来自 JUECSF Main & Beco (@juecs_fellowship) 的最新 Telegram 贴文

JUECSF Main & Beco Telegram 帖子

JUECSF Main & Beco
ይህ በኢትዮጵያ ወንጌላውያን ክርስትያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማህበር (EvaSUE) የጅማ ዩኒቨርስቲ (Main and Beco Campus) ወንጌላውያን ክርስትያን ተማሪዎች ህብረት የመገናኛ የtelegram channel ነው


ለማንኛውም ጥያቄ :
@juecsfmainbeco
0936281818

ንግድ ባንክ አካውንት
1000306692147
(Naol Ararsa and/or Tigist Dereje)
1,512 订阅者
1,345 张照片
19 个视频
最后更新于 09.03.2025 12:13

相似频道

Christian Books
5,888 订阅者
Christian Apologetics
4,814 订阅者
Jimma tutor
1,584 订阅者

JUECSF Main & Beco 在 Telegram 上分享的最新内容

JUECSF Main & Beco

06 Jan, 09:03

413

@YtbAudioBot
JUECSF Main & Beco

06 Jan, 09:03

455

ሌላ ነገር ይቅር ይወራ ስለ እርሱ
በከበረው ደሙ ኃጢአት መደምሰሱ (2x)
እንዳች ሳይባል ሁሉም ሰው ይመነው
ኢየሱስን ማጣት ሁሉንም ማጣት ነው (2x)

የባህል እስርአት የኃጢአት ቁራኛ
እስከመቼ ድረስ እያለን መዳኛ
ብርድና ኩነኔ ለከደነው ሁሉ
መቃብርን ከፋች ኢየሱስ አለ በሉ

አዝ፦ ትልቅ ስራ የተሰጠን ትልቅ ስራ
ስለኢየሱስ ሳንታክት ልናወራ
አንድ መንገድ አንድ እውነት አንድ ሕይወት
የተሰጠን ከእግዚአብሔር ከሠማያት

የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ቃሉን ስለናቅን
በአዳም መተላለፍ ሁሉም ሰው ወደቀ (2x)
የዓለምን ኃጢአት በእንጨት ሊሸከም
ሥጋ ለብሶ መጣ ሁለተኛው አዳም (2x)

ምርኮኛን የሚያስለቅቅ እስራት የሚያስፈታ
ምህረትን ይዞ የመጣውን ጌታ
አምኖ ይቀበለው የሰው ዘር በሙሉ
ኢየሱስ ያድናል የምስራች በሉ

አዝ፦ ትልቅ ስራ የተሰጠን ትልቅ ስራ
ስለ ኢየሱስ ሳንታክት ልናወራ
አንድ መንገድ አንድ እውነት አንድ ሕይወት
የተሰጠን ከእግዚአብሔር ከሠማያት

ሰይጣን የአገዛዝ ቀንበሩን ሲያከብድ
የዓለም እንቆቅልሽ እየበዛ ሲሄድ (2x)
ኃያላን ነገሥታት ፈላስፎች ቢሆኑ
ሊያድን የተቻለው ማነው ለመሆኑ (2x)

የመዳንን እራስ በመስቀል ፈጽሞ
ቤት ሊያዘጋጅልን የሄደልን ቀድሞ
በሕያዋን በሙታን ሊፈርድ የሚመጣው
የጽዮን ሙሽራ ጌታ ኢየሱስ ነው

አዝ፦ ትልቅ ስራ የተሰጠን ትልቅ ስራ
ስለ ኢየሱስ ሳንታክት ልናወራ
አንድ መንገድ አንድ እውነት አንድ ሕይወት
የተሰጠን ከእግዚአብሔር ከሠማያት
JUECSF Main & Beco

06 Jan, 09:03

444

@YtbAudioBot
JUECSF Main & Beco

06 Jan, 09:03

882

¹ ከምድር አፈር ትቢያ ፡ አዳምን አበጀ ፣
በቅዱስ አምሣሉም ፡ በመልኩ ፈጠረ ።
እባብ በተንኰሉ ፡ በኃጢአት ቢጥለው ፣
የዚያን ጠላት ራስ ፡ ጌታ ቀጠቀጠው ።  ክ ብ ር !

ክብር (3*) ለእኛ ጌታ ፡ ይሁን ዘላለም ፣
በማዳን ብርቱ የሆነ ፡ እንደ እርሱ የለም ።

² በቅዱስ ማደሪያዉ ፡ በቤቱ እንድንኖር ፣
በሕይወታችን ዘመን ፡ ለእርሱ እንድንዘምር ፣
ውርደታችንን ፡ ለወጠው በክብር ፣
ጌታ ስላሰበን ፡ በዘላለም ፍቅር ።  ክ ብ ር !

« ክብር ፣... »

³ በሰባት ማኅተም ፡ መጽሐፍ ተዘግቶ ፣
ቢፈለግ ቢጠየቅ ፡ የሚከፍተው ጠፍቶ ።
ከይሁዳ ነገድ ፡ አንበሳው ተነሳ ፣
ማኅተሙን ሊፈታ ፡ ኢየሱስ ድልነሳ ።  ክ ብ ር !

« ክብር ፣... »

⁴ መጽሐፉን ከፍቶ ፡ ማየት የተገባው ፣
እንቈቅልሹንም ፡ መፍታት የተቻለው ፣
የዋጀን በደሙ ፡ ለእኛ የተሰዋው ፣
የትንሣኤው ንጉስ ኢየሱስ ብቻ ነው ።  ክ ብ ር !

« ክብር ፣... »
JUECSF Main & Beco

06 Jan, 09:03

1,129

ለህዝቡ ሁሉ የሚሆን
የምሥራች ተነገረ
ታላቅ ደስታ ነው ልደቱ
ይዘምር እስኪ ፍጥረቱ

አዝ፦ መጣልን (መጣልን)
ጌታ ሊጐበኘን (ሊጐበኘን)
ቤዛ ሊሆንልን
ከኃጢያት እኛኑ ሊያድን
ቃል ሥጋ ሆነና ከድንግል ተወለደልን

ህጻን ተወለደ ለእኛ
በቤተልሔም በረት ተኛ
ለኃጥያተኞች መዳኛ
ሊሆን የበጐች እረኛ

አዝ፦ መጣልን (መጣልን)
ጌታ ሊጐበኘን (ሊጐበኘን)
ቤዛ ሊሆንልን
ከኃጢያት እኛኑ ሊያድን
ቃል ሥጋ ሆነና ከድንግል ተወለደልን

ሥሙ የተመሰገነ
ክርስቶስ ጌታ የሆነ
ተገልጧልና ልዑሉ
ስገዱለት ዕልል በሉ

አዝ፦ መጣልን (መጣልን)
ጌታ ሊጐበኘን (ሊጐበኘን)
ቤዛ ሊሆንልን
ከኃጢያት እኛኑ ሊያድን
ቃል ሥጋ ሆነና ከድንግል ተወለደልን

ተሽቀዳደሙ ኑ እዩት
የሚመስልህ የለም በሉት
አድንቁት እጅግ አክብሩት
ይገባዋል አመስግኑት

አዝ፦ መጣልን (መጣልን)
ጌታ ሊጐበኘን (ሊጐበኘን)
ቤዛ ሊሆንልን
ከኃጢያት እኛኑ ሊያድን
ቃል ሥጋ ሆነና ከድንግል ተወለደልን

በላይ ለእግዚአብሔር ክብር
ለእኛም ሰላም በምድር
ይሁን ብለን እንዘምር
እረፍት አለ መስቀሉ ስር

አዝ፦ መጣልን (መጣልን)
ጌታ ሊጐበኘን (ሊጐበኘን)
ቤዛ ሊሆንልን
ከኃጢያት እኛኑ ሊያድን
ቃል ሥጋ ሆነና ከድንግል ተወለደል
JUECSF Main & Beco

06 Jan, 08:04


JUECSF Main & Beco pinned «»
JUECSF Main & Beco

06 Jan, 08:04

391

ኦ ፡ ቅዱስ ፡ ሌት ፡ ከዋክብት ፡ ያበራሉ
የአዳኛችን ፡ ልደት ፡ ስለሆነ
ዓለም ፡ በኃጢአት ፡ ውስጥ ፡ ስትጨማለቅ
መጣላት ፡ ተስፋዋን ፡ ስትጠብቅ
ግሩም ፡ ተስፋ ፡ ነፍሳቸውን ፡ ያረካል
ደስ ፡ ይበለን ፡ ንጋት ፡ ሆኖልናል
ስገዱለት ፡ የመላዕክቱን ፡ ድምጽ ፡ ስሙ
በቅዱስ ፡ ሌት ፡ በክርስቶስ ፡ ልደት
ቅዱስ ፡ መዝሙር ፡ ለእርሱ ፡ አቅርቡለት

በእምነት ፡ ኃይል ፡ በብርሃኑ ፡ ተመርተን
በደስታ ፡ ልብ ፡ እንይ ፡ ያንን ፡ ህጻን
የኮከቡ ፡ ብርሃን ፡ አይተው ፡ ሲሮጡ
ጥበበኞች ፡ ከሩቅ ፡ ሃገር ፡ መጡ
ህጻኑ ፡ ንጉሥ ፡ በበረት ፡ ተኝቷል
በችግር ፡ ወንድማችን ፡ ሆኗል
የእኛን ፡ ሃሳብ ፡ ድካማችንን ፡ ሁሉ
እርሱ ፡ ያውቃል ፡ ወድቀን ፡ እንስገድለት
የእኛ ፡ ንጉሥ ፡ ተወልዷል ፡ በበረት
JUECSF Main & Beco

06 Jan, 08:04

419

በጨለማ የሄደ ህዝብ : ብርሃን አየ
በሞት ጥላ ለነበሩ : ጌታ መጣ
የህዝቡንም ሀጢያት የሚያስወግድ : የእግዚአብሔር በግ ተገለጠ
ተጨንቃ ለነበረች ነፍስ : ዕረፍት ሆነ ሰላም ሆነ

ህፃን ተወልዶልናል
ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል
እልቅና በጫንቃው ላይ ነው
ስሙም አማኑኤል ነው

መንሹ በእጁ ነው : አውድማውን ያጠራዋል
ስንዴውንም ሰብስቦ : ከጎተራው ይከተዋል
በውሃ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ : በእሳትም የሚያጠምቅ
ቅጥቅጥ ሸምበቆውን : የማይሰበር የሚምር

ድንቅ መካር : ሀያል አምላክ
የዘላለም አባት : የሰላም አለቃ
አማኑኤል : ከእኛ ጋር ነው እግዚአብሄር 

ህፃን ተወልዶልናል
ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል
እልቅና በጫንቃው ላይ ነው
ስሙም አማኑኤል ነው
JUECSF Main & Beco

06 Jan, 08:04

420

አዝ፦ ደስ ፡ ይበለን (፪x)
እንዘምር ፡ በዕልልታ
መቸገራችንን ፡ አይቶ
ወረደልን ፡ ጌታ

መላዕክት ፡ ዘመሩለት ፡ ሰማይም ፡ ደመቀ
ኢየሱስ ፡ መወለዱ ፡ ለድሆች ፡ ታወቀ
መንፈስ ፡ የፀለለው ፡ የከበረ ፡ ሕፃን
መድኅን ፡ ተወለደ ፡ ከኃጢአት ፡ ሊያነፃን

አዝ፦ ደስ ፡ ይበለን (፪x)
እንዘምር ፡ በዕልልታ
መቸገራችንን ፡ አይቶ
ወረደልን ፡ ጌታ

ድግሥ ፡ አዘጋጅቶ ፡ የሰማዩ ፡ ልዑል
በልጁ ፡ ጋበዘን ፡ ሃብታም ፡ ድሃ ፡ ሳይል
መዳን ፡ የሚወዱ ፡ ሁሉም ፡ ይገባሉ
የዘለዓለም ፡ ሐሴት ፡ በእርሱ ፡ ይወርሳሉ

አዝ፦ ደስ ፡ ይበለን (፪x)
እንዘምር ፡ በዕልልታ
መቸገራችንን ፡ አይቶ
ወረደልን ፡ ጌታ

ኢየሱስ ፡ በልባችን ፡ ዛሬ ፡ ተወለደ
ለእኛ ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ እርሱን ፡ ለወደደ
ለተጠጋው ፡ ሁሉ ፡ መቸገሩን ፡ አይቶ
ዛሬም ፡ ይወለዳል ፡ አይተውም ፡ ሰልችቶ

አዝ፦ ደስ ፡ ይበለን (፪x)
እንዘምር ፡ በዕልልታ
መቸገራችንን ፡ አይቶ
ወረደልን ፡ ጌታ

እሰይ የምስራች (እሰይ) : ጌታ ተወለደ (እሰይ)
ከሰማይ ሰማያት (እሰይ) : ለኛ ሲል ወረደ (እሰይ)
JUECSF Main & Beco

06 Jan, 08:04

479

በመጀመሪያ ቃል ነበረ
ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ
ቃልም እግዚአብሔር ነበረ
ኦ ነበረ
ይህም ቃል ስጋ ሆነ
በእኛ ዘንድ አደረ
አምላክ ሆኖ ሳለ የባሪያን መልክ ያዘ
በሰው አምሳል ተገኝቶ ራሱን ባዶ አረገ
ሰው ሆኖ ተገልጦ ራሱን ዝቅ አረገ
(×2)


ፀጋንና እውነትን ተሞልቶ
ካባቱ ዘንድ የመጣውን
ያድያ ልጅን ክብር አየን

ደግሞም
ለተቀበልነው በስሙ ላመንን
የእግዚአብሔር ልጆች እንሆን ዘንድ
ስልጣንን ሰጠን