Последние посты Kokebe Tsibah Secondary School/Yeka Sub-City/ (@kok1924) в Telegram

Посты канала Kokebe Tsibah Secondary School/Yeka Sub-City/

Kokebe Tsibah Secondary School/Yeka Sub-City/
Since 1924
3,362 подписчиков
2,809 фото
16 видео
Последнее обновление 11.03.2025 17:30

Похожие каналы

Stockmarket.et
2,165 подписчиков

Последний контент, опубликованный в Kokebe Tsibah Secondary School/Yeka Sub-City/ на Telegram

Kokebe Tsibah Secondary School/Yeka Sub-City/

24 Feb, 06:59

1,537

የየካቲት 17/2017 ዓ.ም የሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መርሐ-ግብር የአይሲቲ ትምህርት ክፍል ባልደረባ በሆኑት በመ/ ዘላለም ግርማ አማካኝነት ቀርቧል
👉 የጀመርናቸውን የሪፎርም ስራዎች ከምንጊዜውም በላይ አጠናክረን እንቀጥላለን
Kokebe Tsibah Secondary School/Yeka Sub-City/

23 Feb, 10:13

1,581

ማስታወሻ
ለመምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች
የነገ ሰኞ የካቲት 17/2017 ዓ.ም የማለዳ የእውቀት ሽግግር መርሐ-ግብር ያለ መሆኑን እየገለፅን የካቲት 10/2017 ዓ.ም ያቀረቡት የአይሲቲ መምህራን የሚያቀርቡ መሆኑን እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ:- ሰዓት ይከበር !!
/ቤቱ
Kokebe Tsibah Secondary School/Yeka Sub-City/

21 Feb, 16:37

2,206

ዛሬ የካቲት 14/2017 ዓ.ም የት/ቤቶች የስፓርት ሊግ በኮከበ ጽባህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና በከፍተኛ 12 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መካከል ለ2ኛ ቀን ቀጥሎ የጥሎ ማለፍ ጫውታው ፍፃሜውን አግኝቷል።
1ኛ,በተማሪዎች መካከል በተደረገ የእግር ኳስ ውድድር የከፍተኛ 12ኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የኮከበ ጽባህ አቻውን 1ለ0 አሸንፏል።
2ኛ,በመምህራን መካከል በተደረገ የእግር ኳስ ውድድር የኮከበ ጽባህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን የከፍተኛ 12 አቻውን 3ለ0 አሸንፏል።
3ኛ,በጠረጴዛ ቴነስ የከፍተኛ 12 መምህራን ድል ቀንቷቸዋል።
4ኛ,በቼዝ የኮከበ ጽባህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በፎርፊ ባገኘው ነጥብ ወደ ሚቀጥለው ዙር አልፏል።
በሁለቱ ት/ቤቶች መካከል የነበረው ውድድር ስፓርታዊ ጨዋነት የታየበት ሆኖ ተጠናቋል።
Kokebe Tsibah Secondary School/Yeka Sub-City/

21 Feb, 07:01

958

የ12ኛ ክፍል ፈተና ሁሉም ተማሪዎች በተማሩበት ሥርዓተ ትምህርት ይዘት ይዘጋጃል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች በተማሩበት ሥርዓተ ትምህርት ይዘት እንደሚዘጋጅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ ÷የ2017 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ-10ኛ በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም ከ11ኛ - 12ኛ ደግሞ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ መሆናቸውን አንስቷል፡፡

ይሁን እንጂ በ2015 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በናሙናነት በተመረጡ ት/ቤቶች የስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ ላይ የተሳተፉ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንደተማሩ አመልክቷል፡፡

በአማራ ክልል በ2016 የትምህርት ዘመን መፈተን ሲገባቸው በጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም የሚፈተኑ መኖራቸውንም ጠቅሷል፡፡

በመሆኑም የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከላይ የተገለጹትን ሶስቱንም ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ እንደሚዘጋጅ ነው የተገለጸው፡፡

በተጨማሪም ፈተናው ሁሉንም የዘመኑን ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ ስታንዳርዱን፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ እየተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡

ስለሆነም የፈተና ዝግጅቱ ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣ ከ10ኛ ክፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣ ከ11ኛ ከፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች እና ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት እንደሚዘጋጅ ተገልጿል፡፡

የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በስርዓተ ትምህርቱ አዲስ የተጀመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ ተመስርቶ እንደሚዘጋጅ ተጠቁሟል፡፡

ተማሪዎች ከ9ኛ -12ኛ ክፍል በየተማሩበት የሥርዓተ ትምህርት ይዘት ላይ በመመስረት ፈተናው እንደሚዘጋጅ አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አገልግሎቱ አሳስቧል፡፡

ሁሉም ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ወላጆች፣ መምህራንና መላው የትምህርት ማህበረሰብ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግም ተጠይቋል፡፡
Kokebe Tsibah Secondary School/Yeka Sub-City/

20 Feb, 15:53

1,400

ዜና ስፓርት
ዛሬ የካቲት 13/2017 ዓ.ም በኮከበ ጽባህ 2ኛ ደረጃ /ቤት እና በከፍተኛ 12 2ኛ ደረጃ /ቤት :በት/ቤቶች የስፓርት ሊግ ውድድር እና ስነ-ስርዓት መሠረት ስፓርታዊ ጨዋነት የተሞላበት የመረብ ኳስ ውድድር በመምህራን እና በተማሪዎች አድርገዋል ::
ውድድሩ:-
መምህራን ከመምህራን እና ተማሪዎች ከተማሪዎች ጋር የተደረገ ሲሆን በውድድሩ ኮከበ ጽባህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በምህራንም በተማሪዎችም ድል ቀንቶታል።
👉 ነገ ዓርብ በሁለቱ ት/ቤቶች መካከል መምህራን ከመምህራን ጋር እንዲሁም ተማሪዎች ከተማሪዎች ጋር የሚደርጉት የእግር ኳስ ጫዎታ ከወዲሁ በጉጉት ይጠበቃል።
Kokebe Tsibah Secondary School/Yeka Sub-City/

19 Feb, 04:25

1,244

ቀን 12/6/2017 ዓ.ም
ማስታዎቂያ
ለተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች
እሁድ በ09/6/2017 ዓ.ም ከተማሪ ወላጆች ጋር በተለያዩ የተማሪዎችን ውጤት እና ስነ-ምግባር በሚያሻሽሉ ጉዳዮች እና በቀጣይ ከወላጆች/አሳዳጊዎች በሚጠበቁ ተግባራት ላይ ያተኮረ ውይይት ካድረግን በሗላ የ1ኛ ሰሚስተር ውጤት ለወላጅ/አሳዳጊ መስጠታችን ይታዎቃል።
ይሁን እንጂ በተለያየ ምክንያት በዕለቱ ተገኝታችሁ በውይይቱ ያልተሳተፋችሁ እና የልጆቻችሁን ውጤት ያልወሰዳችሁ ወላጆች መኖራችሁን ሰኞ እና ማክሰኞ ከ10-11/6/2017 ዓ.ም ውጤት ይሰጠን በማለት ጥያቄ ስታቀርቡ ለማወቅ ችለናል።
👉 ስለሆነም ከዛሬ የካቲት 12-14/2017 ዓ.ም ማለትም እረቡ :ሐሙስ እና ዓርብ ከጠዋቱ 2:45 -11:30 ሰዓት ባሉት 3 ተከታታይ የስራ ቀናት ወላጅ /አሳዳጊ በአካል የተማሪዎች ክሊኒክ ቢሮ በመገኘት ውጤቱን ፈርማችሁ መውሰድ የምትይሉ መሆኑን እናሳውቃለን
ማሳሰቢያ:- 1,ውጤት ለተማሪ አይሰጥም።
2, ትክክለኛ ወላጅ /አሳዳጊ መሆኑን የሚያረጋግጥ መረጃ ካላቀረበ/ካላቀረበች ውጤት አይሰጥም።
3, ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ ይህን ጥያቄ ተቀብለን እናስተናግድም።
/ቤቱ
Kokebe Tsibah Secondary School/Yeka Sub-City/

18 Feb, 08:45

1,515

የበይነ መረብ (Online) ፈተና ያለው ጠቀሜታ

(የካቲት 11/2017 ዓ.ም)

1. የበይነ መረብ ፈተና ለስህተት በር አይከፍትም

ይህም ለምሳሌ በወረቀት መልስን በማጥቆር ሂደት ተማሪዎች መልስ ሳይሰጡ ሊያልፉና ሊረሱ የሚችሉበት ወይም በመልስ ቅየራ ወቅት የመልስ መስጫ ወረቀት መጎዳት፣ ሁለት መልስ መጻፍ፣ አጋጣሚዎች ሲኖሩ እንዲሁም ከአንዱ ጥያቄ ወደ ሌላኛው ለማለፍ ገጽ ማገላበጥ ወ.ዘ.ተ. ሲኖርባቸው፣ በበይነ መረብ ሲሆን ግን ያልተመለሱ ጥያቄዎች እንዳሉ የሚጠቁም በመሆኑ፣ አንዱን ሳይመልሱ ወደ ፈለጉት ጥያቄ በአንድ “click” የመሄድ እንዲሁም ተመልሰው መስራት የሚፈልጉትን ጥያቄ “flag” በማድረግ ተመልሶ የመስራት እድልን ይሰጣል።

2. ጊዜ ቆጣቢ ነዉ

ወረቀት ላይ መልስ በማጥቆር የሚባክን ጊዜን በማስቀረት በአንድ “click” የፈተና ጥያቄን መልስ ለመስጠት ያስችላል። እንዲሁም ምን ያህል ደቂቃ እንደተጠቀሙ ከመፈተኛ ስክሪን ላይ ማየት ስለሚቻል ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም ያነሳሳል።

3. የተሻሻለ የመረጃ ቋት አለው

የበይነ መረብ ፈተናዎች በቂ የፈተና መረጃዎችን ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በማከማቸት ለተፈታኞች አመጣጥኖ ያቀርባል፡፡ በፈተና ወቅት በተሰጠው ሊንክ የገባ ማንኛውም ተማሪ የሚገባበት የፈተና ቋት በሌላ ማስፈንጠሪያ ከገባ ተማሪ ጋር ተመሳሳይ ነው።

4. ኦዉቶማቲካሊ የተሰሩ ጥያቄዎችን መልስ በራሱ ይልካል

በፈተና ወቅት ጥያቄዎቹን ሰርተው ሳያጠናቀቁ የተሰጠው ደቂቃ ካለቀ አውቶማቲካሊ የሰሩትን በጠቅላላ በራሱ ይልካል (ሰብሚት ያደርጋል) ።

5. ፈጣን ግብረ መልስ ይሰጣል

ፈጣን የውጤት አሰጣጥ እና ግብረመልስ በበይነ መረብ ፈተናዎች ሲሰጡ ውጤታቸው ከሌላው ጊዜ በተለየ ፈጥኖ የመታወቅ እድል ይኖረዋል።

6. ተማሪዎች በቤታቸዉ እያደሩ እንዲፈተኑ እድል ይሰጣል

ትምህርት ቤቶች የተደራጀ የኮምፒውተር ቤተሙከራ ካላቸውና የመፈተኛ ክላስተር ለመሆን አስፈላጊውን መስፈርቶች ማሟላታቸው ከተረጋገጠ ተማሪዎች በተማሩበት ትምህርት ቤት ሆነው እንዲፈተኑ እድል ይፈጥራል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacaebc
Kokebe Tsibah Secondary School/Yeka Sub-City/

17 Feb, 16:11

1,988

KOKEBE TSIBAH GREEN AREA
Kokebe Tsibah Secondary School/Yeka Sub-City/

17 Feb, 10:47

1,956

የካቲት 10/2017 ዓ.ም የሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መርሐ -ግብር በመ/ እንግዳወርቅ ተሾመ እና በመ/ ዘላለም ግርማ ቀርቧል
👉 የእንግሊዝኛ ክበብ አባል ተማሪዎች በመ/ አንዋር ከማል አስተባባሪነት የተለያዩ ፕሮግራሞችን በእንግሊዝኛ ቋንቋ በሰልፍ ስነ-ስርዓት አቅርበዋል
👉 ለተቋማዊ እድገት እየተጋችሁ ያላችሁትን በሙሉ እናመሠግናለን
👌 ሁላችንም የተግባር ሰው እንሁን!!
Kokebe Tsibah Secondary School/Yeka Sub-City/

16 Feb, 11:44

1,049

ዛሬ የካቲት 9/2017 ዓ.ም ከተማሪዎቻችን ወላጆች/አሳዳጊዎች ጋር ውይይት አድርገናል
👉 የተወያየንባቸው አጀንዳዎች:-
1,የ2017 ዓ.ም የ1ኛ ሰሚስተር ውጤት ትንተና
2, የሒሳብ እና እንግሊዝኛ ትምህርት ስትራቴጅክ እቅድ አፈፃፀም
3, የአራትዮሽ የውል ስምምነት አፈፃፀም
4, በአጥጋቢ የመማር ብቃት/MLC/ ላይ የተሰሩ እና በቀጣይ በሚሰሩ ተግባራት ላይ ውይይት ተደርጓል።
👉 ወላጆች/አሳዳጊዎች የ1ኛ ሰሚስተር ውጤት እንዲወስዱ ተደርጓል።
👉 ከወላጆች/ አሳዳጊዎች አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን በመቀበል ውይይታችን በመግባባት አጠናቀናል