ደጀን የለው ብለው ሆነልኝ መከታ (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ)
እንዳሰቡት ሳይሆን እንዳሰበልኝ ነው (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ)
ገና መቼ አዩ ይሄ ጅማሬ ነው (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ)
አምላኬ የእኔማ ተስፋ
እንዳልወድቅ ከቶ እንዳልጠፋ
የእኔ አባት የእኔ መድኃኒት
በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት
አንተ ነህ እኔማ ተስፋ
እንዳልወድቅ ከቶ እንዳልጠፋ
የእኔ አባት የእኔ መድኃኒ
በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት
በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት
በአንተ ነው ሁሉን ያለፍኩት
በአንተ ነው ቀን የወጣልኝ
ጌታዬ ተመስገንልኝ (2x)
አስታዋሽ ለሌለኝ ለተረሳሁ በሰው (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ)
ከተፍ ብሎልኛል ፍቅሩ በተግባር ነው (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ)
እንባ አወጡ አይኖቼ በደስታ ተሞሉ (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ)
ህመሜኮ ያመዋል ስለሆንኩ አካሉ (ጌታዬ ጌታ ጌታዬ)
አምላኬ የእኔማ ተስፋ
እንዳልወድቅ ከቶ እንዳልጠፋ
የእኔ አባት የእኔ መድኃኒት
በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት
አንተ ነህ እኔማ ተስፋ
እንዳልወድቅ ከቶ እንዳልጠፋ
የእኔ አባት የእኔ መድኃኒ
በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት
በአንተ ነው እዚህ የደረስኩት
በአንተ ነው ሁሉን ያለፍኩት
በአንተ ነው ቀን የወጣልኝ
ጌታዬ ተመስገንልኝ (2x)
የምስኪኑ ወዳጅ ለተከፋው ፈራጅ
ለድሃደጉ አባት ለደከመው ብርታት (2x)
ማረፊያ ጥላዬ
መጠጊያ ከለላዬ
ኢየሱስ ጌታዬ (2x)
ኢየሱስ ጌታዬ (4x)