Latest Posts from ልሳኑ ዘያሬድ(lisanu zeyard) (@lisanuzeyaredmedia) on Telegram

ልሳኑ ዘያሬድ(lisanu zeyard) Telegram Posts

ልሳኑ ዘያሬድ(lisanu zeyard)
ወረብ ስርዓተ ማኀሌት በማኀሌት ጊዜ የሚደረሱ መልክአ መልኮች ዜማቸውም አቋቋማቸውም ያሬዳዊ ዜማ እና መንፈሳዊ ነገሮች ሁሉ የሚታዩበት እና የሚሰሙበት
1,765 Subscribers
212 Photos
30 Videos
Last Updated 01.03.2025 14:37

The latest content shared by ልሳኑ ዘያሬድ(lisanu zeyard) on Telegram


ልዩ በዓል በመካነ ሰላም መድኃኔ ዓለም እንደ ዛሬው ከርሞ ያድርሰን🙏 https://www.facebook.com/reel/1117234270084281?fs=e&mibextid=wwXIfr&fs=e

ቢዲዮውን ለማየት ሊንኩን ይጫኑ
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02pgFgygfyL5nToNS9W8rDg8gGixfXmQx4dBNqqHomQhzb1Fe86uia9gBGRfGrWMoNl&id=100065906701230&mibextid=wwXIfr

የልደት በዓላችን በደማቁ የፈቀደ እግዚአብሔር ይመስገን አሸብርቀን አሳልፈናል።
ለከርሞው በሰላም ያድርሰን ቀጣይ ጥምቀትን እንደ አምላክ ፈቃድ እንደምቃለን ያድርሰን።
ወረብ ፦
በጎል ሰከበ ……..

እንኳን አደረሳችሁ !!!
ይህ ወረብ ጎንደር በዓታ አድራሽ በነበርኩበት ሰዓት ከአባቴ እና ከመምህሬ ከቃለ እግዚአብሔሩ መጋቢ ከየኔታ ክቡር ጋር ዑደት ላይ አብረን ያልነው ነው።
መቼም የሊቃውንቱ ብዛት ከሕዝቡ ብዛት የማይተናነስ በሆነ መልኩ ደምቆ ቢታይም፦
ለሕዝቡ መቆሚያ ቦታ እስከሚጠብ ድረስ የቤተ ክርስቲያኑ ግቢ መልቶ ሰው መግባት እስከሚከለከል ድረስ በድምቀት የሚያሸበርቀው የዛሬው የበዓታ ክብረ በዓል ልዩ ነው ።
ከእመቤታችን ረድኤት እና በረከት ይክፍለን መልካም በዓል ለሁሉም አማኝ።
በድጋሜ እንኳን አደረሳችሁ ❤️ሰካም ለኪ ማርያም እምነ❤️

አይኔ ነው? 😁
ጋሽየዋ የኔታ ግዕዝን ነው እያወዛወዘው ያለው???👇
ጎበዝ👍🏾!

እውነት ለመናገር በጣም ነው ደስ የሚል እሄን ማበረታታት ተገቢ ነው።
የኛ ቤተክርስቲያን ማለትም የኢትዮዽያ ማለት ነው ፦
ሁሉም ሕዝብ ወይም አማኝ እንደ ቋንቋው ሊገባው በሚችል እና ሊገነዘበው በሚችለው ቋንቋ ማስተማሩን ባምንበትም ፦
ነገር ግን ከመሰልጠንም ይሁን ከመዘመን ወይ ከስንፍና ይሁን አላውቅም ግዕዝ ቋንቋ አገርክን ፈልግ ተብሎ እንዳው እንዳው ሁሉም በየሲናው በየራሱ ቋንቋ ተከፋፍሎ
አጓጉል መሰልጠን የሚባል አጉል ሁኔታ ላይ ስለደረስን የቤተ ክርስቲያኗን የራሷን መገልገያ ቋንቋ እንዳላስፈላጊ አድርገን አስወጥተን ጥለን የየሰፈራችን እና የየብ*ችን ቋንቋ ሰግስገን ሰግስገን ይህንን ትልቅ ንበረት ገንዘብ ባለማድረግ እና በአግባብ እየተጠቀመበት ባለመሆኑ በጣም ያናድደኛል ።
ግን ደግሞ የኛዎቹ የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች እንደተባለው ወደጎን ቢተውትም ብልሆች አገሮች ገንዘብ አድርገው አክብረው ንብረታቸው አድርገው በስፋት እያስተማሩት እና እየተማሩት ስለሆነ በሂደት የኛውም ሕዝብ መልሶ እንደሚረከበው ተስፋ አደርጋለሁ።
ከነገሩም ከዘገሩም ብሏል ያገሬ ሰው እኮ?
ከነሁሉም ዘረኝነት ጎሰኝነቱም ቀነስ እንዲል ሁሉም ዓለም ላይ ያለች ቤተ ክርስቲያን በግዕዝ ብቻ እያስተማረች አገልጋይ ብታፈራስ ?
ሆ!

ኅዳር ጽዮንን በ New York መልካም በሆነ ድምቀት ደስ በሚል መልኩ እንዲህ አክብረናል።

በድጋሜ ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል በአትላንታ መካነ ሰላም ሚካኤል ወኪዳነ ምሕረት በደማቁ አክብረናል ።
እስመ ለዓለም ፦
ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፦
ቅኝት በሊቀ ጠበብት መምህር ተክሌ ።
አንገርጋሪ/ምልጣን/ ውእቱ ሚካኤል ፦
ምራታ በመምህር ልሳነ ወርቅ ።

ኅዳር ሚካኤልን በካሊፎርኒያ ኦክላንድ ደብረ ምሕረት ሚካኤል ክብረ በዓሉን እንዲህ አሳልፈናል።

❤️ተመየጢን ኢትዮ ያላችሁት ጓዶቼ በሉልኝ እኔ ሳልመየጥ ብየ ትቸዋለሁ።❤️
ናሁ ሀገረኪ ገሊላ እትዊ እግዝእትየ እስከ ማእዜኑ ትሄልዊ ውስተ ምድረ ነኪር።
ናሁ ሀገረኪ ገሊላ እትዊ እግዝእትየ እስከ ማእዜኑ ትሄልዊ ውስተ ምድረ ነኪር።

እምግብፅ ይጽውዖ አቡሁ ራማዊ ለክብረ ቅዱሳን።
እምግብፅ ይጽውዖ አቡሁ ራማዊ ለክብረ ቅዱሳን።

🌹🙏🙏🙏እግዚአብሔር ይመስገን 🙏🙏🙏🌹

ኢትዮዽያኑ ?
ወሚመ አሜሪካ?

ይህ ነገር ኢትዮዽያ ወይስ አሜሪካ ነው?
ግሩም በሚአስብል ሁኔታ ሊቃውንቱ በተገኙበት ጥቅምት መድኃኔ ዓለምን በዚህ መልኩ አክበረናል።

ይህ ቪዲዮ ሼር ይደረግ !

አሜሪካ ውስጥ እንደዚህ ድምቅ ያለ በዓል በቤተ ክርስቲያኔ ውስጥ በመከበሩ እግዚአብሔርን አመስግኛለሁ በእውነት !

መድኃኔ ዓለም እግዚአብሔር ኃደረ ላዕሌሃ።

መድኃኔ ዓለም እግዚአብሔር ኃደረ ላዕሌሃ።

ኪያሃ ዘሠምረ ሐሀገረ ኪያሃ ዘሠምረ ሀገረ።

ኪያሃ ዘሠምረ ሐሀገረ ኪያሃ ዘሠምረ ሀገረ።

ወረብ ዘአንገርጋሪ

አመ ፳ወ ፯ ለጥቅምት መድኃኔ ዓለም ፦

እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን መድኃኒቶሙ ለጻድቃን ።
እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን መድኃኒቶሙ ለጻድቃን ።

አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን በመስቀሉ ወበቃሉ አሠርገዋ ለቤተ ክርስቲያን።
አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን በመስቀሉ ወበቃሉ አሠርገዋ ለቤተ ክርስቲያን።