይህን ክፍል የሰውን ዘር ሁሉ ከአንድ ፈጥሮ በምድር ሁሉ ላይ እንድኖሩ አደረገ፤ የዘመናቸውን ልክና የመኖሪያ ሥፍራቸውንም ዳርቻ ወሰነላቸው ይላል። በሕይወት ጉዞ ላይ በዘፈቀደ የሆነ ነገር የለም፤ ሁሉም በዓላማ ነው እንጂ!

ከሁሉም የሚያስደንቀው የምትወለድበትን ሁኔታ እንኳን እግዚአብሔር የወሰነ መሆኑ ነው። የተወለድክበት ሁኔታና የወላጆች ማንነት ምንም ይሁን ምን፣ እግዚአበሔር ስፈጥር ዓላማ ነበረው። አንተን የወለዱ ወላጆች ጥሩም ይሁኑ መጥፎ ወይም ግድ የለሾች ምንም አይደለም። እግዚአብሔር ግን እነዚህን ሁለት ግልሰቦችን ስያገናኝ በእርሱ ሀሳብ ውስጥ የነበሰክ አንተን ልያመጣ ቀጥታ አገናኝቶቿዋል።

ስለዚህ ወንድሞች እህቶች አሁን ላለህባችሁ ችግርና ፈተና ከፈጣሪይ ዕቅድና አሳብ ውጭ የመጣ አይደለም ነገር ግን ይህን ችግር የምፈተባችሁ መንገድንም ከእርሱ ዘንድ ታገኛለህ እንጂ ከሌላ መሆን ምንም የሚፈይደው ነገር አይኖረም። እግዚአብሔር ማንኛውንም ነገር በድንገድ ስለማያደርግ ነውና። በሥራውም በፍጹም አይሳሳትም/አይፀፀትምም። አንተ ግዙፍ የእሱ ልጅ የሆንክ ይቀረና እንስሳቶችም/ እፀዋቶች የተፈጠሩት በእሱ እቅድ ናቸው።

በሕይወታችን የጎዳን እኛ የተፈጠረንበት የሕይወት ዓላማ ምን እንደሆነ አለማወቃችንና በዚህች በአጭር ዘመን ቆይታ የምድሩን ሕይወት ተላምደን የሠማዩን ሕይወት ምን እንደምመሠል ማየት ስላልቻለን ነው እግዚአብሔርማ ስፈጥረን በእቅድ እና በአላማ ነበር የተፈጠረነው። ስለዚህ ወንድሞች እህቶች ቀልባችን መልሰን ወደ ተፈጠረንበት ወደ መነሻ እንመለስ።

ሙሴም ቢሆን የሕይወት አላማ ከማወቁ በፊት በአማቹ ቤት በግ ጠባቂ ነበር፣ዳዊትም እንደዛው፣ ኤልሳዕም ቢሆን እርሻ ያርስ የነበረ ሰው ነው፣ ኤልያስም በክትክታ ውስጥ ሞትን ተመኘቶ የነበረ ሰው ነው፣ ጳውሎስም ቢሆን አሳዳጅ ነበር....እና ሌሎች ሌሎች ስለዚህ የሕይወታችሁ አላማ ምን እንደሆነ በጊዜ ማወቅ ትልቅ በረከት ነው በአጋጣሚ ስላይደለህ ለራሱ ዓላማ የሠራውን አምላክ ቶሎ ብለን አላማችን ማወቅ ጊዜን ከማባከናችን ያድነናል።

መልካም ዕለት ማክሰኞ ተመኘሁላችሁ🙏

እግዚአብሔር የልመናችን ድምጽ ይስማልን አሜን!!!

🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂ኸኀ🤷‍♀

      🌻የዕለቱን ትምህርት በየማለዳ🌻
        🌸የጉዞአችንን ስንቅ ከማራናታ🌸

                    🌼መልካም ቀን!!!🌼
Any Comment @maranathawoch
Any suggestion @Uwillnverwalkalone

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH
ማራናታ.....MARANATHA

02 Dec, 03:56

2,489

የማለዳ ትምህርት   ዕለት (ሰኞ)
ቀን 23/03/2017 ዓ/ም

ርዕስ፦ከፊትህ እግዚአብሔርን አሰቀድም

በሕይወታችን ምሕረቱን አብዝቶ ለዛሬ ቀን ያደረሰን አምላክ ይመሰገን እያልኩኝ ለዛሬ ማለዳ የሚሆን መልእክትን አቀርባለሁ የማለዳ ርዕስ፦እፊትህ እግዚአብሔርን አሰቀድም በሚል ርዕስ እንማራለን።

ከጥንት ዘመን ጀምሮ ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበሩ ቅዱሳን በሙሉ በእነርሱ ላይ እግዚአብሔር እንድከበር ያድርጉት እና የወሰዱት እርምጃ ቢኖር በእያንዳንዱ ዕለት ከፊታቸው እግዚአብሔርን በማሰቀደምን ነው።

እነ ሄኖክ፣እነ ኖኅ፣ እነ አብርሃም እንድሁም ሙሴ የመሳሰሉ ነቢያታቸው እግዚአብሔርን በድርጊታቸው እፊት በማደረግ ነው። ዘፍጥረት 6፥8፦ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ።

ዘፍጥረት 19፥27፦አብርሃምም በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ወደ ነበረበት ስፍራ ለመሄድ ማልዶ ተነሣ፤
ዘዳግም 12፥25፦በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር ስታደርግ ለአንተ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁ፥ አትብላው።

በዘመናቸው የተባረኩት ቅዱሳን በሙሉ ምስጢራቸው እግዚአብሔርን እፊታቸው ማደረጋቸው እንደሆነ ይታወቅ። ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ ... ዳዊትም በሕይወት ዘመኑ ሙሉ እግዚአብሔርን ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ ይላል። ምሳሌ 5፥21፦የሰው መንገድ በእግዚአብሔር ፊት ነውና፥ አካሄዱንም ሁሉ እርሱ ይመለከታልና። ምሳሌ 16፥9፦የሰው ልብ መንገዱን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቀናለታል።

ስለዚህ ነገ ሰኞ ነው የሥራ ቀን ነው ከሁለት ቀን ኤራፍት በኋላ ወደ ሥራችሁ ትመለሳላችሁ። ስለዚህ እሰከ አርብ ባለው ጉዙ የሚያጋጥሙ እንቅፋቶች መሠናከሎች በጣም ብዙ ልሆኑ ይችላሉ ነገር ግን በማሰተዋል ነገሩን በማወቅና በማጣራት ስለ ነገሩ መልስ በመሠጠት በሰከነ ልብ እያንዳንዱን ድርጊቱን እንድትፈጽሙ ሃደራ እያልኩ ከታች በኩል ባሰቀመጥኩት በእግዚአብሔር ቃል የዛሬውን የማለዳ ትምህርት ክፍልን አበቃለሁ መልካም ሳምንት። ሳልጨምር ማለፍ የማልፈልገው ነገር ቢኖር ከኔገ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሐዋርያት ቤተክርስቲያን አብይ የቄሶች ጉባኤ ለአራት ቀን ይካሄዳል በዚህ ጉባኤ ላይ እግዚአብሔር የቤተክርስቲያን መሪዎቻችን እንድጎበኝና እንድረዳቸው በያላችሁበት ሆናችሁ ፀሎት ማድረግን አትረሱ ኢየሱስ ይባርካችሁ።

መዝሙር 37፥23፦የሰው አካሄድ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይጸናል፥ መንገዱንም ይወድዳል።

መልካም የሥራ ቀን ተመኘሁ

እግዚአብሔር የልመናችን ድምጽ ይስማልን አሜን!!!

🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂ኸኀ🤷‍♀

      🌻የዕለቱን ትምህርት በየማለዳ🌻
        🌸የጉዞአችንን ስንቅ ከማራናታ🌸

                    🌼መልካም ቀን!!!🌼
Any Comment @maranathawoch
Any suggestion @uwillnverwalkalone

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH