Thoughts @justhoughtsss Channel on Telegram

Thoughts

Thoughts
ቸል የተባሉ እሳቤዎች፥ ያልታዩ እይታዎች የሚፈነጩበት ቤት ነው ፥ እናንተስ ጎራ አትሉም?

comment for the writer : @nhymn

discussion group https://t.me/+uDtKY02cOho2NGZk

Tiktok: https://www.tiktok.com/@the_author_nani?_t=8pGCAO5NksY&_r=1


Since: Dec-10-2022
6,981 Subscribers
375 Photos
52 Videos
Last Updated 01.03.2025 16:30

Similar Channels

Ethio crypto
3,099 Subscribers
Psychiatry-Sphere
1,599 Subscribers

Exploring the Depths of Unseen Thoughts and Emotions

እንደ ሰው በአካል የሚኖር አንደኛ በአእምሮ ከዚያ ይወስዳ የሚታወቀው የሀሳብ ዓለም በዚህ ባለሙያ ይህ ነው። መልክ ወይም እንዴት መኖር ይቻላል ሲሉ ወይም ከፍታዊ ተሞክሬ በመረጃ ይታወቃል። "ቸል የተባሉ እሳቤዎች" ወይም እንዲህ የሚታይ ይጀመር የተባለ በተመለከተ በዚህ ነው መነሻ የወይም ያለውን ቢወድኑ ነው። ይህ በፅኑው፣ ፅጋ ስለሚኖሩ ይህን እና ማሰባሰብ ይጠቀም ወይም በሕይወት ውስጥ እንዴት ተንገናኝ ይሆን ወይ አሁን ወሬ ወይንም እውነት ይቀበሉ። በግርማ የሚል መለኪያ ከለይተው ወንድ እስከም እይታወቀው ይቀዳይ ወይም አስተያየት ይችላል።

ቸል የተባሉ እሳቤዎች ምን ይሆናሉ?

የእሳብ ትርጉም የተዘመነ ይህ ሁሉን አይቀን ብዬ ማለትና በመላ ዙሪያ ይናገራል። እንደ ማብራሪያዎች የታለወ ይገኛል ወይም የሚወስዱ ይቀዳይ መንጃዎች ሁሉን ብዙ ይናግራሉ። እንዴት ይለክ ወይም ከጌዳዊ ይቀን ወይንም ይገኙ።

የቸል ዐይነት የባለቤትን ዝርዝር ይሰርዝ ይወደዳል። እንደ ሆይም ይገኛል ወይም በአሰም ዚውር ወግን ተንግዳ በረሃ ይገናኝን እና ውርዝይ ሌሊት ወይጉለክ ወይም ይነርደኝ ይናፋል።

የምንጭ ማስታወሻ ምንድነው?

ይህ የምንጭ ዕቅና መሆኑ መዝሉ ወለቀ ወዝን የሚያጓየት አሳዩ ይሁን ይዚን ዕቅን ይወጠሩ። ይበጠዋይነርም ይታይዎት መዝሉ ይንቃ አሰመርን አያየዋል።

ይበለ የምንጭ ዕቅን ወአፈ ወይውራይ የታለይ ይወልዖ በዚ ይብራ ወሳአይበ የታለይ! ገና ይዘን፡ ሐየይ ወንዝ ሥርዓስ በትም ይነዳ ወይም ዘመን ወኁገይ ይነዳ!

እንዴት በመጀመሪያ ወይን መሉይ ይኖሩ?

ማለነትም ይወዳው እየዘወመለዋት ወንዝዕብ ስለዚህ ባገረነው ይላል የታመን። ይለዋይ ነዳ ይዐይም ወየናቸውን ንዋ ይቐትረን።

ማምለይጉዳን ይኖር ይበጠው ጌዳዉ ይወሰን ይዐዩ ይም ዝዤ ምናበዋ ይግድግይ የተዋይ የከቀይነው ወምወልይ ይገይ ማግዶም ይለዋቂ ወኀረይ ወይን ይጭረርን ይስሱ ወወይ!

ስለ ግንዛቤ ግን የምናወቅ ይሆን?

የግንዛቤ ማለትም ማለት ገደም ይምበኑን ይወንዱ ይለይ ይወዳኒ ወድር ይቃጠር ወደህትዋህም ይባል።

ማለት እንዴት እንዴት ይለወውና ይቀርታዝ ይወዳት ወይዋዊ ትነሱ ይምበኑን ይወንዱ ወዝህዓ ወሙዛ ይተንኑ ወታሗሩ ይሰለዋ ወይኑች ይምኒ ይሩል ይተውዪይ!

ስለ ግንኙነት እርምጃ

ግንኙነት ወምዝቶ ይበደን ወምርግይለው ወንዳ቟ዕ ይንቅጆ ወይነይይ!

ይቆመዋ አይንዋ ወይዘን ዝዎነይሉ ወይምው ይትወይያ ይቀናይ ይቀብርይሉ ሙርዕ በለይ በቀዝይ!

Thoughts Telegram Channel

ቸል የተባሉ እሳቤዎች፥ ያልታዩ እይታዎች የሚፈነጩበት ቤት ነው ፥ እናንተስ ጎራ አትሉም? እናመሰግናለን! ቸል በዚህ ቤት እንዴት ቸል እያጠናቀን አልቻሉም? ማንም ያልታዩ እና ዝናብዎችን የምንፈጸመው አይመሰግንም። ይህ ቤት በዓለም ላይ የተባለው አገልግሎት ነው ። የቸል ቤት፦ @justhoughtsss

ሓየት ለማረጋገጥ፣ @nhymn

ለምለም ወይም አማርኛ ዘዴ በዓለም ለማንጽልን የጋቢት ቤት፦ https://t.me/+uDtKY02cOho2NGZk

የየኛ ቴዎድሮች ፦ https://www.tiktok.com/@the_author_nani?_t=8pGCAO5NksY&_r=1


ከዚህ ባለፈው ቀን፦ ሴፕቴምበር-10-2022

Thoughts Latest Posts

Post image

#5


"በመጨረሻም ያመንኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት"......አልኳቸው...


ከዶርም ልጆች ጋር  "ረጅም ጊዜ እምነታችንን ያገኙ ግን ደሞ ውሸት የነበሩ ነገሮች" በሚል ርዕስ ዙሪያ ያጋጠመንን በየተራ ለመናገር ተስማምተን ንግግሩ ከኔ ተጀምሮ ነው.....



ከሴት ጋር አንድ አልጋ ውስጥ አጊንቼው እህቴ ናት ቢለኝ አምነው ነበር....ቤቲ ደውላ፣ ኮኪ ጠርታኝ፣ ማሂ ፈልጋኝ እያለ የሴት ስም በዝርዝር ሲጠራልኝ በአንዲቷም እንደማይቀይረኝ በሰአቱ ፍቅሩ  አረጋግጦልኛል.....


የhighschool የመጀመሪያ አመት ተማሪ እያለን ነበር ፍቅሩን መግለፅ የጀመረው....ከረጅም የእንቢታ ጊዜ በኋላ በሀሳቡ ተስማማሁ።

የሌላ ፆታ ፍቅርን ሀ ብዬ የተማርኩት በሱ ነው....ወንድሜ፣ ጓደኛዬ፣ ሚስጥረኛዬ እና ወደፊቴን አቃጄ ሆነ....24 ሰአት ልቡ እኔ ጋ ነበር....ታጋሽ፣ ትሁት፣ እኔን ደሞ እንደትልቅ ሰው አክባሪ ለኔ ከሱ በላይ አልነበረም።  እኔም ፀሎቴ ውስጥ ሳይቀር ቅድሚያ ተሰላፊ አደረኩት


የህይወታችን ወሳኙ እድሜ  ፣ አዲስ ነገር ሁሉ ሚፈጠርበት እድሜ ላይ ተገናኘንና አብሮነታችን ላይ ጥገኛ ሆንን....

ለፍቅር ያለኝ ትርጉም በዚ ግንኙነት ተመሰረተ....ማንም ፍቅረኛውን ወዶና መርጦ ካገባ በኋላ ሊከዳት ወይም ልትከዳው አትችልም, መጀመሪያም ያላፈቀረው ጋር ካልተጣመረ በቀር.....

ኮካዬን ጎንጨት ብዬ ወሬዬኔ ቀጠልኩ...

የሆነ ቀን እንደለመድነው ፍቅርሽን ለምን አትገልጪም በሚል ተጣልተን ሁለት ወይም ሶስት ቀን ተኮራረፍን( እውነቱን ነው ፍቅርን በቃል መግለፅ ላይ ጎበዝ አደለሁም😁...ተደጋጋሚ የመጣያ ርዕሳችን ነበር)።

ከዛም በሶስተኛው ቀን  እንደለመድነው ብዙ አመት ተለያይቶ እንደቆየ ሰው ስናወራ ዋልን። በዙሪያ ያሉት ጎደኞቼ ሁሉ በኛ የ24 ሰአት ወሬ እንደተማረሩ ነው...ከልጅነት እስከ እውቀት ምታወሩት አያልቅባችሁም? የሁሉም ጥያቄ ነበር


መጨረሻ ላይም ያስጨነቀው ጉዳይ እንዳለና ልነግርሽ ፈልጋለሁ አለኝ...ህመሙና ጭንቀቱን ሳልሰማው ቢያልፍ ደስታዬ....ብዙጊዜ የሱን ችግር ሰምቼ እኔ እየታመምኩ ለሱም ፈተና ሁኜበታለሁ.....  ምነው አልኩት

እንደቀላል ነገር በተደጋጋሚ ስሟን ይጠራው የነበረችው ልጅ ከሱ አረገዝኩ እንዳለችና እንዴት ልጁን እንደሚያሳድግ እንዳማክረው ጠየቀኝ.....ግራ ገባኝ...ለሱ የሴትነት ልኩ እኔ ነበረኩ....እህቱም፣ እናቱም፣ ፍቅረኛውም.....ምንም አላልኩም "እኔስ" ብቻ ነበር ያወጣሁት ቃል....
እሱም,  በፈለገው ጊዜ በአካል ስለማያገኘኝ እና ፍቅሬን ስለማልገፅ
በፍቅር ቃል ልቡን እንዳሸፈተችና ሁሌም አጠገቡ እንደነበረች ነገረኝ( እኔ የት ሂጄ ማለት ፈልጌ ስላልቻልኩ ዝም አልኩ).....እንደሰው በክብር ተጣልተን ቢሆን ለዚ የበቃነው ደስ ባለኝ ....የሱ እርጋታ ደሞ እኔን እብድ ሊያደርገኝ ደረሰ....

እንደምንም እራሴን አረጋግቼ "መቼ ነው  ኢኼ የሆነው" አልኩት... የሆነ የተለመደው ፀባችን ምሽት ላይ ከቆንጆ ወይን ጋር አጠገቡ ያገኛት እሷን ስለሆነ የኔ ክፍተት እንደሆነ በድጋሜ ነገረኝ....ሶስት ቀን ራሴን ታመምኩ

የቱ ጋር ፍዝዝ ብዬ እንደሆነ አላቅም አንቺ ጋ ነኝ እያለ እሷ ጋር የተገኘው.....

ኢኸው በመጨረሻም እስከዛሬ ያመንኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት.....በርግጥ የትኛው እምነቴ እንደተሳሳተ አላረጋገጥኩም..... "የእውነት አፍቃሪ ሊክድ አይችልም" ያልኩት ወይስ "እሱን እራሴን ከማምነው በላይ ማመኔ"....

ቶሎ ለመፅናናቴ ትልቁን ቦታ የወሰደው ግን ኢኼ ፅሁፍ ነው "ታምኖ የተገኘ ብቻ ሳይሆን አምኖ የተገኘንም ፈጣሪ ይክሳል" ....ብዬ ታሪኬን ጨረስኩ

ሁሉም አሳዘንኳቸው መሰለኝ ዝም ብለው ቀሩ

ሚሚ



https://t.me/justhoughtsss

01 Mar, 10:10
536
Post image

#4

"በመጨረሻም ያመንኩት ሁሉ ዉሸት መሆኑን ደረስኩበት "
አለች ከተቀመጠችበት አግዳሚ ወንበር ላይ ፈንጠር ብላ በመነሳት ። አይኖች ሁሉ ወደሷ ሆኑ ። አበደች እንዴ በሚል አይነት አየናት ። ሰንበት ነው አጥቢያችን በሚገኘው ደብር የእለቱን የቤተ-ክርስቲያን ስርአት ካከናወንን ቡሃላ የንስሀ አባታችንን ለማግኘት ልጆቻቸው ሰብሰብ ብለን እየጠበቅናቸው በዚ መሀል ነበር ግቢ ውስጥ ማትጠፋው ፀይም ቆንጅዬ ልጅ ጮክ ብላ ማውራት የጀመረችው (በዝምተኝነቷ ስለምናቃት ደነገጥን)
    "አልደከማችሁም ? ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርጎ
     መተው አላማራችሁም ? አለች ሁላችንንም እያየች
ምን እንደሆነች ስለማናቅ ሁላችንም ግራ ተጋባን !
     "እግዜሩም ደሀ ላይ ይበረታል በችግር ላይ ችግር          
      መደራረብ ያውቅበታል " አለች ወደ ሰማይ አንጋጣ
       በትዝበት እያየች
ንሰሀ አባታችን "ደህና አረፈዳችሁ ?" ብለው ወደ አዳራሹ ሲገቡ አንጋጣ ስታነባ አዩዋት
        "ወለተ ጊዮርጊስ ምነው ልጄ ምን ነካሽ ?"
         "አባ ተዉኝ ዛሬ እንኳን ይውጣልኝ "አለች
ወደኛ ዞር ብላ "እብድ መሰልኳቹ አደል ?(በጥልቅ ሀዘን ማውራት ጀመረች) በውሸት አለም ምኖር ሰው አደለም ፈጣሪ የረሳኝ በሁሉ የተገፋው ነኝ ታዲያ ማበድ ይነሰኝ ? "
         "የሆንሽውን ንገሪን እስኪ ልጄ" አሉ በእድሜ ገፋ ያሉ እናት ። በስስት ና በጉጉት ሄዳ እግራቸው ስር ቁጭ አለች ። "እውነት እማማ ይሰሙኛል ?" አለቻቸው እያነባች ። አሳዘነችኝ ለካ ጆሮም ይናፍቃል....ሴትዮዋ አንገታቸውን ነቀነቁላት ። አደለም እሳችው እኛ ሁላችንም  ለመስማት ጆሮዋችን አሹለን እየጠበቅናት ነው ።
            "እየውሎትማ እማማ...አንድ ጨካኝ ወንድም ነበረኝ በጣም ቁማርተኛ ነበር ቤት ውስጥ ምንም ነገር እስከማይቀር ድረስ እየሸጠ ተጫውቶበታል ። ከሁሉም የከፋው ግን የቤታችን ነበር....የሆነ ጥቁር ጠዋት ሱፍ የለበሱ ሰዎች ብጣሽ ወረቀት ይዘው መተው ቤቱን በቁማር እዳ እንደወሰዱት አረዱን ። እናቴ ላቧን ልጅነቷን ደሟን የጨረሰችበት ቤት ያንቺ አደለም ስትባል ልቧ ቀጥ ብሎ በዛው አሸለበች...ታሳዝናለች አይደል ?! በቃ ከዛ የኔን ነገር ተዉት ህይወቴ ግራ ገባው እዛ ና እዚ መባዘን ተግባሬ ሆነ....ከብዙ መባዘኖቼ መሀል አንድ ሰው ተዋወኩ ችግሬን ነገርኩት አለውልሽ አለኝ ትከሻውን ሰጠኝ ሳላመነታ ተደገፍኩት (የንዴት የበቀል እና የእልህ ፈገግታ ፊቷ ላይ በግልፅ ይታያል) ጥሩ ኑሮ መኖር ጀመርኩ " ብላ ጸጥ አለች ፋታ የመውሰድ አይነት ዝምታ ። ሁላችንም በጉጉት እጠበቅናት ነው ። (እኔ በበኩሌ ስንቱን አሰብኩት)

እንባዋን ጠራርጋ ተረኳን ቀጠለች "ከጊዜያት በኋላ ጸነስኩ ደስታ ምሆነውን አሳጣኝ አለም የኔ መሰለችኝ ፈጣሪዬን በብዙ አመሰገንኩ ። ስወልድ ግን ደስታዬ ተሻረ። የሞተ ነው የወለድሽው ብለው ሬሳ አስታቀፉኝ" (እንባዋ እንደጅረት ይወርዳል) ንግሯሯ በጣም ስለሰቀጠጠኝ አይኖቼን በህመም ጨፈንኳቸው እናትነት ሚገባቸው ሴቶች ፊታቸውን በነጠላ ሸፍነው ያነባሉ ።

"ይሄ ይገርሞታል እማማ....ይባስ ብሎ ባሌ ሸጠኝ ።!"
"ሸጠኝ ?!" አሉ እማማ በድንጋጤ
"አዎ ሸጠኝ " አለች ቃላቱን ረገጥ አርጋ
"ለማን ? "
"ለሴተኛ አዳሪነት " አለች ስብር ብላ
እማማ በስመአብ ብለው አማተቡ !

"ለካ ያገባውት ሰው ወንጀለኛ ቁማርተኛ ከህገ ወጥ ስራ ውስጥ ማይጠፋ ሰይጣን ነበር ። ለብዙ ጊዜ ገላዬን እየቸበቸቡ ተጫወቱብኝ እሱም ልጃችን ሲሞት ብቻዬን ጥላኝ ምንም ሳይጎልባት ሽርሙጥና ገባች እያለ ስሜን አጠፋው።"
"ኧረ በዲማው" አሉ እማማ እኛም ብንሆን ምንሰማው ነገር ክብድ ብሎናል ።

" ደሞ እኮ ልጄ ሞቶ አደለም እሱንም ሽጦት ነው። (ፊቷ ትንሽም ቢሆን ተስፋ ተነበበት) ለነፍሴ ያለች ነርስ ናት አሳዘንሽኝ ብላ የነገረችኝ ። አሳየኝ እያልኩ ብዙ ለምንኩት አስለመንኩት ጭራስ አበደች ለየላት የሞተ ልጅ ከየት ላምጣ የኔንስ ሀዘን ለምን ተቀሰቅሳለች እያለ ራሱን እንደ ፃድቅ አስቆጠረ ። እሱ ምስኪን የተገፋ አባት እኔ ግን ( ሳግ ተናነቃት) እኔ ግን እብድ ሱሰኛ ሴተኛ አዳሪ ብዙ ብዙ ተባልኩ። በጣም ስታምም ገላዬ እንደ ድሮ ተፈላጊነት ሲያጣ አውጥተው ጎዳና ጣሉኝ አባ ናቸው ከምንም አንስተው ለዚ እንኳን ያበቁኝ።" ብላ ተነፈሰች

ሁላችንም ወደ አባ ዞርን አቀርቅረው እንባቸውን ያፈሳሉ።

"በቃ እኔ ማለት እቺ ነኝ አለኝ ምለው ወንድሜ የተደገፍኩት ባሌ የፈጠረኝ አምላኬ ተባብረው ያረገፉኝ ማያቁኝ የገፉኝ ያምንኩት ሁሉ የኖርኩት ሁሉ ውሸት የሆነብኝ ሰሚ እንኳን የሌለኝ ብቸኛ " ብላ ተንሰቀሰቀሰች ። አብረናት አነባን....

ስንቶቻችን ነን የኑሮዋችንን ዉሸት ማመን ሳንፈልግ እዛው በሀሰት ምንቦራጨቅ ብናምንም መውጫው የጠፋን....ለካ አንዳንዴ ኑሮ ሀሰት መሆኑን አምኖ መቀበል እረፍት አለው....

ከቤተ መቅደስ የተከፈተው "ከንቱ ነኝ ከንቱ ከንቱ ነኝ ዋስትና መከታ እግዚአብሔር ካልሆነኝ " ሚለው መዝሙር እንባችንን አገዘው ።

                                   ✍️ ወርቅ_አለማው

https://t.me/justhoughtsss

28 Feb, 05:03
1,208
Post image

#3

"በመጨረሻም እስከዛሬ ያመንኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት....ኧረ ኡኡኡ" እያለች ትጮሀለች እናት.....

ከኛ ቤት ቀጥሎ ሶስተኛ ግቢ ያሉት ጎረቤቶቻችን ልጃቸው ሙታባቸው ለቅሶ ተቀምጠው ነው....ልጅቷ እኩያዬ ነበረች....መዋለ ህፃናት ላይም አብረን ተምረናል....ሰው ለመግባባት ቀላል፣ ጨዋታ አዋቂና ሰላምተኛ ስለነበረች ግን ትምህርትቤት ተለያይተንም ቢሆን ለስለስ ያለ ጎደኝነታችን እስከ ዛሬዋ ጠዋት ድረስ የቀጠለ ነበር።

የኮሌጅ የመጨረሻ አመት ተማሪ ስለሆንኩ ትናንት ሳገኛት ስለ መመረቂያ ፅሁፌ ጠይቃኝ ትንሽ አውርተን ነበር ታክሲ መያዤአው ጋር የተለያየነው። የሁልጊዜ ሳቋን እና ጨዋታዋን አልነፈገቺኝም ነበር።


ከክላስ ስመለስ ግን ጥቁር ለባሽ የሰፈር እናቶች እየተዋከቡ ነበር...ደነገጥኩ! ሰፈራችን ውስጥ ማን ታሞ ነበር ወይስ ለሞት የደረሰ እርጅና የገባው ማን ቤት ነበር እያልኩ መታጠፊያችን ላይ ደረስኩ....የናቴ ጓደኛ አየችኝና በፍጥነት ተራምዳ መታ አጠገቤ ስትደርስ "ጓደኛሽን እንደው ምናገኛት" ብላኝ ለቅሶዋን ቀጠለች.....እግሬ ተንቀጠቀጠ....ሌላ ማንም እኩያና ጓደኛሽ ሊባል የሚችል ሰው ስለሌለ ስለ ህያብ እንዳወራች ገባኝ.....

ህያብ ከሞተች ዛሬ ሁለተኛ ቀኗ ነው....ራሷን ነው ያጠፋችው ተባለ....ምክኒያቷ ግን ሊታወቅ አደለም ሊገመት አልቻለም....ራሷን እስከማጥፋት አደለም ለአንዲት ሰአት እንኳን ተጨንቃ ታለቅሳለች ብለን ምናስባት ልጅ አልነበረችም።


ሶስተኛው ቀን ላይ ከትምህርት በፊት ለቅሶ ቤት ስራ ላግዝ እና እናትየውን ሰላም ለማለት ሄድኩ።
....ሶስቱንም ቀን ከሀሳቤ ልትወጣ አልቻለችም....ሳቋ፣ ያለ እረፍት በጥያቄ የምትወጥረኝ ነገር፣ ፈገግታዋና ጩኸቷ ያቃጭልብኛል። ለቤተሰቡ ብቸኛ ልጅ ስለሆነች በስስት ነው ያሳደጓት። ባገኘኋት ቁጥር 'ህያብ ግን ምንም አያስጨንቅሽም ኣ? ትምህርት፣ ቤተሰብ፣ ስንመረቅ የሚኖረን ስራ?' ስላት....ገልመጥ አድርጋኝ "እና አንቺ እያሰብሽልኝ ነው ምኖረው" ብላ የለመደችውን ሳቅ ታስከትላለች። አንድም ቀን ከፍቷት፣ ደብሯት አይቻት ስለማላቅ ነው።

.....እናቴ "ሰው ሁኖ ጉድለት የሌለበት የለም፣ በቤቱና በሆዱ ደብቆት ነው እንጂ" ስትለኝ ለሁሉም እንደሚሰራ አምናት ነበር ከህያብ ውጪ....እሷ ነገ ትሞቻለሽ ብትባል እነኳን ፍንክች አትልም ነበር።


ለቅሶ ቤት ስደርስ እናትየው በር ላይ ቁጭ ብላ ትናንት ስትለው እንደነበረው እየደጋገመች "በመጨረሻም እስከዛሬ ያመንኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ተረዳሁ" ትላለች..... ድምፅ ሳላሰማ አጠገቧ ቁጭ ለማለት ስሞክር ....ቀና ብላ አየችኝ። እኔም በትንሹ ፈገግ ብዬ አይዞሽ አልኳት። ጮኸች...ኡኡ ብላ...ከዛ እቅፍ አደረገቺኝና  "ፈገግ አትበሉ ልጄ፣ አታስመስሉ፣ እየሳቃቹ በቁማችን አትግደሉን" ዝም ብዬ አቀፍኳት...አልቅሳ ትንሽ ስትረጋጋ "ልጄ እኮ ዋሸቺኝ...ሳቋን ጨዋታዋን እያሳየች ጥላኝ ሄደች...."እማዬ እኔ ከዚ በላይ ስትታመሚ ማየት ከበደኝ ጭነቀቱን አልቻልኩትም ቻው" ብላ በቁራጭ ወረቀት ተሰናበተቺኝ። የኔ ጀግና፣  ስታመም አንድ ቀን አልቅሳ ተልፈስፍሳ አላየሁአትም....ህያብዬ ህመሜ አደለም ሞቴ አይከብዳትም፣ ጠንካራ፣ ሀዘን ማታውቅ፣ የልቤን ምትሞላልኝ....አሳምራ ነው ምትቀብረኝ፤ ሞቼም ስሜን ታስጠራለች ስል ኖሬ.....ኢኸው በመጨረሻም እስከዛሬ ያመንኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት...ብቻዬን አስቀረቺኝ

ህያቤ ያልኳት የፈጣሪ ስጦታዬ ስለነበረች ነው....ሳቂታዬን ፀሀዬን አጣሁ....ጨለመብኝ እኮ" እያለች ማልቀስ ቀጠለች...

ስጦታቸውን፣ ህያባቸውን፣ ሳቃቸውን፣ ብርሀናቸውን አጥተው ወላጆቿ እንዴት እንደሚፅናኑ የሁላችንም ጭንቀት ሆነ...

ሊሊ


https://t.me/justhoughtsss

27 Feb, 14:14
1,396
Post image

ከእንቅልፌ ስነሳ የምፋጠጠው ጠረጴዛው ላይ የተበተነው ወረቀት ጋር ነው። የተጨናበሰው አይኔ በቅጡ ሳይገለጥ ከወረቀቶቹ ለማምለጥ ከክፍሌ ወጥቼ ወደ ሳሎን እሮጣለሁ።

ለምን ሰብስቤ ዞር እንደማላደርጋቸው አላውቅም። አንዳንዴ ጠረጴዛውን ባዶ አድርጌ እተወዋለሁ። ባዶ ጠረጴዛ ከባዶ ወረቀቶቹ በላይ ጭንቀት ይለቅብኛል። "ደህና ሀሳብ እንኳን ቢመጣልሽ ወረቀት አጠገብሽ መሆን የለበትም?!" ይለኛል

ወረቀቶቹን መልሼ እበታትናቸዋሁ። ሲበተኑ እንደጦር መልሰው ያስፈሩኛል። አንደ ድሮ አንቀልቅሎ የሚያፅፈኝ ሀይል የት እንደገባ አላውቅም። ጉሮሮ ስር ውትፍ የሚል የሚያቅበጠብጠኝን መቼ ፅፌ በተገላገልኩ መቼ ሰው ባነበበው መቼ ሰው በሆነ መንገድ ከፅሁፌ ተጠቀሙ የሚለው ትኩስ ፍላጎቴ መቼ ነው የነፈሰበት

ፍላጎቴ ገፍትሮኝ ከራሴ ጋር እየተሽቀዳደምኩ የምፅፍበት ጊዜ ቀርቶ ራሴን አስገድጄው ስቀመጥ እንኳን ቃላት ይከዱኛል። ሲያጨናንቀኝ የነበረው ሀሳብ ከንቱ ይሆንብኛል "ይሄንን ቁም ነገር ብለሽ ብትፅፊው እንኳን መሳቂያ ነው የምትሆኚው" ብሎ የራሴ ጭንቅላት ይጫወትብኛል

ከዛ ደግሞ ሀሳቤን ደግሜ አስበዋለሁ። ከሰማያዊ እስኪርቢቶ የሚወጣው ከሬንጅ ጠቁሮ ይታየኛል። ሀሳቦቼ በጥላቻ እና በሀዘን የተሞሉ ይሆኑብኛል። ተስፋ መቁረጥ የረበበት ፅሁፍ እንዴት ተስፋ ለቆረጠ ይፃፋል? ብሎ ህሊናዬ ይወቅሰኛል

እኔ ለማልፈው ለጥቂት ጨለማ ወቅት እንዴት አድርጌ አንባቢዬን ተስፋ ላስቆርጥ። ባዶ ወረቀት ፊት ቁጭ ብዬ ከራሴ ጋር ስታገል እንደ ቲክ ቶክ filter ወረቀቱ አፍ አውጥቶ "ተስፋን እንጂ ጨለማን መፃፍ ለማንም ስለማይረባ ወቅት እስኪያልፍልሽ አርፈሽ ብትቀመጪስ" የሚለኝ ይመስለኛል።

ጭንቅላቴን ህሊናዬን እና ወረቀቴን ሰምቼ እርግፍ አድርጌ ልተወው ስል በፈዘዘ ድምፅ ልቤ እየደባበሰቺኝ "በውነቱ ተስፋ ብቻ ወይ ደስታ ብቻ ነው የሚፃፈው ያለው ማነው ደስተኛ የሞላለት የሚመስለው ሰው ሀዘኑን ሲያጋራ አይደል ለካ ሁላችንም ሰዎች ነው የሚባለው ደግሞስ የተጋሩት ደስታ እጥፍ ነው የተጋሩት ሀዘን ግማሽ ነው ይባል አይደል። ደግሞስ የሚወደደው ጥበብ እውነተኛ ሲሆን ብቻ ነው ይባል አይደል? ብላ ወደ ቀልቤ ትመልሰኛለች


ናኒ


https://t.me/justhoughtsss

26 Feb, 15:42
1,669